Posts Tagged ‘ሊቀ ዲያቆናት’
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2021
♰♰♰
ህመም የለም ፣ መዳፍ የለም ፥ እሾህ የለም ፣ ዙፋን የለም። ሐሞት የለም ፣ ክብር የለም ፥ መስቀል የለም፣ አክሊል የለም።
በመስቀል ላይ ሣለ የገሃነመ እሳትን ጠባቂ ጭፍሮች ያስደነገጣቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!
በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን የጸብ ግርግዳ አፍርሶ በመስቀሉ ሠሌዳ ላይ በደሙ ቀለምነት የሕይወታችንን መጽሐፍ የጻፈልን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። መስቀሉ፣ ጦሩ፣ ስሙ ጋሻችን ሆኖልና ድነነናል።
💭 በአቅራቢያዬ የምትገኘውን ውብ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ዛሬ ስጎበኛት ይህን በአክሊል ቅርጽ ተሠርቶ የቆመውን መብራት አብሬ ለማየት ቻልኩ። ከእኅታችን የመስቀል ወረብ ጋር በእውነት ድንቅ ድንቅ ነው!
አቤቱ በዘመኑ ሁሉ የጥፋትና የኃጢአት አውሬ (ዲያብሎስ) እንዳይቀርበን በሐጹረ ቅዱስ መስቀልህ አጥርነት ጠብቀን፤ አሜን!
✞✞✞መስቀል ኃይላችን ነው!✞✞✞
______________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: Aksum, Axum, ሊቀ ዲያቆናት, መስቀል, መስከረም, ሰላም, ስማእት, ቅዱስ እስጢፋኖስ, ብርሃን, ተራራ, ተዋሕዶ, ትግራይ, አክሱም, አዲስ አበባ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ኦርቶዶክስ, ደመራ, ግሪክ, ጦርነት, ጽዮን, Christianity, Greece, Jesus Christ, Light, Maskal, Peace, St.Stephan, The Cross, Tigray, War, Zion | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2021
✞✞✞መስቀል ኃይላችን ነው!✞✞✞
♰♰♰
No Pain, No Gain; No CROSS No CROWN
ያለህመም ማግኘት የለም ፥ ያለ መስቀል ፣ አክሊል የለም
ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፱ ዓ/ም ተመሠረተ። በዚያን ጊዜም ዘመኑ በፈቀድው መልክ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ተጠናቆ ሲወደስበት ሳለ፤ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ ደርሶበት ሕንጻው ተቃጠለ።
ኢትዮጵያ ከ ፋሺስት የወረራ ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ፤ የግንባታው ሥራ በሥራ ሚኒስቴር ኃላፊነት በዘመናዊ መልክ እንዲሠራ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሚኒስትሩ ባላምባራስ (በኋላ ብላቴን ጌታ) ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በአንድ በኩል የአካባቢውም ኗሪ እና የቤተ ክርስቲያኑ ምእመን በመሆናቸው እና በሚኒስቴራዊ ኃላፊነታችው፤ ሥራውን በቅርብ እየተከታተሉና እየተቆጣጠሩ አሠርተውት የአሁኑ ሕንጻ ግንባታ ፍጻሜ አግኝቶ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ የግብጽ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በተገኙበት ተባረከ።
♰ የቀዳሚ ሰማእት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት ነበር | የጽዮናውያንም እንዲሁ
✞ እስጢፋኖስ — በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው። በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው።
✞ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀዳጃቸው ሦስቱ አክሊላት፡–
፩. ስለንፅህናው ስለድንግልናው
፪. ስለሰማዕትነቱ /ስለምስክሩ/ ስለተጋድሎው
፫. ስለስብከቱ /ስለትምህርቱ/ ስለተአምራቱ
✞ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ታንፆበታል። /ሰባት ቤተክርስቲያናትን አንጿል።/
✞ የቤተክርስቲያን አባቶች የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራውን እንድናይበት አድርጎናል ሲሉ ይገልፁታል እውነት ነውና።
_________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: Aksum, Axum, ሊቀ ዲያቆናት, መስቀል, መስከረም, ሰላም, ስማእት, ቅዱስ እስጢፋኖስ, ብርሃን, ተራራ, ተዋሕዶ, ትግራይ, አክሱም, አዲስ አበባ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ኦርቶዶክስ, ደመራ, ግሪክ, ጦርነት, ጽዮን, Christianity, Greece, Jesus Christ, Light vs Darkness, Maskal, Peace, St.Stephan, The Cross, Tigray, War, Zion | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 27, 2021
✞✞✞መስቀል ኃይላችን ነው!✞✞✞
________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia | Tagged: Aksum, Axum, ሊቀ ዲያቆናት, መስቀል, መስከረም, ሰላም, ስማእት, ቅዱስ እስጢፋኖስ, ብርሃን, ተራራ, ተዋሕዶ, ትግራይ, አክሱም, አዲስ አበባ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ኦርቶዶክስ, ደመራ, ግሪክ, ጦርነት, ጽዮን, Christianity, Greece, Jesus Christ, Light, Maskal, Orthodox Christianity, Peace, St.Stephan, The Cross, Tigray, War, Zion | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 28, 2018
ቀዳሚ ሰማእት ቅ/ እስጢፋኖስ በጥቅምት ፲፯ ዕለት ሊቀ–ዲያቆናት ተደርጎ በሐዋርያት ተሾመ፡፡
እንኳን አደረሰን!
መስቀል፤ የመስከረም ፲፯ / ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም ደማቅ ክብረ በዓል
የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያንን ግቢ እንዲህ ግጥም፡ ሙልት ብሎ አይቼው አላውቅም፤ በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማታችን ያሸበረቁ በጣም ብዙ ምዕመናን ተገኝተው ነበር።
ለመንፈሳዊ ሕይወት በጣም ታታሪ የሆነው ክርስቲያን ወገናችን ሊመሰገን፣ ሊወደስና ሊደነቅ ይገባዋል፤ ብዙ ጊዜ ሲኮነን እንጂ ሲደነቅ አንሰማም። ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት አንስቶ እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ ቀዳሚ ሰማዕት ቅ/እስጢፋኖስን ለማስታወስ በቤተክርስቲያኑ ተገኝቷል።
እስኪ የት ሌላ ዓለም ነው ተመሳሳይ ሁኔታ የሚታየው? በየትኛውስ ሌላ ሃይማኖት? ካቶሊኩና ፕሮቴስታንቱ ከአንድ ሰዓት በኋላ፣ እስላሙ ከሠላሳ ደቂቃ በኋላ ነው ለአምላኮቻቸው ጸልይው የሚበታተኑት።
ደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት በ፲፱፻፱ ዓ/ም ተመሠረተ። በዚያን ጊዜም ዘመኑ በፈቀድው መልክ የቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ ተጠናቆ ሲወደስበት ሳለ፤ በጣልያን የወረራ ዘመን፣ በ፲፱፻፴፪ ዓ/ም ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ ደርሶበት ሕንጻው ተቃጠለ።
ኢትዮጵያ ከ ፋሺስት የወረራ ቀንበር ከተላቀቀች በኋላ፤ የግንባታው ሥራ በሥራ ሚኒስቴር ኃላፊነት በዘመናዊ መልክ እንዲሠራ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ሚኒስትሩ ባላምባራስ (በኋላ ብላቴን ጌታ) ማኅተመ ሥላሴ ወልደ መስቀል በአንድ በኩል የአካባቢውም ኗሪ እና የቤተ ክርስቲያኑ ምእመን በመሆናቸው እና በሚኒስቴራዊ ኃላፊነታችው፤ ሥራውን በቅርብ እየተከታተሉና እየተቆጣጠሩ አሠርተውት የአሁኑ ሕንጻ ግንባታ ፍጻሜ አግኝቶ ጥቅምት ፲፯ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ/ም ቅዳሴ ቤቱ የግብጽ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትረያርክ፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛ በተገኙበት ተባረከ፡፡
+ እስጢፋኖስ — በግሪክ ቋንቋ አክሊል ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡
+ ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀዳጃቸው ሦስቱ አክሊላት፡–
-
ስለንፅህናው ስለድንግልናው
-
ስለሰማዕትነቱ /ስለምስክሩ/ ስለተጋድሎው
-
ስለስብከቱ /ስለትምህርቱ/ ስለተአምራቱ
+ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ታንፆበታል፡፡ /ሰባት ቤተክርስቲያናትን አንጿል፡፡/
+ የቤተክርስቲያን አባቶች የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሞት ለክርስትና እምነት መስፋፋት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራውን እንድናይበት አድርጎናል ሲሉ ይገልፁታል እውነት ነውና፡፡
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሊቀ ዲያቆናት, ስማእት, ቅዱስ እስጢፋኖስ, አዲስ አበባ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥቅምት ፪ሺ, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »