Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሚኒሊክ’

በቅ/ጊዮርጊስ ዕለት የኢትዮጵያ ቀለማት አበሩ ፥ የዕምዬ ምኒሊክ ፈረስ “እህህህህህ!“ አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 30, 2020

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ

! የኢትዮጵያ ጠላቶች! ! የተዋሕዶ ጠላቶች! ! የሰንደቁ ጠላቶች!ዋ!

*ፈረስ*

እህህህህህ!

ይህ ድንቅ የክቡር ያሬድ ገብረ ሚካኤል ግጥም የወቅቱን ያገራችንን እና የስደተኛውን ሕዝባችንን ተፈታታኝ ሁኔታ ያንጸባርቅልናል።

የጀግና ባለሟል እኔ አቶ ፈረስ፡

ከተፋፋመው ጦር ወስጄ እማደርስ፡

እዘኑልኝ በጣም ሳልለይ አንድ ቀን፡

ወሪሳ ስመታ ስማርክ ጠላትን፡

ይህ ብቻ ነበረ የኔ ሙያ እስካሁን።

ሐሴትም እንደሆን ይጠየቅ ጐበና፤

ምንም እሱ ቢሞት ሥራው ሁሉ አለና።

መቼም በዚህ ዓለም ሁሉ ሲያልቅ አያምር፤

ጋሪ በወገቤ ያናጥር ጀመር።

በጣታቸው እንኳ የማይነኩትን፡

ሸክም አሸከሙኝ የማልችለውን።

ወንዶች እያወቁ የፈረስን ጥቅም፡

ምጣድ አከንባሎ እንደምን ልሸከም።

በተከበርኩበት ወርቅ ተሸልሜ፡

ይኽው እዞራለሁ በርሜል ተሸክሜ።

እንዲህ ወደ ጓላ ይወለዳል ጉድ፡

የወንዶች ባለሟል ሲሸከም ምጣድ።

ጀግና የሆነ ሰው የፈረስ ስም አለው፡

በዛሬውስ ጊዜ ስሜ ጠፋ ምነው።

ወገቤ ተቆርጧል ጋሪ በመጎተት፡

በወንድ ልጅ አምላክ አሳርፉኝ ጥቂት።

ረረስ ሠረገላ ይስባል ቢሏችሁ፡

ትገርፉት ጀመር ወይ ግንድ አሸክማችሁ፡

ጣልያን እስከ መቼም ነፍስህ አይማር፡

እኔ እሰቃያለሁ በተከልከው ግብር፡

የኔማ የፈረስ ሙያዬ አይነገር፡

የወርቅ የበር ዋንጫ የማስገኘውን ክብር፡

ይኸው ዛሬ ጋሪ ስጐትት በምድር፡

ተገጥቧል ጀርባዬ አልሰማም ወይ እግዜር።

ተመክቼ ነበር በጐበዛዝት፡

አሳልፈው ሰጡኝ ጋሪ እንድጐትት፡

እየገፉኝ ያልፋል በኔ ትዳር ገብቶ።

መቼም በኔ ትዳር ምቀኛዬ በዝቷል፡

በምድር በሰማይ ላይ መንገዱን ዘርግቷል።

ክብረት መታገል መቼም አይቀጣ፡

የሚያስታግሥ ነገር ፈጣሪዬ ያምጣ።

ወርቅ መጣብር ነበር የፈረሱ ጌጥ፡

እዩት የዛሬውን በጋሪ ስጐብጥ።

አንድ ሰው ሲቀመጥ ወትሮ በጀርባዬ፡

እቍነጠነጥ ነበር ልሸምጥ ብዬ።

የዚያን ጊዜ ግፉ እንዳይቀር ብድሩ፡

ሦስቱ በኔ ላይ መሳፈር ጀመሩ።

መቼ ይኽ ብቻ ኧረ አያልቅም ጉዱ፡

ጋሪውና ጎማው አይጣል መካበዱ።

በዚያም በዚያም ሆነ ዛሬ የኔ ሸክም፡

ከስድስት ሰዎች ቢበልጥ እንጂ አያንስም።

እነ ኦቶመቢል ሠልጥነው ዛሬም፡

ሊያስወጡኝ ፈለጉ ከዋናው ከተማ።

ዘመናዊው አውቶ ሉክሱ ኦፔልማ፡

እንደ ውሀ ሲፈስ በመላው ከተማ።

የወሩን ጐዳና ባንድ ቀን ገሥግሦ፡

ደከመኝ አይልም የልቡን አድርሶ።

ሲሔድ አይነቀንቅ ድካም አይሰማ፡

ዓለም አይደለም ወይ በሱ መጓዝማ።

ጐማው ሲፈነዳ ቢነዚኑ ዕልቅ ሲል፡

መቼም አይቀርልኝ ፈረስ ጥሩ መባል።

ምንም አራት እግር ቢኖራት መኪና፡

እንደኔም አትፈጥን መንገዱ ካልቀና

ጐማው እስኪነፋ ቤንዚኑ እስኪገኝ፡

ከኔ ራስ አይወርድም ችግር ገፊ ነኝ።

አትጨክንምና አንተ በፈረስ፡

ከዚህ ጭንቅ አድነኝ ቅዱስ ጊዮርጊስ።

________________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: