Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ሊቀ መላእክት’

የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር | ቤተ ክርስቲያኗን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈነዳ ፥ በቦታው ላይ ይህ መስጊድ ለሉሲፈር ተሠራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 8, 2022

😇 የሊቀ መላእክት ሩፋኤል ክብረ በዓል በታሪካዊቷ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፤ አዲስ አበባ ጉለሌ።

ጳጕሜን ፫፥ ፪ሺ፲ በታሪካዊቷ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፡ ዝናባማ በነበረበት ቆንጆ የቀትር ሰዓት ላይ፡ የጸሎት ስነሥስርዓቱ ልክ እንዳለቀ የመሀመዳውያኑ ጋኔን አዛን ተለቀቀ። (ቪድዮው መጨረሻ ላይ ይሰማል) ወዲያውም ይህ የዲያብሎስ ተንኮል እንደሆነ በመረዳት ወደ አንድ አባት ጠጋ ብዬ፡ ለምን ቅዳሴና ጸሎት ሲገባደድ ይህ ሰይጣናዊ ጩኽት ይከተላል? ከየትስ ነው የሚመጣው? ብዬ አብረዋቸው ከነበሩት ሌላ ሰው ጋር ስጠይቃቸው፤

ከ ፻፴/130 ዓመታት በፊት የዚህች ውብ ቤተክርስቲያን ህንፃ በተሠራ ማግስት አንድ ከቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት ይኖር የነበረ ጭራቅ/ጠንቋይ በየቀኑ እየመጣ ቤተክርስቲያኗን ካላፈረስኩ፣ ካላቃጠልኩ እያለ ለሳምንታት ሲዝት ከቆየ በኋላ አንድ ቀን እራሱ ፈንድቶ ሞተ” አሉኝ።

እኔም፡ በመገረም፡ “በዚህ ፈጽሞ አልጠራጠረም! ግን ጠንቋዩ የሞተበት ቦታ ምን ተደርጎበት ይሆን?“ ብዬ ስጠይቃቸው፤ “ያው!“ አሉኝና፤ ሦስታችንም ዘወር ስንል ለካስ ቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት (በ፶/50ሜትር ርቀት) መስጊዱ ተተክሎ ይታያል። እንዴ፡ “ጠንቋዩ ፈንድቶ በሞተበት ቦታ ላይ ይህ መስጊድ ተሠርቷል ማለት ነው“ እንዳልኩ ሁላችንም በመገራረም እርስበርስ ተያየን።

አዎ! የሚያጠራጥር አይደለም፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ግን ይህን ሁላችንም አናውቅም ነበር፤ በጣም ይገርማል!

ከዚያም ከቤተክርስቲያኗ ግቢ እንደወጣሁ፤ የኔ ቢጤዎች ከነበሩበት ቦታ አስር የሚሆኑ ወጣቶች ተነስተው ከበቡኝና “ምን ፈልገህ መጣህ? ለምን መጣህ? ምን ትሠራለህ? … ወዘተ” እያሉ በሚገርም መልክ ይጨቀጭኩኝ ጀመር። ልክ እዚህ ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው፦ “ለንደን ሃይድ ፓርክ | ሺ ደካማ ጂቦች ጀግናውን አንበሣ አፍነው ሊገድሉት”

እኔም፡ ምንም አለመለስኩላቸውም “በ ስም ልቀቁኝ!” አልኩና ዘወር ብዬ መራመድ እንደጀመርኩ አሁንም ተከተሉኝ፤ በዚህ ወቅት መንገድ ላይ ለነበረው አንድ ፖሊስ “ኧረ እባክዎ ከነዚህ ሰዎች ይገላግሉኝ!“ አልኩት፤ እርሱም “ሂዱ!“ እያለ ይጮኽባቸው ጀመር፤ እኔም ታክሲዎች ወደሚገኙበት ቦታ አመርቼ እንደተሰለፍኩ፤ ልጆቹ አሁንም በየአቅጣጫው ቆመው ወደ እኔ ይመለከቱ ነበር፤ በዚህ ወቅት ከየት መጣ ሳልለው አንድ ደግ ባለ መኪና “ወደ ፒያሳ ነህ?” አለኝና አሳፍሮ ወሰደኝ።

በዚህ ወቅት በ “ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፱” ላይ ሰዶማውያን ወደ አብርሃም ዘመድ ወደ ሎጥ ቤት ወጥተው ለማጥቃት ሲሞክሩ መላዕክት በአካል ወደ ሎጥ ቤት እንግድነት ገብተው አደጋ እንዳይፈጠር በር ሲዘጉና ሎጥን ከጥፋት ሲያድኑ የተነገረን ታሪክ ትዝ አለኝ።

ታዲያ የኔ ቢጢዎች ጋር የነበሩት እነዚህ ልጆች እነማን ናቸው? እያልኩ እራሴን ጠየቅኩ። እነዚህን ከ፲፫/13 እስከ ፳/20 የሚጠጉ እድሜዎች ያሏቸውን፡ በደንብ መናገር የሚችሉትን ጎረምሳዎችን ያውኩ ዘንድ የመሀመድ ዲያብሎስ ምዕመናኑን አዘጋጅቷቸው ይሆን? መቼም ሰይጣን ሁሌ ከቤተክርስቲያን አይርቅምና!

አህዛብ ከዓብያተ ክርስቲያናት ጎን የሰይጣን ማምለኪያ መስጊድ የገነቡት የአዛዜልን አዚምና ማደንዘዣበመበተን ለዘመናት ለቡና፣ ጫትና ጥንባሆ የተጋለጠውን ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደንዘዝ መሆኑ የዛሬው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ምስክር ነው። እንዲያውም አንዳንዴ እኮ ታቦት ሳይቀር በመስጊዶች አካባቢ ሲያልፍ መንቀሳቀስ እንደሚያቅተው በተደጋጋሚ ታዝበናል።

በቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያንም የታዘብኩት ይህንን ነበር። ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይም ይህ መስጊድ ተሠራለት፤ ዲያብሎስን፣ 666 ድል የሚያደርገው ቅዱስ ሩፋኤል መስጊዶቹን በመላዋ ኢትዮጵያ አንድ ቀን ያስወግዳቸዋል፣ ዛሬ የነገሰውንም አረመኔ የኦሮሞ አገዛዝ በቅርቡ ከነ ፒኮኮ ያፈነዳዋል።

ቻይ እና ወዳጅመስለው ለመታየት የሚሹትና በዋቄዮአላህዲያብሎስ አዚም የፈዘዙት ብዙ ወገኖች፣ የተመረጡት ሳይቀሩ በእነዚህ ቀናት፤ “ሁላችንም በየሃይማኖታችን እንጸልይ…’ዱዋእናድርግክርስቲያኑ እግዚአብሔርን ሙስሊሙም አላህን ይማጸንክርስቲያኑ መጽሐፍ ቅዱስንሙስሊሙም ቁርአንን ያንብብእግዚአብሔር ከሁሉም ጋርጸጥ ለጥ ብለን በሰላም እንድንኖር ያዘናልወዘተ.” በማለት እየተዝለገለጉና እይቀበጣጠሩ ነው። በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ ፥ የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ“(ዘጸ. )” የሚሉትን የእዚአብሔርን የመጀመሪያ ትዕዛዛት እየጣሱና ከባድ ኃጢዓት እየሠሩ መሆናችውን አይገነዘቡትምን? እኛ ክርስቲያኖች፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት“(ኤፌ ፬:)! ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል(ማር ፲፮ ÷፲፮)” እያለን አንዱንና ብቸኛውን አምላካችንን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ነው የምናመልከው እንጂ ሌላ አምላክ፣ ሌላውን ሃይማኖት ወይም መጽሐፍ ሁሉ ከዲያብሎስ ነውና አንቀበለውም!

ኢትዮጵያ ሁለት አማልክትየሚመለኩባት ምድር አይደለችምና ባካችሁ እንደ ኤዶማውያኑ ያልሆነ የሃይማኖት እኩልነትና፣ የዲሞክራሲ ቅብርጥሲ የመቻቻል ተረተረትእየፈጠራችሁ በሃገራችን ላይ መቅሰፍቱን አታብዙባት፤ ሃገር በሁሉም አቅጣጫ እየነደደች እኮ ነው።

😈 የዲያብሎስ መንግስታዊ ሕግ የ “መቀላቀል” ሕግ ሲሆን የእግዚአብሔር መንግስታዊ ሕግ ደግሞ የ “መለየት” ሕግ ነው። ምኒልክም የዛሬዋን የአብዛኛውን የዚህ ከንቱ ትውልድ ኢትዮጵያ ስጋን የመሰረቷት በመቀላቀል ሕግ ነው። የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለን ስንወጣ የምናመልጥባት ስፍራ ጭምር ትድናለች፡፡ የሚጠፉትን የምናድነው በመደባለቅ ሳይሆን ጥሪውን ተቀብለን ለእግዚአብሔር በመለየት ነው፡፡

ሸሽተህ አምልጥ

መላእክቱ ለሎጥ ያስተላለፉት ሌላው የሕይወት መመሪያ፡- “እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ” የሚል ነው[ዘፍ. ፲፱፥፲፯]፡፡ ስለ መሸሽ ብቻ አልነገሩትም፣ ወዴት መሸሽ እንዳለበትም አመልክተውታል፡፡ ወደ ተራራ!!

የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች በተለይ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊከሰት ሲል ከሰዎች ቀድመው እንስሳት ያውቃሉ፡፡ በሱናሚ አደጋ ወቅት የተፈጸመ አንድ ታሪክ እናስታውስ፡- በኢንዶኔዥያ የባሕር ዳርቻ ባለ የመዝናኛ ስፍራ የዝሆኖች ትርኢት በማሳየት የሚተዳደር አንድ ሰው ዝሆኖቹን እንደ ወትሮው ለማዘዝ ቢሞክር ባልተለመደ ሁኔታ እምቢ አሉት፡፡ እንዲያውም ይባስ ብለው እየጮኹ ባቅራቢያው ወደሚገኘው ተራራ መሮጥ ጀመሩ፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ባለቤቱ ተከትሏቸው ወደ ተራራው ይሮጣል፡፡ ልክ ተራራው ላይ እንደ ደረሱ የሱናሚ አደጋ ይከሰታል፡፡ አካባቢውም እንዳልነበረ ሆነ፡፡ ያም ሰው ዝሆኖቹን ይዞ ሲመለስ ሁሉም ነገር ወደ አለመኖር ተቀይሮ ያገኘዋል፡፡ ቤተሰቡን ጨምሮ ብዙ ወገኖቹን አጣ፡፡ ዝሆኖቹን ተከትሎ ወደ ተራራው በማምለጡ የራሱን ሕይወት አተረፈ፡፡ መላእክቱም ሎጥን፡- “እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ” አሉት [ዘፍ. ፲፱፥፲፯]።

በተራራው ላይ የመረጣትን ከተማ ጥፋትም ያያል፡፡ ተራራው ከፍ ያለ በመሆኑ ሁሉን ያሳያል፡፡ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም እንኳ በተራራ ተመስላለች [ዕብ. ፲፪፥፳፪]፡፡ እግዚአብሔር ለእኛም ያዘጋጀልን ተራራ አለ፡፡ እርሱም ቀራንዮ ወይም የክርስቶስ ሞት ነው፡፡ ከክርስቶስ ሞት በቀርም ከዘላለም ጥፋት የምንድንበት ምንም ማምለጫ የለም [የሐዋ. ፬&፲፪፤ ዮሐ. ፲፬&፮]፡፡

ሎጥ ስለ ደከመ ወደ ተራራው ሳይሆን በቅርብ ወዳለችው ኋላ ዞዓር ወደተባለችው ከተማ ለመሸሽ መላእክቱን ጠየቀ፡፡ ከተማይቱም ለጥፋት የተቀጠረች ብትሆንም ሎጥ ወደ እርስዋ ሸሽቷልና ከጥፋት ዳነች [ዘፍ.፲፱÷፲፰፡፳፪]፡፡ የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብለን ስንወጣ የምናመልጥባት ስፍራ ጭምር ትድናለች፡፡ የሚጠፉትን የምናድነው በመደባለቅ ሳይሆን ጥሪውን ተቀብለን ለእግዚአብሔር በመለየት ነው፡፡

ሎጥ ሌሊቱን አልተኛም፣ የማምለጫ ሌሊት ሆነለት፡፡ እርሱ ያሰበው እንግዶቹን አብልቶ፣ አጠጥቶ፣ መኝታውን ለቆ ሲያሳርፋቸው ነበር፡፡ ያቺ ሌሊት ግን መልካም የመሥሪያ ሳይሆን የበጎነት ዋጋ የሚከፈልባት ሌሊት ሆነች፡፡ ይህች ሌሊት ለመልካሞቹ ሁሉ የተቀጠረች ሌሊት ናት፡፡ ይህችን ዓለም ትተን ስንወጣ በሰማይ የምንሸለምበት ሌሊት አለች፡፡ ሎጥን በሌሊት ለማውጣት የተደረገው ተልእኮ ዛሬም ጭምር የታገቱትን ለማስመለጥ የሚመረጥ ሰዓት ሆኗል፡፡ ሎጥ ወደ ዞዓር ሲደርስ ፀሐይ ወጣች፡፡ ቃሉ እንዲህ ይላል፡- “እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፡፡ እነዚያንም ከተሞች በዙሪያቸው ያለውንም ሁሉ ከተሞቹም የሚኖሩትን ሁሉ የምድሩንም ቡቃያ ሁሉ ገለበጠ፡፡ የሎጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመለከተች፡፡ የጨው ሐውልትም ሆነች” ይላል [ዘፍ. ፲፱÷፳፫፡፳፮]፡፡

❖[ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፳፪፥፲]❖

“በበሬና በአህያ በአንድነት አትረስ።”

❖[መጽሐፈ ዕዝራ ምዕራፍ ፱፲፤፲፩፤፲፪]❖

“አሁንስ አምላካችን ሆይ። ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡባት ምድር በምድር አሕዛብ ርኵሰት ረክሳለች፥ ከዳር እስከ ዳርም ድረስ ከርኵሰታቸው ከጸያፍ ሥራቸውም ተሞልታለች፤ አሁንም ትበረቱ ዘንድ፥ የምድሩንም ፍሬ ትበሉ ዘንድ፥ ለዘላለም ለልጆቻችሁ ታወርሱአት ዘንድ ሴቶች ልጆቻችሁን ለልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችሁ አትውሰዱ፥ ሰላማቸውንና ደኅንነታቸውንም ለዘላለም አትሹ ብለህ በባሪያዎችህ በነቢያት ያዘዝኸውን ትእዛዝ ትተናልና ከዚህ በኋላ ምን እንላለን?”

❖[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፪፥፵፫]❖

“ብረቱም ከሸክላው ጋር ተደባልቆ እንዳየህ፥ እንዲሁ ከሰው ዘር ጋር ይደባለቃሉ፤ ነገር ግን ብረት ከሸክላ ጋር እንደማይጣበቅ፥ እንዲሁ እርስ በርሳቸው አይጣበቁም።”

❖[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፯፥፩]❖

እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።

❖[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፬]❖

ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዛሬ፡ ቅዱስ ሚካኤል፡ ድል በተነሳውና በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ፡ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 19, 2019

እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ በዓል አደረሰን

ላፍቶ ቅዱስ ሚካኤል ፥ ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.

መንፍሰን የሚያድስ ሌላ ልዩና ውብ የቤተክርስቲያን ግቢቤተክርስቲያኗን እና ሕፃናት ልጆቿን እንዲህ በትዕግሥት፣ በትጋትና ፍቅር ለሚንከባከቧቸው አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች እና እህቶች ምስጋና ይገባል። በእውነት አዲስ አበባ የተዋሕዶ ዓብያተክርስቲያናት ባይኖሩ ኖሮ ከተማዋ አዲስ በረሃ ትባል ነበር።

ይትዐየን መልአከ እግዚአብሔር ዐውዶሙ ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖም ጣዕሙ ወታእምሩ ከመኄር እግዚአብሔር። መዝ.፴፫ (፴፬)

መላእክት የሚለው ቃል መልእክተኞች ተላላኪዎችየእግዚአብሔር ይቅርታ ወደ ሰው የሰውን ልመና ወደእግዚአብሔር የሚያደርሱየእግዚአብሔር ልዩ ወዳጆች ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩ አለቆች ገዥዎች ወይም የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ማለት ይሆናል፡፡ ሚካኤል ማለት መኑ ከመ እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው?” ማለት ነው፡፡ ሚካኤል በስም ተለይቶ መጠቀስ የተጀመረው በመጽሐፈ ዳንኤል /ዳን.፲፥፲፫፪፥፩/ ውስጥ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሄኖክም ለበርካታ ጊዜያት ተጠቅሷል፡፡ከዚህ ሌላ በብሉይ ኪዳን አዋልድ መጽሐፍት በኪዳነ አብርሃም ውስጥ ተጠቅሶም ይገኛል፡፡

ቅዱስ ሚካኤል ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን የምሕረትና የመዳኛ፤ የሰላም መልአክ ነው፡፡ በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” /ዳን.፲፪፥፩/ በማለት በነቢዩ ዳንኤል የተነገረ ሲሆን በሌላ ቦታ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ” /ዳን. ፲፥፲፫/ በማለት ያስረዳል፡፡ በዚህ ቃል ላይ ከዋንኞቹ አለቆች አንዱ የሚለውን በመያዝ ሚካኤል ብቻ የመላእክት አለቃ አይደለም የሚሉ አሉ፡፡ ነገር ግን የሌሎች አለቅነት የተወሰነ ወይም ዝቅተኛ ሲሆን በአንድ ነገድ ላይ በአንድ የመላእክት ከተማ ላይ ነው፡፡ የቅዱስ ሚካኤል አለቅነት ግን በመላእክት ሁሉ ላይከሆነ ከሌሎቹ ይለያል፡፡ በድርሳነ ሩፋኤል ላይ እንደተገለጸው ሰባት ሊቃነ መላእክት ቢኖሩም አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል አርምሞ ትዕግሥትን የሚወድ መልአክ ነው፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገሥጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረምቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር በተሰጠው ኃይል ዲያብሎስን ድል የነሣ መልአክ ነው፡፡ በሰማይ ጦርነት ተነሣ ሚካኤልና እርሱ መላእክት ከዘንዶው ከመላእክቱም ጋር ተዋጉ” /ራእ. ፲፪፥፯/ ይላል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል በዓል ሰኔ ፲፪ የሚከበርበት ምክንያት ዲያብሎስን በፈቃደ እግዚአብሔር ተዋግቶ ያሸነፈበት አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ክብር ይግባውና እግዚአብሔር በዚህች ዕለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ከወገኞቹ ከመላእክት ሁሉ በላይ አክብሮ ሹሞታልይላል ድርሳነ ሚካኤል

ከዚህ በተጨማሪ ይህ ዕለት ቅዱስ ሚካኤል አፎምያን ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ በአንዲት አገር ሃይማኖቱ የቀና ታላቅ መኮንን ከሙ አስተራኒቆስ የሚባል ሰው ነበር፡፡ ሚስቱም አፎምያ ትባላለች፡፡አፎምያ ባልዋ አስተራኒቆስ ታሞ እያለ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አስሎ እንዲሰጣት ለመነችው፤ እንዳለችው አደረገላትና ባልዋ ሞተ፡፡ ከዚህ በኋላ አፎምያ ባልዋ ያሠራላትን ሥዕል ይዛ በሃይማኖት ጻንታ ስትኖር ዲያብሎስ በተለያየ መልኩ ይፈትናት ጀመር፡፡ አንድ ጊዜ ባልቴት እየመሰለ ሌላጊዜ ሌላ እየሆነ ባል ማግባት እንዳለባት መከራት፡፡ መጽሐፍም ጠቀሰላት፡፡ ከንጉሡ ጋር ማጋባት እንዳሰበ ነገራት እርሷ ግን ማግባት እንደማትሻ እግዚአብሔርን እያገለገለች ኖራ ማለፍ እንደምትፈልግ ነገረችው፡፡ ዲያብሎስ ግን ፈተናውን እያባሰ እያባሰ መጣ፡፡ በመጨረሻ ግን በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል አሳፍራ አዋረደችው፡፡

የሰኔ ሚካኤል ዕለት ዲያብሎስ ዳግመኛ ሊፈትናት መጣ፡፡ ሚካኤል ነኝ አላት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል“/፪ቆሮ.፲፩፥፲፫/ እንዳለ በዚህን ዕለት የቀረባት ራሱን ለውጦ የብርሃን መልአክ መስሎ ነበር፡፡ አፎምያ ግን አስተዋይ ስለነበረች የብርሃን መልአክ ከሆንክ የመስቀል ምልክት ያለበት በትርህ ወዴት አለ?“ አለችው፡፡ በኛ በመላእክት ዘንድ የመስቀል ምልክት አይደረግም አላት፡፡ እርሷም ስለተጠራጠረችው የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ልታመጣ ወደ ሥዕል ቤቷ ስትገባ ዘለለና አነቃት፡፡ አፎምያ ጮኸች፤ ቅዱስ ሚካኤልም ፈጥኖ ደርሶ አዳናት ዲያብሎስንም አዋረደላት፡፡

ዲያብሎስ አፎምያ ያሰበችውን ጸጋ ሆኖ የተሰጣትን ኑሮ ትታ በተለየ ዓለም እንድትኖር እንደ መከራት በእኛም ሕይወት እንዲህ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በጋብቻ ወቅት ምንኵስናን እንድናስብበዕርቅ ሰዓት ጥላቻ እንዲሰማንበሰላም ጊዜ ጦርነትንበጾም ጊዜ ምግብንበትዕግሥት ጊዜ ቁጣን በመረጋጋት ጊዜ አድመኝነትን በውስጣችን ሊያኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ እንደ አፎምያ በእምነትና በምግባር ጸንተን በማስተዋል ልንኖር ይገባል፡፡

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ምንጭ፡ሐመር ፲፻፺፭ ግንቦት/ሰኔ

…………ሚካኤል ሆይ! የችግረኛውን ሁሉ ጸሎት ፈጥነው ለሚሰሙ አዕዛኖችህ ሰላምታ ይገባል። የይቅርታ መልአክ ሆይ! ችግሬን አቃልልኝ፤ ጭንቀቴንም አስወግድልኝ። ምክርን ትለግሰኝ ጥበብንም ታስተምረኝ ዘንድ አባት እንዳደረግሁህ አንተም ልጅ አድርገኝ።…………

ሚካኤል ሆይ ! ዳንኤል በአምሳለ አናብስት ምሳሌ ያየውን ሥውሩን ራእይ አብራርቶና ግልጥልጥ አድርጎ ለተረጎመለት አንደበትህ ሰላምታ ይገባል። የሰላም መልአክ ሆይ የምስጋናን መሥዋዕት የምታዘጋጅ አንተ ነህና ጠላት ዲያብሎስ ተረማምዶ በእደ ፃዕረ ሞት እንዳያፍነኝ በአፌ ላይ ጥበቃህን አጠንክር።…………

የቅዱስ ሚካኤል አምላክ ሆይ! በአርአያህ በአምሣልህ የፈጠርከን ሕዝቦችህን ሁሉ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሠውረን ለዘላለሙ አሜን።

ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ
ዛሬም ቆመሃል በኪዳንህ ላሉ
ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፍቴ
ምራኝ መንገዱን እንዳይመሽ ልድረስ አባቴ
እንደት ይገፋል ጎዳናው ያላንተ እርዳታ
ጥመን ቁረጠው በቤትርህ ጭንጫውን ምታ“()

ተጠመጠመ ጠላ በሳት ሰንሰለት
የጌታ መላአክ ካኤል በሰይፍ ወድቆበት
የለም በቦታው ስመለስ አጥቸዋለሁ
የምረዳኝን ተሹሞ አይቸዋለሁ“()

ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሃል
ስለረዳህው ዳንኤል እጅግ ወዶሃል
ይነዋወጣል ባህሩ አንተ ስትመጣ
እግዚአብሔር ይንገስ ድያብሎስ መድረሻ ይጣ“()

አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ
ስትራራልኝ እያየው ጸንቷል ጉልበቴ
ልዘምር እንጅ ላመስግን ታላቁን ጌታ
አንተን የሰጠኝ ጠባቅ በቀን በማታ“()

ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ፤ ዛሬም ቆመሃል በኪዳንህ ላሉ። አሜን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ስለ እኛ ስለሰው ልጆች በጌታ ፊት ቁምልን ምልጃና ጸሎትህ ተራዳእነትህ ጥበቃህ ለዘወትር አይለየን!! አሜንንንንንን።

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: