Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ማይጨው’

የእስስቱ ግራኝ ፓስተር፤ “በፍል ውሃ አጥምቁኝ ምንም አልሆንም!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2022

የፍል ውሃ ፓስተር

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ብዙዎቻችን ኢትዮጵያን አናውቃትም ዓለም ግን ሊወራትና ሊበላት ተነስቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2022

💥 የሚሰማው ብዙ ሆኖ የሚያስተውለው ግን ትንሽ ነው!💥

💭“የኢትዮጵያ ትንሣኤ የተዋሕዶ ክርስትና ትንሣኤ ነው፤ እግዚአብሔርን የሚያመልክ መሪ ሲመጣ ዛሬ የተደበላለቀችው/የደፈረሰችው ኢትዮጵያ ትጠራለች፤ እጇን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ መንፈሳዊነቷን ትቀበላለች፤ ዛሬ ሁላችንም በረሃብ፣ በሥጋ፣ በጥላቻና በእርስበርስዕልቂት ደዌ ተይዘናልና ከዚህ ሁሉ ደዌ ይፈውሰን።

ቆሻሻው የኢትዮጵያ ዘስጋ መሪ አብዮት አህመድ አሊ እርስበርስ እያባላን ነው፤ ኦርቶዶክሳውያንን በመላዋ ኢትዮጵያ እየጨረሰን ነው፣ ሁሉም ኦርቶዶክስን ማጥፋት ነው የሚሻው። እስስቱ አብዮት አህመድ የራሱን እስኪያዘጋጅና እስኪያመቻች ድረስ እያታለለ/እያጭበረበረ ይሳለቅብናል ያለው፤ ግን ጊዜው አጭር ነው እሱም ነገ ይበላል፤ እግዚአብሔር እስከተወሰነ ጊዜ እንዲያጸዳ ስለሚፈልገው ነው እንጂ እሱም አሟሟቱ የከፋ ነው፤”

ዲያቆን ቢንያም ፍሬው

እንኳን አብሮ አደረሰን! አይዞን!✞

_________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አንድ ጌታ፣ አንድ ሐይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት | ምሥጢረ ጥምቀት – ጥምቀት አንዲት ናት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2022

ጥምቀት የማትደገም፣ የማትከለስ አንዲት ናት፡፡ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ልጅነትን የምናገኝባት ጥምቀት የማትደገምና የማትከለስ አንዲት ብቻ መሆንዋን ሲያስተምር ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…አለ›› ብሏል (ኤፌ.4÷5)፡፡

ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንትም ‹‹ኃጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡›› ብለው አስተምረዋል፡፡ በዚህ የተነሣ ኣርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድ ጊዜ ያጠመቀችውን ድጋሚ አታጠምቅም፡፡ ነገር ግን አማናዊቷን ጥምቀት ቀድሞም አልፈጸሙምና ከቤተ ክርስቲያናችን ውጪ በሌላ በማናቸውም ሁኔታ ‹‹ተጠምቀን ነበር›› የሚሉትን ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሲቀርቡ በሥርዓቷ መሠረት አስተምራ አሳምና ታጠምቃቸዋለች፡፡

በሌላ መልኩ ደግሞ ቀድሞ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ተጠምቆ ኋላ ግን ወደ ሌላ እምነት ቢገባ ተናዞ (ንስሐ ገብቶ) በማየ ጸሎት (መጽሐፈ ቄደር ተደግሞለት) ይረጫል እንጂ ድጋሚ አይጠመቅም፡፡ ቄደር የንስሐ እጽበት ነው፡፡ ያደፈ ልብስ እንደሚታጠብ ሁሉ ይህም ሰው ንጽሕት እምነቱን አሳድፏልና ከኃጢአቱ ለመታጠቡ ምልክት ይሆን ዘንድ በማየ ጸሎት ይታጠባል፡፡

ጥምቀት የማይደገምበት ምክንያት

ሀ. ጥምቀት ከእግዚአብሔር ዳግም የምንወለድበት ምሥጢር ነው፡፡

የሥጋን ልደት ስንመለከት ሰው ከእናቱ ማኀፀን የሚወጣው (የሚወለደው) አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔርም በእውነት አንድ ጊዜ ወልዶናል፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ ብቻ እንጠመቃለን፡፡

ለ. ጥምቀት ከጌታ ሞትና ትንሣኤ ተሳታፊ የምንሆንበት ምሥጢር ነው፡፡

‹‹በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ በጥምቀትም ደግሞ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ›› (ቈላ.2÷12)፡፡ ጌታ የሞተውና የተነሣው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም እኛ ከእርሱ ጋር የምንቀበረውና የምነሣው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ለምን በውኃ እንጠመቃለን

  • ፩. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በውኃ ነው እኛም እርሱን አብነት በማድረግ በውኃ ልንጠመቅ ይገባናል (ማቴ.3÷13-16)፡፡
  • ፪. ጌታችን ለኒቆዲሞስ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም›› ስላለ እኛም የጌታን ትእዛዝ ለመፈጸም በውኃ እንጠመቃለን (ዮሐ.3÷5)፡፡
  • ፫. ሐዋርያት ከጌታ በተማሩት መሠረት ያጠመቁት በውኃ ነው፡፡ ጴጥሮስም መልሶ ‹‹እነዚህ እንደ እኛ ደግሞ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እንዳይጠመቁ ውኃን ይከለክላቸው ዘንድ የሚችል ማን ነው? አለ›› (የሐዋ.10÷46ና 47)፡፡ ፊልጶስና ጃንደረባው ሁለቱም ወደ ውኃ ወረዱ አጠመቃቸውም (የሐዋ.8÷28)፡፡
  • ፬. ውኃ የሰውነትን እድፍ እንደሚያጠራ ሁሉ እንዲሁም ጥምቀት የነፍስን እድፍ ያስወግዳል ያነጻል፡፡
  • ፭. ውኃ መልክን ያሳያል እኛም በውኃ በመጠመቅ የሥላሴን ምሥጢር በዓይነ ኅሊናችን እናያለን፡፡
  • ፮. በጥንተ ፍጥረት መንፈስ እግዚአብሔር በውኃ ላይ ረብቦ እንደነብር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ይገልጻል፡- ‹‹የእግዚአብሔርም መንፈስ በውኃ ላይ ሰፍፎ ነበር›› (ዘፍ.1÷2)፡፡ እንዲሁም በውኃ፣ በሕይወትና በመንፈስ ያለውን ግንኚነት ማስተዋል ይገባል፡፡ ልዑለ ባሕርይ ጌታ በነቢዩ በኤርምያስ አንደበት እንዲህ ሲል ተናግራል ‹‹ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች አድርገዋልና እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል…›› (ኤር.7÷13)፡፡
  • ፯. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ አስተምሯል (ዮሐ.7÷39)፡፡ ለሳምራዊቷ ሴትም ‹‹እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፡፡ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት›› (ዮሐ.4÷14)፡፡
  • ፰. ከላይ በተገለጸው መሠረት ውኃ የሕይወት ምልክት ነው፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደምናነበው ውኃ ለሰማያዊው መንግሥት፣ ለዘላለም ሕይወት ምሳሌ ሆኖ ተገልጿል፡፡ ‹‹እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር አንደተተከለች ፍሬዋን በየጊዜው እንደምትሰጥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል›› (መዝ. 1÷3) እና የመሳሰሉትን ሁሉ እናገኛለን (ራእይ.2÷16፣ 22÷1፣ 22÷17)፡፡
  • ፱. እንግዲህ ውኃ ከክፉ ኀሊና ለመንጻታችንና ለመቀደሳችን ማረጋገጫ መሆኑን ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል አስተምሯል፡- ‹‹ከክፉ ሕሊና ለመነጻት ልባችንን ተረጭተን፣ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን፣ በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ›› (ዕብ.10÷22)፡፡
  • ፲. ለንጊኖስ የተባለው ሐራዊ (ወታደር) የጌታን ቀኝ ጎን በጦር በወጋው ጊዜ ትኩስ ደምና ውኃ ባንድነት ፈሷል (ዮሐ. 19÷34)፡፡
  • ፲፩. ደሙ ለመጠጣችን፣ ውኃው ለጥምቀታችን መሆኑን ሲያጠይቅ ነው፡፡ ይህንንም ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ እንዲህ ሲል ገልጾታል ‹‹በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው፡፡ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በውኃና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡… የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም፡፡… የሚመሰክሩተ መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፡፡ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ›› (1ዮሐ.5÷6-8)፡፡
  • ፲፪. ውኃ በሁሉም ቤት ይገኛል፡፡ በሀብታሙም በድኃውም ጥምቀትም ላመነ ሁሉ የተፈቀደ መሆኑን ለማጠየቅ በውኃ ሆኗል፡፡ ስለዚህም በውኃ ብቻ እንጠመቃለን፡፡ ሥርዓተ ጥምቀቱን የሚፈጽመው ካህን አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ሲባርከው ውኃው ተለውጦ በዕለተ ዓርብ ከጌታችን ቀኝ ጐን የፈሰሰውን ውኃ ይሆናል፡፡

ኣከባብራ በዓል ጥምቀት ኣብ ዓብይ አዲ ❖

💭 “ምስጢራዊቷ የዓብይ አዲ ከተማ | ጂኒው ከመስጊዱ ፈለቀ ፥ ግራኝ በአላሙዲን ተመለመለ | የሉሲፈር ኮከብ”

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

✞✞✞ረቡዕ ፥ ሚያዝያ ፲፱/19 ፪ሺ፫ /2003 .(ቅዱስ ገብርኤል ፥ ትንሣኤ ማግስት)✞✞✞

👉 ልክ እንደ ዛሬው ያኔም ቅዱስ ገብርኤል በረቡዕ ዕለት ነበር የዋለው፤ ዋው!

ዘንድሮ ሁለት መቶ ክርስቲያን የጽዮን ልጆች በሉሲፈራውያኑ ወኪል በግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ተጨፍጭፈው የሰማዕትነት አክሊል በተቀዳጁባት በ ዓብይ አዲ ከተማ ከ ፲/10 ዓመታት በፊት ብዙ ምስጢራዊ ነገሮች ተከስተዋል። ይህ ተሽከርካሪ ነፋስ ጋኔን (አቧራ) ከዚህ መስጊድ ከተላከ በኋላ ልክ በዓመቱ ግራኝ አብዮት አህመድ + የግብጹ ሙርሲ + ሸህ መሀመድ አላሙዲን + ፕሬዚደንት ባራክ ሁሴን ኦባማ ብጹእ አቡነ ጳውሎስን እና ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ገደሏቸው።

💭 በሁለተኛው ክፍል ስለ ኮከቡ እና ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ ሃገር ስለ ቱርክ የቀረበውን መረጃ በጥሞና እንከታተለው። በጣም ጠቃሚ ነውና!

👉 ሉሲፈር የዋቄዮአላህ ባሪያውን ሙስሊሙን አብዮት አህመድ አሊን በዚህ ከአብይ አዲ መስጊድ በወጣው ጋኔን ቀብቶታልን?

😈 ከቀናት በፊት ግራኝ ለቱርኩ ኤርዶጋን የሚከተለውን መናዘዙን የማውቃቸው ቱርኮች አውስተውኛል፤

እኔ ሙስሊም ነኝ፣ ለእስልምና ጉዳይ የቆምኩ አህመድነኝ፣ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት ሙስሊሞቹ ቱርኮችንና ግብጾችን ወንድሞቻችንን ያዋረዷቸውን ተዋሕዶ ትግራዋይንና አማራዎችን እርስበርስ እያባላሁ በመጨረስ ኢትዮጵያን አፈራርሰን ልክ እንደ አፍጋኒስታን ታሊባኖች የእስላማዊቷን ኦሮሚያ ኤሚራት ለመመስረት ቆርጬ ተንስቻለሁ፤ ታሪካዊዎቹን ቦታዎችን በማውደም ላይ ነኝ፣ ታሪካዊ የሆኑት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችንም በማዘጋትና በምትካቸውም የእስላማዊቷን ኦሮሚያ ኤሚራት ኤምባሲዎች ለመተካት አቅደናል፤ ይህ እድል እንዳያመልጠን የግራኝ ቀዳማዊን መሸነፍና ሞት አብረን እንበቀል፣ ድሮንህን ስጠኝ፣ ገንዘብ ካስፈለገም ከሸህ አላሙዲን ይገኛል‘” በማለት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ታሪካዊ ጠላት የሆነችውን የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክን ከአምስት መቶ ዓመታት በኋላ ፀረክርስቲያን ጂሃዷን እንድትደግመው በር ከፍቶላታል።

ጂኒው አብይ ከመስጊዱ በወጣው ጋኔን ልክ በቅዱስ ገብርኤል ዕለት ተጠመቀ ፥ በዓመቱም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እና ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ከእነ አላሙዲን እና ኦባማ ጋር ሆኖ በመግደል እራሱን በሉሲፈራውያኑ አስመረጠ። የተቀባው በዓብይ አዲ ጋኔን ነውን?

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አምኖ ያልተጠመቀ አይድንም | በአክሱም ጽዮን ላይ የዘመተ ሁሉ እንደ አህዛብ አልዳንም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 18, 2022

💭 አንድ ጌታ፣ አንድ ሐይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት | ኢትዮጵያ ላይ የሚኖረው የተጠመቀ ብቻ ነው

✞✞✞[ኤፌ. ፬ ፥ ፭]✞✞✞

በጥምቀት-ያልተጠመቀ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስምና

[፩ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕራፍ ፭፥፰]

ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።”

💭 በእነዚህ ቀናት ቀንደኛው የኢትዮጵያ፣ የተዋሕዶ ክርስትናዋ እና የጥምቀቱ ጠላት ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ጥምቀቱን ከኢትዮጵያዊው ለማራቅና ለመንጠቅ ብዙ ዲያብሎሳዊ ተንኮሎችን በመሥራት ላይ ይገኛል። እንደተለመደው በመቀበጣጠር፣ “ጽዮናዊውን የአጼ ዮሐንስን ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ሰንደቅ መያዝ ክልክል ነው! ወዘተ” በማለት፤ እንዲሁም የአሜሪካ ልዑካንን ወደ አዲስ አበባ በመጋበዝ።

ልብ እንበል፤ ባለፈው የጌታችን ልደት ዕለት አሰቃቂ የድሮን ጭፍጨፋዎችን በትግራይ ያካሄደው የአሜሪካ ልዑካን ከአዲስ አበባ በተመለሱ እና ግራኝ ከፕሬዚደንት ባይድን ጋር በስልክ በተነጋገረበት ማግስት ነው? አሁንስ ጽዮናውያንን በኢትዮጵያዊነታቸው ተስፋ ቆርጠው እንዲገነጠሉና የኦሮሚያ እስላማዊት ካሊፋት ምስረታ ሕልሙን ለማሳካት በወገኖቼ ላይ የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮኖችን በመጠቀምን ጭፍጨፋውን ይቀጥልበት ይሆን?

እንኳን ለጥምቀቱ አደረሰን!

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: