ከወር በፊት አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ኃውልት ሥር እሳት መቀስቀሱን ገና አሁን መስማቴ ነው፤ እንዴት ይህን በጊዜው አልሰማነውም? የተቀሰቀሰው እሳት ከየት መጣ? ማን ቀሰቀሰው? የዜና ማሠራጫዎች ለማይረባ ነገር ሃያ አራት ሰዓት ይቅበጣጥራሉ፤ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ላይ ግን ጭጭ። ለምንድን ነው በሲዳማ ስለ ቤተክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ ጅሃድ እስካሁን ምስሎችንና መረጃዎችን ለማግኘት ያልቻልነው? እስኪ ተመልከቱ ስለ ችግኝ ተከላው ጉዳይ ምን ያህል አትኩሮት እንደሰጡት። በጉዳዩ ላይ ሁሉም አካላት(ቤተ ክህነትን ጨምሮ)ሁሉም ፈጥነው ህዝብን ለማነሳሳት በቁ ፤ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጊዜአቸውን፣ ጉልበታቸውና ገንዘባቸውን መስዋዕት አድረገው ለተከላው እንዴት መነሳሳታቸውን ስናይ እራስ ያስነቀንቃል።