Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሚያዚያ ፪ሺ፲፩’

ቃሊቲ ገብርኤል አጠገብ ሁለት አዳዲስና ድንቅ የሆኑ ዓብያተክርስቲያናት በህልሜ ታዩኝ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2019

ህልሜ ይህን ይመስላል፦

በቃሊት በኩል ሳልፍ መጀመሪያ የታየኝ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ቀለማት የተከበበው ጥንታዊው እና ክቡ የቤተክርስቲያን ህንጻ ነው። “ይህን ቤተክርስቲያን እንዴት እስካሁን አላውቀውም?” በማለት እራሴን በመጠየቅ ዘወር ስል ሌላ ቤተክርስቲያን ታየኝ፤ በቦታው ያለውን የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ህንፃ ይመስላል፤ ነገር ግን እርሱም አዲስ ሆነበኝ እንዴት እስካሁን አላየሁትም? በማለት ተገርሜ በቤተክርስቲያኑ ግዙፍነትና ውበት እጅግ በይበልጥ ተደነቅኩ። “ካሜራ ይዤ መምጣት አለበኝ” እንዳልኩ ህልሙ አለቀ።

ይህን ቪዲዮ ሳዘጋጅ ባለፈው ዓመት ልክ በሁዳዴ ፆም መግቢያ፣ ረቡዕ፣ የካቲት ፯፣ ፪ሺ፲ ዓ.ም ላይ በቃልቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ድንገተኛ የእሳት አደጋ መድረሱን አስታወስኩ።

ይህ ህልም የታየኝ በአቡነ አረጋዊ ዕለት እና (የቆሼን አደጋ አስመልክቶ ቪዲዮዎች አቅርቤ ነበር)በሁዳዴ ፆም ማብቂያ ላይ ነውምን ሊሆን ይችላል? ቅዳሜ የቅዱስ ገብርኤል ዕለት ነውሁሉም ለበጎ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ!

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: