Posts Tagged ‘መንፈሳዊ ሕይወት’
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 3, 2023
😈 ሰዶም እና ገሞራ ብራዚል በእግዚአብሔር ላይ ተሳለቁበት ከዚያም ጎርፍ እና እሳት ተከተለ፤ የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ !
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 😇 መርቆርዮስ 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፬፥፴፯፡፴፱]❖
“የኖኅ ዘመን እንደ ነበረ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናልና። በዚያች ወራት ከጥፋት ውኃ በፊት፥ ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ፥ ሲበሉና ሲጠጡ ሲያገቡና ሲጋቡም እንደ ነበሩ፥ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ እንዳላወቁ፥ የሰው ልጅ መምጣት ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።”
😈 Brazil’s Satanic Carnival 2023! The Days of Noah IS HERE!
❖ [Matthew 24:37-39] ❖
“But as the days of Noah were, so shall also the coming of the Son of man be. For as in the days that were before the flood they were eating and drinking, marrying and giving in marriage, until the day that Noe entered into the ark, And knew not until the flood came, and took them all away; so shall also the coming of the Son of man be.”
A Demonic Parade In Brazil! They Worshiped Satan in front of everyone. They Mocked God Then This Happened! The Dark Side of Brazil’s Carnival
In 2023, Brazil’s carnival celebrations took a dangerous turn when parade floats mocking Jesus Christ and using the devil caused a devastating flood.
Christians need to wake up to the end times prophecies that are coming to pass! similar to others like:
Man Act like Jesus Mocks God and Receives Instant Karma at Brazil’s Carnival
The Rio de Janeiro Carnival is a world-famous festival that attracts people from all over the world. It is known for its vibrant costumes, music, and dance. Unfortunately, some groups choose this moment to make a mockery of Jesus and the Bible. After almost two years without activity, this year’s Carnival resumed its activities. However, a samba school in Rio de Janeiro known as Gavioels de Fiel decided to mock God and the Bible with their themes and parade.
⚡ Gigantic Jet Lightning Bolt Falls on The Head of Christ The Redeemer Statue in Brazil
⚡ኃይለኛ መብረቅ በብራዚሏ ሪዮ ዲ ጄኔሮ በሚገኘውን ግዙፉ የ ‘ ክርስቶስ መድሓኒ ‘ ሐውልት ራስ ላይ ወደቀ።
_______ _______
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: Aksum , Axum , መብረቅ , መንፈሳዊ ሕይወት , ሪዮ ዲ ጃኔሮ , ስድብ , ብራዚል , ነጎድጓድ , አክሱም , አውሎ ንፋስ , ካርናቫል , ክርስቶስ መድሓኒ , ጎርፍ , ጽዮን , ፌዝ , blasphemy , Brazil , Carnival , Christ The Redeemer , Flood , Lightning , Mockery , Rio , Rio de Janeiro , Spiritual Life , Statue , Thunder , Zion | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2023
⚡ኃይለኛ መብረቅ በብራዚሏ ሪዮ ዲ ጄኔሮ በሚገኘውን ግዙፉ የ’ክርስቶስ መድሓኒ’ ሐውልት ራስ ላይ ወደቀ።
ኃውልቱ በተደጋጋሚ የመብረቅ ጥቃት ይደርስበታል፤ ነገር ግን ፍንክች አይልም።
❖ የካቲት 11, 2023
❖ ጥር 18 ቀን 2014
በእውነት በመብረቅ በተመታባቸው በእነዚህ ሁለት አጋጣሚዎች በአንዱም ላይ ጉዳት አለማድረሱ አስገራሚ ነው።
❖❖❖[ መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፴፯ ]❖❖❖
፩ ስለዚህም ልቤ ተንቀጠቀጠ፥
፪ የድምፁን መትመም ስሙ፥
፫ እርሱን ወደ ሰማያት ሁሉ ታች፥
፬ በስተ ኋላው ድምፅ ይጮኻል፤
፭ እግዚአብሔር በድምፁ ድንቅኛ ያንጐደጕዳል፤
፮ በረዶውንና ውሽንፍሩን ብርቱንም ዝናብ።
😇 የክርስቶስ ሐይል አሁን በጣም ከፍ ብሎ እየተንቀሳቀሰ ነው …. አንዳንዶቻችን ይሰማናል።
❖ February 11th, 2023
❖ January 18th, 2014
Amazing that it has not been damaged on any of the 2 occasions when it was really struck by lightning.
😇 The power of Christ is running real high right now….some of us can feel it.
❖❖❖[Job 37:3]❖❖❖
“Under the whole heaven He lets it loose, And His lightning to the ends of the earth.„
Christ the Redeemer Statue receives around 1,000 lightning strikes a year due to its height and exposure to thunderstorms. This means that in the more than 80 years of its existence, it has been struck by thousands of lightning strikes. It is important to note that the Christ the Redeemer is built with materials resistant to electricity, so it has not suffered serious damage despite being repeatedly struck by lightning.
In 2014 The 125-foot-tall figure that presides over the Brazilian city had its right thumb damaged when a lightning bolt struck its outstretched .
_______ _______
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , News/ዜና | Tagged: Aksum , Axum , መብረቅ , መንፈሳዊ ሕይወት , ሪዮ ዲ ጃኔሮ , ብራዚል , ነጎድጓድ , አክሱም , ክርስቶስ መድሓኒ , ጽዮን , Brazil , Christ The Redeemer , Lightning , Rio de Janeiro , Spiritual Life , Statue , Thunder , Zion | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020
VIDEO
የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሃብተማርያም የማእጠንት ፀሎት በተወሰኑ የቨርጂንያ መንደሮችና ጎዳናዎች
[ የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፰፤ ]
፩ ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ ።
፪ በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው ።
፫ ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው ።
፬ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ ።
ሌላ የሚገርመው ነገር፤ ልክ እዚህ አካባቢ ነበር ባለፈው ጊዜ የሚከተለው የተከሰተው፦
VIDEO
______________ _________________________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Health | Tagged: መንፈሳዊ ሕይወት , ቃሌ , ቨርጂኒያ , አሜሪካ , አቡነ ሀብተ ማርያም , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , እስትንፋስ , እጣን እና ከርቤ , ዋሽንግተን , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን , ገዳም , ጋኔን , ጤንነት , Ethiopia , Frankincense & Myrrh , Holy Water , Water | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020
VIDEO
[ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፥፲፮ ]
“እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና። ”
ይህን ሳይ የሚሰማኝ፤ “እግዚአብሔር እኛ ኢትዮጵያውያንን በመላው ዓለም በስደትም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከአገራችን አውጥቶ የሚልከን በርገር እየበላን በከንቱ እንድናውደለድል ሳይሆን እንደዚህ እጣኑን እያጨስን መንፈሳዊ ውጊያውን እንድንመራለት፣ ከጠፉት ጋር አብረን እንድንጠፋ ሳይሆን፣ ሁሉም እንዲድን መድኃኒቱን እንድናሳይ ነው።” የሚለው ነው። በእውነት ነው የምለው፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በከንቱ ሌላውን ለመምሰል ብንታገልም ምናልባት 90% መንፈሳውያን ሰዎች ነን።
እንግዲህ ያውልሽ አሜሪካ፤ ግብጻውያን አውሮፕላን አብርረው ከሰማይ – ጠቀስ ፎቆችሽ ጋር በማላተም ሦስት ሺህ ዜጎችሽን ገደሉብሽ፣ ፕሬዝደንትሽ ለጉብኝት ወደ ግብጽ ሲመጡ በንቀት ጫማቸውን ወረወሩባቸው … ዛሬ የከዳሻቸው ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ግን መቅሰፍቱ ሁሉ ከምድርሽ እንዲርቅ ክቡር እጣኑን ከደመናው ጋር አዋሐዱልሽ። ይህን ውለታ አትርሺ፤ አሜሪካ !
የፃድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን !
መምህር ዘመድኩን እንዳካፈለን፦
• መፍትሄው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ጭንቅ ውስጥ በገባችው አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየአደባባዩ፣ በየመንደሩ፣ እየዞረች የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያምን ዕጣን እንድታጥን ተጠይቃ ይኸው ቃሏን አክብራ በጻድቁ አቡነ ኃብተ ማርያም ጸሎት ምድሪቱን እያጠነች ነው።
ዛሬ መጋቢት ፲፫ / ፪ ሺ ፲፪ / 13/2012 ዓ . ም (Mar.22/2020)
በአሜሪካን ሀገር በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 5:00 PM ላይ በኸረንደን ቨርጂንያ 2472 Centreville Rd.Herndon, VA 20171 የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናቱ የጻድቁ የአቡነ ሀብተ ማርያም ሥዕላቸው ተይዞ
•በኸረንደን፣
•በረስተን፣
•በቻንትሊን፣
•በእስትርሊንግና በሌሎችም ከተሞች የሚገኙ አደባባዮችና አውራ ጎዳናዎች በማጠን ላይ ይገኛሉ።
• ለዚሁ የአሜሪካን ከተሞችና መንደሮች የማዕጠንት አገልግሎት
• መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን
• መጋቤ ካህናት መ / ር ቀሲስ ዮናስ ፍቅረ
• ሊቀ ስዩማን መ / ር ቀሲስ ኢዮብ ደመቀ
• ሊቀ ልሳናት መ / ር ቀሲስ ጌቱ ተገኑ
• ሊቀ ማዕምራን መ / ር ዮሐንስ ለማ
• ሊቀ ትጉሀን ዲ / ን አብርሐም ቶማስ
• ሊቀ ዲያቆን ገረመው ተዘጋጅተው አገልግሎቱን ጀምረዋል።
አሜሪካ ደንግጣለች። ቤተ ጸሎቶች በሙሉ ተዘግተዋል። የመኪና መንገድ አውራ ጎዳናዎች ሁሉ ጭር ብለዋል። ነገር ግን በእኒህ ሞት ባጠላባቸው የአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶቻችን ጸሎት እንዲያደርጉ የአሜሪካ መንግሥት ፈቅዶላቸዋል። በእውነት ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። ይሄ ምልክት ነው። ወደድንም ጠላንም መጪው ዘመን የኦርቶዶክስ ነው። ኦርቶዶክሳዊነት የዓለሙ ሁሉ ሃይማኖት ይሆናል። ሰዎች ሁሉ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ይተምማሉ። የኢትዮጵያ ሃይማኖት የዓለም ሃይማኖት ይሆናል የሚባለው የአበው የትንቢት ቃል በቅርቡ ፍጻሜውን ያገኛል።
ከኢትዮጵያ ውጪ ብቸኛው የጻድቁ አቡነ ሃብተ ማርያም ታቦት የሚገኘውም እዚሁ ቦታ ነው። በቦታውም ብዙ ህሙማን እየተፈወሱ መካኖች መወልዳቸው ብዙዎችን ሲያስደንቅ መኖሩም ተነግሯል። በእውነት “ መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ ” እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል “( መዝሙረ ዳዊት 68:35 ፤ )
በጻድቁ ዜና ገድል ( ገድለ አቡነ ሀብተማርያም ገጽ .117) ላይ ተጽፎና ተመዝግቦ እንደምናገኘው ልዑል እግዚአብሔር ለጻድቁ በሰጣቸው ቃል ኪዳን መሰረት ስማቸው፣ በተጠራበት፣ ማዕጠንታቸው በታጠነበት፣ ዜና ገድላቸው በተነበበትና ባለበት፣ ጠበላቸው በተረጨበት ሥፍራ ፭ቱ መቅሰፍታት ማለትም :-
፩ኛ . መብረቅ
፪ኛ . ቸነፈር
፫ኛ . የረኀብ ጦር
፬ኛ . ወረርሽኝና
፭ኛ . ሰደድ እሳትና የመሳሰሉት ቦታ የላቸውም። ዜና ገድላቸው እንደሚነግረን በአንድ ወቅት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ልጆቻቸው በእነዚህ ፭ቱ መቅሰፍታት እንዳይጠቁና እንዳይጎዱ ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያምን በቃል ኪዳናቸው ልጆቻቸውን እንዲጠብቁላቸው ሲማጸኑዋቸው የጻድቁ የአቡነ ሀብተማርያም መልስ የነበረው “ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ፤ በእኔ ስም ልጆችህና ወዳጆችህ በቃል ኪዳኔ የሚድኑ ከሆነ ይሁን ብለው ቃል እንደገቡላቸው ተመዝግቧል። ይህ ቃል ኪዳን ደግሞ ዘመን ተሻጋሪና ጊዜ የማይሽረው ነው። በእውነት ያለ ሀሰት። እንጠቀምበት።
በኢትዮጵያም በትናንትናው ዕለት የቃሌ አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ካህናት አዲስ አበባ ቃሌ አከባቢ ሲያጥኑ መዋላቸው ተዘግቧል። ትናንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የዐድዋውን ዘማች ታቦተ ጊዮርጊስን ይዛ ማዕጠንቱን ብታካሂድ ወረርሽኙ ድራሹ ይጠፋል በማለት ያሳሰብኩትም ማሳሰቢያዬም መልስ አግኝቷል። የአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መጋቢት 20 ታቦቱን ይዘው ሊወጡ ነው። የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከትም መጋቢት 13 በአዲስ አበባም የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራትም በጋራ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አዲስ አበባን እንዲያጥኑ መመሪያ ተላልፏል።
VIDEO
በጣልያን ሊቀጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን አናግሬያለሁ። የጣልያን መንግሥት ፈቃድ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ እኛ ዝግጁ ነን ብለዋል። የጀርመኑን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ዲዮናስዮስንም እንዲሁ አግኝቼ አውርተናል። ፈቃዱ ከመንግሥት ካለ እኛ ዝግጁ ነን።
_____________ _______________________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Health | Tagged: መንፈሳዊ ሕይወት , ቃሌ , ቨርጂኒያ , አሜሪካ , አቡነ ሀብተ ማርያም , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , እስትንፋስ , እጣን እና ከርቤ , ዋሽንግተን , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን , ገዳም , ጋኔን , ጤንነት , Ethiopia , Frankincense & Myrrh , Holy Water , Water | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020
VIDEO
በዚህ በጣም ተደስቼ ነው የዋልኩት፤ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን !
ትንሽ ቅር ያለኝ ነገር ግን እዚህ ድንቅ ገዳም ተራራ ጫፍ ላይ አንጋፋውን መስቀል ለማስተከል መስነፋችን ነው።
VIDEO
VIDEO
VIDEO
የፃድቁ አባታችን አቡነ አብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን !
___________ _____________________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith , Health | Tagged: መንፈሳዊ ሕይወት , ቃሌ , አቡነ ሀብተ ማርያም , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , እስትንፋስ , እጣን እና ከርቤ , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን , ገዳም , ጋኔን , ጤንነት , Ethiopia , Frankincense & Myrrh , Holy Water , Water | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 21, 2020
VIDEO
ቫይረሱ ጋኔን መሆኑን አረጋገጠልን !
