Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መምህር ዮርዳኖስ’

ገዳይ አብይ ተንቤንን በአውሮፕላን የሚደበድበው አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅን ለመበቀል ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 14, 2020

አባ ዓቢየ እግዚእ በ፲፬/14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ተወለዱ

+ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከ ፩/1ሺህ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል

ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ እ..አ በ2014 .ም በሉሲፈራውያኑ ተቀባ

እንደ ግራኝ አህመድ ቀዳማዊ አባቱ። ዲቃላው አብዮት አህመድ አሊ የሴቲቱን የገዥነት ስምና ክብር በመያዝ ነው በአክሱም ጽዮን ላይ ጦርነቱን ያወጀው። እንደምናስታውሰው ከመቶ ሃያ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያውያን በአድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል ምንም እንኳ ባጠቃላይ የእግዚአብሔር ድል ይሁ እንጅ በውስጡ ግን የሚያስተላልፈውና የሚናገረው ሌላ ምስጢር ነበር፤ ይህም የአደዋው ድል የእቴጌ ጣይቱ ብጡል ድል መሆኑን ነው። ድሉ የሴቶችን የበላይነት ይናገር ነበር፤ የሴቶች የበላይነት ስምና ክብር የታየበት፣ የተገለጠብትና የነገሰበት ድል ነበር። ይህ ደግሞ አዲሱ የዓለም መንግስት የተመሰረተበት ህግ ወይም መልክና ምሳሌ ነው። በተቀደሰችው ምድር በኢትዮጵያ ላይ ይነግስ ዘንድ ያለውም የአህዛብ የስጋ ማንነትና ምንነት በዚህ መልክና ምሳሌ የሚገልጽ ነበር። አንድ ወንድ እንኳን በምድሪቱ ውስጥ ስላልነበረ ያ የስጋ ማንነትና ምንነት በሴቲቱ መልክና ምሳሌ በኩል በመንግስቱ ዙፋን ላይ ሊነግስ የከለከለው አልነበረም።

በግራኝ አብዮት አህመድ በኩልም እየተለጸ ያለው ይህ የስጋ ማንነት እና ምንነት ነው። “ገና በሰባት ዓመቴ እናቴ ንጉሥ ትሆናለህ ብላኝ ነበር” እያለ ሲሽለመጠመጥ ነበር ፥ ከፕሬዚደንቷ እስከ ሰላም ሚንስትሯ ድረስ ቀጣፊ ሴቶችን በብዛት ማንገሱ ያን ለአህዛብ የተሰጠ የዲያብሎስ የስጋ ማንነትና ምንነት በራሱ ላይ አንግሶ የመጣ የእግዚአብሔር ቀንደኛ ጠላት ስለሆነ ነው። ይህን በሃጋር፣ በእስማኤል፣ በግራኝ አህመድ ቀዳማዊ፣ በአፄ ምኒሊክ፣ በእቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ፣ በመንግስቱ ኃይለማርያም እና በኃይለማርያም ደሳለኝ ላይ የነገሰውን የዲያብሎስ የስጋ ማንነትን እና ምንነት በራሱ ላይ በማንገስ ነው ዛሬ ግራኝ አብዮት አህመድ በአክሱም ጽዮን ላይ ለመዝመት የደፈረው።

ጻድቁ አባታችን አባ ዓቢየ እግዚእ በሚኖሩበትበማርያም ታምባ ተንቤን ዙሪያ፡ ይህን በምጽፍበት ወቅት፡ የውጊያ አውሮፕላኖች ብዙ ድብደባዎች በማካሄድ ላይ መሆኑ በክርስቶስ ተቃዋሚነቱ እና በፀረተዋሕዶ አቋሙ ምን ያህል እርቀት እንደሄደ ነው የሚያሳያን። ይህን እያዩ ከዚህ የክርስቶስ ተቃዋሚ ጎን የተሰለፉ “ኢትዮጵያውያን ነን፣ ተዋሕዶ ነን” የሚሉ ከንቱ ግብዞች ሁሉ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች እና የኢትዮጵያም ጠላቶች ስለሆኑ አብቅቶላቸዋል፣ ወደ ጥልቁ እየፈረጠጡ ያሉ ሰውመሰል የሰይጣን ፈረሶችና የሳጥናኤል ባሪያዎች ሆነዋል።

ይህ የእባብነት ቆዳ ቀይሮ በመምጣት በቅድስት ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አዲሱን የሉሲፈርን የዓለም መንግስት ለመመስረትና ሕዝቡንም ሊገዛ የተገሰለ ቆሻሻ፣ ጨካኝ፣ አላጋጭ የዲያብሎስ የግብር ልጅ ክፉ አሟሟትን እንደሚሞታት ምንም ጥርጥር የለኝም።

👉 ❖❖❖ አባ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)❖❖❖

አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ፲፬/14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው። የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ። አጥምቀው ‘ዓቢየ እግዚእ’ ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጉመ መጻሕፍት ናቸው። ትርጉሙም “በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው” ማለት ነው።

+ ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ። ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኩሰዋል።

+ በገዳሙ በጾም: በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል። በጊዜው በ፵/40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር።

+ ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል። ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ

አባትም ነበሩ። ከትግራይ እስከ ደንቢያ ደግሞ ሃገረ ስብከታቸው ነው።

+ አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ። ቀኑ ነሐሴ ፲/10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ፫ ቀናት ባለመጉደሉ ከ፩ሺህ በላይ

ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ። ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና “አምላከ ሙሴ” ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ።

+ ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ። ይሕን ድንቅ ያዩ ከ ፩/1ሺህ በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል። ይሕም ዘወትር ነሐሴ ፲/10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው(ጐንደር)ይከበራል።

+ ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ። ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች። ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር።

+ በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሠል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት። ይሕንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ። በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ።

+ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም።

በሰማይም እሳትን አያዩም። ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም።ብሏቸው አርጓል።

+ ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል። ይሔው እኛ ምን ብንከፋ: ጻድቁንም ብንረሳቸው እግዚአብሔር ግን ዛሬም በጻድቁ ምልጃ ከተማዋን ጠብቆ

ይኖራል። ነገን ደግሞ እርሱ ያውቃል። ዛሬ ቤተ ክርስቲያኑ የታነጸበት ቦታ (ጎንደር ቀበሌ 09 ኪዳነ ምሕረት) ጻድቁ የጸለዩበት ቦታ ነው። እንኳን በወርሃዊ በዓላቸው (በ፲፱/19) ይቅርና ዓመታዊ በዓላቸው (ግንቦት ፲፱/19) ለንግስ የሚመጣው

ሰው ቁጥር ያስተዛዝባል።

+ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው: ፫ ሙታንን አስነስተው: ብዙ ድውያንን ፈውሰው: ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው: የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው: በ፻፵/140 ዓመታቸው ግንቦት ፲፱/19 ቀን አርፈዋል።

የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው።

+ ተአምሪሁ ለጻድቅ አቡነ ዓቢየ እግዚእ – – – ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም። አሜን።

👉 ❖❖❖ ከበዙ ተአምራቱ አንዱን ❖❖❖

ጻድቁ አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው #ተንቤን (መረታ) ሳሉ አንዲት መበለት መጥታ አባቴ! የምጠጣውን ጸበል ባርከህ ስጠኝ?” አለቻቸው። ጻድቁም በውሃው ላይ ጸሎትን አድርሰው: በመስቀላቸው ባርከው ሰጧት።

+ ወደ ባልንጀራዋ ስትደርስ ግን ሐሳቧን ቀየረችና ልጠጣውብላ የተቀበለችውን ማይ (ጸበል)

ልትጠመቅበት (ልትጸበልበት) ወሰነች። ባልንጀራዋንም በላዬ ላይ አፍሺልኝስትል አዘዘቻት።

+ ባልንጀራዋም እሺብላ ልታፈስላት (ልትጸብላት) በፋጋ(ግማሽ ቅል) ያለውን ጸበል አነሳች። ልታፈሰው ስትዘቀዝቀው ግን ከሆነው ነገር የተነሳ 2ቱም ደነገጡ። ጸበሉ የረጋ ደም ወደ መሆን በቅጽበት ተለውጧልና።

+ ፍጹም ፍርሃት የወደቀባቸው ሴቶቹ እየተሯሯጡ ወደ አባ ዓቢየ እግዚእ በዓት ደረሱ። ከውጭ ሆነውም አባ! አባ! የሰጠኸን ጸበልኮ የረጋ ደም ሆነአሏቸው። ጻድቁም እንዳላዋቂ ምን አጠፋችሁ?” ሲሉ ጠየቁ።

+ “አባታችን! ምንም አላጠፋንም። ብቻ አፍሺልኝ ብየ ስሰጣት እንዲህ ሆነስትል አንዷ መለሰች። ጻድቁ ግን በየውሃት ልጆቼ! ሁሌም : ‘ምንም አላጠፋንምአይባልም። ሰው ሆኖ የማይበድል የለምና።

+ . . . አንቺም ልጄ! እኔን ያልሺኝ የምጠጣው ጸበል ስጠኝነበር። ግን ልትጸበይበት ወደድሽ። ስሕተትሽ ከዚህ ይጀምራል። (የቅዳሴ ጸበል ለመጸበል አይሆንምና)

¤ በዚያ ላይ አልቦ ዓቢይ ኃጢአት ከመ ወልጦ ቃል . . .ከውሸት በላይ ከባድ ኃጢአት የለም።” [ዮሐ. :፵፬]

+ . . . በተጨማሪ ደግሞ ያለ ስልጣኗ እህትሽን አጥምቂኝአልሻት። ስለነዚህ ነገሮች ጸበሉ ተለውጦባቹሃልብለው ወደ ጸበሉ በመስቀል አማተቡ። እፍሲሉትም የረጋ ደም የነበረው ማይ ወደ ጸበልነቱ ተመለሰ። ይህንን ያዩ ሴቶቹ በግንባራቸው ተደፍተው ለጻድቁ ሰገዱ።

👉 ጸሎቱ ወበረከቱ የሃሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም። አሜን።

አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን።

__________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ማንን ለመምታት ነው ወደ ሰማይ ጥይት የተኮሳችሁት? ለየትኛው ድል? ለማን ሠራዊት?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2020

👉 ጦርነት እና ሰላም

ጦርነቱ የተጀመረው እኮ ኦርቶዶክሳውያንን እርስበርሱ አጋጭቶ፤ በትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያንን ሆድ እና ጀርባ ለማድረግ ነው፤ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል።

☆ “ክፉ ትውልድ ደረቅ ሴትን ይመስላል፤ እግዚአብሔርን “ቅሰፈኝ!” ይለዋል”

በጦር አንደበት፣ በፈረስ ጉልበት ያሸነፍን ይመስል ሙሉ አማራ ክልል እንዲህ ሲጨስ ያደረ ለምንድን ነው? በሰንበት ምድር ሰው ማሕሌትና ቅዳሴ ይስማ ወይስ የእነሱን ጥይት ይስማ? እያንዳንዷ የቀልሃ ጠብታ አንድ ቀን ትጠማዋለች። ፈጽሞ የሚያሳዝን፣ የሚያሳፍር ነገር ነበር።

ዛሬ እኮ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ ተብሎ የተከለለው ክልል ጣልያን የከለለው እንጂ እንዲህ የሚባል ክልል እኛ አናውቅም፤ ጠላት ያሰመርልን ክልል አንቀበልም። እኛ የምናውቀው አንዲ አገር፤ ከዚያ ባለፈ ክፍለ ሃገር ነው የምናውቀው፤ በጌምድር፣ ጎጃም፣ ትግራይ፣ ወሎ፣ ሸዋ፣ ወለጋ፣ አርሲ፣ ሲዳሞ፣ ሐረርጌ፣ ኢሉባቡር፣ ጋሞጎፋ የሚባሉትን ክፍለ ሃገራት ብቻ ነው።

ፖሊስ ሌባ እያባረረ ወደላይ ቢተኩስ ለማስፈራራት ነው፤ ተኩሶ ላለመምታት ነው፤ ግን በባዶ ሜዳ ለደስታ ተብሎ ጥይት ወደ ሰማይ የሚተኮሰው ወደ ሰማይ ያለው ማን ነው? እግዚአብሔር አይደልን? ማንን ፍለጋ ነው ወደ ሰማይ የምንተኩሰው? ይህ እኮ ባቢሎናውያኑ የነ ናምሩድ የነ ሰናኦር ሥራ ነው፤ ኑ እግዚአብሔርን እንውጋው! ወደ ሰማይ ጦር ይወረውሩ የነበሩ እነርሱ ናቸው። እንዴት አንድ አማኝ ክርስቲያን ቁጭ ብሎ ወደ ሰማይ ጥይት ይተኩሳል? ለስድስት ሰዓት ሙሉ እንዴት ጥይት በከንቱ ያለማባራት ወደ ሰማይ ይተኮሳል። በገንዘብ ደረጃ እንኳን ሲታሰብ እያንዳንዱ ጥይት በሚሊየን ብር ዋጋ ያወጣል፤ በዚህ እንኳን ብልጠት የለም። ሲጀመር እኮ ጦርነቱ ተጀመረ እንጂ አላለቀም፤ መቀሌን ለመቆጣጥር? መቀሌ እኮ የጠላት ከተማ አይደለችም የእኛው ናት፤ አስመራን፣ ካርቱምን ወይ ናይሮቢን አይደለም እኮ የያዝነው። እኛ የያዝነው እኮ የገዛ ከተማችንን ነው፤ እዚያም ያሉት እኮ ወገኖቻችን ናቸው፤ ምኑ ነው ተዓምሩ? ለመሆኑ እስካሁን በተደረገው ጦርነት ስንት ወገን የሞተ ይመስላችኋል? ስንት ተዋጊ፣ ስንት ንጹሐን ተገድለዋል? ቀላል አይደለም! እንደው የሰውን ጨለማ ልብ፣ የሰውን አለማስተዋል ለመግለጥ ቃል ያጥረኛል። እነርሱ እንደሚሉት እሺ ቲፒኤልኤፍ ጠፋች፤ ግን ተውትና መንግስት ጡጦ የሚያጠባው የእሷ ትንሽ ወንድሟ ኦነግ አለ አይደለም እንዴ?! ኧረ ኦነግንም ተውት፤ እራሱ ብልጽግና ብሎ የሚጠራው ፓርቲ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ይመስላችኋልን? ዋናው ጠላት እሱ አይደለ እንዴ!

ደግሞ እኮ “ቅዱስ ገብርኤል ነው በዕለተ ቀኑ ለድል ያበቃን!” እያሉ በየፌስቡኩ በመለቅለቅ ሊቀ መላዕክቱን የእነርሱ ወራዳ ሥራ ተሳታፊ ያደርጉታል፤ እንዴ ምኑን ከምኑ ነው የሚያገናኙት? ቅዱስ ገብርኤል ነው እንዴ ጦርነቱን ያስጀመረው? ሠራዊቱ ገብርኤል እርዳኝ እያለ ነው የተዋጋው? እንደው ያሳዝናል፤ “ክፉ ትውልድ ደረቅ ሴትን ይመስላል” እንዲሉ ይህ ክፉ ትውልድ እግዚአብሔርን “ቅሰፈኝ” ይለዋል።

ለመሆኑ የጦርነቱ ዓላማ ቤተ ክርስቲያንን ለማገዝ ነው? እኛ “ቲፒኤልኤፍ ትጥፋ ከተጀመረ ላይቀር” አልን እንጅ ጦርነቱ የተጀመረው እኮ ኦርቶዶክሳውያንን እርስበርሱ አጋጭቶ፤ በትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚገኙትን ኦርቶዶክሳውያንን ሆድ እና ጀርባ ለማድረግ ነው፤ ደግሞ ተሳክቶላቸዋል።

ወገን፤ ወታደር አያድንም፣ መከላከያ ሰራዊት አያድንም፣ ፋኖ አያድንም፣ ሚሊሺያ አያድንም፣ ልዩ ኃይል አያድንም፣ የሚያድን መድኃኔ ዓለም ብቻ ነው።

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤ መምህር ዮርዳኖስ! አስተዋይ ወገን አያሳጣን! “አባት፣ መምህር፣ ሊቅ” የተባለ ሁሉ ስንቱ ልሂቃን ከንቱ ነገር እየተናገረ፣ ከንቱ እንደሆነ፣ የተሳሳቱ ምልክቶችን እያሳየና ስጋዊ የሆኑ መል ዕክቶችን እያስተላለፉ እንደሆነ እያየንና እያዘንን ነው።

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የማንቂያ ደወል | አህዛብ ለአሠርተ ዓመታት የደገሱልን ድግስ ፍንጣቂ እየታየን ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 18, 2020

ትንፋሽ የሌለው ሰው የሞተ እንደሆነ ሁሉ፣ የማትናገር ቤተክርስቲያንም የሞተች ነች” – አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ

ለሃገር የቆመች ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት!”

ቃለ ሕይወት ያሰማለን፡ መምህር ዮርዳኖስ፤ የደፋሩን ሸህ እና የ666እስልምና ጣዖት አምልኮ እባባዊ አካሄድን በደንብ ደርሰህበታል። የአገራችን ተቀዳሚ ችግር ይህ መሆን በተገባው ነበር፤ የማንቂያው ደወልም ወደዚህ እውነት ሊወስደን በተገባው ነበር።

አብዛኞቹ እራሳቸውን በማታለልና በመሸጥ ከገዳይ አብይ ጎን ቆመው ወለም ዘለም በሚሉበት በዚህ የመተዛዘቢያና የመለያያ ዘመን እንዲህ በግልጽና በቀጥታ የሚናገር መምህር መኖሩ ተስፋ የሚሰጥ ነው። በተለይ በዚህ ዘመን ጊዜውን እየዋጀ የአብይ አህመድ አሊን እና የ666እስልምናን አደገኛነት በግልጽ ወጥቶ የማያጋልጥና የማያወግዝ መምህር ወይም ሰባኪ ከቁምነገር ሊቆጠር አይገባውም። የፈለገው ችሎታና እውቀት ይኑረው፤ ለዚህ ዘመን ካልተገለገለበት ሁሉም ነገር ዝርያ ነው፤ ለመቼስ ሊሆን ነው?

እስኪ ይታየን፤ ምን ዓይነት የክርስትና መምህር ነው ሁሉም በየእምነቱ ጸሎት ያድርግ፣ እኔ ለእግዚአብሔር አምላክ፣ እናንተ ደግሞ ለዋቄዮአላህ ዲያብሎስ ፥ ተቻችለን እንኑር፤ እኔ ብቻ ገነት ልግባ እንጅ ሌላው አይመለከተኝምበማለት የወገኑን ወደ ሲዖል መግባት የሚመኝ? ምን ዓይነት ስንፍና፣ ግድየለሽነትና ጭካኔ ነው? ምናለ በአንዷ ሴት በእህተ ማርያም ላይ ያሳዩትን ዓይነት ወኔ እና ጀግንነት ኢትዮጵያውያንን ጠፍሮ ባሠረው የእስልምና ዲያብሎስ ላይ ቢያሳዩት!

የሚገርም ነው እኮ፤ አንዱ መምህር የሽሁን እጅ ይስማል ሌላው የስየጣን ቤት መስጊድ ያሠራልጉድ እኮ ነው!

እውነቱን ለመናገር፤ በዚህ ዘመን እኛ ክርስቲያኖችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ደጋግሞ ከሚሰብከን ሰባኪ ይልቅ የእስልምናን 666ትነት፣ የመሀመድን ሐሰተኛ ነብይነትና ክርስቶስ ተቃዋሚነት የሚያጋልጠውን ሰባኪ አምነዋለሁ፣ አከብረዋለሁ ፤ ታታሪ ነህ!” እለዋለሁ።

ብዙዎች ግን ዛሬ ሁሉም ነገር ግልጥልጥ ብሎ እየታየ አውቀው ተኝተዋል። መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያን ነቅተው ሲነሱ ኢትዮጵያም አብራ ትነሳለች። የኢትዮጵያ ስምና ክብር የተዘጋጀው በመንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን ስኬት በኩል ብቻ ነው። መንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን ነቅተው ተነስተው የሃገሪቱን አመራር ከስጋውያን ኢትዮጵያውያን በፍጥነት ካልተረከቡ ኢትዮጵያ ትሞታለች። ኢትዮጵያ የበለጸገችና ገናና እንዲሁም ልዕለ ኃያል የሚለውን ስሟንና ክብሯን እንደገና ማመለስና መውረስ የምትችለው መንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን በማንነትና በምንነታቸው ሲገለጡና ሲነግሱ ብቻ ይሆናል። ጠላት ይህን ያውቃል።

በሃገራችን፣ በቤተ ክርስቲያናችን እና በሰላማዊ ልጆቿ ላይ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ወንጀል፣ ግፍና መከራ በዚህ በአህዛብ መንግስት በየቀኑ ሲፈጸሙ እያዩ ለምንድን ነው ሌሎች መምህራን ወጥተው እውነቱን ለመናገር የማይደፍሩት? ምንስ የሚይዛቸው ነገር አለ? እውነት ለስጋቸው፣ ለተወዳጅነታቸውና ለዝናቸው አስበው ይሆን?” የሚሉት የብዙ የተዋሕዶ ልጆች ጥያቄውች ናቸው።

በርግጥ መምህራኑ ከእኔ እና እናንተ የበረታ ፈተና የሚገጥማቸው ናቸው፤ ሆኖም ግን ለረጅም ጊዜ ሳከብራቸው እና ሳደንቃቸው የነበሩት እንደ መምህር ምህረት አብ አሰፋ፣ መምህር ዳንኤል ክብረት፣ መምህር ዘመድኩን በቀለ፣ መምህር ዘበነ ለማ እና መምህር ግርማ ወንድሙ የመሳሰሉትን ታዋቂ መምህራን በሃገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የአህዛብ መንግስት እየፈጸመው ያለውን ጂሃድ በግልጽ ከማውገዝና ጉዳዩንም አስመልክቶ ተገቢውን ትምህርት ከመስጠት መቶጠባቸው የግብረሰዶማዊው የአብይ አህዛብ መንግስት ተባባሪዎች አያደርጋቸውምን?

የመምህራኑን የህይወት ታሪክና የአገልግሎት ጉዟቸውን መለስ ብለን ብንመረምር፤ ሁሉም የተጠሩት የአህዛብን እና መናፍቃንን አስተምህሮዎች ለማጋለጥ በዚህም ተዋሕዷውያንን ለማንቃት ነበር። በዚህም ግርም ሥራ ሠርተው ነበር! ነገር ግን በኋላ ላይ ሁሉም ይህን እርግፍ አድርገው በመተው በባቢሎን ሃገራት መንሸራሸሩን መርጠዋል። እስኪ እንታዘበው፤ መምህር ምህረተ አብ እነዚያን የተደሰትንባቸውን የማንቂያ ደወል መርሃ ግብሮች በአፈቄሳር ዳንኤል ክብረት አጋዥነት ካቆመ በኋላ ኢትዮጵያን ለቅቆ ወደ ሰዶም እና ገሞራ ላስ ቬጋስ አመራ። በጣም ነበር ያዘንኩት፤ እስኪ ይታየን የአውሬው መንግስትን ከንቱ አዋጅ አልቀበልም ብሎ የማንቂያ ደወሉን ቢቀጥልበት ምን ዓይነት ድንቅ የሆነ ክርስቲያናዊ አብዮት በኢትዮጵያ ሊቀስቀስ ይችል እንደነበር።

ዛሬ እንደምናየው፤ ላለፉት 150 ዓመታት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪ፣ ገዥና የበላይ መንግስት ወይም ህግ የደቡብ ህዝብ ስጋዊ ማንነትና ምንነት ነው። መንፈሳዊው የሰሜኑ ህዝብና መንግስት ጸጋውንና በረከቱን በፈቃዱ ለስጋዊው የደቡብ ህዝብ አበርክቷል። ገዥ ስምና ክብር የሚሆነው የዚህ እንግዳ ፣ ባዕድ ፣ አዲስና ጸጉረልውጥ ህዝብ ማንነትና ምንነት ነው የሚሆነው። ይህ አንዳንድ ሙሉ በሙሉ ያልነቁትን ወገኖቼን ይከነክናቸው ይሆናል፤ ነገር ግን አፄ ሚኒሊክ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ እና ህወሃቶች የመንፈሳዊው ሰሜን ህዝብን ጸጋና በረከት ለስጋዊ ደቡብ ሕዝቦች አበርክተዋል። በተለይ ባዕድ ለሆኑት ኦሮሞዎችና ሶማሌዎች። ከሰሜን የተነሱት ህወሃቶች በሰሜንነታቸው እጅግ በጣም ለሚጠሏቸው፣ ኢትዮጵያን ለሚጠሏት ለስጋውያኑ ለኦሮሞዎችና ለሶማሌዎች በጭራሽ የማይገባቸውን አንጋፋውን የኢትዮጵያን ምድር ቆርሰው መስጠታቸው አይገርምምን? በጣም እንጅ!

የመንፈሳዊውን የሰሜኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ጸጋና በረከት የወሰደውና ለራሱ ስምና ክብር ያደረገው ስጋዊው የደቡቡ ህዝብ ሲሆን ይህም እውነት ዛሬ በምናየው የኢሀዴግ ብሔር ብሔረሰቦችበሚለው ተልካሻ ስጋዊ ህገመንግስት ተገልጦ በሁሉ ላይ ነግሶ ይታያል።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ ሁለት በተፈጥሯቸው ጠላት የሆኑ ማንነቶችና ምንነቶች ያላቸው ህዝቦች የሚኖሩባት አገር ናት። እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ ከተሳሳትኩ እንጂ እነዚህ ላይ የተጠቀሱት ስጦታው የተሰጣቸውና ሳከብራቸው የነበሩ መምህራን ምናልባት የተፈጠሩበት ስጋዊው የደቡብ አፈር የነገሰውን ስጋዊ የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት ማንነትና ምንነት የራሳቸው አድርገው በመቀበላቸው የሚፈጽማቸውን በደሎች ከማውገዝ እንዲቆጠቡ አድርጓቸው ሊሆን ይችላል።

የሚገርም ነው፤ ሁሉም መምህራን ከደቡብ ኢትዮጵያ ናቸው፦

  • . መምህር ምህረት አብ አሰፋ (መቱኢሉባቦር)
  • . መምህር ዳንኤል ክብረት(አገው፤ ስጋዊ ደቡብ ነው)
  • . መምህር ዘመድኩን በቀለ (ሐረር)
  • . መምህር ዘበነ ለማ (???)
  • . መምህር ግርማ ወንድሙ(ጎባ – ባሌ)

እና ብዙ ሌሎችም

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የዘመነ ኮሮናን አጋጣሚ ባለመጠቀማችን የቤተ ክርስቲያንን ክብሯን ለባዕድ አሳልፈን ሰጠን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2020

አባቶቻችን “ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቍሞ ማውረድ ይከብዳል!” ያሉት ተረት ደረሰብን።

እጅህን ካልታጠብክ ትጠፋለህ የሚል ህግ ፈሪሳዊ ህግ ነው!

አሁንም ገና በትንሣኤ በመዘጋት ነገሩ የሚያበቃ እንዳይመስላችሁ። ምክኒያቱም በየአጋጣሚው ቤተ ክርስቲያንን ከማንደድ፣ ምዕመናንን ከመጉዳት እማይቆጠቡ አህዛብና መናፍቃን በየስልጣኑ ወንበር ላይ ባሉበት ዘመን ላይ በገዛ ቦታችን ደብዳቢ ጽፈን፡ “ቤተ ክርስቲያን ትዘጋ! ሰው በቤቱ ይዘጋ” ብለን” ይሄ እኮ የቤተ ክርስቲያን ሥራ አይደለም፤ እሷ ባትኖር መንግስት ማለቱ አይቀርም እኮ ፥ እውነቱ ግን መፍትሔው ያለው በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው ፤ ንጉሥ የወደደውን ዘመን የወለደውን አትከተሉ!

በቃ! ቤተ ክርስቲያንን ክፈቱ! ዛሬውኑ ክፈቱ!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይገርማል! | የተዋሕዶ ልጆች በሊብያ እና በናዝሬት በአንድ ዕለት ነው የተሰዉት | በትንሣኤ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2020

+አንድ ማሳሰቢያ!+

የአውሬውን የ”Copyright” ጨዋታ መብት በመጠቀም ይህን ቻነል ለማዘጋት እየሠሩ ያሉ “ተዋሕዶ ነን” የሚሉ ዩቱበሮች፦

👉 ቻነል ፦ “Lule Quanquayenesh (ሉሌ ቋንቋዬ ነሽ)”

👉 Content removed by Lule Quanquayenesh (ሉሌ ቋንቋዬ ነሽ)

👉 ቪዲዮዎች፦

+ “ኢትዮጵያ ማለት ቤተክርስቲያን ናት ፤ እየታረዱላት ያሉትም የተዋሕዶ ልጆች ናቸው”

+ “የሰይጣን ምልክት 666 ነው ፥ የክርስቶስ የሆኑት ደግሞ ባንገታቸው ላይ ያለው ማሕተብ ነው”

👉 ቻነል Semayat/ ሰማያት

👉 ቪዲዮ፦ + “በዶክተሮች ሊፈታ የማይችለው ወረርሽኝ በጻድቁ ማእጠንት ይታጠናል | የማእጠንት ፀሎት በአሜሪካ”

Content removed by Semayat የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም የማእጠንት ፀሎት በተወሰኑ የቨርጂንያ መንደሮችና

እንግዲህ እነዚህ ዩቱበሮች አውሬው ተነካባቸው መሰለን በምናቀርበው ነገር የተደሰቱ ሆነው አላገኘናቸውም። መልስ እንዲሰጡን ጊዜ ሰጥተናቸው ነበር።

ማንም የሜዲያ ሰው ነኝ ማለት በሚችልበትና መላው የሰው ልጅ በወረርሽኝ ጉዳይ በተጠመደበትና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወገን መቀራረብና መፈቃቀር በሚኖርበት በዚህ የጭንቀት ዘመን ነጋዴ እንጅ አንድ “ክርስቲያን ነኝ” የሚል አካል በጭራሽ “Copyright“ የተባለውን ዝባዝንኬ እንደ መሀመዳውያኑ መጠቀም የለበትም። በተለይ በፋሲካ ሰሞን፤ ያውም “ሰለጠነች” በምትባለዋ አሜሪካ እየኖሩ። የኛን ቪዲዮዎች ማንም መጠቀም ይችላል፤ እንዳውም ደስ ይለናል!

ልብ ብላችሁ ከሆነ እንደ ውቂያኖስ ሰፊ በሆነ የዩቱብ ቪዲዮዎች ዓለም “Copyright“ን በብዛት የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊ ነን” የሚሉ ዩቱበሮች ናቸው። ታዲያ ይህ የስግብግብነት፣ የምቀኝነት፣ የክፋትና የጠላትነት መገለጫ አይደለምን? 21ኛው ክፍለ ዘመን ፤ ምናልባትም ኢንተርኔት የሚባል ነገር በቅርቡ እልም ብሎ ሊጠፋ በተዘጋጀበት ወቅት በራስህ ወገን ላይ ይህን መሰል እቃ እቃ ጨዋታ መጫወቱ አያሳዝንምን? ሰው እንዲማርበት ነው፤ ““ኮፒራይት” ከ666ቱ ምልክቶች አንዱ ነው፤ የአውሬው ባሪያ ከመሆን ለመዳን ከዩቱብና ጓደኞቹ ገንዘብ አትቀበሉ” ለማለት ነው።

ይህ ቀላል ነገር ነው፤ ዋናው እና ትልቁ ተል ዕኳችን አውሬውን መታገል ነው፤ ሕዝባችንን የሚያሰቃይብንን፣ ሕፃናቱን የሚገድልብንን፣ ካህናትን የሚያስርና የሚገድልብንን፣ እናቶችን የሚያፈናቅልብንን የአውሬ ሥርዓት ማጋለጥ ነው፤ የተሰውትን ሰማዕታት ወገኖቻችንን ማስታወስ ነው።

ለማንኛውም ሌላው ቻነላችን እዚህ ይገኛል፦

+++ዘመነ ኢትዮጵያ+++

ከምስጋና ጋር

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: