Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መምህር’

ኒቆዲሞስ (የዐቢይ ጾም ሰባተኛ ሳምንት) ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 2, 2023

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 😇 ተክለ ሐይማኖት 👉 መርቆርዮስ 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

  • ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
  • ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
  • ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው። ዮሐንስ ፫፥፲
  • ኒቆዲሞስ ምሑረ ኦሪት ነው። ዮሐንስ ፯፥፶፩

ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ ፩–፪)

በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ ፯፥፵፰–፶፪። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።

የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ­ የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሐንስ ፫፤፪

ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?

/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለም ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል በትህትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።

ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና › ዮሐንስ ፱፤፬

/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን

ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ ዮሐንስ ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።

/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል

በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው› ማቴ ፲፫፡፳፫

አንዳንዶቻችን ጸሎት እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሄርን ቃል ይነዳል ልባችን ሌላ ቦታ ይንጎዳጎዳል በማህበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመሃል ሳይን አውት አርገን ልክ ሲፈጸም አለቀ እንዴ ብለን ሳይን ኢን የምናደርግ አንጠፋም።

/ ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለም ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈግ ያስረዳናል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሃ ውስጥ ሆነን የምንሰማ ያለንስሃ የምንሰማው ቃል በህይወታችን ፍሬ የማፍራት እድሉ ጠባብ ነው ምክንያቱም በንስሃ ከልባችን ያልጸዱት ክፉ ምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና

ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀው› ማቴ ፲፫፤፰ ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው።

፭/ ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣ ነበር ብሉያት ከሓዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል አንዳንዶች ዛሬ ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋህዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነው ለዚህም ነው ጌታ ሲያስተምር‹እውነት እላችኋለው ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም› ማቴ ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረው ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰአት ለመማር ችⶀል እኛም ከሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባ አይጠፋምና ምንም ስራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜ አይጠፋምና ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ልንሰት ይገባል።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2023

😇 በተለይ በዚህ ዘመን አባታችን፣ ካኽናችን፣ ፓትርያርካችን፣ መምህራችንና መሪያችን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።

💭 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው። ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም። ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥ በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥ በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ። እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ።

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፫]❖❖❖

፩ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው።

፪ ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።

፫ ስለዚህ ያዘዙአችሁን ሁሉ አድርጉ ጠብቁትም፥ ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ።

፬ ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ፥ እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳ ሊነኩት አይወዱም።

፭ ለሰውም እንዲታዩ ሥራቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ ዘርፉንም ያስረዝማሉ፥

፮ በምሳም የከበሬታ ስፍራ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር፥

፯ በገበያም ሰላምታና። መምህር ሆይ መምህር ሆይ ተብለው እንዲጠሩ ይወዳሉ።

፰ እናንተ ግን። መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።

፱ አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም። አባት ብላችሁ አትጥሩ።

፲ ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና። ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ።

፲፩ ከእናንተም የሚበልጠው አገልጋያችሁ ይሆናል።

፲፪ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል።

፲፫ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።

፲፬ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በጸሎት ርዝመት እያመካኛችሁ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ፥ ወዮላችሁ፤ ስለዚህ የባሰ ፍርድ ትቀበላላችሁ።

፲፭ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።

፲፮ እናንተ። ማንም በቤተ መቅደስ የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል የምትሉ፥ ዕውሮች መሪዎች፥ ወዮላችሁ።

፲፯ እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?

፲፰ ደግማችሁም። ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል ትላላችሁ።

፲፱ እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች፥ ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?

፳ እንግዲህ በመሠዊያው የሚምለው በእርሱና በእርሱ ላይ ባለው ሁሉ ይምላል፤

፳፩ በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤

፳፪ በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።

፳፫ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።

፳፬ እናንተ ዕውሮች መሪዎች፥ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ።

፳፭ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውስጡ ቅሚያና ስስት ሞልቶ ሳለ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ስለምታጠሩ፥ ወዮላችሁ።

፳፮ አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፥ ውጭው ደግሞ ጥሩ እንዲሆን አስቀድመህ የጽዋውንና የወጭቱን ውስጡን አጥራ።

፳፯ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ በውጭ አምረው የሚታዩ በውስጡ ግን የሙታን አጥንት ርኩሰትም ሁሉ የተሞሉ በኖራ የተለሰኑ መቃብሮችን ስለምትመስሉ፥ ወዮላችሁ።

፳፰ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጭ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ፥ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል።

፳፱ እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ የጻድቃንንም መቃብር ስለምታስጌጡና።

፴ በአባቶቻችን ዘመን ኖረን በሆነስ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር ስለምትሉ፥ ወዮላችሁ።

፴፩ እንግዲያስ የነቢያት ገዳዮች ልጆች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ ትመሰክራላችሁ።

፴፪ እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ።

፴፫ እናንተ እባቦች፥ የእፉኝት ልጆች፥ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?

፴፬ ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤

፴፭ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።

፴፮ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።

፴፯ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም።

፴፰ እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል።

፴፱ እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም።

______________

Posted in Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መላዋ ፈረንሳይ እና ፕሬዚዳንቷ በሙስሊሞች አንገቱን ለተቀላው መምህር ብሔራዊ ክብር ሰጡ | እኛስ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 24, 2020

ሳሙኤል ፓቲይ የተባለው መምህር በክፍሉ ውስጥ አወዛጋቢ የነብዩ መሐመድ የካርቱን ስዕሎችን ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ ከትናንት በስቲያ አንድ የ፲፰ ዓመት ወጣት ትምህርት ቤት አቅራቢያ አንገቱን መቅላቱ ይታወሳል።

ሳሙኤል ፓቲይ የሚያስተምርበት ትምህርት ቤት መምህራንን ጨምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች “እኔም መምህር ነኝ” “እኛ ፈረንሳይ ነኝ” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል።

ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን መምህሩ አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው “በእስላማዊ የሽብር ጥቃት ነው” ብለው ነበር።

አሸባሪው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የኢትዮጵያ መሪ እንዳልሆነና የሃገራችን ጠላት እንደሆነም በተደጋጋሚ አይተነዋል ስለዚህ በዋቄዮ-አላህ ልጆች በመገደል ላይ ስላሉት ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች እንኳን ብሔራዊ የመታሰቢያ ቀን ሊያውጅ የማይሰማውን “ሃዘኑን” እንኳን እንደ ፖለቲከኛ ለመግለጥ እንደማይሻ ከአንዴም አሥር ጊዜ አይተነዋል። በሌላ በኩል ግን የተደራጁ ኢትዮጵያውያን ተቋማት ለምሳሌ ቤተ ክህነት ለምንድን ነው ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን በጎቿን “ወደ መንገድ እንውጣና ሃዘናችንን እንግለጥ! ታግተው የተሰወሩት ሴት ተማሪዎች የት እንደደረሱ እንጠይቅ!” የማትለው?

____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ታዋቂው የክርስትና መምህር ስለ አህመድ ዲዳት ብዙ ያልተሰማውን ጉድ አጋለጡ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 25, 2020

በምዕራቡ ዓለም ብዙ ዕውቅናንና ተወዳጅነትን ካተረፉት ድንቅ የክርስትና ጠበቃዎች መካከል ትውልደ ሕንዱ ደራሲና መምህር ዶ/ር ራቪ ዘካርያስ አንዱ ናቸው። በግንቦት ወር ላይ ሕይወታቸው ያረፈው (ነፍሳቸውን ይማርላቸው!) እኝህ ካናዳዊአሜሪካዊ ኢአማንያንን ያንቀጠቀጡ፣ ሞርሞኖችን ጸጥ ያሰኙ፣ ሸሆችንና ኢማሞችን ጨምሮ በጣም ብዙ ሙስሊሞችን ከእስልምና ባርነት ነፃ ያወጡ ግለሰብ ነበሩ። በንግግር የማሳመን ችሎታቸው በጣም የሚደነቅ ነበር። እናዳምጣቸው

ከዕለታት አንድ ቀን በማሌዢያ ጥንታዊ በሆነው የእስልምና ዩኒቨርሲቲ ንግግር እያደርኩ ነበር። በወቅቱ በጣም ውጥረት ነበር፤ እስልምና እምነታቸውን እንደማላጠቃባቸው፤ ነገር ግን ክርስትና እምነቴን እንደምከላከል ቃል ገባሁላቸው፤ ስለ ክርስትና የፈለጉትን እንዲጠይቁኝ ነገርኳቸው።

የማላይ እስላም ዩኒቨርሲቲ የእስላማዊ ጥናቶች መምሪያ ሊቀመንበር ባሃራዲን የተባለች ሴት ነበረች፤ አሉ የተባሉትን ሙላዎችና የእስልምና ሊቆችበመጀመሪያው ረድፍ ወንበር ላይ ቦታ እንዲይዙ አድርጋቸው ነበር፤ በጣም ውጥረት የተሞላበትና አስፈሪ ሁኔታ ነበር።

መከላከያዬን ማቅረብ የጀመርኩት ኢየሱስ ክርስቶስ በቃሉ ውስጥ ነኝ ስላለው አምላክነቱ በማውሳት ነበር።

ለ፵፭ ደቂቃ ያህል ውጥረት በተሞላበት መልክ ለጥያቄዎቻቸው ሁሉ መልስ ሰጠሁ፤ ከዚያም ወደ ሊቀመንበሯ ጽሕፈት ቤት እንዳመራሁ በኢየሩሳሌም ስላገኘሁትና የሃማስ መስራቾች ከነበሩት መካከል አንዱ ስለሆነው ሸህ ታሪክ ነገርኳት።

ሽሁ የክርስቶስን አምላክነት በሚያሳምን መልክ ሳስረዳው “ሌላ ጊዜ ባገኝህ ደስ ይለኛል” ብሎ ሁለቱንም ጉንጮቼን ስሞ ተሰናበተኝ።” አልኳት።

የዩኒቨርሲቲው ሊቀመንበሯም “አቶ ዘካርያስ፤ ክልክል ባይሆን ኖሮ እኔም እንደ ሸሁ ለስንብት ጉንጮችህን እስማቸው ነበር፤ ለዩኒቨርሲቲው እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ነው ዛሬ የሰጠኸንና” አለችኝ። እኔም፤ /ሮ ባሃራዲን እኔ የክርስቶስ አምባሳደር ነኝ” አልኳት።

በዚህ ወቅት አንድ ክርስቲያን ፕሮፌሰር () ወደኔ መጥቶ እንዲህ አለኝ፤

/ር ዛካርያስ ዛሬ ምን ያህል ወሳኝ ቀን እንደሆነ ታውቃለህን? ፥ ደቡብ አፍሪቃዊው ፀረክርስቶስ፣ መርዘኛ፣ ጉረኛ፣ ጠላተኛ የእስልምና ሊቅአህመድ ዲዳት ዛሬ እዚህ መጥቶ ክርስትናን በመናቅ በአጸያፊ ሁኔታ ሲሰድብ፣ ሲያንቋሽሽና ሲያጣጥል አይቼ “ይህ ሰው ይህ ሰው ሊሠራው የፈለገው ነገር ምንድር ነው? ምን ይጠቅመዋል?| ብዬ እራሴን ጠየቅኩ።

በዚህ ወቅት በአዳራሹ እጄን አንስቼ “ፕሮፌሰር ዲዳት እኔ ክርስቲያን ነኝ ለምንድን ነው ክርስትናዬ እምነት የሚጣልበት ሃይማኖት አይደለም” ያልከው ብዬ ጠየቅኩት፤ ወዲያውም አህመድ ዲዳት ቆጣ ብሎ፤ “ወደዚህ ና! መድረኩ ላይ ውጣ!” አለኝ።

መድረኩ ላይ እንደወጣሁም አህመድ ዲዳት እጁን በሰፊው ዘርግቶ ፊቴ ላይ ክፉኛ አጮለኝ፤ በዚህ ወቅት መቆም እስኪያቅተኝ ጉልበቴ መንቀጥቀጥ ፊቴም መጮኽ ጀመረ፤ ዲዳት ግን „ሌላኛውን ጉንጭህን አዙረው” አለኝ።

በዚህ ወቅት “አምላኬ በእውነት እፈልግሃለሁ” እያልኩ መጸለይ ጀመርኩና ጉንጬን አዞርኩለት፥ አህመድ ዲዳትም ቡጢውን ሰብስቦ “ጉዳዩን ፈጣን ማድረግ አለብን፤ ሸሚዝህን አውልቅ!” አለኝ፤ እኔም ሸሚዜን አውልቄ ሰጠሁት፤ “ሱሪህንም አውልቀህ ስጠኝ” አለኝ ፥ እኔም በአዳራሹ ሰልሚገኙት ተማሪዎቼ ዘወር ብዬ “ይቅርታ አድርጉልኝ፤ ግን ጥያቄውን ለማሟላት ሱሪየን አውልቄ እሰጠዋለሁ” አልኳቸው።

መድረክ ላይ በተማሪዎቼ ፊት እርቃኔን ቀረሁ፤ ሸሚዜንና ሱሪየን ለአህመድ ዲዳት አስረክቤ ወደ ጽሕፈት ቤቴ አመራሁ፤ እዚያም ከፊቴ ህመም ጋር በማልቀስ አምላኬን ለሰጠኝ ብርታት አመሰግነው ጀመር።

በዚህ ወቅት በሩ ተንኳኳ፤ እንደከፈትኩትም፤ ብዙ ተማሪዎች ረጅም ሰልፍ ሠርተው አየኋቸው፤ 98% ሙስሊም ተማሪዎች ናቸው። አህመድ ዲዳት በክርስቲያኑ ፕሬፌሰር ላይ ለፈጸመው ወራዳ ተግባር ይቅርታ ለመጠየቅ ሁሉም ተንበርክከው መለመን ጀመሩ።

ፍቅር ጭፍን ጥላቻን ያሸንፋል ፥ ጥላቻ ማንንም ከማጥፋቱ በፊት ጠይውን ያጠፋል ፥ ፍቅር በሰው ልብ ውስጥ ያሉትን ይዘቶች አሸንፏል ፣ በመጨረሻም ፣ ውጭውን ያሸንፋል።

ባንድ ወቅት ዝነኛው የቀድሞው የፈረንሳይ መሪ ናፖሊዎን ቦናፓርት እንዲህ ብሎ ነበር፤

የታላቁ አሌክሳንደር እና የእኔ መንግስታት መጨረሻቸው ይመጣል፥ የክርስቶስ ግን ዘላለማዊ ነው፤ ምክኒያቱም እኛ በጦር መሳሪያ ሃይል ስላሸነፍን ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በፍቅር ስላሸነፈ ነው”።

______________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: