መታሠርና ለፍርድ መቅርብ ያለባቸው እንደ እነዚህ ዓይነት ያሉ ሰዎች ናቸው…
ቢልየነሩ ባለኃብት ጄፍሪ ኤፕሽታይን የዓለም አቀፉ ዲያብሎሳዊ የሕፃናት ደፋሪዎች አውታር መሪ እንደሆነ ባለፉት ዓመታት ሲወሳ ቆይቷል። ይህ ጽንፈኛ አውታር የቀድሞዎቹን የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች ክሊንተንን፣ ኦባማን፣ ቡሽን፣ የብሪታኒያ ልዑሎችን እና ሌሎችንም ብዙ ታዋቂ ባለጌ ሰዎችን ያካተተ ዲያብሎሳዊ አውታር ስለሆነ፡ በዚህ መልክ አሁን ከተጋለጠ ለዓለማችን ትልቅ ድል ነው የሚሆነው።
ጄፍሪ ኤፕሽታይን ባለፈው ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ተልካ የነበረችውን “ሶፊያ” የተባለች ሮቦትን ለመሥራትና በመላው ዓለም ለመላክ የገንዘብ ድጎማ ሲያደርግ የነበረ ቆሻሻ ሰው ነው። የዚህች ሮቦት ተልዕኮ ግብረ–ሰዶማዊነትን እና ሕፃናት–ዸፋሪነትን በአገራችን ከማስፋፋት ጋር የተያያዘ ነው።
የሳውዲ ዜግነት የተሰጣት ሮቦት ሶፊያ፡ በዘመነ ግራኝ አህመድ በመካ መዲና በኩል አድርጋ ወደ ኢትዮጵያ ማምራቱ ያለምክኒያት አይደለም። እዚህ ይመልከቱ፦ What Is the Connection Between Pedophilia and A.I. (Artificial Intelligence)?
የሚከተለው ከዓመት በፊት ልክ በዚህ ዕለት ያቀረብኩት ጽሑፍ ነው፦
ግብዞች በእግዚአብሔር አፈጣጠር እና ፍጥረታት ላይ እያመጹ ነው፤ እራሳቸውን አምላክ ለማድረግ ይሻሉ። በትንቢተ ዳንኤል እና በ ዮሐንስ ራዕይ መጻሕፍት ላይ ሁሉም ነገር ተብራርቶ ይነበባል። አሁን ብዙ እየትወራለት ያለው የሰው ሠራሽ አዕምሯዊ ጥናት ዘመቻ የፀረ–ክርስቶሱና የአውሬው መንፈስ የቀሰቀሰው ዘመቻ እንደሆነ ምንም አያጠራጥርም።
ተራቅቀናል የሚሉት አመጸኞቹ ሰዎች አሁን ሮቦቶችን እየሠሩ ቀስ በቀስ እንደ እግዚአብሔር እንዲመለኩ ማድረግ ይጀምራሉ።
ባለፈው ዓመት፡ “ሶፍያ” የተሰኘች “ሴት” ሮቦት በሳውዲ አረቢያ ተወዳጅነት ማትረፏና ከሁሉ አገሮች ቀድማ የሳውዲ አረቢያን ዜግነት ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘቷ፡ የፀረ–ክርስቶሱ ኃይል በምዕራባውያኑ ኤዶማውያን ቴክኖሎጂና በእስማኤላውያኑ ዶላር ድጋፍ በመላው ዓለም እንደሚሠራጭ ይጠቁመናል። ሆንግ ኮንግ የተሠራችው “ሶፊያ” በሳውዲ አረቢያ በ666ቱ መንፈስ ከተጠመቀች በኋላ፡ ወደ ተመረጡ አገሮች ተጓዘች።
“ሶፊያ” ከመሠራቷ ከአምስት ዓመታት በፊት ቅሌታሙ ባለ ኃብት አሜሪካዊ፡ ሕፃናት ደፋሪው፡ ‘ጀፍሪ ኤፕሽታይን‘ የሚደግፈው የሰው ሠራሽ አዕምሯዊ ጥናቶችን ማካሄጃ ተቋም በኢትዮጵያ ተምሠረተ፤
(በአዲስ አበባ ‘ሉሲ‘ አጠገብ)፤ እዚያም ‘አበበ‘ የተባለ እግር ኳስ ተጫዋች ሮቦት ተሠራ፤ ከዚያ በኋላ ሮቦት “ሶፊያ” ተሠራች፤ ከሳምንት በፊት ሮቦት “ሶፊያ”ን ወደ ኢትዮጵያ እንድትመጣ የጋበዛት ይህ ተቋም ነው። (አዳም እና ሔዋን መሆናቸው ነው)
የዚህ ተቋም ኃላፊ የሆነው ሊቅ ጌትነት አሰፋ የሚከተለውን ከንቱ ዓረፍተ ነገር ተናግሯል፦
„በመጪዎቹ አሥር ወይም ሃያ አመታት ውስጥ የሰው ልጅ የሚባል አይኖርም፤ በማሽን ይተካል”
“I don’t think Homo sapiens-type people will exist in 10 or 20 years’ time.”
ይህን ዲያብሎሳዊ ህልምና ዕቅድ በሥራ ላይ ለማዋል፡ ሰኔ ፪ሺ፲ ዓ.ም፡ “ሶፊያ ወደ ኢትዮጵያ እንድትጓዝ ታዘዘች፣ የባህል ልብሳችንን አለበሷት፣ ቋንቋችንን ተናገረች፣ ሰንደቅ ዓላማችን ላይ ካረፈው የሉሲፈር አምስት መዓዘናዊ ኮከበ እና ከዶ/ር አብይ ጋር አብራ እንድትታይ ተደረገች። ጎልቶ የሚታየው ኮከቡ ነው!
[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፫፥፲፭]
“የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።”