Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መምሕር ግርማ’

በተዋሕዶ አምላክ ጆሮዋ የተከፈታላት እናት እስልምናን በመተዋ ሙስሊሞች ወደ ክርስቲያኖች ዮቱብ ገጽ መጥተው ጋኔናቸውን ያራግፋሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 29, 2017

እያንዳንዱ ሙስሊም ውስጥ መንፈሳዊ እባብ አለ!

ክርስቲያኖች ቪዲዮውን አይተው ክርስቲያናዊ ፍቅራቸውንና ደስታቸውን ሲገልጹ፤ መሀመዳውያኑ ግን በድንቁርና እባባዊ መርዛቸውን፣ ጥላቻውን፣ ስድቡንና እርግማኑን ያስታውኩታል

ክርስቲያኖች ይህን ይላሉ፦

  • ዛሬ ላንቺ የደረሠልሽ ቅዱስ ገብርኤል ለኛም ይድረስልን ያሳደገኝ አምላክ አባ እረጅም እድሜ ይስጥልን አሜን
  • የኔ መድሀኒት አለም ላንተ ምን ይሣንሀል ሥራህ ድንቅ ነው ሥምህ የተመሠገነ ይሁን አባ ረጅም እድሜ ይሥጦት
  • ስለ ማይነገረው ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን እልልልልልልልልልልልልልል ለአባታችን እረጅም እድሜና ጤና አብዝቶ ይስጥዎት ለእናታችን የደረሰ አምላክ ለኛም ይርዳን ይፈውሰን አሜን አሜን አሜን
  • የቁልቢው ገብርኤል የራህማው ጌታ አንቺን የሰማሽ ጌታ እኛንም ይስማን የኔ አባት እረጅም እድሜ ይስጦት ያመነ የተጠመቀ ይድናል እኛም በተስፋ እንጠብቃለን
  • ኡፍፍፍ አልቅሼ ልሞት ነዉ እንኳን ደስ አለሽ የኔ እናት ድንቅ ነዉ የእግዚአብሄር ስራ እድሜዎን ያርዝምልዎት አባቴ
  • ተዋህዶ እቺ ነች ዝር ሃይማኖት አትምርጥም አባታችን ፈጣሪ እርጅም እድሜ ይስጥውት
  • ሙስሊሞች እባካችሁ አትሳደብ ሁሉም ስው የሚወደውና የሚፈቅደውን ሀይማኖት የመያዝ መብት አለው እግዚአብሔር ለሁላችንም ምህረትንና ድህነቱን ያድለን ለአባታችን እድሜና ጤና ይስጥልን አሜን
  • መልስ ያጣሁለት ጥያቄ ቢኖር የአላህን ስም ጠርታችሁ ለምን ትገላላችሁ ለምንስ ትሰግዳላችሁ የመለሰልኝ የለም ?????
  • አመነች ዳነች
  • አባታችን እድሜና ጤና ይስጥልን ለበረከት ያብቃን ከስደት መልስ
  • እግዚአብሔር ይመስገን በእውነት እግዚአብሔር ምን የሚሳነው ነገር አለ አህዛቦች ንቁ ለዘሀራ የደረሰ አምላክ ለእናንተም ይድረስላችሁ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር ለእባታችን እረጅም እድሜና ጤናን ያድልልን አሜን
  • ያነበብኩትማ እኔ እንደ ገባኝ ስለ ዳነች ተናደሽ ነው እና ወደ ብርሀን ስለመጣች ለምን ደንቁራ አልቀረችም ነው “”ስለ አመነች ዳነች ፦እንዲህ ናት ኦርቶዶክስ
  • ሙስሊም እማ ናት ሳትሆን ነኝ አትልም ደግሞ ምን ብላ አንቋሸሸች አልተሳደበች እስልምናን ስለ ዳንኩ ኦርቶዶክስ እሆናለሁ አለች እንጅ
  • ክብሩ ይስፋ ለመድሐኒ አለም አባ እድሜና ጤና ይስጥልን አሜን!!
  • እህቴ እንባዬን አስመጣሽው በእውነት ከስጋሽ የበለጠ ነብስሽ ንም አዳንሻት ፈተናውንም እንድትቋቋሚው ያርግሽ ክርስትና ሃይማኖት አልጋ በአልጋ አይደለችምና ምክንያቱም መስቀሉን ተሸክመናልና
  • ምን አለበት ሙስሊም እህቶቸ ዝም ብትሉ አስገድዶ እዩ ያላችሁ ሰው የለ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ እህቶቻችንን እዩዋቸው የሰዉን እምነት አያቆሽሹም
  • እኔ ምለው ሙስሊሞች ለምን ትሳደባላቹ ሰው የፈለገውን ማምለክ ይችላል ጥያቄው ለራሱ ነው ለማንኛውም ፈጣሬ እንኮን ማረሽ እናተን ይቅር ይበላቹ
  • ሙስሊሞች አትንጫጩ ክብር ምስጋና ለመድሀኒአለም እንኳን የክርስቲያን ልጅ ሆንኩ መዳን በእየሱስ ክርስቶስ በድንግል ማሪያም ልጅ ብቻ ነው
  • መናፍቅና ሙስሊም የሚሳደቡት በውስጣቸው ያለው አጋንት ነው ማስተዋል ያድላቸው ኦርቶዶክስ ለዘላለም ትኑር አባ እድሜወትን ያርዝምልን አሜንንንነ አሜንንን አሜንን
  • እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ተፈወሽ እህት ከጣዎት አምልኮት እንኳን ወጣሽ አላህ የሚባል አምላክ የለም ።
  • የነሱ ሀይማኖት ምን ይላል የአላን ቃል ያልተቀበለ ይገደላል ይላል የኛ ግን ያድናል ድንግን ክብረሽ ይሰፋ
  • ለሙስሊሞች ትምህርት ይሁን

ሙስሊሞች ይህን ያላሉ፦

  • አኡዙቢላሂሚነሸይጧን ረጅም ከኩፍር ጠብቀኝ
  • ዛራ አላህ እውነት አላህ ወደ ሀይማኖት እውነተኛ ወደ ሆነ ኢስሊምና ይመልስሽ ጆሮሽ ተደፍኖ ብቀር ይሻላል
  • ካወቅሽ አሁን ነው የተደፍነብሽ ጆሮሽ ሁሉ ነገርሽ አላህ የማይወልደው የማይወለደው የእየሱስ ጌታ የሆነው አምላካችን ህድያ ይስጥሽ
  • ትክክክል እኔማ ገና ስሰማት አኡዙቢላሂ ሚነሸይጣን ሮዥም እፍፍፍ ገና መስሚያዋ ጆሮተዘጋ አይ
  • ሲጀመር ካፊር ናት ድራማ ልተዉን አሰልጥነዋት ነዉ በሙስሊም ስም
  • ሙስሊም አመስለኝም ቀጣፊ ናት ሙስሊም እዛ አይሄድም አላህ ይድፈንሽ
  • ወሬኛ በያት እይው ኡስታዝ አቡ በከር ነገሩን ጨርሶታበኢስልምና ቆይቶ ክርስቲያን የሚሆኑት ስሙን ብቻ የያዙናቸው ምክንያቱም ቁርአን ምንእንደሚል የማያውቁናቸውብሏል ትክክልነው ይችም አላህ ህድያውን ይስጣት
  • ማንኛውም የየሰውዘር አላህአንድአሎለደምአልተወለደም ማንምያውቃልይሄን እዚህ በመዳምዋይፋይን አፋችሁንአትክፈቱብን አፋችሁን ቆጥቡ ምግብ ብሉበት
  • ይች አላህን የት ታውቂውአለሽ የኛ መድሀኒታችን ቁርአን ነው አንች ሲጀመር ሙስሊም አይደለሽም ውሸታሞች
  • ሠይጣን የተላበሠሽ ድሮም ካፊር ነሽ ሠይጣን ቀዉሥ
  • ቅማላም ድሮም ለሠዉ አይደለም ለቄሡ ሥገጅለት ሁለታቹም ሠይጣኖች አመዳሟች
  • ኤጭ ሲጀመር የሆንሽ ባለዛር ነው እምትመስይው ሀሀሀሀ ምን ትመስላለች ስይጣናም
  • ወይ እህት ጆሮሺ ባይስማ ይሻልሺ ነበራ ከብራሀን ወደ ጨለማ ጋባሺ አላህ ስብብ ባያደራግልሺ አትዲኒም ነበራ አሁንም ወደ ፈጠረሺ አማላክሺ አንድ አላህ ሱብሀኑ ተአላ ተመለሺ አላህ አንድ ነው አይወልዲም አይወለድም
  • አይ ጉድ አላህ ሆይ አሳሳቾችን ያዝልን እድካሁን ጆሮሽ ነበር አሁን ግን ሁለመናሺ ተዘግቶል ሱብሀን አላህ
  • ኢሥላም አሰዳቢ ሙተሽ ብሆን ይሻአልሽ ነበር እምነት ሽን ከመቀየር
  • ሸይጧኖች ምላስሽን ይዝጉት አቦ ምን አይነቷናት በአላህ እንዴት ታሻርካለች እየሱስ የአላግ ባሪያ መሆኑን እያውቀች እነዚህ አባ ተብየውች የሸይጧኖችና የአጋንት አሽከሮችን ናቸው እንፈውሳለን እያሉ እሳት የሚቅጨምሩ ያ አላህ አኽላቃችንን አሳምረህ እንደፈጠርክ ግደለን !!
  • ለዘላለም ይዝጋልሽ ሸይጣን አምላኪ ሲጀመር ሙስሊም አደለሺም ብትሆኒ ንሮ እዚህ እቀጣፊ ቄስ ጋ አትሄጅም ነበር ጅል

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

Ethiopian Exorcist — መምሕር ግርማ በቅዱስ እስጢፋኖስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2012

መንፈሣዊ ነፃነት ያለው ሰው ሥጋዊ ነፃነትም አለው!

_

 

ቪዲዮው ላይ የምናየው መምሕር ግርማ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ብዛት ካላቸው ምእመናን አጋንንት ሲያወጡ ነው።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከገጠሙኝ አስደናቂ የሆኑ ሁኔታዎች ይህ አንዱ ነበር።

መምሕር ግርማ በተመሳሳይ ድርጊት ተሠማርተው የቀረጹት ቪዲዮ ከሁለት ዓመታት በፊት እዚህ ብሎግ ላይ አቅርቤ ነበር። ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ እሳቸው በአዲስ አበባ እንደሚገኙ አላውቅኩም ነበር።

ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከገጠሙኝ አስገራሚና ድንቅ ከሆኑት ሦስት ሁኔታዎች መካከል ይህ አንዱ ነበር። ሦስቱም አጋጣሚዎችበጣም ተመሳሳይ በሆነ መንገድ የተከሰቱ መሆናቸው እስካሁን ድረስ ያስገርመኛል።

ዕለቱ ረቡዕ ነው፤ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ጎተራ አካባቢ አውቶብስ ቁጥር 56 (ባልሳሳት) ውስጥ ገብቼ ወደ ሽሮ ሜዳ ለመጓዝ ወሰንኩ። (የአዲስ አበባ አውቶብስ ካልሞላ በቀር በሁሉም መስክ በከተማዋ የተሻለ መጓጓዣ ሆኖ ነው ያገኘሁት)። ትንሽ መጓዝ እንደጀመርን የአውቶብሱ ነጂ እብድነት የተሞላበት ዓይነት አነዳድ ነበረው፡ አውቶብሷን ልክ እንደ ስፖርት መኪና ወዲያና ወዲህ እያዋዥቀ ሌሎች መኪናዎችን በግራና በቀኝ በችኮላ እይቀደመና ጥንቅቃቄ በጎደለበት ሁኔታ ፍሬን እየያዘ በአውቶብስ ውስጥ የነበረነውን 20 የምንሆን ተጓዦች በመረበሽ በደብረዘይት መንገድ መሃል መንገድ ላይ ይነዳ ነበር። ሁኔታው ስላላስቻለኝ ፡ ጠጋ ብዬ ቁጣየን በጩኽት ገለጥኩለት፤ ምናለ ተጠንቅቀህ ብትነዳ፤ ይህን ሁሉ ሰው ጭነህ፤ ከጓደኞችህ ጋር በጎን እያወራህ መንዳት ተገቢ አይደለም፤ ምናለ ይህን ምስኪን መንገደኛ ባክብሮትና ትህትና ብታገለግሉ…” ሌሎች መንገደኞችም የኔን ቁጣ በመደገፍ ይወቅሱት ጀመርሹፌሩ ግን ይባስ ብሎ አውቶብሷን በይበልጥ ያርገበግባት ነበር። እኔም አላስቻለኝም፤ ልክ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት አውቶብሷን ሲያቆማት ወርጄ የአውቶብሷን ታርጋ መዘገብኩ። በእውነት፡ አንበሳ አውቶብስ ድርጅት በቅርብ የማውቃቸው ሰዎች ስለነበሩ የዚህን ሹፌር ጉዳይ እንዲከታተሉ አደርጋለሁ ብዬ ዛትኩ።

እስጢፋኖስ ጋር ከወረድኩ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኗ አመራሁ። እዚያም በጣም ብዙ ሰዎች ተሰባስበው አንዳንዶቹም ሲጮሁና ሲወራጩ አየሁ። ምን ይሆን ብዬ አንዷን እናት ስጠይቃቸው፡ ሰዎቹ መምህር ግርማን ብለው መምጣታቸውን ነገሩኝ። ሙሉ በሙሉ በውሃ ርሰው የነበሩት ሴትዮዋም፡ ና! ልጄ ይህን የመሰለ መቁጠሪያ እዚያ ማግኘት አለብህ ብለው መቁጠሪያው ወደሚገኝበት ቦታ ወሰዱኝ። አባ ግርማ ከሚገኙበትና ብዙ ሰዎች ከተሰበሰቡበት የቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ በጥግ በኩል አንድ ተለቅ ያለ መኪና ውስጥ የነበሩ ሴትዮ መቁጠሪያውን በ20 ብር ይሸጡ ነበር። ሴትዮም፡ መቁጠሪያ ነው የምትፈልገው?” አሉና አውጥተው ሰጡኝ። እኔም፡ ይቅርታ ያድርጉልኝና፡ አባ ግርማን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ማንሳት ይቻል ይሆን?” ብዬ ሴትዮዋን ስጠይቃቸው፡ ሴትዮዋም በቁጣ፡ አይቻልም! ፈጽሞ አይቻልምብለው መለሱልኝ። ለመሆኑ ጉዳዮ እርስዎን ይመለከታል ወይስ ሌላ ፈቃድ ሊሰጠኝ የሚችል ሰው አለ?” አልኳቸው። እሳቸውም ወደ እኔ ቀና ብለው ሳይመለከቱ ቁጣቸውን ቀጠሉ። እኔም የሴትዮዋ ትህትና አልባነት ገርሞኝ ትንሽ ራቅ ብለው ወደሚገኙ ለአንድ ቄስ አባት ሁኔታውን አወሳኋቸው። ልጄ ከውጭ ነው የመጣኽው መሰለኝ፤ ይህን የመሰለ ቦታ ላይ ብዙ ዓይነት መናፍሳት ስለሚገኙ አንዳንዱ ሰው ሊፈተን ሊረበሽ ይችላልና አይድነቅህ ፡ ዝም ብሎ ማለፉ ነው የሚመረጠው ፡ ፎቶ ለማንሳት ከፈልግህ መምህር ግርማን ሄደህ ጠይቃቸውአሉኝ፡ በትህትና። እኔም ትክክለኛነታቸው ከምስጋና ጋር ካሳወቅኳቸው በኋላ፡ ወደ መምህር ግርማ ጠጋ ብዬ ከበስተኋላቸው ለሚገኙትን ረዳቶቻቸው እሳቸውን ማነጋገር እንደምፈልግ ሹክ አልኳቸው። ጋኔን በማስወጣት ላይ የሚገኙት መምህር ግርማም ዘወር አሉና፡ አንተ ማን ነህ? ከየት ነህ? ምን ፈልገህ ነው?” ብለው በያዙት መስቀል ግንባሬን ገፋ አደርጉት። ቀጥለውም እጃቸውን ወደ አንገቴ ሰደድ አድርገው እዚያ የሚገኘውን መስቀሌን መዳሰስ ጀመሩ፤ ምንድነው መስቀሉ በጨሌ የታሠረው?|” ፡ እሺ፡ ግድ የለም ፊልም ማንሳት ትችላለህበማለት ፈቃዳቸውን ገለጹልኝ። እኔም ከምስጋና ጋር አማተራዊ የፊልም አንሺ ሥራ ውስጥ በመግባት እጅግ በጣም አስገራሚ የሆኑትን ሁኔታዎች መታዘብ ጀመርኩ። ስማ፡ እዚያ ጋር፡ እዚያ ጋር፡ ፊልም ማንሳት አይቻልም!” የሚሉ የተለያዩ ድምጾች ከያቅጣጫው ይመጡብኝ ነበር። ነገር ግን እንደተፈቀደልኝ ሲያውቁ ፀጥ አሉ።

በርግጥ መምህር ግርማ ልዩ ጸጋ የተሰጣቸው፡ እድነስማቸውም ግርማ ሞገስ ያላቸው አባት መሆናቸውን ጠጋ ብሎ በማየት መገንዘብ ይችላል። ጸበሉ በተፈለገው ዓይነት መንገድ ይፍለቅ፡ በሰው ላይ የሚፈጥረው መንፈሳዊ ክስተት ኃያልና እውነትነት የተሞላበት ነው።

ከፍተኛ መንፈሳዊ ጦርነቶች በሚካሄዱባት አገራችን ዲያብሎስ ህዝባችንን እያዘናጋ ወደርሱ ወጥመድ ለማግባት ሌት ተቀን ደፋ ቀና እንደሚል፡ ቤተክርስቲያኖቻችን፡ ጸበላችንና መስቀላችን ከርሱ ጦር መከላከያ ይሆኑን ዘንድ የተሰጡን ውድ በረከቶች መሆናቸውን ይህን በመሳሰሉት አጋጣሚዎች በዓይኔ፡ በአካል ለመታዘብ እድሉ ስለነበረኝ፡ ያው ምስክር ሆኛለሁ።

ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያንም ልዩና ቅዱስ ከሆነው መንፍስ ጋር አብሬ ከወጣሁ በኋላ፡ የ 56 ቁጥር አውቶብሱ ሹፌር ሁኔታ ትዝ አለኝ፤ ሹፌሩን መገሠጼ ትክክል ቢሆንም ለቀጣሪው ክስ ላቀርብበት የነበረው ስሜታዊ ኃሳብ ትክክል እንዳልሆነ ገባኝ። እንዲያውም ምስኪኑ ሹፌር እኔን ያለ ፕላኔ በተዘዋዋሪ መንገድ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ያደርሰኝ ዘንድ የሆነ ኃይል ልኮት መሆኑን በመገንዘቤ፡ በወቅቱ ደግሜ አግኝቼው ቢሆን ኖሮ ሞቅ ያለ የወንድማዊ ሰላምታ ልሰጠው በጣም ተመኝቼ ነበር።

አበው ይናገሩ

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ

የምንኩስና ግብር ምን ነበር ሚስጢሩ

የክርስቲያን ህይወት ምን ነበር ተግባሩ

መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ

እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና

ወልድ ዋህድ ብሎ በእምነቱ የፀና፡፡

ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ

ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ

ነቢያት በመጋዝ የተሰነጠቁት

ሀዋርያት ቁል ቁል የተዘቀዘቁት

ሰማእታት በእሳት የተለበለቡት

ቅዱሳን ገዳም ደርቀው የተገኙት

ሚስጥሩ ምን ነበር አበው ይናገሩት፡፡

ይናገር ዝቋላ ጊሸን ላሊበላ

የቅዱሳንን አጽም ለምን እንዳልበላ፡፡

ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር

እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡

ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት

ወይስ ሃብት ንብረት የተሟላ ቤት

ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት

እናንተ ገዳማት ምስጢሩን አውሩት፡፡

ጎበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና

ምግባር ሃይሞኖቱን በእጅጉ ያቀና፡፡

እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት

ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡

የጊዮርጊስ ወዳጂ የት ነው የሚገኘው

በመሃል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው

ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው፡፡

ወገን ሰው ናፈቀኝ አይኔን ሰው አማረው

የሃይማኖት ጀግና የት ነው የማገኘው?

ልጋባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት

ማህበረ ስላሴ ከቅዱሳ ቤት

አክሱም ጊሸን ማርያም ከቃልኪዳን ቦታ

ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ፡፡

ፈርሃ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ

ቤተክርስቲያንን ያልተዳፈረ

የት ነው የሚገኘው ለሃይማኖቱ ሟች

ለተዋህዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች

የወገን መመኪያ የከሃዲ መቅሰፍት

ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሳ ቀስቅሱት

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ

የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምስጢሩ

የክርስቲያን ህይወት ምን ነበር ተግባሩ

መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

ወገን ሰው ናፈቀኝ አይኔን ጀግና አማረው

በእምነት የፀና የት ነው የማገኘው፡፡

ወልድ ዋህድ ብሎ በእምነቱ የፀና

ብቅ ይበል እንየው እሱ ማን ነው ጀግና

በጎችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ

መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ

የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ

እንደዚያ እንደጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ፡፡

የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው

የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው

የዓለም ደስታዋ ልቡን ያልማረከው

የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?

ምስጢርን ከምስጢር አንድ አድርጎ ተምሮ

ወልድ ዋህድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ

እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ

ከጳውሎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር

መሆኗን የሚያምን ማህደረ እግዚአብሔር

ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን

ትንታግ ምልስ ጭንግፍግፍን

ልሣነ ጤዛ መናፍቅን

ወልደ አርዮስነ ዲቃላውን

በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ

ጀግና ማን ነው ብቅ ይበላ፡፡

ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት

እስኪ ጎርጎርዮስ ይምጣና ጠይቁት፡፡

ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ

ምስጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ

የክርስቶስ ባሪያ የአጋንንት መቅሰፍት

ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት

ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት

የፀሎት ገበሬ ገብረመንፈስ ቅዱስንም ይነሳ ቀስቅሱት

ይነሳ ጊዮርጊስ ይመስክር ምስጢር

የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ

ዲያቢሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ

ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ

እመር ብለው የወጡት ከስጋ ገበያ

ፆም ፀሎት ነበር የሃይማኖት ጋሻ

እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት

አላማው ምንድን ነው የዘመኑ ወጣት፡፡

እኔስ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና፡፡

ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ

ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

ምንጭ፡ ደቂቀ ናቡቴ

_

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: