Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሕይወት ማጥፋት’

የኢራን እና ኦሮሚያ ሲዖል ሲነፃፀር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 9, 2020

በገና ዋዜማ ሽብር ፈጣሪው የኢራን ጄነራል በአሜሪካ ተገደለ። ይህን አስከትሎ ሊቀሰቀስ የሚችለውን ጦርነትና የአሜሪካንን ቁጣ ከአረቢያ እና ኤራን ለማራቅ የዋቄዮአላህና የአረቦች ባሪያዎች የሆኑት ሶማሌዎች በኬኒያ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ጥቃት ፈጸሙ፤ ሦስት አሜሪካውያን ወታደሮች ተገድለዋል። ከአሜሪካ በኩል ይህ ነው የሚባል መግለጫ እስካሁን አልተሰጠም።

ኢራናውያን አንድ ጄነራል ተገደለብን፤ “ሞት ለአሜሪካ! ሞት ለእስራኤል! ልክ እንደ ነብያቸው መሀመድ ሞት ለአይሁድና ክርስቲያኖች እያሉ የያዙን ልቀቁን ድራማ በመሥራት ላይ ናቸው። የአሜሪካውያንና እስራኤላውያንን ደም ማፍሰስ ስላልተቻላቸው የራሳቸውን ሕዝብ ደም በጌታችን ልደት ዕለት አፈሰሱ፤ በማግስቱ ደግሞ የዩክሬይንን የሲቪላውያን አውሮፕላን ጥለው የራሳቸውንና የካናዳውያንን (ትውልደ ኢራን) ደም አፈሰሱ። ልክ እንደ ሁልጊዜው ያልታጠቁ ሰዎችን ደም በማፍሰስ የደም መስዋዕት ለዋቄዮአላህ አቀረቡ ፥ አላህም በጣም ደስስስ ተሰኘ።

በመጀመሪያው የገልፍ ጦርነት የሳዳምን ኢራቅ እንኳ ማሸነፍ ያልቻለችዋ ጉረኛዋ ኢራን የመሀመዳውያኑን የፌንጣ ቁጣ ለማብረድ ከባራክ ሆሴን ኦባማ በተሰጣት ገንዘብ የተገዙትን የሣር ቤት ማፍረሻ ሚሳኤሎች ወደ ኢራቅ ማወንጨፍ ጀመረች። ይህ ድርጊት በተከሰተ በአንድ ሰዓት ውስጥ በኢራን ኃይለኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ተሰማ (4.9) ይህን መሬት መንቀጥቀጥ ሊፈጥር የሚችለው ከፋርስ ባሕረ ሰላጤ ውሃ ሥር የተቀበረ የአሜሪካ የኑክሌር ወይም ተመሳሳይ መሬት መንቀጥቀጥ ፈጣሪ መሣሪዎች ናቸው። ይህ ክስተት በተፈጠረ በሰዓት ውስጥ የኢራን ሙላዎቹ “ኧረግ! ኧረግ! በቃን! ከእንግዲህ ወዲያ ሚሳየሎች አንልክም፣ ሰላም!ሰላም!” አሉ። ጉረኞችና ቦቅቧቃዎች ናቸውና።

በገና ዋዜማ በጀነራል ሶሌይማኒ ቀብር ላይ 56 መሀመዳውያን ኢራን ተረጋግጠው ሲሞቱ ብልጭ ብሎ የታየኝ የ“መስከረም 2009 “ቢሾፍቱ” ሆራ ኢሬቻ ዕልቂት ነበር። የክርስቶስ ልጆች ለበዓላታቸውም ሆነ ለሃዘን ሲወጡ በሰላምና በፍቅር ወደ ቤቶቻቸው ይመለሳሉ፤ መሀመዳውያን ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መጮህ፣ መባላትና ደም ማፍሰሱን ይመርጣሉ።

በልደት ዕለት የ 176 ተጓዦቹን ህይወት የቀጠፈው አውሮፕላን ተከሰከሰ ሲባል የታየኝ ኢራኖች አውሮፕላኑን እንደመቱት፤ በቢሾፍቱ ሆራ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድም በገዳይ አብይ አህመድ ትዕዛዝ አሻጥር ተሠርቶበት እንደወደቀና የ157 ሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ ነበር። ሁለቱም አውሮፕላኖች የተለያዩ ሞዴሎች ቢሆኑም ከቦይንግ ተቋም መሆናቸው ለጉዳዩ ሌላ ተጨማሪ ክብደት ሊሰጠው ይገባል።

የገና ዕለት ኢራን ሚሳኤሎችን መተኮሷን ስሰማ ወዲያው የታዩኝ ከዘራና ድንጋይ ይዘው የሚዝቱትን የኛዎቹን የዋቄዮ አላህ ልጆች ነበሩ።

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: