በቤይሩት የቅድሱ ዲሚትሪዮስ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባት አባ ዮኢል ናሲፍ ነው ይህን ለቢቢሲ የተናገሩት።
የቅዱስ ዲሚትሪዮስ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሚገኘው የቤይሩት ፍንዳታ ከተከሰተበት ቦታ አንድ ኪሎ ሜትር ብቻ ርቆ ነው፡፡
አባ ዮኢል ናሲፍ ቤተክርስቲያኑ የደረሰበትን ጉዳት ለመመርመር በፍጥነት ወደ ቤተክርስቲያኑ በመሮጥ ቤተክርስቲያን ሲገቡ የቤተክርስቲያኑ የመጀመሪያ ክፍል(ቅኔ ማህሌት)ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ ነገር ግን ቤተ መቅደሱ ለጭረት እንኳን አልተነካም ነበር ፥ በፍንዳታው ወቅት ሁሉ እንደበራ የቆየውን የዘይት ሻማ መብራት ጨምሮ፡፡