ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ ጦርነት አውጆ ለመዝመት መወሰኑ በጣም ያሳፍራል፤ “እሰዬው! በለው! በለው!” በማለት የሚያጨበጭቡት ደግሞ በይበልጥ ያሳፍራሉ፣ ያሳዝናሉ፣ ያስቆጣሉ። ምናለ በኦሮሚያ ሲዖል ታግተው ለተሰወሩት እህቶቻችን እና እየተጨፈጨፉ ላሉት ወገኖቻችን እንዲህ ቢቆሙላቸው!?
እስኪ አስቡት እነ ጀነራሎች አሳምነውን እና ሰዓረን የረሸነ፣ እነ ስመኘው በቀለን በመስቀል አደባባይ ካሜራ አጥፍቶ ለገደለ፣ ምስኪን የገበሬ ልጆችን አግቶ ለሰወረ፣ ገበሬዎችን ትምህርት ቤት ሰብስቦ ለጨፈጨፈ፣ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ተዋሕዶ ወንድሞቻችንን እና ሕፃናትን ለገደለ፣ ቀሳውስትንና ካህናትን ላሳረደ፣ እናቶችን ከጎጆዎቻቸው ለአፈናቀለ፣ ኮንዶሚኒየም እየሰረቀ ለጋላ ወገኑ ላከፋፈለ፣ “ወላሂ! ወላሂ!” ብሎ በመማል ግድቡን ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፎ ለሰጠ፣ ሰላማዊ በሆኑ ሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ በፌስቡክ ጦርነት ላወጀ “የአገር ጉዳይ ነው” ተብሎ ድጋፍ ሲሰጠ፤ ኧረ ማለቂያ የለውም። እስኪ አስቡበት!
በዘመነ መሳፍንት እንኳን የቀደሙት አባቶቻችን በሌላ ክፍለ ሃገር ላይ በይፋ ጦርነት ሲያውጁ አልተሰሙም። አዎ! “እኛ እኮ ከተናቅን ቆይተናል!”
___________________________