ምን እንደሆነ አላውቅም እስከ አለፈው ነሃሴ ወር ድረስ ምናልባት በወር አንዴ ብቻ ነበር እጣን የማጤሰው፤ ካለፈው ጥቅምት ወር አንስቶ ግን በቤትም በመሥሪያ ቤትም በጣም አዘውትሬ አጤሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው፤ ቅዱስ መንፈስ ማድረግ የሚገባንንና የሚጠቅመንን ነገር ሳናስበውና ሳንዘጋጅበት እንድናደርገው ወደ በጎው ነገር ይመራናል።
ዛሬ ወደዚህ አይሁድ ቪዲዮ እንዴት እንደገባሁ ሁሉ አላውቅም፣ ያውም እጣንን በሚመለከት የገባሁበት ገጽ አልነበረም ፤ ግን ያው ! ለኮሮና ጋኔን መፍትሄ ይሆናሉ ብዬ ሳስባቸው ከነበሩት ከጸበል፣ ከጸሎት ጎን እጣን እና ከርቤ እንደሚኖሩበት አረጋገጠለን። አሁን በዚህ በጣም እርግጠኛና ደስተኛ ነኝ።
ደካሞችና ምስጋና ቢሶች ሆነን ነው እንጂ አምላካችን እኮ የሚጠቅሙንን ነገሮች ሁሉ ሰጥቶናል፤ ጸበሉንም፣ ጸሎቱንም፣ እጣኑና ከርቤውንም በነጻ ሰጥቶናል። እጣንና ከርቤ ከወርቅ በላይ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ለብዙ በሽታዎች ፈውስ እንደሆኑ ሳይንሱ ሳይቀር እያረጋገጠልን ነው። Seeing the Unseen of the Combination of Two Natural Resins, Frankincense and Myrrh
እጣኑን በአግባቡ እናጢስ፤ ወገኖቼ፤ ነገር ግን ከተለመደው የቡና ስነ ሥርዓት ወቅት፣ በተለይ ከኦጋዴን እና አረብ ዕጣኖች ጋር አብሮ ማጤሱን ዛሬውኑ ማቆም አለባችሁ ! አባቶች ይህን አስመልክቶ አንድ ይበሉን !
አየን አይደለም ?! ጠላት ዲያብሎስ ለብዙ ሳምንታት በቂ የኮሮና ቫይረስ በአውሮፕላን እንዲረጭ ካደረገ በኋላ ወሮበላው መንግስት “በረራዎችን አቁሜአለሁ ፣ ይቅርታ ቅብጥርሴ ” አለን። ቫይረሱ ልክ እንደ አንበጣ እስኪፈለፈል የሁለት ሳምንታት ጊዜ ይወስድበታል ተብሏል። ስለዚህ አባቶች ልክ እንደ ጆርጂያ ኦርቶዶክስ አባቶች በተለይ አዲስ አበባን በመኪና እና በሄሊኮፕቶር እየዞሩ ዛሬውኑ ደጋግመው ጸበል ቢረጩና እጣን ቢያጤሱ ትልቅ ሥራ ይሆን ነበር። በተለይ ምዕመናን ለቅዳሴ የማይመጡ ከሆነ ይህ መደረግ አለበት። ቀዝቃዛዎቹ የጉንፋን ወራት ከመጀመራቸው በፊት አስቀድሞ መደረግ ያለበት አንዱ ተግባር ይህ ሊሆን ይገባል።
UPDATE
የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እያየን ነው፡ ወገኖቼ ? ዋው ! የሚገርም ነው፦ ያው መምህር ጳውሎስም እንዲህ ይለናል፦
“የማዕጠንት ጊዜ ነው፤ ማዕጠንት ጥሩ ነው፤ በሽታ የሚያርቅ ነው፤ እጣኑንን እያሸተታችሁ … ካህናት በየቤቱ በመዞር ጸሎተ ማርያም እየደገሙና ማዕጠንት እያደረጉ ቢያልፉ በሽታው ያልፋል … ከተማው ይታጠላንል አስፈላጊ ከሆነ”።
ወደ እዚህ እንግባና ሙሉውን እናዳምጥ፦
“አስደናቂ ስብከት በሽታው የሚርቀው በማዕጠንት ነው መምህር ጳውሎስ መልካሥላሴ ክፍል፪
VIDEO
ቃለ ሕይወት ያሰማልን !
_________ __________________
Like this: Like Loading...
Posted in Curiosity , Ethiopia , Faith , Health | Tagged: መንፈሳዊ ሕይወት , መጽሐፍ ቅዱስ , አዲስ አበባ , ኢትዮጵያ , እስትንፋስ , እጣን እና ከርቤ , ኮድ , ውሀ , የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን , ጋኔን , ጠበል , ጤንነት , ጸበል , Ethiopia , Frankincense & Myrrh , Holy Water , Water | Leave a Comment »