Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2023
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሕማማት’

ቀዳም ሥዑር | የቅዱስ እሳት ተአምር በኢየሩሳሌም | The Miracle of the Holy Fire in Jerusalem

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2021

✞✞✞ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ።✞✞✞

የማያቃጥለው እና የክርስቲያኖችን ነፍስ የሚያስደስተው ይህ ድንቅ ሥነ-ስርዓት በኢየሩሳሌም በሚገኘው የትንሳኤ ቤተክርስቲያን ውስጥ በቅዱስ ቅዳሜ ይካሄዳል።

ፋሲካ የሚውልበት ቀን በየዓመቱ እንደ አዲስ ይወሰናል፡፡ የቀን እና የሌሊት ርዝመት እኩል በሚሆንበት የፀደይ እኩልነት እና ከአይሁድ ፋሲካ በኋላ የመጀመሪያ እሁድ መሆን አለበት። ስለዚህ ብዙ ጊዜ የተለያዩ መስፈርቶችን በመጠቀም ከሚወስነው የካቶሊክና ፕሮቴስታንት ፋሲካ ቀን ይለያል።፡ የቅዱስ እሳት በዓለም ምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በጣም የታወቀ ተዓምር ነው፡፡ ለዘመናት በየአመቱ በተመሳሳይ ቦታ፣ በተመሳሳይ ጊዜና በተመሳሳይ ሁኔታ ይካሄዳል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደዚህ በመደበኛነት እና ያለማቋረጥ የሚከሰት ሌላ ተዓምር አይታወቅም። የሚከናወነው በኢየሩሳሌም በሚገኘው የትንሳኤ/ የቅዱስ ጎለጎታ ቤተ ክርስቲያንን ውስጥ ነው ፣ በምድር በጣም በተቀደሰው ስፍራ ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታሰረበት፣ በተሰቀለበት እና በመጨረሻም ከሞት በተነሳበት፡፡

The ceremony, which awes the souls of Christians, takes place in the Church of the Resurrection in Jerusalem. The date for Pascha is determined anew for every year. It must be a first Sunday after the spring equinox and Jewish Passover. Therefore, most of the time it differs from the date of Papal Protestant and Protestant Easter, which is determined using different criteria. The Holy Fire is the most renowned miracle in the world of Eastern Orthodoxy. It has taken place at the same time, in the same manner, every single year for centuries. No other miracle is known to occur so regularly and so steadily over time. No other miracle is known to occur so regularly and so steadily over time. It happens in the Church of the Holy Sepulchre in Jerusalem, the holiest place on earth, where Christ was crucified, entombed, and where He finally rose from the dead.

Breaking News from #Jerusalem the Resurrection Church :blood is leaking from the stone Jesus body was laid before his burial . You can hear the Israeli police closed the area.

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጌታችን ስቅለት በዓል የአዲስ አበባ አድባራት በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተው በነበሩበት ዘመን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2021

ዛሬስ? ዛሬማ የአርዮስ ኢሬቻ በላይና አጋንንት መንጋው መፈንጫዎች ሆነዋል።

✞✞✞ዓርብ ስቅለት በደብረ ቤቴል አበ ብዙሃን-አብርሃም ገዳም✞✞✞

✞✞✞ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን✞✞✞

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ የድኅነት ቀንይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

፩. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጌታችን ስቅለት ከ፸፫/73 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅዱስ ኡራኤል ዕለት ዋለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2021

✞✞✞ዓርብ ስቅለት ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ነው✞✞✞

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተ ወስዳችሁ እንደሕጋችሁ ፍረዱበት፤ አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት ኢትቅትል ብእሴጻድቀወኀ ጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንም ከፍርድ አታድን፤ ትላለችና እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞች ነን፤ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ የድኅነት ቀንይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤

፩. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

👉 ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”

. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ

. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው

፬. እመቤታችንን “ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ”፤ ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤

፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ”

. ተጠማሁ

፯. “ዅሉ ተፈጸመ (ማቴ. ፳፯፥፵፭-፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫-፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲-፴)፡፡

ከሰድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ጨለማ ኾኖ ከቈየ በኋላ ከዘጠኝ እስከ ማታ እንደ ተለመደው ብርሃን ሁኖአል፡፡ “ወፍና ሠርክ ይበርህ ብርሃነፀሐይእንዲል (ዘካ. ፲፬፥፯)፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. ፪፥፲፤ ቈላ. ፩፥፳)፡፡ ጌታችን ጠዋት በሦስት ሰዓት ተገረፈ፤ በስድስት ሰዓት ተሰቀለ (ማቴ. ፳፯፥፩-፴፯፤ ሉቃ. ፳፫፥፩-፵፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፩)፡፡

ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. ፲፱፥፴፬)፡፡ በዐሥራ አንድ ሰዓት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው ሽቶ እየረበረቡ በድርብ በፍታ ገንዘው ቀበሩት (ሉቃ. ፳፫፥፶-፶፬፤ ዮሐ. ፲፱፥፴፰-፵፪)፡፡ ነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዳ ነፍሳትን ነጻ አወጣች (፩ኛ ጴጥ. ፫፥፲፱)፡፡ በዚህ ጊዜ በርሃነ መለኮቱ በሲኦል ተገለጠ፡፡ ስለዚህም “ንሴብሖለእግዚአብሔር እየተባለ ይዘመራል፡፡ ከሆሣዕና አንሥቶ ተከልክሎ የነበረው ኑዛዜ ይናዘዛል፤ ጸሎተ ፍትሐት ይደረጋል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

በዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ የተሰየመው ቅዱስ ኡራኤል ነው።

ቅዱስ ኡራኤል

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና ምስጋን አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልአክ በችሎታችን መጠን እንድናመሰግን እግዚአብሔር ይርዳን፤ አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ ምስጢሩን ይግለጥልን አሜን፡፡

ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” [/ዕዝ. ሱቱ. ]

በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ

በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። መዝ. [/፺፩/፥፲፩፡፲፮]

አፈቅሮ ፈድፋደ፡ዑራኤል ሆይ፣ ከመልኮች ሁሉ ይልቅ ያንተን መልክአ ጸሎት እወዳለሁ፡፡ የመልክህ ስነ ጸዳል በደመ ወልድ እግዚአብሔር የታተመ ነውና፡፡

ዑራኤል ሆይ፣ እግዚአብሔር ሀይሉን የሚገልጽብን መልአከ ብርሃናት አንተ ነህ፡፡ በዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ አንተ ተሰይመሃልና፡፡ ስለክብርህ የሰማይ መላእክት አደነቁ፡፡

ለተፈጥሮትከ፡

ዑራኤል ሆይ፡ያለ መናገር በጥንት አርምሞ ከነፋስና ከእሳት ለተፈጠረ ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ የተፈጥሮና የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድናልና፡፡

ለዝክረ ስምከ፡

ዑራኤል ሆይ፡ከማርና ከወተት ይልቅ ለሚጥመው ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡

ዑራኤል ሆይ፡ክፍልህ /ክንፍህ/ በደመ ወልድ እግዚአብሔር የተከበረ /የታለለ/ ነውና፡፡ ለዓለሙ ሁሉ መድሃኒት ትሆን ዘንድ ግሩም የሚሆን የእግዚአብሔር ሥልጣን በክብር ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ (መልክአ ዑራኤል)

የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” [መዝ.፴፫/፴፬/፥፯]የሊቀ መልአኩ የክዱስ ዑራኤል ረድኤቱ በረከቱ ፍጹም አማላጅነቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣኝ፣ ካለማወቅ ወደ መረዳት ያደረሰኝ አነሳስቶ ላስጀመረኝ አስጀምሮ ላስፈጸመኝ ጥንት ላሌለው ቀዳማዊ ፍጻሜ ላሌለው ድህራዊ ያልኖረበት ጊዜ የሌለ የማይኖርበት ጊዜም የማይኖር የዘላለም ንጉስ ሁሉን ቻይ ፈጣሪ እግዚአብሔርን በራስ ፀጉሬ ቁትር በአጥንቶቼም ልክ አመሰግናለሁ፡፡

በሰማይ ያሉ መላእክት በምድርም የሚኖሩ የአዳም ዘር ሁሉ የሚያመሰግኗት በአማላጅነቷ ሁል ጊዜ የማትለየኝ ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበራ የብርሃን እናት የሁሉ እመቤት የአምላክ እናት ከተመረጡ የተመረጠች ከተለዩ የተለየች ከተከበሩ የተከበረች እናቴ እመቤቴ ድንግል ማርያም በቃላት ልገልጸው ከምችለው በላይ አመሰግናለሁ፡፡ ሌሊትና ቀን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑና ሳይሰለቹ የሚጠብቁን ሊቀነ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱስ ዑራኤል ቅዱስ ራጉኤል ቅዱስ ፋኑኤል እልፍ አእላፋት የሆኑ ጠባቂ መላእክት ሳመሰግን በደስታ ነው፡፡

በጸሎታቸው ያልተለዩኝን ጻድቃን አባቶቼን አቡነ ተክለሃይማኖትን አቡነ ገብረምንፈስ ቅዱስን አቡነ ሀብተማርያምን አቡነ አረጋዊን አቡነ ኪሮስንና ሌሎች ቅዱሳን አባቶቼን እንዲሁም እናቶቼን ቅድስት ክርስቶስ ሰምራን ቅድስት አርሴማን ብዙ ያልጠቀስኳቸው ቅዱሳንን ለማመስገን ቃላት የለኝም፡፡

በሰማኝትነታቸው የጥንካሬ ምሳሌ የሆኑልኝ በጸሎታቸው የረዱኝን ቅዱሳን ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ቅዱስ እስጢፋኖን መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስንና ሌሎችን ቅዱሳን ሰማዕታትን ሁሉ በእጅጉ አመሰግናለሁ ለዘላለሙ አሜን፡፡

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

___________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2020

ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡

👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል

  • . ፀሐይ ጨለመ፤
  • . ጨረቃ ደም ኾነ፤
  • . ከዋክብት ረገፉ፤
  • . የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
  • . አለቶች ተፈረካከሱ፤
  • . መቃብራት ተከፈቱ፤
  • . ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)

👉 ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል

  • . “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”
  • . “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ
  • . “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው
  • . እመቤታችንን ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ ደቀ መዝሙሩንም እናትህ እነኋትበማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
  • . አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ
  • . ተጠማሁ
  • . ዅሉ ተፈጸመ (ማቴ. ፳፯፥፵፭፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲)፡፡

+_______________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

አስደናቂ ዕይታ | በደመናዎች መሃል የገባው የፀሐይ ብርሃን መስቀል ሠርቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2019

ፍኖተ መስቀል – የመስቀል መንገድ

ፍኖተ መስቀል ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከጲላጦስ ዐደባባይ አንሥቶ መስቀሉን ተሸክሞ እስከተሰቀለበት ተራራ ቀራንዮ ድረስ የተጓዘበት መንገድ ማለት ነው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐሙስ ማታ እንደተያዘ ሌሊቱን ሁሉ መከራ ሲቀበል አድሮ ዓርብ ጧት የአይሁድ ሽማግሌዎችና አለቆች ተሰብስበው ወደ ሹሙ ወደ ጲላጦስ ቤት ይዘውት ሔዱ፡፡ ከዚያም ይህ ሰው ከሕጋችን ጋር የማይስማማ ትምህርት ሕዝቡን ያስተምራልና እንደ ሕጋችን ሞት ይገባዋል፡፡ ንጉሥ ነኝ፣ እያለም ያታልላል በማለት በሹሙ ፊት ቀርበው ከሰሱት፡፡ ጲላጦስ ግን ብዙ ቢዋሹበትና ቢከሱት አላመናቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱም መርምሮ በደል አላገኘበትምና ሊያድነው አስቦ ነበር፡፡ ግን ሊያድነው አልተቻለውም፡፡

ጲላጦስ ጌታችንን ሲመረምር ለብቻው አቁሞ መጠየቅ የሮማውያን ልማድ ነበርና አዳራሽ አስገብቶ ለብቻው የተከሰሰበትን ነገር ጠየቀው፡፡ አይሁድ ግን በዓለ ፋሲካ ደርሶባቸው ነበርና ስለ በዓሉ ክብር ሲሉ ወደ ፍርድ ቤት አልገቡም፡፡ ከውጪ ተሰብስበው እርስ በእርሳቸው እንደፈቃዳቸውና እንደምኞታቸው ጌታን ለመስቀል ያስቡ ነበር፡፡

ጲላጦስም ጌታን ለብቻው በጥያቄ ከመረመረው በኋላ ከአዳራሹ ወደ ውጭ ብቅ ብሎ በዚህ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ወይም ምክንያት አላገኘሁበትም ያውላችሁ አላቸው፡፡ እነሱም ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሏልና ሞት ይገባዋል፡፡ ስቀለው፣ ስቀለው እያሉ መለሱለት፡፡ እሱም እንደገና ለብቻው ጠይቆና መርምሮ የሚሞትበት በደል ስላላገኘበት ከአዳራሹ ወደ ውጭ ወጣና ውኃ አስመጥቶ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ፡፡ ከዚህም ሰው ደም ንጹሕ ነኝ ሞት አልፈርድበትም እያለ ሐቁን መሰከረ፡፡

አይሁድ ግን ይህ ሰው ንጉሥ ሳይሆን ንጉሥ ነኝ ብሏል፤ ንጉሥ ነኝ የሚል ሁሉ የቄሳር ተቃዋሚ ጠላት ነው፡፡ የቄሳር ወደረኛ መሆኑን እኛ እየመሰከርን አንተ ግን የቄሳር ሹም ሆነህ ብትለቀው አንተ ታውቃለህ እያሉ ጲላጦስን አስፈራርተውታል፡፡ ጲላጦስም ይህን ሲሰማ በራሱ ላይ ክስ እንዳይመጣበት ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷቸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ጌታችንን ወታደሮቹ ተቀብለው ወደ ሌላ አዳራሽ አስገቡት፡፡ ልብሱን ገፍፈው፣ ሌላ ቀይ ልብስ አልብሰው፣ የሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፍተው፣ ዘንግ በእጁ አስይዘው፣ ሎቱ ስብሐት ንጉሥ ከሆንህ ለአንተ ስግደት ይገባል፡፡ ልብሰ መንግሥት ያምርብህ ይሆን? ክርስቶስ ከሆንህ ትንቢት ንገረንእያሉ ፊቱን ሸፍነው ራስ ራሱን በዘንግ እየመቱ ተሳለቁበት፡፡

ከያለበሱትንም ልብስ ገፍፈው የቀድሞ ልብሱን አልብሰው፣ መስቀሉን አሸክመው ወደሚሰቀልበት ቦታ ወደ ቀራንዮ ሲወስዱት የተነሡበት ቦታ ገበታ /ገበጣ/ ተብሎ ይጠራል፡፡ ከዚህ ቦታ ተነሥቶም መስቀሉን ተሸክሞ መከራውን ታግሶ እስከ ቀራንዮ የተጓዘበት ፍኖተ መስቀል ይባላል፡፡

___________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

ያስለቅሳል! ግን፡ ዓርብ ስቅለት ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 25, 2019

ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት

ጌታችን ሲሰቅልም የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል

. ፀሐይ ጨለመ፤

. ጨረቃ ደም ኾነ፤

. ከዋክብት ረገፉ፤

. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤

. አለቶች ተፈረካከሱ፤

. መቃብራት ተከፈቱ፤

. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩፶፬)፡፡

ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤

. ‹‹ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)››

. ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ››፤

. ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው››፤

. እመቤታችንን ‹‹ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ››፤ ደቀ መዝሙሩንም ‹‹እናትህ እነኋት›› በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤

. ‹‹አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ››

. ‹‹ተጠማሁ››፤

. ‹‹ዅሉ ተፈጸመ›› (ማቴ. ፳፯፥፵፭፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲)፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት ( ዘሰሉስ)

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 15, 2014

             ማክሰኞ

 
HimamateTrumpetበዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ ማቴ.21÷23-25፤ ማር.11÷27፣ ሉቃ.20÷1-8፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡
 
ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ በአንድ አገር የንግድ ቦታን የሚያጸድቅ መንግሥት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልመለሰም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሷል፡፡ “በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ፤ በማን ሥልጣን ነው ይህን የምታደርገው?” ነበር ያሉት፡፡ በራሴ ሥልጣን ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡
 
ጌታችን እኩይ የሆነውን የፈሪሳውያንን አሳብ በመረዳት “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር ሲል” ጠይቋቸዋል፡፡ ከሰማይ ያልነው እንደ ሆነ ለምን አላመናችሁበትም ይለናል÷ ከሰው ያልነው ከሆነ ሕዝቡ ይጣላናል፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ከዚህ የተነሣ ያቀረቡት የፈተና ጥያቄ ግቡን ሳይመታ ከሽፎባቸዋል፡፡ ማቴ.21÷25፤ ማር.11÷27-30፤ ሉቃ.20÷1-8፡፡
 
ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡፡
 
ምንጭ

__

 

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: