Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መዝሙር’

😇 ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 7, 2022

በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከከበሩት ቅዱሳን መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል /ጦቢት ፲፪፥፲፭/፡፡

ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ መልአከ ጥዒና ወሰላም /የሰላምና የጤና መልአክ/ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሩፋኤልየሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡

የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ኹሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል /ሄኖክ ፲፥፲፫/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” እንዳለ ሄኖክ /ሄኖክ ፮፥፫/፡፡

ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው ለማኅፀን ችግር ኹሉ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት፣ በማኅፀን እያለ ተሥዕሎተ መልክዕ” (በ አርአያ መልኩ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በወሊዳቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡

አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል /ጦቢት ፫፥፰-፲፯/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል “ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ተብሎ እንደ ተጻፈ /ሄኖክ ፫፥፭-፯/ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው /ሄኖክ ፪፥፲፰/፡፡

______________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

❖ ይእከለናባ! ❖ | ዘማሪት ትርሃስ ገብረ እግዚአብሔር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 6, 2021

✞✞✞[ድጕዓ ኤርምያስ ምዕራፍ ፫፥፵፰]“ብጥፍኣት ሕዝበይ ካብ ዓይነይ ከም ማይ ርባ ንብዓት ይውሕዝ ኣሎ።”

✞✞✞[ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫፥፵፰] “ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች።”

“ደጕዓ” የሚለው የትግርኛ ቃል “ሰቆቃው” ማለት መሆኑን ዛሬ ተማርኩስለ ዘማሪት እኅታችን ትርሃስ ገብረ እግዚአብሔር ከሰማሁ በጣም ቆየሁ፤ እስኪ ዛሬ ባለ እግዚአብሔር ነውና ትርሃስን ልፈልግ ስል ይህን ድንቅ መዝሙር አገኘሁና እምባዬ መጣ። ከሁለት ቀናት በፊት በዕለተ መድኃኔ ዓለም “መልክአ መድኃኔ ዓለም”ን ለማንበብ ወደ በረንዳ ስወጣ ሁለት ነጫጭ እርግቦች መጥተው ደረጃው ላይ አረፉ፤ ያኔም በደስታና በመገረም እምባዬ መጣና መልክ አ መድኃኔ ዓለምን ሳነብ የሚከተለው አንቀጽ ትኩረቴን በይበልጥ ሳበው፤

❖❖❖“ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ አቤቱ ከችግርና ከፈተና አድነኝ፣ አባትህም ‘በምስሕ ደብረ ጽዮን‘ በሚያደርገው ታላቅ የምሳ ግብዣ ላይ ይዘኽኝ ግባ፣ ከአንተ በቀር ሌላ የማውቀው ዘመድ የለኝምና።”

እንግዲህ ወዲያው ብልጭ ብለው የታዩኝ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ነበሩ። “ምን ሊሆን ይችላል?” ብዬ በመጠየቅ እስካሁን በማሰላሰል እና መልሱን ለመገመት በመሞከር ላይ ነኝ። በጣም ይገርማል!

ባለ እግዚአብሔር ሆይ በዕለተ ቀኑ ሐገራችን ኢትዮጵያን ከነገሡባት እርኩስ ጠላቶቿ አድነህ ስላም አድርግልን፣ በትግራይ የሚሰቃዩትን አባቶቻችንን፣ እናቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንን እና እኅቶቻችንን ሁሉ ጠብቅልን፣ ለታመሙት ምሕረት ላጡት ማግኘቱን፣ በስደት ዓለም ያሉትንም በያሉበት ጠብቅልን። መልካም ዕለተ ስንበት፣ መጭዎቹንም የተባረኩና የተቀደሱ ሳምንታት፣ ወራት እና ዓመታት አድርግልን።❖

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቤተ ክርስቲያን ሆይ መከራሽ መብዛቱ፤ ከአንቺው አብራክ ወጥተው ጎራዴ አነገቱ፤ ተባብረው ሊወጉሽ ባንቺ ላይ ዘመቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2020

ሳሪስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በንቀት የሚያየን መንግስት የማምለጫ ቀዳዳ ተትቶለታል፤ እንደለመደው በዲያብሎስ ምክር ወደ መፈጸሚያው ጨለማ ካልሄደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 18, 2019

+________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቤተ ክርስቲያን ሆይ መከራሽ መብዛቱ፤ ከአንቺው አብራክ ወጥተው ጎራዴ አነገቱ፤ ተባብረው ሊወጉሽ ባንቺ ላይ ዘመቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 15, 2019

+_________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያን አትርገም ባላቅ እንዳዘዘህ ፥ ከእግዚአብሔር መጣላት እንዳይሆን ፍጻሜህ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 20, 2019

የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ – “ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን ተጣላልኝ” ብሎ በለዓምን ከምሥራቅ ተራሮች አስጠራው።

ባላቅ በአንድ ወቅት የሞዐብ ንጉስ የነበረ ሲሆን፤ በለዓም ግን ከሞዐብ ትንሽ ራቅ ያለ ሥፍራ ላይ ተቀምጦ በረጋሚነት የሚተዳደር ሰው ነበር፡፡ እስራኤላውያን ከግብጽ ወጥተው ወደ ከነአን ጉዞ መጀመራቸውን ተከትሎ በምድሩ እንዳያልፉ፡ በተለይም ከሰማው ዝናቸው አንጻር ሰግቶ በለዓምን አስመጥቶ በሙዋርት ሊያስረግማቸውና መንገድ ሊያስቀራቸው ሽቶ ነበር፡፡ በዚህ መልክ ነው እንግዲህ በለዓምን የሚያግባቡ ተለቅ ተለቅ ያሉ ሰዎች ተልከው ከቀናት በኋላ ተክተልትለው አብረው የደረሱት፡፡ ቢሆንም እቅዳቸው ሳይሰምር ቀረ፡፡ ለሦስት እና ለአራት ጊዜ ፈጽሞ መባረክ ብቻ እንጂ መርገም ከቶ አልተቻለም ነበረና፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር በስውር ለሕዝቡ እየተሟገተ ነበር፡፡ ምንም እንኳ በዘኁልቁ መጽሐፍ ላይ ሁለቱ ሰዎች በዚህ መልክ እንደተለያዩ ቢገልጽም፤ አዲስ ኪዳንን ጨምሮ በሌሎች ስፍራዎች ላይ በለዓም የሰራው ተንኮል ቁልጭ ብሎ ወጥቷል፡፡

በለዓም ሁለት መልክ ያለው፣ ሁለት ምላስ ያለው፣ ከባድ ሰው ነበር፡፡ ፊት ለፊት እስራኤልን ይመርቃል፣ ያደንቃል ፣ እግዚአብሔር በመካከላቸው ያለ ታላቅ ሕዝብ መሆኑን ይናገራል፣ ከአንበሳ ደቦል ጋር ያመሳስላቸዋል፣ ሞታቸውን እንኳ እኔ ልሙት ብሎ እስኪመኝ ደርሶ ይታያል/ዘኁ.2310……../፤ ዞር ብሎ ደግሞ የሚጠፉበትን፣ ተሰነካክለው የሚወድቁበትን ጉድጓዳቸውን ይቆፍራል፡፡ ያወቀውን ድካማቸውን አጋልጦ ሰጠ! ድካማቸውን ፈጽመው እንዲወድቁበት ተጠቀመበትከፊት ጥሩ ስለሚናገር ማንም እርሱን ጠላት ነው ብሎ ሊፈርጀው አይደፍርም ከጀርባ ግን ሐሜት አለ! እየሳቀ የሚገድል ቀን ጠብቆ አሳልፎ የሚሠጥ ከባድ ሰው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት መተት ያላጠፋው ሕዝብ፣ ሙዋርት ያልገደለው ሕዝብ፣ ከቶ እርግማን ሊሰራበት ያልቻለ፣ ሊረገምም ያለተቻለ የእግዚአብሔር ሕዝብ በድካሙ ምክንያት መንገድ ቀረ‹! በአንድ ቀን ብቻ ሃያ አራት ሺህ ሰዎች ሞቱ! ይለናል / ዘኁ.25.9/፡፡

በለዓምም ከተራራ ላይ ሆኖ ሕዝቡን እያዬ፦“ …በአምቦች ራስ ላይ ሆኜ አየዋለሁ፥ በኮረብቶችም ላይ ሆኜ እመለከተዋለሁ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚቀመጥ ሕዝብ ነው፥ …. ይህ ሕዝብ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፥ እንደ አንበሳም ይነሣል…..” እያለ ባርኮቱን ቀጠለ።

ይህኔ ንጉሡ ተበሳጭቶ በለዓምን፦ “ይህን ሕዝብ እንድትረግምልኝ አስመጣሁህ፤ አንተ ግን ሦስት ጊዜ ባረካቸው፤ ምንድነው እየሠራህ ያለኸው?” ሲለው በለዓምም እንደሚከተለው መለሰለት፦” እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? አንተ እንድረግማቸው አስጠራኸኝ፤ ጥሪህን አክብሬ ያልከኝን ላደርግ መጣሁ፤እግዚአብሔር ግን የምርቃትን ቃል በአፌ አኖረ።”

እኛስ ከዚህ ምን እንማራለን? እየሳቁ የሚገድሉ፣ ፊት ለፊት ጥሩ ነገር ያወሩና ከጀርባ ጉድጓድ የሚቆፍሩ …በተለይ እግዚአብሔር ቤት ውስጥ በርካቶች እንዳሉ ሲሰማ አያምም ወይ? ዞረው የሚያሙ፣ ድካሙን እንዲያስተካክል ለወንድማቸው ከመናገር ይልቅ ለሌላው /ለገዳይ/ አሳልፈው የሚሰጡ፣ በለዓም ለደሞዝ ተታሎ ይህን እንዳደረገ ተጠቅሷል፡፡ እንዲህ ባለ ምድራዊ ጥቅማ ጥቅም የሚታለሉ፣ እውነትን የሚሸቃቅጡ፣ ለሆዳቸው ያደሩ፣ እውነትን መጋፈጥ አንድ ቀን እንኳ የተሳናቸው፣ ዘላለማዊውን ነገር የረሱትን ይመስላል፡፡

ትንሽ ከፊት ሲሆን ሀገር ያሳንሳል

ታላቋን ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ ያሉት በለዓማውያን ጠላቶቿም፡ ሕዝባችን እንደ እንስቲቱ አንበሳ ጋደም ሲል፤ የተኛና ያንቀላፋ እየመሰላቸው በግፍ ላይ ግፍ፣ በበደል ላይ በደል ሲፈጽሙበት በተደጋጋሚ ይስተዋላሉ። ከዚያም አልፈው “ተቆጣጥርነዋል፣ እንዳሰኘን መንዳት እንችላለን፣ ከእንግዲህ ጠራርገን በልተነዋል፤ ሀገራዊ (ኢትዮጵያዊ ስሜቱን) ጨርሰን አጥፍተነዋል።” ብለው የደመደሙባቸው አጋጣሚዎችም ጥቂት አይደሉም። ይሁንና የተስፋ ክር የሰለሰለበትና ሁሉ ነገር ያለቀለት በሚመስልበት ሰዓት ይህ እንደ እንስቲቱ አንበሳ ጋደም ያለው ሕዝብ ድንገት አፈፍ ብሎ “ኢትዮጵያ!” በማለት እየተነሳ ሲያስደነግጣቸው ይታያል።

“…ከፊት ጥሩ ስለሚናገር ማንም እርሱን ጠላት ነው ብሎ ሊፈርጀው አይደፍርም ከጀርባ ግን ሐሜት አለ! እየሳቀ የሚገድል ቀን ጠብቆ አሳልፎ የሚሠጥ ከባድ ሰው ነበር

“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸውየሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸውከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይብለህ ተርትባቸውብሎን የለ በለዓም አብዮት አህመድ አሊ

ባላቅ (ባራክ ሁሴን ኦባማ) በለዓም (አብዮት አህመድ አሊ)

ሁለቱም የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸላሚዎች ናቸው፤ ሁለቱም ሙስሊሞች ናቸው፣ ሁለቱም ግብረሰዶማውያን ናቸው፣ ሁለቱም ለወርቅ እና ለጥቅም የሚኖሩ አታላዮች ናቸው፣ ሁለቱም እየሳቁ የሚገድሉ ቀን ጠብቀው አሳልፈው የሚሰጡ ከሃዲዎች ናቸው፣ ሁለቱም እንደ ጠዋት ጤዛ (Snowflakes) የሚርግፉ ናቸው።

ኢትዮጵያዊነት በነበለዓም እርግማንና ሟርት አይጠፋም! በሁለቱም ላይ እሳት ይወረድባቸዋል!!!

[የይሁዳ መልእክት ምዕራፍ ፩፥፲፩]

ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።”

***ኢትዮጵያን አትርገም***

ኢትዮጵያን አትርገም ባላቅ እንዳዘዘህ /2/

ከእግዚአብሔር መጣላት እንዳይሆን ፍጻሜህ /2/

በለአም ሆይ ለወርቅ ለጥቅም አትገዛ

ንጉስም ይረግፋል እንደ ጠዋት ጤዛ (አዝ)

እግዚአብሔር ሳይረግም የኢትዮጵያን ህጻን

እንዴት ትረግማለህ አምላክ ያልጠላውን

በአንባዎች እራስ ሆኜ አየዋለው

ኢትዮጵያ ኃያል ነው በረከት የሞላው

አዝ ————-

በአንባዎች እራስ ሆኜ አየዋለው

ኢትዮጵያ ኃያል ነው በረከት የሞላው

በኮረብቶች አናት ግርማ የለበሰው

ኢትዮጵያዊ ሁሌም አሸናፊ እኮ ነው

አዝ ————-

ብቻውን ይኖራል በአህዛብ ተከቦ

በክረምት በበጋ በጸደይ አብቦ

የኢትዮጵያን እርቦ ማነው የሚቆጠረው

የማይነዋወጽ የእግዚአብሔር ግንብ ነው

አዝ ————-

ሀሰት የለበትም እግዚአብሔር አይዋሽም

በኢትዮጵያ ከጥንት ፊቱን አልመለሰም

እግዚአብሔር አምላኩ ከእርሱ ጋር ነውና

ቢወድቅም ይነሳል በሃይማኖት ከጸና

አዝ ————-

ህዝቡ እንደ አንበሳ ይነሳል አይቀርም

በባላቅ እርግማን ሞት አያገኘውም

አዳኙን ይበላል ጠላቱን ይጥላል

ኢትዮጵያ ጽኑ ነው በአምላኩ ተወዷል

አዝ ————-

ኢትዮጵያን አትርገም ባላቅ እንዳዘዘህ /2/

ከእዚአብሔር መጣላት እንዳይሆን ፍጻሜህ /2/

በለአም ሆይ ለወርቅ ለጥቅም አትገዛ

ንጉስም ይረግፋል እንደ ጠዋት ጤዛ

_________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Music | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ጊዮርጊስ + መንፈሳዊ መዝሙር + ጽጌረዳ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 31, 2015

የቆንጆዋ ጽጌረዳ ውዝዋዜ (ነፋስ) ከቤተክርስቲያኗ ከሚወጣው የሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ መዝሙር ጋር አብሮ አይሄድም? ጽጌሬዳዋስ ላይ የሆነ ፊት ገጽታ አይታይም?

ለማንኛውም፡ ሰሞኑን የቱርኩ እና የግብጹ ፕሬዚደንቶች በአገራችን የሚያደርጉትን ቆይታ አሳጥረውና ምድረ ኢትዮጵያን ቶሎ ለቀው እንዲሄዱልን ቅዱሳን ረድተውናል። ይህ ትልቅ ምልክት ነው፡ መሪዎቻችን ይህን እንዲገነዘቡ ጸሎቱን እናድርግላቸው።

ቸሩ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: