ፓሪስ ከተማ በሚገኝ ህንጻ በአራተኛ ፎቅ ባልኮን ላይ ተንጠልጥሎ ሊወድቅ የነበረውን ሕጻን ልጅ ለማዳን በ 30 ሰከንድ ውስጥ አራት ፎቆችን እንደ ሸረሪት በመውጣት ነበር ሊያድነው የበቃው። የሕፃኑ ወላጆች በወቅቱ ቤት አልነበሩም።
የ 22 ዓመቱ የማሊ ተወላጅ፡ ማማዱ ጋሣማ ሕይወቱን ለመገንባት ከጥቂት ወራት በፊት ነበር ወደ ፈረንሳይ የመጣው።
አሁን በዚህ የጀግነነት ድርጊቱ፡ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት አማኑኤል ማክሮን ጋር በኤሊሴ ቤተመንግስት ለመገናኘት በቅቷል። በዚህም ወቅት፡ ፈረንሳይ ማማዱ ጋሳማን የፈረንሳይ ዜጋ እንዲሆን እንደምታደርግና በእሳት አደጋ ቡድን ተቀጥሮ እንደሚሰራም ፕሬዚደንቱ ቃል ገብተውለታል።
ጋሳም አሁን ‘ስፓይደርማን‘ ወይም ‘ሸረሪት ሰው‘ የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቶታል።