እስኪ “ዲፕሎማሲ ቅብርጥሲ” የሚለውን የአውሬ ማታለያ ትተን እራሳችንን በሐቀኝነት እንጠይቅ፤ ኤምባሲዎች፤ በተለይ የምዕራቡና አረቡ ዓለማት ኤምባሲዎች ሕዝባችንን ከመተናኮል ሌላ ለሃገራችን የሚያደርጉት ምን በጎ ነገር አለ? ምንም!
ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን የቆመ መሪ በለገጣፎ፣ ሱሉልታና ቃሊቲ የድኸ ኢትዮጵያውያንን ቤት ከማፈራረስ አንጋፋ የሆኑትን የአሜሪካን፣ ፈረንሳይን እና ብሪታኒያን ኤምባሲዎች ቅጽር ግቢ ቆርሶ ለኢትዮጵያውያን ይለግሳል። አይታችኋል የእነዚህን ኤምባሲዎች ቅጽር ግቢ ስፋት? ለኢምፔሪያሊዝማዊ ተንኮል አስበውበት፣ ወይንም ተንኮል ሊሠሩበት ካልሆነ ሌላ ምን ሊያደርጉበት ነው?