Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መስከረም ፪ሺ፲፪ ዓ.ም’

የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 14, 2020

ጊዜው የሚያዘናጋ፣ የሚያዘልል፣ የሚያስፈነጭ የሚያስጨበጭብ ጊዜ አይደለም ፥ ለፀሎት የምንነቃበት ጊዜ እንጂ: ሕዝብ ሲያምጽ፣ ኃጢዓት ሲበዛ፣ ጽዋ ሲሞላ እምቢ ለሚል እግዚአብሔርን ለሚገዳደር በተናጠል ይቀጣል

[መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫፥፩፡፰]

ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

የሰይፈ ሥላሴ ፀሎት ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን!

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የማርያም መቀነት በሐዋሳ ጥምቀት | ገዳይ አብይ እስኪ ውጣና መቀነቱን በሜንጫህ አውርደው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 21, 2020

እኛ እግዚአብሔር አምላካችንን እንዲህ ስለምነወድደው ከዚህ የተነሳ ሰይጣን በቅናት፣ በጥላቻ እና በእብደት ይሞላል። ዲያብሎስ ሁሉም እግዚአብሔርን የሚወዱትንና የሚያገለግሉትን ፍጥረታት መግደል እና ማጥፋት ይፈልጋል።

ያው እንግዲህ ዲያብሎስ በሸቀ፣ አበደ፣ ቅጥል አለ። ዲያብሎስ ሰይጣን ወደ እኛ የማለፍ ፈቃድ ካገኘ ይሰርቃል፣ ይገድላል እንዲሁም ያጠፋል። መስረቅ፣ መግደል እና ማጥፋት የእርሱ የደመ ነፍስ ስራዎች ናቸውና እግዚአብሔርን የሚወዱትን ለመግደል ወደ ሐረርና ድሬዳዋ አመራ።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅድስት ሥላሴ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ይባርኩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2020

እንኳን ለአግዓዚተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰንየአብርሃሙ ሥላሴ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። ሕዝባችንንም በሰላም በፍቅር በአንድነት ያኑርልን

ወደ መጨረሻ ላይ ያለውን መልዕክት እናዳምጥና እራሳችንን እንጠይቅ፤ “እንደው በዚህች ዓለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትሮ የሚሄድ፣ በጾምና በጸሎት የሚተገባ ሕዝብ ይኖራልን? እኔ መመስከር እችላለሁ፤ የለም! የትም ሃገር የለም። ሃጢአተኞች ሁላችንም ሃጢአተኞች ነን፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያን እየተቃጠለ ያለው እኛ ከዓለም ሁሉ የከፋ ሃጢአት ሰርተን ሳይሆን ክርስቲያን ወገናችንን እና ቤተክርስቲያናቱን ለመከላከል ዝግጁ ባለመሆናቻን፣ የእኛና የአምላካችን ጠላት ከሆኑት አህዛብ ጋር በመደባለቃችን፣ የሃገር ጠላት ከሆነው መንግስት ጋር በመደመራችን ብሎም እንደ ቀደሙት አባቶቻችን መንግስትን በቁጣ ለመገሰጽና ለማስጠንቀቅ ባለመድፈራችንና በራድ ወይ ትኩስ ስላልሆንን ነው። ስለዚህ መንግስትን ለመቃወም “ሰልፍ አትውጡ፡ እኛ እንደራደራለን!” ቅብርጥሴ የሚለው መልዕክት የትም አያደርሰንም። እንዲያውም የተዋሕዶ አርበኞች በቁጣ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት አምርተው ባለሥልጣናቱ ሁሉ እንዲወገዱ መጮኽና አጥሩን መነቅነቅ ይኖርባቸዋል። ለሁሉም ጊዜ አለው፤

ከወዳጆችህ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጠላቶችህም ጋር እንኳ ሳይቀር በሰላም ኑር፤ ነገር ግን እንዲህ የምልህ ካንተ ከግል ጠላቶችህ ጋር እንጂ ከእግዚአብሔርና ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጋር አይደለም፡፡አንድ ገዳማዊ አባት

ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

በዚህ የጥምቀት በዓል ከአባቶች የምጠብቀው መልዕክት፦

ሴት ልጆቼ በደምቢዶሎ ጫካ ውስጥ የጥምቀት በዓልን እንዲያሳልፉ አልሻም፤ ስለዚህ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቃህ፡ ስልጣኑን አስረክብና በሥላሴ ስም ተጠመቅ!”

የሚለውን መልዕክት ነው።

እስኪ እናስበው፤ አቡነ ማትያስ ይህን ቢናገሩ፤ ምንም ጥርጥር የለኝም ብዙ እንቅስቃሴ ሊታይ ይችል ነበር።

የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፡ በቃን! ስሜታዊ አትሁኑ!” እያላችሁ ሰውን አታስተኙት፤ ወኔውን አትንጠቁት! እንዲያውም “ምርጫ” የተባለው ነገር የሚካሄድ ከሆነ በመጭዎቹ ሳምንታት ምእመናኑን ለእነ አብዮት አህመድ፣ ለእነ ብርሃኑና ስብሐት ነጋ፣ እንዲሁም ለሌሎቹ አቋምየለሽ ልክስክስ ፓርቲዎች በጭራሽ ድምጽ እንዳይሰጡ ማስጠንቀቅ፤ በተቃራኒው ደግሞ ለእስክንድር ነጋ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ግልጽ የሆነ ቅስቀሳ ማካሄድ አለባቸው።

ሜዲያው ሁሉ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ አሉታዊ በሆነ መልክ 24 ሰዓት ቅስቀሳ በሚያደርጉባት ሃገራችን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በጣም አመች የሆነው የቅስቀሳ እና የትምህርት መድረክ በቤተክርስቲያን ነው የሚገኘው።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሕዝብ ሲያምጽ፣ ኃጢዓት ሲበዛ፣ ጽዋ ሲሞላ እምቢ ለሚል እግዚአብሔርን ለሚገዳደር በተናጠል ይቀጣል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 17, 2019

[መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፫፥፩፡፰]

ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ ከሰማይ በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ወቅት አለው፤ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤ ለመግደል ጊዜ አለው፤ ለማዳንም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፤ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለመሣቅም ጊዜ አለው፤ ለሐዘን ጊዜ አለው፤ ለጭፈራም ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመጣል ጊዜ አለው፤ ድንጋይ ለመሰብሰብም ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፤ ለመለያየትም ጊዜ አለው፤ ለመፈለግ ጊዜ አለው፤ ለመተው ጊዜ አለው፤ ለማስቀመጥ ጊዜ አለው፤ አውጥቶ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፤ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፤ ለሰላምም ጊዜ አለው።

የሰይፈ ሥላሴ ፀሎት ከክፉ ነገር ይጠብቀን!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቤቱ ወደ አንተ መልሰን ፥ እኛም ወዳንተ እንመለሳለን ፥ ዘመናችንን እንደ ቀድሞው አድስልን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 20, 2019

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: