Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ማተብ’

የእግዚአብሒር ድንቅ ሥራ | በድጋሚ ሕፃኗ ማህተብ አሥራ ተወለደች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 2, 2020

ትክክለኛዋ እምነት በተዓምር፣ በማርያም መቀነት / በቀስተ ደመና የታጀበች እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ አድዋ ዘምታ ጊዮርጊስ ድል ያደረገላት፣ መከላከያ ሚንስትሯ ጊዮርጊስ የሆነ፣ ጳጳሳቷ ለአገር የሞቱ፣ አንድነት የምትሰብክ፣ የድኾች መጠጊያ፣ ፀበሏ የሚፈውስ፣ እምነቷ የሚፈውስ፣ ደመራዋ የሚያምር፣ ጥምቀቷ የሚያምር፣ አፅዋማቷ የሚያምሩ፣ ሥርዓቷ፣ መጻሕፍቷ፣ ገዳማቷ፣ ውቅር ዓብያተክርስቲያናቷ፣ የካህናቱ ዝማሬው፣ ቅኔው፣ ማሕሌቱ፣ ቅዳሴው፣ አለባበሳችን ፥ ሁሉ ነገራችን እንደ ኦርቶዶክሶች የሚያምር የለም።

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

የሰይጣን ምልክት 666 ነው ፥ የክርስቶስ የሆኑት ደግሞ ባንገታቸው ላይ ያለው ማሕተብ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 13, 2019

ትክክለኛዋ እምነት በተዓምር፣ በማርያም መቀነት / በቀስተ ደመና የታጀበች እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ አድዋ ዘምታ ጊዮርጊስ ድል ያደረገላት፣ መከላከያ ሚንስትሯ ጊዮርጊስ የሆነ፣ ጳጳሳቷ ለአገር የሞቱ፣ አንድነት የምትሰብክ፣ የድኾች መጠጊያ፣ ፀበሏ የሚፈውስ፣ እምነቷ የሚፈውስ፣ ደመራዋ የሚያምር፣ ጥምቀቷ የሚያምር፣ አፅዋማቷ የሚያምሩ፣ ሥርዓቷ፣ መጻሕፍቷ፣ ገዳማቷ፣ ውቅር ዓብያተክርስቲያናቷ፣ የካህናቱ ዝማሬው፣ ቅኔው፣ ማሕሌቱ፣ ቅዳሴው፣ አለባበሳችን ፥ ሁሉ ነገራችን እንደ ኦርቶዶክሶች የሚያምር የለም።

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡ ወንድማችን!

+______________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ማሕተቡን አሥራ የተወለደችው ሕፃን እናት ሚስጥሩን ይፋ አደረገች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 11, 2019

ለኢትዮጵያውያን ክብራቸው፣ ኩራታቸውና ደስታቸው ማሕተባቸው እንጂ በደም የተቀባው የኖቤል ሜዳሊያና የአይ.ኤም.ኤፍ ዶላር አይደለም። ከእነ ማሕተቡ መወለድ የበለጠ ፀጋ አለን?

ነፍሳቸውን የሸጡት ሜዲያዎችና እንደ እስስት ተለዋዋጪዎቹ የማሕበራዊ ድህረገጽ ተዋንያዮች ስለ እነ ገዳይ አብይ የቱርክ ድራማ ሌት ተቀን ከመለፈፍ ይልቅ ለራሳቸው ሲሉ ስለ ልጃችን የማሕተብ ተዓምር በማውሳት የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ያለማቋረጥ ማወደስ ቢችሉ ይመረጥ ነበር። ግን አለመታደል ሆኖ አብዛኛዎቹ ሜዲያዎች በአውሬው እጅ ውስጥ ገብተዋል። ስለዚህ፡ ምስክራችን ከላይ ብቻ ነው!!!

የዚህች መልአክ የመሰለች ሕፃን የማሕተብ ተዓምር ዜና የበሰረበት ወቅት ልክ ገዳይ አብይ የኖቤል ሰላም ሽልማቱን ከሚቀበልበት ወቅት ጋር መገናኘቱ ያለምክኒያት አይደለም፤ ሰውየው ከክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ አንዱ እንደሆነ 100% እርግጠኛ ነኝ፤ ስለዚህ፡ በተፈጥሯዊው ማሕተብ በኩል እግዚአብሔር እጅግ በጣም ትልቅ የሆነ መልዕክት እያስተላልፍልን ነው። ጆሮ ያለው ይስማ ፣ ዓይን ያለው ይመልከት፣ ላልደረሰው ያድርስ፡ ለ አስራ ሁለት ሩብ ጉዳይ ሆኗል!

+ ማተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ+

እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ

ፊተኛ ነንና አንዳንሆን ኋላኛ

ህዝቤ ተነቃቃ ተነስ አትተኛ

ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን ጩኽት

የተዋህዶ ልጆች አሁነ ነው ሰዓቱ

አይተን እንዳላየን ስንቱን አሳልፈናል

የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል

አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር

+ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ሚስጢር+

ክርስቲያን ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው!

+____________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው | በማህተብ ምክኒያት መሀመዳውያኑ አንገት በመበጠሳቸው ሕፃኗ ከነማህተቧ ተወለደች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 10, 2019

በእውነት በጣም የሚገርም ነው፤ ያውም በመድኃኔ ዓለም ዕለት ነው ሕፃኗ የተወለደችው። የአብ ሥራ እፁብ ድንቅ ነው! እግዚአብሔር በጥበቡ ያሳድግልን!

[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፩፥፭]

በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።

በአንገቷ ልዩ ምልክት ያሰረች ሕፃን ተወለደች::

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዳንግላ ወረዳ በአባድራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በአንገቷ ላይ ልዩ ምልክት ያሰረች ህፃን መወለዷ ተገለጸ፡፡

የአባድራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አዋላጅ ነርስ እውነቱ አብየ እንደገለፁት ጥቅምት 27 ቀን 212.ም ከሌሊቱ 8፡ዐዐ አካባቢ በውፍታ ዳጢ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ጥሩወርቅ አብነት በአንገቷ ላይ የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉትን የማተብ ምልክት በአንገቷ ያሰረች ሕፃን መውለዳቸውን ተናግረዋል።

ሕፃኗ ስትወለድ 3 ኪሎ ግራም የምትመዝን ስትሆን አሁን ላይ ሕፃኗም ሆነ እናቷ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የሕፃኗ እናት ወይዘሮ ጥሩወርቅ አብነት ስትወለድ ክስተቱ አስደንግጦኝ ነበር፤ አሁን ግን ልዩ ማተብ አድርጋ የተወለደች ሕፃን ልጅ እናት ስለሆንኩ ደስተኛ ነኝብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ዳንግሌላ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: