ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ መጥፋታቸው የማይቀር ነውና፡ አላሙዲንን፡ “ና! ወደ ቅድመ አያቶችህ ቤተክርስቲያን ተመለስ!’ እንበለው።
የአላሙዲን ድርጅት “ሜድሮክ” በለገንደቢ ወርቅ እንዳያወጣ መከልከሉ ጥሩ ነው፡ ትክክለኛም ውሳኔ ነው። እነዚህ “ባለ ሃብቶች” በአንድ በኩል ወርቁን፣ ዕንቁውን፣ እህሉንና ከብቱን ይዘርፋሉ፣ ገነዘቡንም ወደ ውጭ ይዘው ይጠፋሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ወንዙን፣ ውሃውን፣ መሬቱንና አየሩን እያድፈረሱ፣ እየበከሉና እያረከሱ ልጆቻችንን ለአስከፊ በሽታዎች ያጋልጧቸዋል፣ ብሎም የፈረንጁ “መድኃኒት” ባሪያ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል። ይህ እኮ ተወዳዳሪ የሌለው ግፍ ነው!
[መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፭፥፳፮]
“በኀጥእ ፊት የሚወድቅ ጻድቅ እንደደፈረሰ ፈሳሽና እንደ ረከሰ ምንጭ ነው።”
የሚከትለውን አጭር መልዕክት ከሁለት ዓመታት በፊት ነበር ያቀረብኩት፤ በዚያ ወቅት “ጠበል አያድናችሁም፡ እንዲያውም ያሳምማችኋል!“ ሊለን ነው?“ በማለት እራሴን ጠይቄ ነበር።
ፀበላችን ለኛ ፈዋሻችን ለዳቢሎስ ደግማ እንደ እሣት የሚቃጠልበት ነውና በያዝነው ዓመት ላይ፡ ቅ/ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ የመድኃኔ ዓለም ፍልውሃ ፀበል ሲወጣ፡ እነ “ሸገር ኤፍ ኤም” “ውሃው ኬሚካል አለበት መርዝ ነው!“ ብለው የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ በመርጨት ፈውስ–ፈላጊ ኢትዮጵያዊ አማኝን ሊያስፈራሩት ሞክረው ነበር።
ሰይጣን ከቤተክርስቲያን አይርቅም | ዲያብሎስ ብርቅ ውሃችንን እና ጠበሎቻችንን ሊበክልብን ይሻል
ይህ እጅግ በጣም አሳዛኝና ዲያብሎሳዊ የሆነ ሥራ ነው። ዲያብሎስ፡ ክርስቲያን ኢትዮጵያን ከሁሉም አቅጣጫ እየተፈታተናት ነው!
ይህች አነስተኛ ወንዝ ሳሪስ አካባቢ ትገኛለች። ወንዟ የምታልፈውም – እኔ ከደረስኩባቸው አካባቢዎች መካከል – በ ላፍቶ መድኃኒዓለም፣ ኪዳነምህረት እንዲሁም ሳሪስ አቦ አብያተክርስቲያናት እና ጠበላት አቅራቢያ ነው። ወንዙ ውስጥ ለሚታዩት ነጭ የአረፋ እና ቀይ፡ ደም መሰል ቀለማት መንስዔው ያው ፋብሪካ ነው። ለቡ /ላፍቶ አካባቢ የሚገኙ ፋብሪካዎች የኬሚካል ቆሻሻዎቻቸውን እንዳፈቀዳቸው ወደ ወንዙ እየደፉ ብርቅ የሆነውን ውሃችንን በመበከል፤ እጅግ አሳዛኝ የሆነ ተግባር፣ ከፍተኛ ወንጀል እና ኃጢአት ይሠራሉ። ለጊዜው ጠበላቱን እንደማይነካ ደርሼበታለሁ፡ ግን፡ እስከ መቼ?! “ጠበል አያድናችሁም፡ እንዲያውም ያሳምማችኋል” ሊለን ነው?
ቸሩ እግዚአብሔር ንብረቱን ይከላከላልና፡ ሕዝባችንንም በአግባቡ ይጠብቅልን!