Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሥራ’

አንዲት ክርስቲያን እናት እሁድ እሁድ ለመሥራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው 21 ሚሊዮን ዶላር ተሸለሙ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 20, 2019

የ60 ዓመቷ እናት “ማሪ ጄን ፒዬር”፡ በፍሎሪዳዋ ማያሚ ሂልተን ሆቴል ቅርንጫፍ እቃ አጣቢ ሆነው ለአሥር ዓመታት ያህል ሠርተዋል። ትውልደ ሃይቲዋ ማሪ ጄን ሰንበት ሰንበት ለመሥራት ፈቃደኛ ያልነበሩ አጥብቂ ክርስቲያን በመሆናቸው፡ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ይችሉ ዘንድ ለስድስት ሰንበታት ያህል ወደ መሥሪያ ቤት አልሄዱም ስላሉ በሆቴሉ አለቃዋ ከሥራቸው ተሰናበቱ። በዚህም ምክኒያት በቀድሞ አሠሪዋ ላይ ክስ ለመመስረት ተገደዱ።

ጉዳዩም ለፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት እናት ማሪ የሚከተለውን ብለው ነበር፦

እግዚአብሔርን ስለምወደው ሰንበት ሥራ የለም በእሑድ እግዚአብሔር መከበር አለበትና”

የማሪ ጠበቃም በማከል፦

ማሪ የክርስቶስ ወታደር ናት፤ በተመሳሳይ መልክ አድልዎ እየደረሰባቸው ላሉት ለሁሉም ሠራተኞች አርአያ ትሆናለች

ብለዋል።

ባለፈው ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤቱ የማሪድሞ አሠሪ፡ ሂልተን 21 ሚልዮን ዶላር እንዲከፍል እንዲሁም ለቀጣይ ክፍያ 35,000 ዶላር እና ለደረሰባቸው ስሜታዊ እና አእምሯዊ ህመም $ 500,000 ተጨማሪ መክፈል እንዳለበት ወስኗል።

ጠበቃዋም ውሳኔውን አስመልክቶ የሚከተለውን ብሎ ነበር፦

ይህ ጉዳይ ገንዘብን የሚያመለክት ጉዳይ አልነበረም፣ እንደ ሂልተን ሆቴል ትላልቅ ለሆኑ ድርጅቶች መልእክት ለመላክ እንጂ” “የፈለግከውን ያህል አንጋፋ ብትሆን፣ የሰራተኞቹን ደም እና ላብ መውሰድ ከፈለጉ እነሱን በተሻለ ሁኔታ መንከባከብ ይገባቸዋል ወይም ቢያንስ በእምነታቸው ባይጋፏቸው ጥሩ ነው።”

አርአያችን ሊሆኑ የሚገባቸው ጎበዝ እናት ናቸው! ግሩም የፍርድ ቤት ውሳኔ!

ሁሌ የሚያሳስበኝ በአገራችን፡ ሰንበትን ጨምሮ በበዓላቱ ሁላ ሱቆች፣ ገባያዎችና ዳንኪራ ቤቶች ገንዘብ ሲያሽከረክሩና ሲጯጯሁ መታዘቤ ነው። እመነተቢስ የሆኑት ብዙ የምዕራባውያን አገራት እንኳን ለሰንበትና ለበዓላት ሱቆቻቸውን እንዲዘጉ ያደርጋሉ።

____________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: