Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • June 2023
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  2627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ማሪያም አብርሃም’

ባራክ ሁሴን ኦባማ እና ማሪያም አብርሃም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 9, 2014

ErgibEbabሰይጣን ተፈቷል፤ በእሥር ቤት ተዘግቶበት በነበረበት ጊዜ፡ መሠሪና ሥውር ትእዛዙን በረቂቅ መንገዱ እያስተላለፈ፡ ጭፍሮቹና ሠራዊቱ በሆኑት ሰብአውያን ፍጡራን አማካይነት ሲያካሄድ የቆየውን የክፋትና የጥፋት ተልእኮውን አሁን በርኵሱ የመንፈስ አካሉ በገሃድ እየተዘዋወረ ራሱ ሊያስፈጽም እነሆ ነጻነትን አግኝቷል።

ዲያብሎስ እራሱን በግልጽ ለማሳየት ደፍሯል፡ የልብ ልብ ብሎታል፡ በዚህች ባጭሩዋ የነጻነት ጊዜው ብዙ ነገሮችን ለመጣል በብርቱ ይራወጣል፤ ምድራውያንና ሥጋውያን የሆኑትን የዓለም ሰዎች እርስ በርሳቸው ሊያስተላልቅ ከዚህ የተነሳም ፍጥረተ ዓለሙን ለኅልፈት ወደሚያደርሰው የድምሳሴ ጦርነት ያነሳሳቸዋል፤ ያሳልፋቸዋልም።

በሱዳኗ ኦምዱርማን አስቀያሚ እስር ቤት ውስጥ ከዓመት በላይ በመማቀቅ ላይ ያለችው ማሪያም አብርሃም ክርስቲያን በመሆኗ እና ክርስቲያን ባል በማግባቷ ለዚህ ስቃይ በቃች። ፕሬዚደንት ኦማር አልበሽር በ2011 .ም ንግግራቸው ሱዳን የአረብ እና የእስላሞች አገር ብቻ ትሆናለችብለው ነበር። እንዳቀዱትም፡ እንደ ማሪያም በመሳሰሉት ክርስቲያኖች ላይ አስከፊ የሆነ ሁኔታ ከእለት ወደ እለት በመጨመር ላይ ይገኛል። ወንድሟየተባለው ግለሰብ ማሪያም እንድትገደል በግልጽ መናገሩ ባካባቢያችን ምን እንደሚከሰት ብዙ ነገር ሊያስተምረን ይችላል፤ የጎረቤቶቻችን ጉድ ዓይን ያለው እዚህ ይመልከት፣ ጆሮ ያለው ይስማ!

የማሪያም ጉዳዩ የዓለም አቀፍን መገናኛ ብዙኃን ትኩረት ማግኘቱ ያለምክኒያት አይደለም። የእስልምና ተከታዮች በአፍሪቃ ሆነ በእስያ፡ በአውሮፓ ሆነ በሰሜን አሜሪካ ሙስሊም ባልሆኑ ሰዎች ላይ እያደረሱ ያሉት በደል ብዙ አገሮችንና ሕዝቦችን በማስቆጣት ላይ ይገኛል። በአሜሪካ እና በአውሮፓ 2/3 የሚሆኑት ነዋሪዎች ሙስሊም የሆኑ ሰዎች ወደ አገሮቻቸው እንዳይገቡ ይሻሉ። በአመራር ቦታ ላይ የሚገኙት ሃይሎች ግን ይህን ግልጽ የሆነ ክስተት ማየት/መገንዘብ አይፈልጉም፤ ምክኒያታቸው፡ ምናልባት፡ አሕዛቡን ክንዴት አድርሶ አብዮታዊ ሁኔታ በመፍጠር ሉሲፈራዊ ተልኳቸውን ለማሟላት ስላቀዱ ሊሆን ይችላል። እየተሠራ ያለው ሥራ ዓይን ያወጣ ነው! ያሁኗ አሜሪካ የምናውቃትና የምንወዳት አሜሪካ አይደለችም።

ባራክ ኦባማ ይህን ሉሲፈራዊ ተልዕኮ ለማራመድ የተመረጡት ግለሰብ ይሆኑ?

ማሪያም አብራሃም ልክ እንደ ባራክ ኦባማ ከሙስሊም አባት የተወለደች ናት። ከሙስሊም አባት የተወለደ ሙስሊም ነው የሚል እምነት በሙስሊሞች ዘንድ አለ። ማሪያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ በሆነችው ኢትዮጵያዊት እናቷ በማደጓ፡ አምልኮ ጣዖት ባሕርይ ያለውን እስልምናን በዜሮ ታባዛዋለች። ስለዚህ አባቷ በሕይወቷ ምንም ዓይነት ሚና አይጫወትም። ባራክ ኦባማ ዒአማናዊት በሆነቸው እናቱ እንዲሁም ሙስሊም በሆኑት ኪኔያዊ እና ኢንዶኔዢያዊ አባቶች ስላደጉ እሳቸው ሙስሊም ናቸው ማለት ነው። እሳቸው ክርስቲያን ነኝእንደሚሉት በርግጥ ክርስትናን የተቀበሉ ግለሰብ ከሆኑ፡ እንደ አንደ ከዳተኛ እስላም ወይም፡ በማርያም ላይ እንደተፈረደው፡ ይገደሉ ዘንድ ፋትዋይታወጅባቸው ነበር።

ባራክ ኦባማ ጣት ላይ የተሰካው የጋብቻ ቀለበት የእስልምና እምነትን ሸሀዳየሚገልጽ ዓረፍተ ነገር በአረብኛ ተጽፎ ይነበባል። ፕሪዚደንት ኦባማን በአማካሪነት ያገለግሉ ዘንድ ስልጣን የተሰጣቸው ብዙ የሙስሊም ወንድማማቾች አባላት አሉ። ባለፈው ዓመት የ ሲአይኤ ሃላፊ ሆነው የተመረጡት፡ ጆን ብሬነን በሳዑዲ አረቢያ ቆይታቸው እንደሰለሙ ይወራል። ኡ ኡ ኡ!!!

ፕሬዚደንት ኦባማ የሚወነጀሉበትን መንገድ ሆን ብለው በመፈለግ ላይ ይሆኑ?

የአሜሪካን ወታደራዊ ሠራዊት በመክዳት ላለፉት 5 ዓመታት ከአፍጋኒስታን ታሊባኖች ጋር ተቀላቅሎ የነበረው አሜሪካዊ ወታደር፡ Bergdahl’ (ስሙ ከBenghazi (Sep 11 2012), Baghdad ጋር ይመሳሰላል) በፕሬዚደንት ኦባማ ጥረት ተፍቷል። ይህ ከዳተኛ ወታደር6 አሜሪካውያን ወታደሮች ሞት ተጠያቂ ከመሆኑም አልፎ እስልምናን ተቀብሎ በአሜሪካ ላይ ጂሃድ ለማካሄድ ፕሮፓጋንዳ ይነዛ እንደነበር ታውቋል። አብዛኛውን የአሜሪካ ሕዝብ ያሳዘነው እና ያስቆጣው፡ የዚህ ቅሌታም ግለሰብ አባት በ ኋይት ሃውስከፕሪዚደንት ኦባማ ጎን ቆሞ ቢስሚላህየሚለውን እስላማዊ ቃል መናገሩ ነው። ( ቢስሚላህ” = 666 ) አባትዬው ይህን የአውሬ ቃል ሲተነፍስ ፕሬዚደንት ኦባማ ወዲያው ያሳዩትን ፈገግታ እዚህ እንመልከት

ማሪያም አብርሃም ስለደረሰባት በደል፡ ፕሬዚደንት ኦባማ አንዲትም ቃል አልተነፈሱም። የአሜሪካዊ ዜግነት ያለውን ባለቤቷንና ልጆቻቸውን ከሱዳን ነፃ ለማውጣት እና ወደ አሜሪካ ለማምጣት፡ በካርቱም የአሜሪካ ኢምባሲ እንዳይተባበር ትእዛዝ የተሰጠ ይመስላል። በሌላ በኩል ግን ፕሬዚደንት ኦባማ የዩኤስ ምክር ቤትን ሳይነጋግሩ ለብዙ አሜሪካውያን ሞት ምክኒያት የሆኑትን አፍጋኒስታውያን ሽብር ፈጣሪዎች ከእስር ቤት በመልቀቅ፣ ከዳተኛውን አሜሪካዊ ወታደር እንደ አንድ ጀግና ለመቀበል በመዘጋጀት ላይ ናቸው። በዚህ አሳፋሪ ሁኔታ የተቆጡ አሜሪካውያን ለግለሰቡ ምንም ዓይነት ያቀባበል ሥነስርዓት እንደማያካሂዱ ወስነዋል። በሌላ በኩል፡ በግለሰቡ እና ቤተሰቦቹ ላይ የግድያ ዛቻዎች በመጉረፍ ላይ ናቸው። አባትየውም አሁን ምርመራ እየተካሄደበት ነው።

ማሪያም አብርሃም እሥር ቤት የወለደችውን ሴት ልጇን ማያየሚል ስም በሰጠች በማግስቱ፡ ታዋቂዋ ጥቁር አሜሪካዊት ደራሲ ማያ አንጀሉአረፈች። ይህ ምን ሌላ የሚነግረን መልዕክት ይኖር ይሆን?

__

 

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: