Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መንፍቅለ መንግስት’

አሜሪካ ከ፪ ዓመታት በፊት መፈንቅለ መንግስት አካሄደች፤ አሁን ደግሞ እስረኞችን አስፈታች | ሉዓላዊነት?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2020

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስት ቴለርሰን ህዋሀት መንግስቱን ለኦሮሞዎች አስረክባ ወደ መቀሌ እንድትሄድ አዘዟት፤ ዛሬ ደግሞ የጣልያን ዝርያ ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ኢትዮጵያ አባይን ለግብጽ እንድትሰጥ፣ አብዮት ደግሞ እስረኞችን እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተው ሳውዲ ገቡ።

መንፈሳዊ ወኔያቸው ተወዳዳሪ ባልነበረው በቀደሙት አባቶቻችን መስዋዕት ነፃነቷንና ማንነቷን ጠብቃ ለአምስት ሺህ ዓመታት የቆየችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እውነት ዛሬ ሉዓላዊ ግዛት ናትን? እንዴት ነው፤ እግዚአብሔር በሰጠን ግዛት እኮ ማንኛውም ምድራዊ ኃይል እንዲህ አድርጉ! አሊያ…” ብሎ ሊያዘን አይችልም። ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ወንበዴዎች እኮ በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለውን የክህደት ተግባር እየፈጸሙ ነው። ላለፉት 150 ዓመታት ከተፈጸሙት በመዋዕለ ሕፃናት ደረጃ የሚፈጸሙ ስህተቶች እንዴት መማር አቃተን?

እስኪ ተመልከቱ፦

ጠላቶቻችን መላዋን ኢትዮጵያን እንደ በሬ ቅርጫ ከዳር እስከ ዳር እየተከፋፈሏት ኢትዮጵያውያን ግን አትኩሮታቸውን፣ ጊዚያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ገንዘባቸውን መጀመሪያ በትንሿአዲስ አበባ ላይ ብቻ ከዚያም በአንድ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ላይ፣ ቀጥሎም የክርስቲያኖች ደም በፈሰሰባት አንዲት ለአንድ በሬ የግጦሽ ቦታ እንኳን የማትበቃ ቦታ ላይ ብቻ እንዲያውሏቸው ኋላቀር የሆነ ዲያብሎሳዊ ተንኮል ተጠቀሙ። በበታችነት ስሜት የተሞሉት ጉረኞቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ እንኳን ኢትዮጵያን መላዋ አፍሪቃን መምራት እንችላለን!” የሚል ከንቱ መፈክር በማሰማት ልክ በሬ ለመሆን ብላ ሰውነቷን ስትነፋ በመጨረሻ ፈንድታ እንደ ሞተችው እንቁራሪት በመነፋፋት ላይ ናቸው ፤ መንደርተኛ እንዲሆን የተደረገውና የተዳከመው ኢትዮጵያዊው ግን ለቁራጭ ቦታ እንኳን ከጠላቶቹ ፈቃድ እንዲሰጠው ደጅ በመጽናት ላይ ይገኛል። እግዚአብሔር በሰጠው ሃገር!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንግስት በላይ ናት፤ ስለዚህ በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችው ይህች ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፡ በቀራንዮ የፈሰሰው የጌታችን ደም አቅጣጫውን እንደጠቆማት፣ መንፈስ ቅዱስ እንደመራት በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት፤ ከደቡብ ግብጽ እስከ ሞቃዲሾ ቤተ ክርስቲያን የመሥራት ሙሉ መብት አላትና የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለባትም። በ22/24 ስህተት የተፈጸመው፤ ልክ ቤተ መንግስት ቤተ ክርስቲያኑን ሲያፈርስና ሰማዕታቱ ወንደሞቻችንም በአብይ አህመድና ታከል ዑማ ትዕዛዝ ሲገደሉ ሕዝቡ ዶማና አካፋ፣ ሲሚንቶና ጡብ ይዞ ወደቦታው በማምራት የቤተ ክርስቲያን ህንጻ ግንባታውን ወዲያው መጀመር ነበረበት። አምስት ሚሊየን የአዲስ አበባ የተዋሕዶ ልጅ ወደዚያ ቢያመራ የትኛው ምድራዊ መንግስት ነው

ሊመክተው የሚደፍረው?!

ይህ አሁን መታየት የጀመረው የመንግስት መለሳለስ የተለመደው እባባዊ መለሳለስ ነው።

ምክኒያቱም፦

1. እንዲለሳለስ ትዕዛዙ የመጣው ከአሜሪካ ነው።

2. ኢንጂነር ስመኘውን፣ ጄነራሎቹንና ክርስቲያኖቹን የገደላቸው፣ እህቶቻችንን ያገታቸው/የገደላቸው

እርሱ መሆኑን እስራኤልና አሜሪካ በማወቃቸው ይሄን ካላደረግክ፤ ዋ!” እያሉ ስላስፈራሩት ነው።

3. ሰሜናውያኑ/ ደገኞቹ የተዋሕዶ ልጆች በመጭው የይስሙላ ምርጫእንደማይመርጡት ስላወቀ በመደናገጡ ነው።

ስለዚህ፤ ወገን ኧረ በቃህ! ኧረ አትታለል!ኧረ ከእባብ እንቁላል የዶሮ ጫጩት አትጠብቅ! ይህ መንግስት ስልጣኑን ሳይወድ በግድ አስረክቦ ለፍርድ እስካለቀረበ ድረስ ወደኋላ አትበል!ፍላጎቱንና ዕቅዱን ነግሮሃል፣ ተግባሩና ዓላማውም ቁልጭ ብለው እየታዩ ነው።

___________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቴለርሰን ግራኝን ዙፋን ላይ አስቀምጦ ተጠረገ፣ ቦልተን ብልጽግናን መሥርቶ ተጠረገ ፥ ፖምፔዮስ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 19, 2020

አባይን ለግብጽ ሸልሞ ይጠረግ ይሆን?

በአብዮት አህመድ መንግስት እጅ የታገቱትን፡ ምናልባትም የተገደሉትን እህቶቻችንን እያስታወሰን!

👉 ከሁለት ዓመታት በፊት፤ አብይ ጾም/ ሑዳዴ ፪ሺ፲ .

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስ ቴለርሰን ሲ.አይ.ኤ ኮትኩቶ ያሳደገውን አብዮት አህመድን በመምረጥ የእስላም መንግስትን በኢትዮጵያ ለማቋቋም እንዲችል ትዕዛዝ ሰጥተውት እንደነበር አሁን እያየነው ነው። በወቅቱ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ይህን በማወቃቸው ነበር በዚሁ ዕለት ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው የነበሩት ማለት ነው። በሌላው ዓለም እንደሚደረገው፣ የህዋሃት መንግስት ለምን ሕዝባዊ ምርጫ በጊዜው አልጠራም?

ከዚህ የሬክስ ቴለርስን ጉብኝት ጥቂት ሳምናታት በፊት ቲለርሰን በቅድሚያ ከግብጹ ፕሬዚደንት አልሲሲ

ጋር በካይሮ ተገናኝተው ነበር። ከአባይ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በአብዮት አህመድ የሚመራ መፈንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ ለማካሄድ የወሰኑበት ስብሰባ ነበር ማለት ነው። በኋላ ላይ ይህ ከሃዲ “ወላሂ! ግብጽን አልጎዳም!” በሚለው መሃላው ይህን አረጋግጦልናል።

👉 ..አ ማርች 13/ 2018 .

ከኢትዮጵያ በተመለሱ በሦስተኛ ቀናቸው የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ቴለርሰን ከሥራቸው ተባረሩ፤ እንዲያውም ገና አውሮፕላን ላይ እያሉ ነበር የስንብት ዜናውን እንዲሰሙ የተደረጉት።

👉 ፪ሺ፲፩ / 2011 .ም የ ብልጽግና አፍሪካ” ስልት ምስረታ

የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን “አዲሱን የአፍሪካ ስትራቴጂ” አቀረቡ። ይህንም ስልት “ብልጽግና አፍሪካ” የሚል ስያሜ ሰጥተውት ነበር።

ጆን ቦልተን አሜሪካ ለአፍሪካ አዲስ አጋርነት ስልት እንዳዘጋጀች ጠቅሰው የዚህ ስልት ከፊሉ የቻይናና ሩሲያን ተጽዕኖ በተለይ በኢትዮጵያ ላይ መቀነስ ያለመ ነው ብለው ነበር።

ይህን ስልት በሥራ ላይ ለማዋልም ጥንታዊቷን ኢትዮጵያን በቅድሚያ መቆጣጠር አለብን ብለው ስለሚያምኑ ጆን ቦልተን አብዮት አህመድ ኢሃዴግን ፐውዞ ሙሉ በሙሉ ለሉሲፈራውያኑ ታዛዥ የሆነውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመሠረት ትዕዛዝ ሰጡት። ይህን ባደረጉ ማግስት፤ ልክ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መስከረም ፩ / ፪ሺ ፲፪ ዓ.ም ከስልጣናቸው እንዲወገዱ ተደረጉ (ልክ እንደ ቴለርሰን)

👉 ኅዳር ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ላይ በአሜሪካ ሲ.አይ.ኤ ግፊት በከሃዲ ቅጥረኛ አባላት የተሞላው የእስላማዊው የብልጽግና ፓርቲ ተመሠረተ

👉 ትናንትና የካቲት ፲ / ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ላይ የቀድሞው የሲአይኤ (CIA) ዲሬክተር የአሁኑ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ አባይን ለግብጽ ለመስጠት ወደ አዲስ አበባ አመሩ

የእርሳቸውስ ዕጣ ፈንታ ምን ይመስል ይሆን?

በሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ በጎ ያልሆነ ዕቅድ በመያዝ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የሚደፍር ባለስልጣን፡ ስልጣኑን ብዙም ይዞ አይቆይምና፤ ሬክስ ቴለርሰንና ጆን ቦልተንም የድብቁን መንግስታቸውን ተልዕኮ ፈጽመው በተመለሱ ማግስት ባለተጠበቀ መልክ ከውጭ ጉዳይ ምኒስትርነትና ከብሔራዊ ደህነነት አማካሪ ኃላፊነቶቻቸው ተወገዱ።

__________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የ ግራኝ አህመድን መንግስት ከመረጡ በኋላ ከስልጣን ወረዱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 19, 2018

አቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት በፊትና በኋላ የአሜሪካ መንግስት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትሩን መንበር እንዲረከቡ፣ አቶ ደመቀ መኮንንም ምክትላቸው እንዲሆኑ ከፍተኛ ፍላጎት ከማሣየት አልፎ ግፊትና ምክርም መስጠቱ የሚታወቅ ነው።

ፕሬዚደንት ባራክ ሁሴን ኦባማ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ በነበሩት ሁለትና ሦስት ቀናት ውስጥ ከዋይትሐውስ በስልክ ከአቶ ኃይለማርያም ጋር መወያየታቸውና “አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ሳታቋርጥ እንደምትቀጥል” ቃል ገብተው ነበር። በወቅቱ በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር ሱዛን ራይስ በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ የቀብር ሥነሥርዓት ላይ ሰፊ ንግግር ካደረጉ በኋላ በሸረተን አዲስ ከአቶ ኃይለማርያም ጋር ረዘም ያለ ውይይትም ማካሄዳቸው የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ መንገድ፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት ሬክስ ቴለርሰንም ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ በአቶ አብይ አህመድ የሚመራና የወደፊቱን የእስላም መንግስት በኢትዮጵያ ለማምጣት የሚረዳ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ትዕዛዝ ሰጥተው ከስልጣናቸው ተሰናበቱ።

ቀደም ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሄንሪ ኪሲንጀር የፀረክርስቲያኑን የደርግ መንግስት፣ እነ አምባሳደር ሄርማን ኮኸን የኢሃዴግና ኦነግ ፀረተዋሕዶ መንግስትን ለማደራጀት ትልቅ ሚና ተጫውተው ነበር።

ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም፤ አዲስ ነገር ቢኖር አሁን አምባሳደሮች ወይም ረዳቶች (ጄንዳይ ፍሬዘር ጆኒ ካርሰን) ሳይሆኑ፥ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እራሱ ወደ ኢትዮጵያ መላኩ ነው፤ ክብራችን ትንሽ ከፍ አለች።

..አ ሜይ/ 2013 .

የ ቢቢሲ “ሃርድ ቶክ” ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሺቲ፤ ሉሲፈራዊው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር፡ ጆን ኬሪ፦ „እናንተ አፍሪቃውያን ከቻይና ጋር ያላችሁን ግኑኝነት ቶሎ አቋርጡ፡ አለዚያ ወዮላችሁ!!ይሉናል፤ አገራችን መጥተው።

መስከረም ፪ሺ፭ ዓ.

አቶ ኃይለማርይም ደሳለኝን ቀደም ሲል በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት እንዲመረጡና፡ በኋላም ላይ ጠ/ምኒስትር መለስ ዜናዊን እንዲተኩ፡ አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ ምክትል ጠ/ሚንስትር እንዲሆኑ

ባራክ ሁሴን ኦባማጆን ከሪና ሱዛን ራይስ ትዕዛዝ ተሰጠ። “ሰሜናዊ የተዋሕዶ ሰው መሪ መሆን የለበትም” የሚል መመሪያ አላቸው። በኦርቶዶክሱ የሩሲያው ፕሬዚደንት ላይም መሰናክል የሚሠሩባቸው አጥባቂ ክርስቲያን በመሆናቸው ነው።

ፕሮቴስታንቱ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ልክ እንደተመረጡ፦ “ተዋሕዶዋ እናቴ ገና አልዳናቸም፤ በዚህ አዝናለሁ” ረዳታቸው ሙስሊሙ አቶ ደምቀ መኮንን ደግሞ፦ “ቁርአንን በአረብኛ በደንብ አድርጌ ቀርቸዋለሁ” በማለት ለሉሲፈራውያኑ የዓለማችን መሪዎች የሥራ ማመልከቻዎቻቸውን አቀረቡ።

የሴቶች ቀን፡ እ..አ ማርች 8/ 2018 .

ጀግኖቹ እህቶቻችን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ወደ አርጀንቲና አበረሩ።

የሴቶች ቀን እ..አ ማርች 8/ 2018 .

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ርጌ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ገቡ።

የሴቶች ቀን እ..አ ማርች 8/ 2018 .

የአሜሪካና የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች፤ ሰርጌ ላቭሮቭና ሬክስ ቴልርሰን በአዲስ አበባ ሸረተን ሆቴል አልጋዎችን ያዙ።

አብይ ጾም/ ሑዳዴ ፪ሺ፲

ቴለርሰን በአብይ ጾም ዶ/ር አብይን በመምረጥ የእስላም መንግስትን በኢትዮጵያ ለማቋቋም ትዕዛዝ ሰጥተው ነበርን? ላቭሮቭስ ይህን በማወቃቸው ይሆን በዚሁ ዕለት ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የወሰኑት?

ከዚህ የሬክስ ቴለርስን ጉብኝት ጥቂት ሳምናታት በፊት ቲለርሰን በቅድሚያ ከግብጹ ፕሬዚደንት አልሲሲ

ጋር በካይሮ ተገናኝተው ነበር። ከአባይ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ

የወሰኑበት ስብሰባ ይሆን?

..አ ማርች 13/ 2018 .

ከኢትዮጵያ በተመለሱ በሦስተኛ ቀናቸው የውጭ ጉዳይ ምኒስትር ቴለርሰን ከሥራቸው ተባረሩ፤ እንዲያውም ገና አውሮፕላን ላይ እያሉ ነበር የስንብት ዜናውን እንዲሰሙ የተደረጉት።

ኢትዮጵያን ለተንኮል የሚጎበኝ ባለስልጣን፡ ስልጣኑ ላይ አይቆይምና፤ ሬክስ ቴለርሰንም፡ ኢትዮጵያን በጎበኙ ማግስት ባለተጠበቀ መልክ ከውጭ ጉዳይ ምኒስትርነት ኃላፊነታቸው ተወገዱ፡ ማለት ነው።

***ዓለምን የሚያስተዳድራት ስዉር መንግስት የሉሲፈር ሲሆን፥***

+++ኢትዮጵያን የሚጠብቃት ስዉር መንግስት የእግዚአብሔር ነው።+++

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: