Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 19, 2022
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡
ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠው ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡
ጥያቄውም አይሁድ ጌታችንን “ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያኝ ካህናት አይደለህ፤ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” የሚል ነበር፡፡ እርሱም ሲመልስ “እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፤ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይን? ወይስ በሰው ፈቃድ?” አላቸው፡፡ እነርሱም “ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፡፡” ተባብለው “ከወዴት እንደሆነ አናውቅም” ብለው መለሱለት፤ እርሱም “እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም፡፡” አላቸው፡፡ ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፤ ልቦናቸው በክፋትና ጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡[ማቴ ፳፩፥፳፫፡፳፯]
ዳግመኛም ይህ ዕለት ጌታችን ስለዳግም ምጽአቱ ሰፊ ትምህርት የሰጠበት ዕለት ነው፡፡ [ማቴ ፳፬ እና ፳፭ እንዲሁም ማር ፲፪ እና ፲፫፣ ሉቃ ፳ እና ፳፩] ላይ የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሠንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡
ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: Abiy Ahmed, Addis Ababa, Aksum, Anti-Ethiopia, Axum, መርገመ በለስስቅለት, መስቀል, ማክሰኞ, ረሃብ, ሰሙነ ሕማማት, ተዋሕዶ, ትግራይ, አረመኔነት, አርብ, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢሳያስ አፈወርቂ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ኤዶማውያን, እስማኤላውያን, ኦርቶዶክስ, ኦሮሚያ, ኦሮሞ, ወንጀል, የጦር ወንጀል, ግራኝ አህመድ, ግድያ, ጠላት, ጥላቻ, ጥያቄና ትምሕርት, ጦርነት, ጭካኔ, ጭፍጨፋ, ጽዮናውያን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, Ethiopia, Famine, Genocide, Holy Tuesday, Holy Week, Jesus Christ, Massacre, Passion Week, Rape, Tewahedo Faith, Tigray, War Crimes | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2021
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
✞✞✞ ሰሙነ ሕማማት ዕለተ ማክሰኞ (ዘሰሉስ)✞✞✞
❖የጥያቄና የትምህርት ቀን❖
በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፫፡፳፭ ፤ ማር.፲፩፥፳፯ ፣ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡
ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ በአንድ አገር የንግድ ቦታን የሚያጸድቅ መንግሥት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልመለሰም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሷል፡፡ “በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ፤ በማን ሥልጣን ነው ይህን የምታደርገው?” ነበር ያሉት፡፡ በራሴ ሥልጣን ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡
ጌታችን እኩይ የሆነውን የፈሪሳውያንን አሳብ በመረዳት “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር ሲል” ጠይቋቸዋል፡፡ ከሰማይ ያልነው እንደ ሆነ ለምን አላመናችሁበትም ይለናል÷ ከሰው ያልነው ከሆነ ሕዝቡ ይጣላናል፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ከዚህ የተነሣ ያቀረቡት የፈተና ጥያቄ ግቡን ሳይመታ ከሽፎባቸዋል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፭]፤ [ማር.፲፩፥፳፯፡፴ ፤ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡
ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡
በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።
👉መድኅንኤል 👉ሕይውታኤል 👉አውካኤል 👉ተርቡታኤል 👉ግኤል 👉ዝኤል 👉ቡኤል
❖ የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን❖
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከልዩ ድንጋፄና ፍርሃት እድን ዘንድ ይህን የቅዱስ ገብርኤልን ድርሳን እንዲህ እያልኩ እጸልያለሁ፤ መድኅንኤል ፣ ሕያውታኤል ፣ አውካኤል ፣ ተርቡታኤል ፣ ግኤል ፣ ዝኤል ፣ ቡኤል ፤ ይህን አስማተ መለኮት እግዚአብሔር ለቅዱስ ገብርኤል የሰጠው መልአኩ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በጀመረ ጊዜ ድል እንዲነሣበት፤ እንዲሁም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማብሠር በተላከ ጊዜ ከቃሉ ግርማ የተነሣ እንዳትደነግጥና እንዳትፈራ መጽንዔ ኃይል እንዲሆናት ነው።
አቤቱ ለእኔ ለአገልጋይህም እንደዚሁ ኃይልና ጽንዕ ሰጥተህ ከመዓልትና ከሌሊት ድንጋፄ አድነኝ፤ አሜን።
ከላይ ከሰማይ ወደ ድንግል የተላክህ ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ደስታን አብሣሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ፅንሰ ቃልን አስተምረህ የምታሳምን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ሰማያዊ ነደ እሳት ዖፈ ርግብ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ፍጹም ደስታን ተናጋሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ከእደ ሞት የምታድን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። የአንተን አማልላጅነት በመዓልትም በሌሊትም ተስፋ ስለምናደርግ ጥበቃህ አይለየን። በነፍስም በሥጋም ታደገን። የእግዚአብሔር ልዩ ባለሟል ነህና፤ ለዘላለሙ አሜን።
አቡነ ዘመሰማያት።
__________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: Addis Abeba, ማክሰኞ, ሰሙነ ሕማማት, ቅዱስ ገብርኤል, ትግራይ, አክሱም, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ክርስትና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥያቄና መልስ, ጦርነት, ጭፍጨፋ, ጽዮን, ፈሪሳውያን, Ethiopia, Holy Tuesday, Holy Week, Jesus Christ, OrthodoxFaith, Passion Week, Pharisees, Questions, St.Gabriel, Tewahedo | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
በእኛ ላይም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላከ፤ የቅድስት ቢተ ክርስቲያንህንም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት እንዲከፈቱ አድርግልን። እስከ መጨረሻዪቱ ሕቅታም ድረስ ልዩ ሦስትነትህን ማመንን ፈጽምልን።
የቤተክርስቲያን ሸምጋይ እና አስታራቂ ሆኖ የመጣው ልወደድ–ባይ የአውሬው መንግስት ኮሮናን ተገን አድርጎ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከቤተ ክርስቲያን ለማራቅ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ እንደሆነ እያየነው ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚው የቤተ ክርስቲያንን ቦታ ለመውረስ ተወዳጅነት እያጡ የመጡትን ቴሌቪዥን እና ኢንተርኔት ጣቢያዎች (ኢቢሲ፣ ፋና)የሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎት በቀጥታ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል። የቤተ ክርስቲያንን እና ሜዲያዎቿን ኃላፊነት በመንጠቅ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎች ይመታል ማለት ነው።
ሲጀመር ዲያብሎስ አስታራቂ ሆኖ እንዲገባብን መደረግ አልነበረበትም፤ ካሜራዎቹንም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲያስገባ መፈቀድ አልነበረበትም። መንግስትና ሜዲያዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየሠሩት ያሉት ወንጀል ለይቅርታ፣ ለዕርቅና ለንስሐ የሚያበቃ አይደለምና።
በደመራ ዕለት መስቀል አደባባይ አጥር ላይ የተላተመችውን የኢቢሲ ድሮን ካሜራ እናስታውሳለን? በሬውንስ? እነዚህ ነገሮች ያለምክኒያት አልተከሰቱም! ዛሬ ግራኝ አህመድ በክቡር መስቀሉ የተሰየመውን አደባባይ እና የጃን ሜዳን ጥምቀተ ባሕር ለመውረስና ያለመውንም አንጋፋ መስጊድ በቅርቡ ለመሥራት በመንቀሳቀስ ላይ ነው። በኮሮና ድራማ ተጠምደን ጸጥ ብለናል፤ አይደል! አዎ! የበሬውን አንጀት ለሞኙ ኢትዮጵያዊ ሰጥቶ አፉን ይዘጋና ሰንጋውን ለራሱ በማግበስበስ ላይ ነው። ትንሽ ከፊት ሲሆን ሀገር ያሳንሳል!
“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው…የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው” ብሎን የለ ተሳላቂው አብዮት። በመስቀል አደባባይ ደመራ ዕለት በሬው የተላከውም በቤተ ክርስቲያን እና ክቡር መስቀሉ ላይ ለመሳለቅ ታስቦ ነበር። አንርሳው!
ወገኖቼ መታለሉ ይብቃ! ይብቃ! ይብቃ! ንቁ! እንንቃ! ነፍሱ እንዳይታወክበት የሚሻ የተዋሕዶ ልጅ ይህን የቀጥታ ስርጭት በዚህ ሰሙነ ሕማማት ከመከታተል መቆጠብ ይኖርበታል።
__________________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ማክሰኞ, ሰሙነ ሕማማት, ትምህርት, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥያቄ, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, Holy Week, Jesus Christ, Passion Week | Leave a Comment »