Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መርሐ ግብር’

ቤተ ክርስቲያን ሆይ መከራሽ መብዛቱ፤ ከአንቺው አብራክ ወጥተው ጎራዴ አነገቱ፤ ተባብረው ሊወጉሽ ባንቺ ላይ ዘመቱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 15, 2020

ሳሪስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የማንቂያ ደወል | ተዋሕዶ በጨለማው ውስጥ ታበራልችና ጧፋችሁን ከፍ አድርጉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 1, 2020

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፫፥፲፭]

የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው።

እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ሁሉንም ይጠብቃቸው። የፍጻሜ ዘመን ላይ ደርሰናል፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢታዊ ምስክርነት የፍጻሜ ዘመን ቃጭል እንደሆነ እያየን ነው።

የኮሮና ቫይራስ ክስተት ባስከተለው ስጋት በቻይና፣ በደቡብ ኮሪያ፣ በጣልያን ዓብያተ ክርስቲያናት በሮቻቸውን ዘግተዋል፤ የተለመደውን የሰንበት አገልግሎት ሁሉ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ይህን የማንቂያ ደወል ስነ ሥርዓት ስመለከት ብልጭ ብሎ የሚታየኝ ዲያብሎስ በዚህ ሁሉ ብርሃን እንዴት ቅጥል እንደሚል ነው። ከሳምንታ በፊት በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የተከሰተው ይህ ነበር። “ይህች ዓለም የኔ ነች” ብሎ የሚያምነው ዲያብሎስ አይተኛም፣ መሸነፍን አይወድም፤ ዛሬም በንዴት እንዳጓራ ነው፤ ስለዚህ እንዲህ የመሳሰሉትን የፍቅር፣ የሰላምና የብርሃን መድረኮችን፣ እንዲሁም ክርስቲያናዊ አገልግሎቶችን ሁሉ ከቤተ ክርስቲያን ለማራቅ የተቻለውን ሁሉ ይሞክራል።

ቅዱስ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡፡” ፣ “ከእኔ በኋላ የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃችኋል”፣ “የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ” እያለ ምሥጢራትን / ምስጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ንስሐን እና ምስጢረ ቁርባንን / እንድንካፈል ያስተምረናል፡፡

ጥምቀት፣ ቁርባን፣ ንስሐ ስንት መንፈሳዊ ሀብትና ጸጋ እንደሁም ከፍ ያለ የእግዚአብሔር ልጆች ክብር ስለሚሰጡን በተለይ በአሁኑ ጊዜ ተቀዳሚዎቹ የዲያብሎስ ጥቃት ዒላማዎች ናቸው። ባሕረ ጥምቀተን በመከልከል፣ የጥምቀት በዓልን በመተናኮል፣ ፀበላቱንና የሕይወት ህብስትን በመመረዝ፣ ብሎም ለንስሐ የተዘጋጁትን የክርስቶስ ልጆች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በመግደል በፀረቤተ ክርስቲያን ዘመቻው ዲያብሎስ ምን ያህል ርቆ ለመሄድ እንደበቃ ዓይናችን እያየው ጆሮአችንም እየሰማው ነው።

በድጋሚ እግዚአብሔር ይጠብቀን እንጂ በቀጣዩና በቅርቡ ዲያብሎስ አውሬው በሃገራችን ሊፈጽመው ያቀደው ክስተት እርሱን የማይቀበለውንና ለእርሱ የማይሰግድለትን ሕዝበ ክርስቲያኑን ከቤተ ክርስቲያን ማራቅ ለዚህም እንደ ኮሮና ቫይረስ የመሳሰሉትን ተላላፊ በሽታዎች ከማሰራጨት ጋር የተያያዘ ነው። ልክ ዛሬ በቻይና፣ ደቡብ ኮርያ እና ጣልያን እንደሆነው በሃገራችንም ዓብያተ ክርስቲያናት በሮቻቸውን የሚዘጉበት፣ የሰንበት ቅዳሴዎች የሚቋረጡበትና እነደእነዚህ የመሳሰሉት ድንቅ “የማንቂያ ደወል መርሀ ግብራት” የሚቆሙበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። እግዚአብሔር እስከፈቀደልን ድረስ እንዲህ በትጋት እንቀጥልበታለን፤ ነገር ግን ለሁሉም ነገር አስቀድመን ብንዘጋጅ ጥሩ ነው!

የሚገርም ነው፤ “የማንቂያው ደወል መርሐ ግብር” በብዛት በዓርብ ዕለት ነው የሚካሄደው። ይህም በተጨማሪ ትልቅ “የማንቂያ መልዕክት” ይኖረዋል። በዚህ ዕለት የአዲስ ኪዳን ሥርዓት ክቡር ደሙ የፈሰሰበት የሕይወት ህብስት ቅዱስ ሥጋው የተቆረሰበት ዐረፍተ ማእከል የተናደበት እጸ መድኃኒት ቅዱስ መስቀሉ ተሰጠን። የክርስቶስ ተቃዋሚው፣ የመስቀሉ ጠላት አውሬው ግን የሚሰግዱለትን ልጆቹን (ሙስሊሞችን) በየመስጊዱ በዚሁ ዕለት ለመሰብሰብ ሆን ብሎ ይህን ዓርብ ዕለት መርጦታል። የእኛ የመንቂያ ቀን አርብ የእረፍት ቀን ሰንበት፤ የአውሬው “የዕረፍትና” ድል የተነሳበት ቀን ዓርብ ነው።

2012 – የኢትዮጵያ ግመሎች – ሳውዲ አረቢያ – ኮሮና ቫይረስ

በነገራችን ላይ፤ ኮሮና ቫይረስ አሁን ሁላችንም እንደሰማነው በቻያና መቀስቀሱን ነው። ይህም ሆን ተብሎ የተደረገ ነው። ነገር ግን ኮሮና ቫይረስ የጀመረው ከሰባት ዓመታት በፊት፡ በአውሮፓውያኑ 2012 .ም ላይ በሳውዲ አረቢያ ነው (ከኢትዮጵያ ወደ ሳውዲ የተላኩ ግመሎች ያመጡት ፤ “MERS‐CoV / መርስኮሮናቫይረስ”)። በፈረንጁም በኛም 2012 ብዙ ነገሮች ያየንበት / የምናይበት ቁልፍ ዓመት ነው።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የማንቂያ ደወል | አህመድ ይገድላል ይሞታል ፥ ኃይለ ሚካኤል ይገደላል ይኖራል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 23, 2020

ይህን ሰላማዊ የሆነ ሕዝብ የሚጠሉት ዲያብሎስና የግብር ልጆቹ ዘረኞቹ፣ አህዛብ፣ መናፍቃን እና ግብረሰዶማውያን ብቻ ናቸው። እየተገፋ፣ እየተበደለና እየተገደለ ጧፍ አብርቶ ይዘምራል፤ ይህ የትም ዓለም የለም፤ ድንቅ ነው! በተቀረው ዓለምና በኦሮሚያ ሲዖል እኮ ሰውን ዘቅዝቆ ለመስቀልና ለመበቀል አውሬው እንዴት እንደሚቸኩል እያየነው ነው።

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በአራት ቀናት ልዩነት “ክቡር“ መልአኩ ሰይጣን ሆነ | ምዕመናኑን የማስተኚያ ዲያብሎሳዊ ስልት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 14, 2020

ሊቀ መልአክት የነበረው ሉሲፈርም እንዲህ ነው የወደቀውየወደቁት ቤተ ክርስቲያናችንም ውስጥ ሰርገው ገብተዋልእዩት

ለመሆኑ እባባዊ የሆነውን የዲያብሎስን አካሄድ እየተከታተልን ነውን? ዘንዶው እዚህ እዚያ፣ ወዲያ ወዲህ እያለ ግራና ቀኝ ይዝለገለጋል፤ አንዴ እነደዚህ ሌላ ጊዜ እንደዚያ፣ አንዴ ሙቅ ውሃ ቆየት ብሎ ቀዝቃዛ፣ ትናንት ሽብር ፥ ዛሬ ፍቅር ፣ ዛሬ ደጋፊ፣ ነገ ተቃዋሚ፣ ዛሬ ኬኛ በበነገታው ኢትዮጵያ ሱሴ። ይህ እንግዲህ በቅርቡ ላዘጋጁት የዘር ጭፍጨፋ ሰውን በማለማመድ ላይ መሆናቸውንና፤ ሕዝቡም ከሲዖል ጣዕም ጋር እንዲተዋወቅ እየተደረገ መሆኑ ነው የሚነግረን። ነገሮችን ሁሉ በማዘበራረቅ የሰውን አንጎል ማጠብ፣ መበጥበጥና መቆጣጠር እንደሚቻል አውቀውታል / አምነውበታል። ሰው ነቅቶ ከአልጋው በመነሳት ለአመጽ እንዳይነሳሳና በአዲስ አበባ ለፈሩት የተቃውሞ ሰልፍ እንዳይወጣ የገዟቸውንና ያሰማሯቸውን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት፣ የስነ ልቦና እና የሜዲያ “ልሂቃን” ይጠቀማሉ። እንደምናየው “ተቃዋሚ ነን” ሲሉ የነበሩ ደካሞች ሳይቀሩ ሁሉም በገንዘብና በልጆቻቸው ሊከተል በሚችለው የግድያ ማስፈራሪያ ወይ አፋቸውን ዘግተውባቸዋል ወይ ወደ እነሱ ካምፕ አምጥተዋቸዋል።

እንደው እንደእነዚህ ዓይነት ቋቅ የሚያሰኙ አስቀያሚ “መሪዎች” በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ታይቶ ይታወቃልን። አይታወቅም! በፍጹም! አብዮት አህመድ እነ ሂትለርን፣ ሙሶሊኒን እን መንግስቱን ያስንቃል።

ወገኔ፡ ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ከዚህ የከፋ ጭካኔ፣ ውድቀትና ውርደት የታየበት ዘመን የለም። እናቶችህ ከየቤታቸው ይፈናቀላሉ፣ ወጣት ሴት ተማሪዎችህ ታግተው የደረሱበት አይታወቅም፣ ሕፃናቶችህ እየተበከሉ፣ እየተመረዙና እየታረዱ ነው፣ መንፈሳዊ አባቶችህ እንደ እብድ ውሻ እየታደኑ፣ እየታገቱና እየተገደሉብህ ነው ፥ መሀንዲሶችህ፣ ሐኪሞችህ፣ የጦር መሪዎችህ እየተረሸኑ ነው ፥ ልጆችህ፣ ሴቶችህ፣ አየርህ፣ ውሃህ፣ ወንዞችህ፣ አፈርህ፣ እህልህ፣ ጤፍህ፣ ዘይትህ፣ ዶሮዎችህ፣ በጎችህ ፍራፍሬህ፣ አየር መንገድህ፣ ባንክህ፣ ቴሌህ ፥ ባጠቃላይ ሃገርህ ለባዕዳውያኑ የታሪክ ጠላቶችህ እየተሸጡብህ ነው፤ አይኖችህ እያዩ ጆሮዎችህ እየሰሙ።

እስኪ ተመልከቱ፦ ሃያ አንድ ሴት ተማሪዎች ታግተው በጠፉበት ማግስት፣ የጥምቀት ታቦታት በኦሮሞ ሙስሊሞች ድንጋይ በተወረወረባቸው ማግስት፣ የኦሮሞ ፖሊሶች ቤተክርስቲያን ገብተው ምዕመናን በገደሉበት ማግስት እንዲሁም ቤተክርስቲያናቸውን ባፈረሱበት ማግስት አብዮት አህመድ በባሌ “ሰሜን ኢትዮጵያውያንን ሰበርናቸው፤ ፊንፊኔ ኬኛ” አለ።

ይህን የትዕቢተኞችና ጉረኞች “ድል የታወጀበትን” ንግግር ለማክበርና ሰሜን ኢትዮጵያውያንን ቀስበቀስ እየጨረሰላቸው ያለውን እብድ መሪያቸውንም ለመደገፍ ሲሉ ኦሮሞዎች በጅማና ዱባይ ስታዲየሞች ግልብጥ ብለው በተከታታይ መውጣት ወሰኑ። የምድር ሲዖል ባደረጓትና በተሰረቀችው ክልላቸው በተዋሕዶ ልጆች ላይ የሚካሄደውን ጭፍጨፋና የታገቱትን ሴት ተማሪዎች ጉዳይ አስመልክቶ ግን ስበዓዊነታቸውን በማሳየት ሰልፍ ለመውጣትና ድምጻቸውንም ለማሰማት፡ ያው ሁለት ዓመት ሆነው፡ ፈቃደኞች እንዳልሆኑ ኢትዮጵያ እያየችውና እየመዘገበችው ነው። ታዲያ እነዚህ “ኦሮሞ ነን” የሚሉ ከሃዲዎች ከነመሪዎቻቸው ከኢትዮጵያ ምድር በእሳት ቢጠረጉ ሊገርመን ይገባልን? በጭራሽ!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: