Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘#ማይክሮዌቭ ጨረር’

በጨረር እየጠበሱን ነው | ራዕይ ዮሐንስ ይህን ጠቁሞን ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2020

ለነገሩማ 5ጂ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ የተንቀሳቃስሽ ስልክ ግኑኝነት ቴክኖሎጂ ትውልድ 1ጂ፣ 2ጂ፣ 3ጂ ፣ 4ጂ መዘዝ ይዞብን ነው የመጣው። እንዲያውም የራዲዮና ቴሌቪዥን ማይክሮዌቭና ሳተላይት ቴክኖሎጂ ገና እንደጀመረ ነው ሕዝብን በሰፊው የመቆጣጠሪያ፣ የግለሰቦችንና ሕዝቦችን ባሕርያትን የመቀየሪያ ባጠቃላይ ዲያብሎሳዊ ተግባራታን የመፈጸሚያ ሁኔታዎች የተፈጠሩት።

ይህን አስመልክቶ እ..አ ከ2005 .ም አንስቶ እኔ በግሌ ገና በዩርኒቨርሲቲ እያለሁ የልዑል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እየመራኝ ብዙ አስገራሚ የሆኑ ነገሮችን ለማየት መብቃቴን በጦማሬ ላይ በጊዜው አስፍሬው ነበር። አንቴናዎቹ ገና ሳይስፋፉ ግርግዳን አልፈው ለማዳማጥ፣ ለማየትና ሰዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ተንቀሳቃሽ ቴክኖሎጂዎችን በመኖሪያ አካባቢዎች በየጎረቤቱ አስገብተዋል፤ ይህንም ለማንቀሳቀስ በተለይ መጀመሪያ ላይ ቺፑ የተቀበረባቸውን ግብረሰዶማውያንን ይጠቀሙባቸው እንደነበር በጊዜው አውስቻለሁ።

በተለይ መንፈሳዊ የሆኑ ሰዎች፤ በተለይ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን (ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል መምህራን፣ ካህናት ወዘተ ያልተለመደ የባሕርይ መቀያየር እያሳዩ ነው፤ + “NileSat”, “EthioSat”) ይህን በደንብ ተረድተው አስፈላጊውን መንፈሳዊ ሥራ በመስራት እራሳቸውንና ወገኖቻቸውን ሁሉ መከላከል ይኖርባቸዋል። አባቶች ባካችሁ ወደ ውጩ ዓለም ለህክምና አትሂዱ!” እላለሁ ደጋግሜ። ውጭ ያለን ኢትዮጵያውያንም ይህን አውቀርን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፤ ምስጢሩ ከገባን ምንም የሚያስፈራ ነገር አይኖርም!

ይህን የቅዱስ ዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ በደንብ እናጥናው። 1ጂ፣ 2ጂ፣ 3ጂ፣ 4ጂ፣ 5ጂ፣ መጪዎቹ 6ጂ እና 7ጂ የሰባቱ መላዕክትን ቦታዎች የሚይዙ ይሆኑ? በጣም አስደናቂ ነገር ነው!

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፮]

  • ለሰባቱም መላእክት። ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።
  • ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።
  • ሁለተኛውም ጽዋውን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ እንደ ሞተም ሰው ደም ሆነ፥ በባሕርም ከሚኖሩት ሕይወት ያለበት ነፍስ ሁሉ ሞተ።
  • ሦስተኛውም ጽዋውን በወንዞችና በውኃ ምንጮች ውስጥ አፈሰሰ፤ እነርሱም ደም ሆኑ።
  • የውኃውም መልአክ። ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ፥ ቅዱስ ሆይ፥ እንዲህ ስለፈረድህ ጻድቅ ነህ፤
  • የቅዱሳንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፥ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።
  • ከመሰዊያውም። አዎን፥ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው ብሎ ሲናገር ሰማሁ።
  • አራተኛውም ጽዋውን በፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰዎችንም በእሳት ልታቃጥል ተሰጣት።
  • ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፥ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፥ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሐ አልገቡም።
  • አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች ከስቃይም የተነሳ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፥
  • ፲፩ ከስቃያቸውና ከቍስላቸውም የተነሳ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፥ ከስራቸውም ንስሐ አልገቡም።
  • ፲፪ ስድስተኛውም ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከፀሐይም መውጫ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲሰናዳላቸው ውኃው ደረቀ።
  • ፲፫ ከዘንዶውም አፍና ከአውሬው አፍ ከሐሰተኛውም ነቢይ አፍ ጓጕንቸሮች የሚመስሉ ሦስት ርኵሳን መናፍስት ሲወጡ አየሁ፤
  • ፲፬ ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።
  • ፲፭ እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።
  • ፲፮ በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።
  • ፲፯ ሰባተኛውም ጽዋውን በአየር ውስጥ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ። ተፈጽሞአል የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ።
  • ፲፰ መብረቅና ድምጽም ነጎድጓድም ሆኑ፥ ትልቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ሰው በምድር ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናውጥ ከቶ አልነበረም፤ ከሁሉ በለጠ።
  • ፲፱ ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።
  • ደሴቶችም ሁሉ ሸሹ ተራራዎችም አልተገኙም።
  • ፳፩ በሚዛንም አንድ ታላንት*1* የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሰፍት የተነሳ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፥ መቅሰፍቱ እጅግ ታላቅ ነውና።

______________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: