Posts Tagged ‘ሃጢአት’
“ሥልጣኔ” ከሀገርና ከባህል፣ ከቋንቋና ሥርዓት ውጪ የጥፋትና ሃጢአት ምክኒያቶችን ይዞ ወደ ሀገር ከገባ ብዙ ሰው በሃጢአት ቀንበር ውስጥ ሊወድቅ ይችላል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 3, 2019
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሃጢአት, መስከረም ፪ሺ፲፩, መድኃኔ ዓለም, ትምሕርት, አዲስ አበባ, ዝሙት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ፈተና, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
ከመጥፎ ሃሳብ፣ ከአጋንንት ሥራ፤ ወገን እና ወገንን በቋንቋ ምክኒያት ከሚለያይ ከዘረኝነት እግዚአብሔር ይሠውረን!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 6, 2018
“ነገሥታት መኳንንት ግብር ለመሰብሰብ በየዞኑና በየክፍለሃገሩ ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው በከፋፈሏቸው አካባቢዎች ምክኒያት በማድረግ፡ ወገን እና ወገን፡ ሁላችንም የክርስቶስ ልጆች፣ የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ሆነን፡ ነገር ግን በተልያየ ምክኒያት፤ በቋንቋ ምክኒያት፣ በወንዝና በተራራ ምክኒያት ከመጠላላት፣ ከመወጋገዝ፤ ከመጎዳዳት እግዚአብሔር ይሠወረን! ስነ ልቦናችን በጎ በጎውን እንዲያስብ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ያሳድርብን! ኃይለ አጋንንትን ያስወግድልን! የአጋንንት ሥራ ነው።
ሰዎች ከህገ እግዚአብሔር ወጣ ወጣ ሲሉ እግዚአብሔር ወደ ዓለም ቅጣቶችንና የቅጣት ምልክቶችን ያመጣል። የእኛ ለእግዚአብሔር አለመታዘዝ ባህልና ስልጣኔ እየመሰለን የውጭ ባህሎችን፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣሉ ባህሎችን እየተከተልን፤ ካለባበሳችን ስርዓት ጀምሮ፣ ለሃጢዓትና ለዝሙት ከሚጋብዙ አለባበስ ስነ ሥርዓትና ባህል ጀምሮ፤ መብትና ዲሞክራሲ ተብሎ ሰዶምን እስከመፈጸም ጀምሮ፡ ዓለማችን ዲሞክራሲ ብሎ እግዚአብሔርን የሚያስቆጡ፣ በሰዶም ዘመን ሰዶምና ገሞራ የተቀጡበትን ነገር ባህል ብሎ እንደ ቀላል ነገር ዓለም እየተቀበለው እንደሆነ እናያለን።
ወገኖች፡ ከህገ እግዚአብሔር ወጣ ባልን ቁጥር እግዚአብሔር ዓለምን ይቀጣል”
ድንቅ ትምህርት፥ ቃለ ሕይወት ያሰማልን!
______
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሃጢአት, መስከረም ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም, ስብከት, ቤተክርስቲያን, ቦሌ መድኃኔ ዓለም, አዲስ አበባ, ዘረኝነት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጥላቻ, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »