Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 4, 2020
“አለም የኢትዮጵያ መንደር” የተስኘውና በአሜሪካዋ ሚልዋኪ መሃል ከተማ / ዊስኮንሲን ግዛት ቅዳሜና እሁድ በተካሄደው የተቃውሞ አመጽ ወቅት ሰዎች ምግብ ቤቱ ገብተው በከፊል አውድመውታል ፡፡ ሁለት መስኮቶች ተሰባብረዋል።
ከአስር ዓመት በፊት የተከፈተው ይህ ምግብ ቤት በባለትዳሮቹ ሰለሞን በቀለ እና ሙሉ ሃብተ ሥልሴ የሚተዳደር ነው። ውድመቱ ባስከተለው ወጪ የተጨነቁት ሁለቱ ወገኖቻችን ከአካባቢው ነዋሪዎች በተካሄደ የመዋጮ ማራቶን እስከ 12 ሺህ ዶላር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊሰበስብላቸው ተችሏል።
ተመስገን! አይዟችሁ ወገኖቼ!
_________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos, Life | Tagged: Alem Ethiopian Village, ሚልዋኪ, ምግብ ቤት, አለም የኢትዮጵያ መንደር, አመጽ, አሜሪካ, Milwaukee | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2019
ያን ምስኪን በሬ እናስታውሰዋለን?
በዚያን ወቅት እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቄ ነበር፦
ለመሆኑ
-
በሬው የማን ነው?
-
በሬውን ማን አመጣው?
-
በሬው እንዴት ጥብቅ ፍተሻ ሲደረግበት ወደ ነበረው ወደ መስቀል አደባባይ ሊገባ ቻለ?
-
በሬው ወደ ቅ/እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ለምን ተወሰደ?
-
በሬው ፌደራል ፖሊሶችን ለምን አሳሰባቸው? በጠዋትስ ለምን በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተገኙ?
ከደመራ አንድ ሳምንት በፊት በመስቀል አደባባይ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን እና ግዮን(አባይ) ሆቴል አቅራቢያ የሚፈሰውን ወንዝ የዋቄዮ–አላህ ልጆች ከለሉት፣ ከዚያም የሩጫ ውድድር አካሄዱ፣ የደመራ ችቦ በበራ በሳምንቱ ሰይጣናዊውን የኢሬቻን በዓል በመስቀል አደባባይ በማክበር አጋንንታቸውን በአካባቢው አራገፉ።
አዎ! ይህ በመስቀል አደባባይ እና ቅዱስ እስጢፋኖስ አካባቢ ያለው ቦታ ከፍተኛ የመንፈሳዊ ውጊያ የሚካሄድበት ቦታ ነው። ነገሮችን ለማባባስ በቤተክርስቲያን እና ቤተክህነቷ ውስጥ ሰርገው የገቡ እንደ ኢሬቻ በላይ የመሳሰሉ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ናቸው።
„ “….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው…የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው” ብሎናል አይደል ግራኝ አብዮት አህመድ።
አዎ! እኔ ሰይጣን ብሆን ኖሮ የማደርገው ልክ አሁን በቤተክርስቲያን ላይ እይተሠራ ያለውን ነገር ነው። ቤተክርስቲያንን በሞቃታማ ጦርነት ብቻ ተዋግቶ ማሸነፍ እንደማይቻል አውቀውታል፣ ስለዚህ በአንድ በኩል ያዘጋጇቸውን አሕዛብንና መንፋፍቃን ለጥፋት ማሰማራት፣ በሌላ በኩል የኤሬቻ ባሪያዎችን ሰርገው እንዲገቡ ማድረግ፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ የቤተክርስቲያንን አመራር በጥቅም መያዝ አስፈላጊ ነው። እንግዳችንን በቁንጣን ለማሰቃየት ብዙ ጉርሻ ማጉረስ እንዳለብን ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማፈንና ከተቀዳሚ የመንፈሳዊ መንገዷ ለማሰናከል ለዓብያተ ክርስቲያናቱ ሰፋፊ መሬት መስጠት፣ ከዚያም “ልማት” በተባለ ዘመቻ አብያተክርስቲያናቱ በንግድ ቤቶች፣ በምግብና መጠጥ ቤቶች፣ በጋራጆች ወዘተ እንዲከበቡ ማድረግ፣ “ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ…” ተብሎ ይተረትባታል።
ባለፈው መስከረም ላይ አርብ ዕለት ወደምወዳት የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አመራሁ፤ ፀሎት ካደረስኩ በኋላ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ምሳ ለመብላት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ወደ ሚገኙት ምግብ ቤቶች አመራሁ። አሳላፊዋ እንደመጣች፣ “የጾም ምግብ መብላት እፈልግ ነበር፤ ግን ምግቦቻችሁን በጭቃው ዘይት (የዘምባባ ዘይት) የምትሠሩ ከሆነ ይቅርብኝ” አልኳት፡ እርሷም “አይ ሁሉም በጭቃው ዘይት ነው የሚሠራው፣ ሁሉም ሰው ተስማምቶ ይበላዋል” አለችኝ። ብዙ ሰው ነበር፤ ወጣቶች። በጣም በማዘን፤ “ምነው! ምነው! እሺ አምቦ ውሃ አምጭልኝ” አልኳት፣ “እሱም የለም ሚሪንዳና ስፕራይት ወይም ሃይላን ውሃ ብቻ ነው ያለን” አለችኝ። ለስላሳ መጠጥ ስለማልጠጣ ውሃ አዝዤ ቁጭ አልኩ። በዚህ ወቅት ባለቤቱ መሰለኝ በእጁ የያዘውን ገንዘብ እየቆጠረ ወደ እኔ መጣና “ውሃው ተስማማህ?… ኑሮ ውድ ስለሆነብን እኮ ነው የጭቃውን ዘይት የምንጠቀመው ፥ ሁሉ ነገር ተወደደ” አለኝ። እኔም፡ “ቤተክርስቲያን ግቢ ይህን መርዛማ ዘይት ለምዕመናኑ በመቀለባችሁ መቅሰፍት እንደሚመጣባችሁ እውቀቱ፣ ጤናማ የሆነውን ዘይት ተጠቅማችሁ ምግቡን ትንሽ ማስወደደ አይሻለም?” አልኩትና ሂሳቡን ሰጠሁት፡ ከዚያም አንገቱን ደፍቶ ሄደ።
ብዙም አልቆየም አንድ አረጋዊ ካህን አባት ምግብ ቤቱ በር ላይ ቆመው ምግብ ሲያዙ አየኋቸው።
የታሸገ ነገር ተሸክመው መራመድ እንደጀመሩ ተከትያቸው ሄድኩና “እንድምን ዋሉ አባ? አንዴ ላናግርዎት?” አልኳቸው። “ከዚህ ምግብ ቤት ምን ዓይነት ምግብ ገዝተው ይሆን? በመርዛማው ጭቃ ዘይት የተሠራውን ምግብ ገዝተው ይሆን?” ስል ፥ እሳቸውም፡ “አይ ልጄ እንጀራ ነው የገዛሁት፣ ምን ዛሬ እንጀራው ውስጥስ ምን እንደሚያስገቡበት ይታወቃል፣ ሰጋቱራ ምናምን ይባላል” አሉኝ፤ በዚህ ጊዜ ሰዎች ከበቡን፡ እኔም፤ “እንዴ አባ ይህ ቦታ የቤተክርስቲያን ንብረት አይደለምን? ማን ምን እንደሚሸጥ ቁጥጥር መካሄድ የለበትምን?” እንዳልኩ በዚህ ጊዜ የከበበን ሰው ቁጥር ጨመረ። ዘበኛ ነገሩም እንደተለመደው “ምንድን ነው? ምንድን ነው?….. ይህን ጉዳይ ሌላ ቦታ ሄደህ አሳውቅ…ቅብርጥሴ” እያለ መጣ። እኔም “አያገባህም…መንፈስ ቅዱስ ነው የላከኝ፣ በርገር ሁሉ ትሸጣላችሁ…” በማለት ድምጼን “እንደ እብድ” በይበልጥ ከፍ ማድረግ ጀመርኩ። ካህኑም “ተወው ይናገር” በማለት ዘበኛውን ከእኔ አራቁት። አንድ ሌላ ቄስ ወደ እኔ መጥቶ “ኑሮ ውድ ነው፣ በተገኘው ነገር ምግብ ቢሠራ ምን ክፋት አለው? በርገርስ ምግብ አይደለምን?” እንዳሉኝ በይበልጥ ቱግ ብዬ በመጮኽ “ምን ዓይነት መርገም ነው? ቤተክርስቲያን ግቢ እንዴት መርዝ ይሸጣል? በርገር የአሳማ፣ የአህያ ወይም የውሻ ስጋ ሊደባለቅበት እንደሚችል አታውቁምን? ለመሆኑ በጣም ብዙ ምዕመናን ያለው ይህ ድንቅ ቤተክርስቲያን ለምንስ የንግድ ቦታዎች አስፈለጉት? ቤተክርስቲያናችን ሁለት ሺህ ዓመታቱን ሁሉ የዘለቀችው በገንዘብ ነውን? ምግብ ቤቶች መከፈት ካለባቸው እንኳን ባለቤቶቹ ጥንቃቄ የሚያደርጉ የተዋሕዶ ክርስቲያኖች ብቻ መሆን አለባቸው፣ አሊያ ሁሉም መዘጋት ይኖርበታል። ከአህዛብ ሃገር ከማሌዢያ በመጣ በመርዘኛ ዘይት ምግብ ተሠርቶ እየተሸጠ በምን ዓይነት ተዓምር ነው ምዕመናን ከቤተክርስቲያን ተባርከው ሊወጡ የሚችሉት? ቅዳሴው፣ ፀሎቱና ጸበሉ ሁሉ እኮ ኃይላቸውን እየተነጠቁ ነው፣ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለሁለተኛ ጊዜ በድንጋይ እይወገራችሁት ነው!” በማለት ስናገር ሁሉም በሃፍረት አንገታቸውን ደፍተው ይታዩ ነበር። (የጉልበቶቻቸውንና ክንዶቻቸውን መገጣጠሚያዎች ስለታመሙ አባቶች መስቀል እንዲያሳርፉባቸው የሚጠይቁ ብዙ ወጣቶች አይቻለሁ፤ ጭቃው ዘይት)።
በአንድ በኩል ጉዳዩ በጣም የሚያሳዝንና መፍትሄም ቶሎ የሚሻ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ግን በተለይ የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ምዕመናን እሮሮ አሁን በዚህ መልክ መሰማት መጀመሩ ለበጎ ነገር ስለሆነ በከፊል አስደስቶኛል። አካባቢው ከፍተኛ መንፈሳዊ ውጊያ የሚካሄድበት ነውና፣ ዲያብሎስ ከሁሉም አቅጣጫ ነው እየተዋጋን ያለው።
የሚቀጥለው ቪዲዮ ስለ አቡነ ሀብተማርያም ገዳም የቅኔ ተማሪዎች እሮሮ ይሆናል
አባታችን አቡነ ሀብተማርያም እግዚአብሔር ለቅድስና ሥራ ስለመረጣቸው በእናተቸው ጀርባ ታዝለው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው በሕጻን አንደበታቸው ከቀዳሹ ካህን ጋር “እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ” በማለት ይጸልዩ ነበር፡፡ ባደጉም ጊዜ ይህን ጸሎት ደጋግመው ይጸልዩ ነበር፡
ሰላም ለዝክረ ስምክ፡– በዃለኛው ዘመን የዚህን ዓለም ረሃብና ጥም የሚያስረሳና ከወይን ዘለላ ይልቅ ለሚወደድ ስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ህጻን የሆነ የማርያም ልጅ ወዳጅ ጻድቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ሆይ በቦታው ታርፍለት ዘንድ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አጥብቆ እንደ ለመነ እኛንም ልጆችህን ከሀዘን ሁሉ ታድነንና በቤታችንም ታርፍ ዘንድ እንለምነሃለን፡፡ እግዚኦ ማሐረነ ክርስቶስ!
የአባታችን የጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ረድኤት፣ በረከት፣ ምልጃና ቃል ኪዳናቸው አይለየን፡
__________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: መስቀል, መስከረም ፳፻፲፪, ምግብ ቤት, ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን, በሬ, ንግድ ቦታ, አዲስ አበባ, ኢሬቻ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ዘምባባ ዘይት, የምዕመናን እሮሮ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ደመራ, ጭቃ ዘይት, ፖሊሶች, Demera, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, Meskal, Ox | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 25, 2018
በአንድ የበርሊን ከተማ የ KFC ፈጣን ምግብ ቤት ውስጥ የ 118 ዩሮ ምግብ እየበሉ እንዳሉ ነበር የሬስቶራንቱ ሠራተኞች ፖሊስ ጠርተው እንዲባረሩ የተደረጉት።
ከእንግሊዝ አገር የመጡት ሦስቱ ጥቁር ሴቶችና አራቱ ጥቁር ወንዶች ምግቡን በልተው በበርሊን ከተማ በዓል ላይ ያነሷቸውን ቪዲዮዎች እያዩ ሲሳሳቁ ነበር። ሌሎችም እንግዶች እንዲሁ ተመሳሳይ ጨዋታዎችና መሳሳቆችን ሲለዋወጡ ይሰማ ነበር። ነገር ግን የKFC ሠራተኞች ወደ ጥቁሮቹ ብቻ መጥተው ነበር ጸጥ እንዲሉ ያሳሰቧቸው። ይህ ያስቆጣው አንዱ ጥቁር፦ “ምን አጠፋን? እንደ ሌሎቹ እኛም እየተጫወትን ነው፤ ለምን እኛን ብቻ?” ብሎ ሲጠይቅ፤ ወዲያው ፖሊስ እንዲጠራ ተደረገ።
ቀሪው ከቡድኑ ጋር አብራ በነበረችው ሴት የተነሳው ቪዲዮ ላይ ተመዝግቧል።
ይህም ሐሙስ ግንቦት 18 እና 21 2018 ዓ.ም በጥቁሮቹ ላይ የደረሰው ድርጊት ዘረኝነት የተሞላበት ነው በማለት ግለሰቦቹ ሬስቶራንቱንና ፖሊስን ወንጅለዋቸዋል።
አሁን በማሕበራዊ ድህረገጾች የዘረኝነት ክሶች እና የፀረ-KFC ዘመቻ ጥሪዎች እየጨመሩ ነው። በጥቂት ቀናት ብቻ ቪዲዮው ግማሽ ሚሊየን ጊዜ ቋ! ተደርጎል
ይህ ጉዳይ ባለፈው ሚያዝያ መጨረሻ ላይ በአሜሪካዋ ፊላደልፊያ ውስጥ፡ በአንድ የስታርባክስ ቡና ቤት የተከሰተውን ክስተት የሚያስታውስ ነው። እዚያም ሁለት ጥቁር አሜሪካዊያን ነጋዴዎች ቡና ቤት ውስጥ ባልደረባቸውን በመጠበቅ ላይ እያሉ አንድ የቡናቤቱ ሠራተኛ ፖሊስ በመደወል ከቡና ቤቱ በሰንሰለት ታሥረው እንዲወጡ ተደርገው ነበር። ይህ ክስተት በአሜሪካ ውስጥ ዘረኝነትን አስመልክቶ ብዙ ክርክር አስነስቶ ነበር።
ከዚያ በኋላ የስታርባክስ ኃላፊ የፀረ–ዘረኝነት ስልጠናን ለሰራተኞቹ ለማጠናከር ሲል 8,000 ቅርንጫፎችን ለአንድ ቀን በመዝጋት “የሙያ ስልጥና” አካሄዶ ነበር። ዋና ሥራ አስኪያጅ ኬቪን ጆንሰን ግለሰቦቹን ይቅርታ ተጠይቋል። ሠራተኞቹ ፖሊስ መጥራታቸው “ሙሉ ለሙሉ ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ነው” በማለት ምላሽ ሰጥቶ ነበር።
ስለዚህ ጉዳይ ብዛት ያላቸው የጀርመን ሜዲያዎች ሪፖርት አቅርበዋል። ለምሳሌ አንጋፋው “ዲ ቬልት” ጋዜጣ ላይ በጣም ብዙ አንባብያን ዘግበዋል፤ (እስከ 400 የሚሁን ዘጋቢዎች)፤ ታዲያ ከድርጊቱ ይበልጥ በጣም የሚያሳዝነው፤ ሁሉም፤ (100%) የወነጀሉት ጥቁሮቹን መሆኑ ነው፤ አንድ እንኳን “አላየሁም፣ አላውቅም፣ በቦታው አልነበርኩም” በማለት ሚዛናዊ አመለካከት የነበረው የለም። በብዛት “ላይክ” የተደረገላቸውም ጥቁር የሚሏቸው ሕዝቦችን የሚኮንኑት ዘገባዎች ናቸው። “ነጮች የጥቁር ሰዎችን ችግር ለመረዳት አይፈልጉም” ወይም “ስሜታዊ ዓልባ ናቸው” “Empathy የላቸውም“ የሚለው ነገር፡ ምናልባት እውነት ሊሆን ይችላል። ምን ዓይነት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ ይገርማል!
— When Did Fried Chicken Become a Symbol of Racism?
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia | Tagged: ምግብ ቤት, በርሊን, አፍሪቃውያን, ዘረኝነት, ጥቁሮች, ፖሊስ, Berlin, Germany, KFC, Police, Racism, Restaurant | Leave a Comment »