Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘መልአክ’

የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር | ቤተ ክርስቲያኗን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈነዳ ፥ በቦታው ላይ ይህ መስጊድ ለሉሲፈር ተሠራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 8, 2022

😇 የሊቀ መላእክት ሩፋኤል ክብረ በዓል በታሪካዊቷ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፤ አዲስ አበባ ጉለሌ።

ጳጕሜን ፫፥ ፪ሺ፲ በታሪካዊቷ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፡ ዝናባማ በነበረበት ቆንጆ የቀትር ሰዓት ላይ፡ የጸሎት ስነሥስርዓቱ ልክ እንዳለቀ የመሀመዳውያኑ ጋኔን አዛን ተለቀቀ። (ቪድዮው መጨረሻ ላይ ይሰማል) ወዲያውም ይህ የዲያብሎስ ተንኮል እንደሆነ በመረዳት ወደ አንድ አባት ጠጋ ብዬ፡ ለምን ቅዳሴና ጸሎት ሲገባደድ ይህ ሰይጣናዊ ጩኽት ይከተላል? ከየትስ ነው የሚመጣው? ብዬ አብረዋቸው ከነበሩት ሌላ ሰው ጋር ስጠይቃቸው፤

ከ ፻፴/130 ዓመታት በፊት የዚህች ውብ ቤተክርስቲያን ህንፃ በተሠራ ማግስት አንድ ከቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት ይኖር የነበረ ጭራቅ/ጠንቋይ በየቀኑ እየመጣ ቤተክርስቲያኗን ካላፈረስኩ፣ ካላቃጠልኩ እያለ ለሳምንታት ሲዝት ከቆየ በኋላ አንድ ቀን እራሱ ፈንድቶ ሞተ” አሉኝ።

እኔም፡ በመገረም፡ “በዚህ ፈጽሞ አልጠራጠረም! ግን ጠንቋዩ የሞተበት ቦታ ምን ተደርጎበት ይሆን?“ ብዬ ስጠይቃቸው፤ “ያው!“ አሉኝና፤ ሦስታችንም ዘወር ስንል ለካስ ቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት (በ፶/50ሜትር ርቀት) መስጊዱ ተተክሎ ይታያል። እንዴ፡ “ጠንቋዩ ፈንድቶ በሞተበት ቦታ ላይ ይህ መስጊድ ተሠርቷል ማለት ነው“ እንዳልኩ ሁላችንም በመገራረም እርስበርስ ተያየን።

አዎ! የሚያጠራጥር አይደለም፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ግን ይህን ሁላችንም አናውቅም ነበር፤ በጣም ይገርማል!

ከዚያም ከቤተክርስቲያኗ ግቢ እንደወጣሁ፤ የኔ ቢጤዎች ከነበሩበት ቦታ አስር የሚሆኑ ወጣቶች ተነስተው ከበቡኝና “ምን ፈልገህ መጣህ? ለምን መጣህ? ምን ትሠራለህ? … ወዘተ” እያሉ በሚገርም መልክ ይጨቀጭኩኝ ጀመር። ልክ እዚህ ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው፦ “ለንደን ሃይድ ፓርክ | ሺ ደካማ ጂቦች ጀግናውን አንበሣ አፍነው ሊገድሉት”

እኔም፡ ምንም አለመለስኩላቸውም “በ ስም ልቀቁኝ!” አልኩና ዘወር ብዬ መራመድ እንደጀመርኩ አሁንም ተከተሉኝ፤ በዚህ ወቅት መንገድ ላይ ለነበረው አንድ ፖሊስ “ኧረ እባክዎ ከነዚህ ሰዎች ይገላግሉኝ!“ አልኩት፤ እርሱም “ሂዱ!“ እያለ ይጮኽባቸው ጀመር፤ እኔም ታክሲዎች ወደሚገኙበት ቦታ አመርቼ እንደተሰለፍኩ፤ ልጆቹ አሁንም በየአቅጣጫው ቆመው ወደ እኔ ይመለከቱ ነበር፤ በዚህ ወቅት ከየት መጣ ሳልለው አንድ ደግ ባለ መኪና “ወደ ፒያሳ ነህ?” አለኝና አሳፍሮ ወሰደኝ።

በዚህ ወቅት በ “ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፱” ላይ ሰዶማውያን ወደ አብርሃም ዘመድ ወደ ሎጥ ቤት ወጥተው ለማጥቃት ሲሞክሩ መላዕክት በአካል ወደ ሎጥ ቤት እንግድነት ገብተው አደጋ እንዳይፈጠር በር ሲዘጉና ሎጥን ከጥፋት ሲያድኑ የተነገረን ታሪክ ትዝ አለኝ።

ታዲያ የኔ ቢጢዎች ጋር የነበሩት እነዚህ ልጆች እነማን ናቸው? እያልኩ እራሴን ጠየቅኩ። እነዚህን ከ፲፫/13 እስከ ፳/20 የሚጠጉ እድሜዎች ያሏቸውን፡ በደንብ መናገር የሚችሉትን ጎረምሳዎችን ያውኩ ዘንድ የመሀመድ ዲያብሎስ ምዕመናኑን አዘጋጅቷቸው ይሆን? መቼም ሰይጣን ሁሌ ከቤተክርስቲያን አይርቅምና!

አህዛብ ከዓብያተ ክርስቲያናት ጎን የሰይጣን ማምለኪያ መስጊድ የገነቡት የአዛዜልን አዚምና ማደንዘዣበመበተን ለዘመናት ለቡና፣ ጫትና ጥንባሆ የተጋለጠውን ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደንዘዝ መሆኑ የዛሬው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ምስክር ነው። እንዲያውም አንዳንዴ እኮ ታቦት ሳይቀር በመስጊዶች አካባቢ ሲያልፍ መንቀሳቀስ እንደሚያቅተው በተደጋጋሚ ታዝበናል።

በቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያንም የታዘብኩት ይህንን ነበር። ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይም ይህ መስጊድ ተሠራለት፤ ዲያብሎስን፣ 666 ድል የሚያደርገው ቅዱስ ሩፋኤል መስጊዶቹን በመላዋ ኢትዮጵያ አንድ ቀን ያስወግዳቸዋል፣ ዛሬ የነገሰውንም አረመኔ የኦሮሞ አገዛዝ በቅርቡ ከነ ፒኮኮ ያፈነዳዋል።

ቻይ እና ወዳጅመስለው ለመታየት የሚሹትና በዋቄዮአላህዲያብሎስ አዚም የፈዘዙት ብዙ ወገኖች፣ የተመረጡት ሳይቀሩ በእነዚህ ቀናት፤ “ሁላችንም በየሃይማኖታችን እንጸልይ…’ዱዋእናድርግክርስቲያኑ እግዚአብሔርን ሙስሊሙም አላህን ይማጸንክርስቲያኑ መጽሐፍ ቅዱስንሙስሊሙም ቁርአንን ያንብብእግዚአብሔር ከሁሉም ጋርጸጥ ለጥ ብለን በሰላም እንድንኖር ያዘናልወዘተ.” በማለት እየተዝለገለጉና እይቀበጣጠሩ ነው። በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ፥ የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ“(ዘጸ. )” የሚሉትን የእዚአብሔርን የመጀመሪያ ትዕዛዛት እየጣሱና ከባድ ኃጢዓት እየሠሩ መሆናችውን አይገነዘቡትምን? እኛ ክርስቲያኖች፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት“(ኤፌ ፬:)! ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል(ማር ፲፮ ÷፲፮)” እያለን አንዱንና ብቸኛውን አምላካችንን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ነው የምናመልከው እንጂ ሌላ አምላክ፣ ሌላውን ሃይማኖት ወይም መጽሐፍ ሁሉ ከዲያብሎስ ነውና አንቀበለውም!

ኢትዮጵያ ሁለት አማልክትየሚመለኩባት ምድር አይደለችምና ባካችሁ እንደ ኤዶማውያኑ ያልሆነ የሃይማኖት እኩልነትና፣ የዲሞክራሲ ቅብርጥሲ የመቻቻል ተረተረትእየፈጠራችሁ በሃገራችን ላይ መቅሰፍቱን አታብዙባት፤ ሃገር በሁሉም አቅጣጫ እየነደደች እኮ ነው።

😈 የዲያብሎስ መንግስታዊ ሕግ የ “መቀላቀል” ሕግ ሲሆን የእግዚአብሔር መንግስታዊ ሕግ ደግሞ የ “መለየት” ሕግ ነው። ምኒልክም የዛሬዋን የአብዛኛውን የዚህ ከንቱ ትውልድ ኢትዮጵያ ስጋን የመሰረቷት በመቀላቀል ሕግ ነው። የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለን ስንወጣ የምናመልጥባት ስፍራ ጭምር ትድናለች፡፡ የሚጠፉትን የምናድነው በመደባለቅ ሳይሆን ጥሪውን ተቀብለን ለእግዚአብሔር በመለየት ነው፡፡

ሸሽተህ አምልጥ

መላእክቱ ለሎጥ ያስተላለፉት ሌላው የሕይወት መመሪያ፡- “እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ” የሚል ነው[ዘፍ. ፲፱፥፲፯]፡፡ ስለ መሸሽ ብቻ አልነገሩትም፣ ወዴት መሸሽ እንዳለበትም አመልክተውታል፡፡ ወደ ተራራ!!

የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች በተለይ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰት ሲል ከሰዎች ቀድመው እንስሳት ያውቃሉ፡፡ በሱናሚ አደጋ ወቅት የተፈጸመ አንድ ታሪክ እናስታውስ፡- በኢንዶኔዥያ የባሕር ዳርቻ ባለ የመዝናኛ ስፍራ የዝሆኖች ትርኢት በማሳየት የሚተዳደር አንድ ሰው ዝሆኖቹን እንደ ወትሮው ለማዘዝ ቢሞክር ባልተለመደ ሁኔታ እምቢ አሉት፡፡ እንዲያውም ይባስ ብለው እየጮኹ ባቅራቢያው ወደሚገኘው ተራራ መሮጥ ጀመሩ፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ባለቤቱ ተከትሏቸው ወደ ተራራው ይሮጣል፡፡ ልክ ተራራው ላይ እንደ ደረሱ የሱናሚ አደጋ ይከሰታል፡፡ አካባቢውም እንዳልነበረ ሆነ፡፡ ያም ሰው ዝሆኖቹን ይዞ ሲመለስ ሁሉም ነገር ወደ አለመኖር ተቀይሮ ያገኘዋል፡፡ ቤተሰቡን ጨምሮ ብዙ ወገኖቹን አጣ፡፡ ዝሆኖቹን ተከትሎ ወደ ተራራው በማምለጡ የራሱን ሕይወት አተረፈ፡፡ መላእክቱም ሎጥን፡- “እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ” አሉት [ዘፍ. ፲፱፥፲፯]።

በተራራው ላይ የመረጣትን ከተማ ጥፋትም ያያል፡፡ ተራራው ከፍ ያለ በመሆኑ ሁሉን ያሳያል፡፡ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም እንኳ በተራራ ተመስላለች [ዕብ. ፲፪፥፳፪]፡፡ እግዚአብሔር ለእኛም ያዘጋጀልን ተራራ አለ፡፡ እርሱም ቀራንዮ ወይም የክርስቶስ ሞት ነው፡፡ ከክርስቶስ ሞት በቀርም ከዘላለም ጥፋት የምንድንበት ምንም ማምለጫ የለም [የሐዋ. ፬&፲፪፤ ዮሐ. ፲፬&፮]፡፡

ሎጥ ስለ ደከመ ወደ ተራራው ሳይሆን በቅርብ ወዳለችው ኋላ ዞዓር ወደተባለችው ከተማ ለመሸሽ መላእክቱን ጠየቀ፡፡ ከተማይቱም ለጥፋት የተቀጠረች ብትሆንም ሎጥ ወደ እርስዋ ሸሽቷልና ከጥፋት ዳነች [ዘፍ.፲፱÷፲፰፡፳፪]፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለን ስንወጣ የምናመልጥባት ስፍራ ጭምር ትድናለች፡፡ የሚጠፉትን የምናድነው በመደባለቅ ሳይሆን ጥሪውን ተቀብለን ለእግዚአብሔር በመለየት ነው፡፡

ሎጥ ሌሊቱን አልተኛም፣ የማምለጫ ሌሊት ሆነለት፡፡ እርሱ ያሰበው እንግዶቹን አብልቶ፣ አጠጥቶ፣ መኝታውን ለቆ ሲያሳርፋቸው ነበር፡፡ ያቺ ሌሊት ግን መልካም የመሥሪያ ሳይሆን የበጎነት ዋጋ የሚከፈልባት ሌሊት ሆነች፡፡ ይህች ሌሊት ለመልካሞቹ ሁሉ የተቀጠረች ሌሊት ናት፡፡ ይህችን ዓለም ትተን ስንወጣ በሰማይ የምንሸለምበት ሌሊት አለች፡፡ ሎጥን በሌሊት ለማውጣት የተደረገው ተልእኮ ዛሬም ጭምር የታገቱትን ለማስመለጥ የሚመረጥ ሰዓት ሆኗል፡፡ ሎጥ ወደ ዞዓር ሲደርስ ፀሐይ ወጣች፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፡፡ እነዚያንም ከተሞች በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ ከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ፡፡ የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፡፡ የጨው ሐውልትም ሆነች” ይላል [ዘፍ. ፲፱÷፳፫፡፳፮]፡፡

❖[ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፳፪፥፲]❖

“በበሬና በአህያ በአንድነት አትረስ።”

❖[መጽሐፈ ዕዝራ ምዕራፍ ፱፲፤፲፩፤፲፪]❖

“አሁንስ አምላካችን ሆይ። ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡባት ምድር በምድር አሕዛብ ርኵሰት ረክሳለች፥ ከዳር እስከ ዳርም ድረስ ከርኵሰታቸው ከጸያፍ ሥራቸውም ተሞልታለች፤ አሁንም ትበረቱ ዘንድ፥ የምድሩንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ለዘላለም ለልጆቻችሁ ታወርሱአት ዘንድ ሴቶች ልጆቻችሁን ለልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችሁ አትውሰዱ፥ ሰላማቸውንና ደኅንነታቸውንም ለዘላለም አትሹ ብለህ በባሪያዎችህ በነቢያት ያዘዝኸውን ትእዛዝ ትተናልና ከዚህ በኋላ ምን እንላለን?”

❖[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፪፥፵፫]❖

“ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ፥ እንዲሁ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም።”

❖[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፯፥፩]❖

እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።

❖[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፬]❖

ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

The Book of Enoch Written in Ethiopic-Ge’ez about The Archangel Gabriel | በግዕዝ የተጻፈው መጽሐፈ ሔኖክ ስለ ቅዱስ ገብርኤል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 26, 2022

😇 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

😈 ዓለምን ሲያውኩት ያጋንንት ሥራቸው እንዳይተርፈን ለእኛ የእነርሱ ግብራቸው ገብርኤል በሰይፉ ቀጥቅጦ ጣላቸው፤ እናመልክት ለሱ እናስታውስ ጠዋት ማታ እንዲያስተራርቀን ለምኖ ከጌታ።

ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው ❖

😇 “ሰለጠነ” የተባለውን ዓለም ጨምሮ ምስጢራዊውን ዓለም ሁሉ እያስደነቀ ያለው ድንቁ መጽሐፈ ሔኖክ የተጻፈበት የግእዝ ቋንቋ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ዛሬ እነ “አቡነ” ናትናኤል፤ “ኦሮሞ” ነን ብለውና ክቡር ስጦታ፤ ትልቅ ስጦታ የሆነውን የግ እዝ ቋንቋን የሰሜናውያን ቋንቋ ነው አንፈልግውም፤ በሚል ድፍረትና ምስጋና-ቢስነት ቅዳሴውን አጋንንታዊ በሆነው የኦሮምኛ ቋንቋ ለማድረግ ደፍረዋል። በምኒልክ የብሔር-ብሔረሰብ ርዕዮተ ዓለም የሰከሩት የሕወሓት ቀሳውስትስ፤ በትግርኛ ካልቀደስን ይሉን ይሆን? በትግራይ ጽዮናውያን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱ ልክ ሊጀምር ሦስት ወር ሲቀረውና “ምርጫ” የተባለውን የሙቀት መለኪያ ለማካሄድ በሚዘጋጁበት ዋዜማ እነ ዶ/ር ደብረ ጽዮን፤ “ካሁን ጀምሮ የግዕዝ ቋንቋ በመላዋ ትግራይ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እንደ መደበኛ ትምህርት ይሰጥ!” የሚል ትዕዛዝ አስተላለፈው ነበር። ዛሬስ እንዲህ ያለ ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ይሹ ይሆንን? አይመስለኝም። ያኔም ትክክለኛዎቹን አጋዚያን-ተጋሩ-ጽዮናውያንን ለመደለል የተደረገ እርምጃ መሆኑን ዛሬ በግልጽ እያየነው ነው። ሕወሓቶችን ጨምሮ ሁሉም ምንሊካውያን ጦርነቱን በጋራ ጀምረውታልና።

👉 ጦርነቱ ልክ እንደጀመረ፤ ለመሆኑ ይህ ጦርነት ማንን ነው “የሚጠቅመው”?” በሚል ጥያቄ ሥር

የጦርነቱ ዓላማ ፤ ኢአማንያኑ የሻእቢያ እና ህዋሀት ቡድኖች ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ቅዱስ ያሬድን፣ አቡነ አረጋዊን፣ አባ ዓቢየ እግዚእን፣ ነገሥታቱን ኢዛናን፣ ዮሐንስን፣ ሰንደቁን፣ ግዕዝን፣ አክሱምን አጥፍተው በሃምሳ ዓመታት ውስጥ በተገኘ ጣዖታዊ ማንነት “ኢአማኒ የትግራይ ሶሻሊምዝብልጽግና” ርዕዮተ ዓለምን በመከተልና የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የቻይና ባንዲራም በማውለብለብ ከኤርትራ ጋር ለብቻቸው መኖር ይሻሉና ነው። በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የግራኝ አብዮት አህመድ እና የስብሃት ነጋ ጦርነት ነው።” በማለት ጽፌ ነበር።”

😈 ጠላታችን ዲያብሎስ ለመንፈሳዊ ሕይወት ብዙም የማይረዱንን ወይንም መንፈሳዊ ድክመት ያላቸውን(አማርኛ፣ ትግርኛ)እንዲሁም አጋንንታዊ የሆኑትን ቋንቋዎችን (ኦሮምኛ፣ አረብኛ፣ ሶማልኛ) ተጠቅሞ እርስበርሳችን እንድንጨፋጨፍ፣ ሰአራዊቱን እየላከ ያልተደቀለውን የትግራይን ሕዝብ ደቅሎ በማዳከም የኤዶማውያኑን እና የእስማኤላውያኑን የእንግሊዝኛን እና የአረብኛን ቁንቋ ከእነ ሉሲፈራዊ አምልኮታቸው ለማንገስ ሲል ነው በትግራይ ጽዮናውያን ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን በምዕራቡም በምስራቁም እርዳታ የጀመረው። የገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም የቅርስ ማውደም ጂሃዱን የከፈተባቸውም የመንፈስ ማንነታቸንና ምንነታቸውን አጥፍቶ እንደ ኦሮሞው የስጋን ማንነትና ምንነትን ለማንገስ ነው እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ሁሉንም ነገር ሸፋፍኖ ምንም ነገር እንዳይታወቅበት በስልት መረጃዎችን በማጥፋት/በመሰወር ላይ የሚገኘው።

ይህ ጥቃት/ጂሃድ የጀመረው የእግዚአብሔር የሆነውንና ለመንፈሳዊ ሕይወት በዓለማችን ተወዳዳሪ የሌለውን የግእዝ ቋንቋችንን በኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ሤራ ጠንሳሽነት የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው ጋላ/ ኦሮሞ ወራሪዎች በኩል ለማጥፋት ከተነሳበት ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት አንስቶ ነው። ጂሃዱን ጦርነቱን በስጋችን ላይ ብቻ አይደለም የከፈቱብትን፤ በነፍሳችን፣ በመንፈሳዊ ሕይወታችን፣ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖታችን፣ በቋንቋችን፣ በጽዮናዊው ሰንደቃችን፣ በታሪካችንና በባሕል/ትውፊታችን ላይም ጭምር ነው። ይህ ውጊያ በየደረጃው/በየዘመኑ ከመቶ ሰላሳ ዓመታት፣ ከአምስት መቶ ዓመታት፣ ከአንድ ሺህ አምስት መቶ ዓመታት በፊትና ከስድስት ሺህ ዓመታት አንስቶ ዲያብሎስ እና ጭፍሮቹ ዝግጅት አድርገው ሲያካሂዱት/እያካሄዱት ያለው ውጊያ ነው። በአክሱም ጽዮን ላይ ያተኮሩበት ምስጢርም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላዋ መንፈሳዊቷ ዓለማችን ቁልፍ መሠረት በጥልቁ ተደብቆ የሚገኝባት ምድር ስለሆነች ነው። ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ይህን በደንብ ያውቁታል/ደርስውበታል።

ለዚህም ነው፤ በጽዮናውያን ላይ የዘር፣ የሃይማኖት፣ የታሪክ፣ የትውፊት፣ የቅርስ፣ የቋንቋ ማጥፋት ጂሃዳዊ ዘመቻ የከፈቱት ኤዶማውያንና እስማኤላውያን ( መሀመዳውያን + ፕሮቴስታንቶች + ኢ-አማንያን + ኦሮሞዎች + ሶማሌዎች + ከሃዲ አማራዎች + ከሃዲ ተጋሩዎች)ሁሉ የኤርታ አሌ እሳተ ገሞራ ተከፍቶ እየተንከተከተ ይጠብቃቸዋል የምንለው። ፻/100%

በተለይየዛሬይቷ ኢትዮጵያ ብሎም መላዋ አፍሪካ እና ዓለም መዳን የሚችሉት ሕዝቦቻቸው የእግዚአብሔር የሆነውንና በመንፈሳዊ ጠቀሜታው ከዓለማችን ቋንቋዎች ሁሉ በጣም ግዙፍ የሆነውን የግእዝ ቋንቋን በብሔራዊ ቋንቋ መልክ መናገር ሲጀምሩ ብቻ ነው። ኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያን ይህን ደርሰውበታል!

😇 ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል

ትውፊታዊ ታሪኩ

ግእዝ የእግዚአብሔር ቋንቋ ነው ተብሎ በትዉፊት ይነገራል። ፍጥረታት በሐሌዎበነቢብና በግብር የተፈጠሩ ሲሆን በተለይ ነቢቡ (ንግግሩ) ግእዝ ነበር ብለዉ የሚከራከሩና የራሳቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ ሊቃውንት አሉ። ግእዝ የመጀመሪያ ቋንቋ ነው ስንል አዳም ማለት ያማረ የተዋበ ማለት ሲሆን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ” ብሎ ሠራዊተ መላእክትን ያረጋጋው በግእዝ ነው፤ አዳምም ለ ፯ ዓመታት በገነት ሳለ በፀሎት ሲተጋ የነበረውና ከሄዋን ጋር ይነጋገርበት የነበረው ቋንቋ በግእዝ ነው በማለት ቋንቋውን የመላእክትም የሰውም መግባቢያ ያደርጉታል።

😇 ግእዝ የአዳምና ሔዋን (የተፈጥሮ ቋንቋ) የመጀመሪያው መነጋገሪያ ልሳን መኾኑ ለማረጋገጥ ከሚያቀርቧቸው ፲ ምክኒያቶች መካከል፦

፩ኛ. የ ”ግእዝ” የጥሬ ዘሩ ቃል ትርጉም፡ “መጀመሪያ”, “ነፃ” እና “የጥንት ተፈጥሮ ጠባይ ወይም ባህሪይ” ማለት መኾኑ

፪ኛ. የእያንዳንዱ ፊደል የመጀመሪያ ቅርጽ አፍ ሳያስከፍት በድን በኾነው በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ የሚነገር መኾኑ

፫ኛ. የፊደሉ መነሻ “አ” “አዳም” በሚል ቃል በወንድና ሴት ጾታ ለተፈጠሩት ለመጀመሪያዎቹ ሰዎች መጠሪያ መኾኑ

፬ኛ. በሰባት ብዛት የሚወሰን ቁጥር፤ የመለኮታዊ ሥራ ምሥጢር እንዳለበት ስለሚታመን፤ እያንዳንዱ ፊደል፤ በሰባት ስሞች ድምጾችና መልኮች ተለይቶ የሚታወቅና የሚነገር መኾኑ

፭ኛ. ሌሎቹ የሰዎች ቋንቋዎችና ፊደሎቻቸው በተናጋሪዎቻቸው ሕዝቦች ወይም ጎሣዎች ስም ለምሳሌ፤ ዐማርኛ፤ በዐምሓሮች፤ ትግርኛ በትግሬዎች፣ ኦሮምኛ በኦሮሞዎች፣ ሶማልኛ በሶማሌዎች፣ ዕብራይስጥ በዕብራዊያን፤ ዐረብኛ በዓረቦች፣ እንግሊዝኛ በእንግሊዞች፣ ቻይንኛ በቻይኖች ስም ሲጠሩ “ግዕዝ” ግን በራሱ ብቻ የሚጠራ መኾኑ

፮ኛ. በ ”አ” ጀምሮ በ “ኦ” የሚፈጸም ፊደል ያለው እርሱ፤ ግእዝ ብቻ ከመኾኑ ጋር “አልፋና ኦሜጋ፤ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ” ብሎ፡ ኃላ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ፤ ራሱን በሰውነት የገለጸው “እግዚአብሔር” በዚህ ስሙ የታወቀበትና አምልኮቱ የሚፈጸምበት ቋንቋና ፊደል ኾኖ በሕያውነት እስከዛሬ መቀጠሉ

፯ኛ. በምድር ላይ የሚኖሩ የሰው ልጆች ኹሉ፡ ተወልደው በሕፃንነታቸው መናገር በሚጀምሩበት ጊዜ ቋንቋቸውና ፊዲፈላቸው የተለያዩ ሲኾኑ፤ አፋቸውን መፍታት አባቶቻቸውናና እናቶቻቸውንም ለይተው መጥራት የሚጀምሩበት “አባባ”፤ “እማማ!” የሚባሉት ቃላት “አብ አብ አብ”፤ “እም እም እም” የተባሉት፤ ትርጉማቸው፡ “አባት አባት አባት”፡ “እናት እናት እናት” የኾነውን ቀጥታ የግእዙን ቃላት መኾኑ ናቸው።

፰ኛ. «ግእዝ» የሚለው ቃል እራሱ አንደኛ፣ የመጀመሪያ ማለት ነው። የሰው ልጅ የመጀመሪያ የሆነው ቋንቋ አንደኛቢባል ይስማማዋል።

፱ኛ. የዚህ ቋንቋ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሰው አዳም ነው። የዚህ ሰው ስም በቋንቋው ትርጉም ሊኖረው ይገባል። በግእዝ «አዳም» ማለት ያማረ ማለት ነው።

፲ኛ. ሌላው ነገር የግእዝ ፊደላት ከአምላክ የተገኙ ናቸው ለዚህም የአዳም ሶስተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖስ በሰማይ ገበታ እንዳያቸው አባቶች ይናገራሉ።

አማርኛ ቋንቋ ከግእዝ ያገኛቸውን በሙሉ ይዞ ሌሎች ፯ ፊደላትን በመጨመር ግእዝ ፳፮ ሲሆን አማርኛ ደግሞ ፴፫ ነው “ቨ”ን ሳይጨምር ማለት ነው።

😇 የግእዝን ፊደሎች ትርጉም ስንመለከት፦

ሀ፦ ብሂል ሀልዎቱ ለአብ እምቅድመ ዓለም ፥ የአብ አኗኗሩ ከዓለም በፊት ነው

ለ ፦ ብሂል ለብሰ ሥጋ እምድንግል ፥ ክርስቶስ ከድንግል ሥጋን ለበሰ

ሐ ፦ ብሂል ሐመ ወሞተ ፥ ስለኛ ታመመና ሞተ

መ፦ ብሂል መንክር ግብሩ ለእግዚአብሔር ፥ የእግዚአብሔር ሥራው ድንቅ ነው

ሠ ፦ ብሂል ሠረቀ በሥጋ ፥ በሥጋ ተገለጠ

ረ ፦ ብሂል ረግዓት ምድር በቃሉ ፥ ምድር በቃሉ ረጋች

ሰ ፦ ብሂል ሰብአ ኮነ እግዚእነ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ቀ ፦ ብሂል ቀዳሚሁ ቃል ፥ ቃል መጀመሪያ ነበር

በ ፦ ብሂል በትሕትናሁ ወረደ ፥ ጌታችን በትሕትናው ወደኛ ወረደ

ተ ፦ ብሂል ተሰብአ ወተሰገወ ፥ ጌታችን ሰው ሆነ

ኀ ፦ ብሂል ኀያል እግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔር ኀያል ነው

ነ ፦ ብሂል ነስአ ደዌነ ወጾረ ሕማመነ ፥ መከራችንን ያዘልን ሕመማችንን ተሸከመልን

አ ፦ ብሂል አእኵቶ ወእሴብሖ ለእግዚአብሔር ፥ እግዚአብሔርን ፈፅሜ አመሰግነዋለሁ

ከ ፦ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር ፥ ጌታችን ቻይ ነው

ወ ፦ ብሂል ወረደ እምሰማይ ፥ ጌታ ከሰማይ ወረደ

ዐ ፦ ብሂል ዐርገ ሰማያተ ፥ ወደ ሰማይ ዐረገ

ዘ ፦ ብሂል ዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር ፥ ጌታ ሁሉን የሚይዝ

የ ፦ ብሂል የማነ እግዚአብሔር ገብረት ኃይለ ፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይልን ታደርጋለች

ገ ፦ ብሂል ገብረ ሰማያተ በጥበቡ ፥ ጌታ በጥበቡ ሰማያትን ሠራ

ጠ ፦ ብሂል ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር ፥ ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱና ዕወቁ

ጰ ፦ ብሂል ጰራቅሊጦስ መንፈሰ ጽድቅ ፥ ጰራቅሊጦስ እውነተኛ መንፈስ ቅዱስ ነው

ጸ ፦ ብሂል ጸጋ ወክብር ተውህበ ለነ ፥ ጸጋ እና በረከት ተሰጠን

ፀ ፦ ብሂል ፀሐይ ጸልመት በጊዜ ስቅለቱ ለእግዚእነ ፥ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ፀሐይ ጨለመች

ፈ ፦ ብሂል ፈጠረ ሰማየ ወምድረ ፥ ጌታ ሰማይ እና ምድርን ፈጠረ

ፐ ፦ ብሂል ፓፓኤል ስሙ ለአምላክ ፥ ፓፓኤል የአምላክ ህቡዕ ስም

ትርጉማቸዉ ይሄን ይመስላል።

😇 ስለዚህ ግእዝ የአዳም ቋንቋ ነው የሚለው መላምት የበለጠ ጥንካሬ አለው።

አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከጻፏቸው መጻሕፍት እና ሌሎች ድርሰቶች ተነስተን ፍቺውን ስንመለከት ደግሞ ግእዝ (የዜማ ስም፥ ግእዝ፣ እዝል እና አራራይ። የፊደል ስም ሀ ፦ ግእዝ ሁ ፥ ካዕብ ሂ ፥ ሳልስ …… ) በመጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ ፲፩ ፥ ፮ ላይ እግዚአብሔርም አለ ” እነሆ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው” ይላል።

_______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በማንቸስተር ሕይወቱ ያለፈችው ሕፃን ‘ቅዱስ’+ የማርያም መቀነት የሚነግሩን ትልቅ ነገር አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 18, 2020

በቅድሚያ ለሕፃን ቅዱስ ወንድወሰን፤ ቤተሰቦች መጽናናቱን ይስጥልን! እናቱ ፊት በሚያሳዝን መልክ ማረፉ ልቤን ነበር የሰበረው

👉 ዛሬ ፲፪/፲፪/፲፪ ነው – ቅዱስ ሚካኤል + ፍልሰታ ለማርያም

በመስኮቴ በኩል ሁለት የማርያም መቀነቶች ታዩኝ፤ ወዲያው ብልጭ ያለብኝ በስቅለት ዕለት በአዲስ አበባ የታዩት ድንቅ የማርያም መቀነቶች ነበሩ። ያኔ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ተደፋፍረው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲሄዱ የታየ ምልክት ነው፤ ባካችሁ ከዓርብ እስከ እሑድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተሰባስባችሁ ሂዱ! ባካችሁ! ባካችሁ!” ለማለት ደፍሬ ነበር። በማግስቱ ዲያብሎስ የዩቲውብ ቻኔሌን አዘጋብኝ። ዛሬም እዚህ የታዩኝ ሁለት የማርያም መቀነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ ተዋሕዷውያን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የዐቢይ አህመድ የቄሮ አገዛዝ በመቆጣጠር ላይ ወዳለው ቤተ መንግስት በማምራት አጥሩን የሚነቀንቅና ትልቅ ተጋድሎ የሚጠይቅ ተቃውሞ ሰልፍ አዘጋጁ አለዚያ እጅግ በጣም የከፉ ሳምንታትና ወራት ይጠብቋችኋል! ባካችሁ! ባካችሁ ድምጻችሁን በአደባባይ ቶሎ አሰሙ! ነፍጠኛነታችሁን አሳዩአቸው፣ ተፋለሟቸው።እላለሁ። ሕፃን ቅዱስ ወንደወሰንም የሚጠቁመን ይህን ሊሆን ይችላል።

👉 ማንቸስተር ብሪታኒያ እሑድ ነሐሴ ፲ ፪ሺ፲፪ ዓ./ መስቀለ ኢየሱስ

የ፮ ዓመቱ ሕፃን ቅዱስ ወንድወሰን ብስክሌቱ ላይ በመኪና ተገጭቶ ሕይወቱ አለፈች።

ሕፃናት የግል ምርጫ ለማድረግ የሚችሉበት እድሜ ወይም ብስለት ላይ ከመድረሳቸው በፊት ቢሞቱ በእግዚአብሔር ምህረትና ጸጋ ከእግዚአብሔር ፍርድ አምልጠው የዘላለም ሕይወት ያገኛሉ። እግዚአብሔር ሕፃናትን እኛ ከምንወዳቸው በላይ ያፈቅራልና።

ቅዱስ ወንድወሰን የማንቸስተር ዩናይትድና የተጨዋቹ ማርቆስ ራሽፎርድ ደጋፊ እንደሆነ የእንግሊዝ ሜዲያዎች አሳውቀዋል ፥ ማርቆስ የሃዘን መልዕክት ለቤተሰቦቹ አስተላልፏል፤ ከሰሞኑ እንደሚጎበኛቸውም ቃል ገብቶላቸዋል።

የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ማርቆስ ራሽፎርድ በብሪታኒያ ቢወለድም ዘሩ ግን በካሪቢያን ባሕር ላይ ከምትገኘው ደሴት ሃገር ከ ቅዱስ ኪትስ እና ኔቪስነው። ቅዱስ ኪትስ እና ኔቪስ / St. Kitts und Nevis ስሙ ላይ ስናተኮር ቅዱስ ወንድወሰን ጋር የሚመሳሰል ሆኖ እናገኘዋልን። ብንጨምርበት ማርቆስ ራሽፎርድ ፥ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው

👉 ሕፃን ቅዱስ ወንደወሰን ምን ሊያሳየን የፈለገው ነገር አለ?

ከሁለት ወር በፊት ኢትዮጲስበተሰኘው የዩቲውብ ቻነል ደራሲ አቶ ታዲዮስ ታንቱጌጥዬ ያለዉከተሰኘው ጋዜጠኛ ጋር ስቱዲዮ ውስጥ ሳያቸው፤ ጋዜጠኛው ከኳስ ተጨዋች ማርቆስ ራሽፈርድ

ጋር በጣም እንደሚመሳሰል ገርሞኝ ስስቅ ነበር። እንዲያውም የሁለቱንም ምስሎች በኮምፒውተሬ

ላይ አስቀርቼ ቪዲዮ ለመሥራት እየተዘጋጀሁ ነበር። ያው ከሁለት ወራት በኋላ ልክ በዕለቱ ይህ አስደናቂ አጋጣሚ ተፈጠረልኝ።

ኢትዮጲስቻነል በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የተመሠረተና በመጀመሪያዎቹ ወራት ለለገጣፎ እና ሱሉልታ ተፈናቃዮች ከፍተኛ ድምጽ የነበረ ቻነል ነው። ሽብርተኛዎቹ ዐቢይ አህመድና ታከል ዑማ በዚህ ጣቢያ ስላልተደሰቱ ጋዜጠኞቹን በማሰር ሊያዳክሙት በቅተዋል።

አሁን ይህ ኢትዮጲስየተሰኘው ቻነል ቄሮ ቄሮ / Kero Kero“ የሚል ስም የያዘና የኦሮሚያ ባንዲራ ያነገበ ቻነል ሆኖ ይታያል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? የሽብርተኛው ዐቢይ አህመድ ቄሮ አገዛዝ ወርሶታልን? ቻነሉ ለአንድ ወር ያህል ምንም አዲስ ነገር አላቀረበም።

👉 ሕፃን ቅዱስ ወንድወሰን ምንን እየጠቆመን ነው?

  • ቅዱስ
  • መልአክ (ቅዱስ ሚካኤል?)
  • ቅዱስ ማርቆስ
  • ኢትዮጲስ
  • እስክንድር ነጋ (ቪዲዮውን ሰርቼ ስጨርስ ጋላዋ አዳነች አበቤ *(አአ)በአዲስ አበባ *(አአ) ከንቲባነት መመረጧን ሰማሁ)ዋው!
  • አብይ አህመድ(ቄሮ)(መልአኩ ሰይፍና እሳት ይዞ ይመጣባቸዋል)

👉 ከሕጻን ቂርቆስ ጋር አብረን እናስታውሰው፦

ሦስት ዓመት እንኳን ሳይሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበለው ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሞስ (ስምዖን) እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ በሕዳር ፲፭ ቀን የተወለደ ሲሆን ሀገሩ በታችኛው እስያ ልዩ ስሙ ሀንጌቤን ይባላል፡፡ ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ነበርና መምለኬ ጣዖት የሆነው ንጉሥ እስክንድሮስ ቅድስት ኢየሉጣን ለጣዖቴ ስገጂብሎ አስገደዳት፡፡ እርሷም

ሕጻኑ ልጄ መጥቶ ይመስክርብላ ስትናገር ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጠራና ተጠየቀ፡፡ ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስም ለጣዖት አንሰግድም፣ ዘላለማዊ የሆነ የማይሻር አምላክ ስላለ ለእርሱ ነው የምንሰግደውብሎ የአምላኩን ክብር በሕፃን አንደበቱ መሰከረ፡፡ ሕፃኑም ይህንን በመሰከረ ጊዜ ዕድሜው ገና ሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወሩ ነበር፡፡

እጅግ በጣም የሚገርመው ቅዱስ ቂርቆስ በከሃዲው ንጉሥ ፊት የጌታችንን ክብር በመሰከረ ጊዜ ንጉሡ እጅግ ተቆጥቶ አርባ ጋን ውኃ የሚይዝ በርሜል አስጥዶ አርባ ቀን ሙሉ እሳት አስነድዶ ቅንጭብ፣ ዘይት፣ ዝፍጥና ሌላም በእጅጉ የሚጎዱ ነገሮችን በውስጡ ጨምሮ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱን ቅድስት ኢየሉጣን ወደዚያ እቶኑ እሳት እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡

ንጉሡም እሳቱ እንዳልጎዳቸው ሲያውቅ ከዚያ አውጥቶ በሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አፍና አፍንጫ መርዝ ከተተበት፣ ነገር ግን መርዙ ምንም አልጎዳውም እንዳውም ምግብ ሆነው፡፡ ዳግመኛም ጨውና በርበሬ በዐይኑ አነደደበት፡፡ አሁንም ምንም አልነካውም፡፡ ከዚህም በኀላ ሹም እስክድሮስም አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች ያመጡ ዘንድ ዳግመኛ አዘዘ፡፡ ሰባቱን በእናቱ አካል ሰባቱን በሱ አካል ውስጥ ይተክሉ ዘንድ ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዓይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይተክሉ ዘንድ አዘዘ፡፡በሕፃኑም ላይ ሹሙ እንዳዘዘው አደረጉበት፡፡ አሁንም ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና ፈወሳቸው፡፡

ዳግመኛም የሕጻኑን እራስ ከነቆዳው ገፈው በእሳት ውስጥ ይጨምሩ አንድ ሹም አዘዘ፡፡

እንዲሁም አደረጉበት፡፡ ዳግመኛም ቅዱስ ገብርኤል እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ ይህንን መከራ ከሕፃኑ አራቀለት፡፡ ዳግመኛም ሹሙ በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ከዚህም መከራ መልአኩ አዳነው፡፡ በዛሬዋ ዕለት ሐምሌ 19 ቀን በዓሉን በታላቅ ድምቀት የምናከብረው ይህንን ሁሉ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልን ተራዳኢነት በማሰብ ነው፡፡

ንጉሡም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በብዙ ጭንቅና ሥቃይ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ለ፫ ዓመታት አሠቃያቸው፡፡ እነርሱም መከራን እየተቀበሉ በከሀዲው ንጉሥ ፊት የአምላካቸውን ስም እየጠሩ መሰከሩ፡፡ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ክብሩን ይመሰክሩለት ዘንድ የቢታንያን ድንጋዮችና የበለዓምን አህያ አንደበት ከፍቶ ያናገረ አምላክ ሦስት ዓመት እንኳን ባለሞላው በሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ሕፃን ልጅ ላይ አድሮ በወቅቱ የነበሩ ዓላውያን ነገሥታት ክብሩን እንዲያውቁ አደረገ፡፡

በመጨረሻም ሕጻኑ ቅዱስ ቂርቆስ ተጋድሎውን ፈጽሞ ጥር ፲፭ ቀን በ፫ ዓመት ከ፩ ወር ከ፫ ቀኑ አንገቱን በሰይፍ ተቆርጦ ሰማዕትነትን ተቀብሏል፡፡ ሲሰየፍም ከአንገቱም ደም፣ ውኃና ወተት የወጣ ሲሆን ሦስት አክሊላትም ወርደውለታል፡፡ ጌታችንም የመከራውን ጽናት የትዕግስቱን ብዛት አይቶ ከመከራ ሊያሳርፈው ፈቀደና ተገልጾለት ‹‹ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ቂርቆስ›› አለው፡፡ ‹‹ሰላም ላንተ ይሁን፤ የመከራህን ጽናት፣ የትዕግስትህን ብዛት አይቼ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍህ መጣሁብሎ ብዙ ቃልኪዳን ሰጠው፡፡ “…ስምህ በተጠራበት፣ ቤተመቅደስህ በታነጸበት፣ ስዕልህ ባለበት ቦታ ሁሉ የሕፃናት እልቂት፣ የከብት በሽታ፣ የእህል እጦት ርሀብ፣ ቸነፈር አይደርስም›› የሚል አስደናቂ ቃልኪዳንም ገብቶለታል፡፡ ሕፃኑም በምድር ላይ አልተቀበረም ይልቁንም ጌታችን በኤልያስ ሰረገላ ሥጋውን አሳርጎለታል፡፡ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣም በጥር ፲፮ ቀን ሰማዕትቷን በክብር ፈጽማለች፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፡፡ እኛንም በአማላጅነታቸው የምታመን ሁላችንን የብርሃናዊውን መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን፣ የሕጻኑ ቂርቆስንና የቅድስት ኢየሉጣን ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን፡፡ በጸሎታቸው ይማረን፡፡

_________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: