“ሃጂ” የተባለው የዓለማችን በጣም ቆሻሻው ሰው ለ60 ዓመታት ያህል አልታጠበም
ለ 80 ዓመቱ አረጋዊ ኢራናዊ ቆሻሻነቱ በጣም ያስደስተዋል። ለዚያም ነው ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ፈጽሞ ታጥቦ የማያውቀው። በደቡባዊ የኢራናውያን አንድ መንደር ውስጥ ብቻውን መቀመጥ ይወዳል።
ሃጂ ከውኃ ጋር ያለውን ግንኙነት ይጠላል። የመታጠብ ሀሳቡ ብቻ ሲነሳ በጣም ያናድደዋል።
የሃጂ ቆዳ የምድር ቀለም ይመስላል። ከአካባቢው ጋር ሙሉ በሙሉ ተደምሮ መኖር ችሏል። እንዲያውም ብዙ ከተቀመጠ ስለማይነቀናቅ ድንጋይን ወይም የዓለት ቅርፅን ይመስላል።
ሃጂ እምብዛም የማይታየው ገላ መታጠብ ብቻ አይደለም። ንጹሕ ምግብን እና ንጹሕ መጠጥን በጣም ይጸየፋቸዋል። በምትኩ ግን የሚወደው የበሰበሰና የገማ ስጋ ነው። ለጤንነት ሲል በቀን 5 ሊትር ያህል ውሃ ይጠጣል፥ ነገር ግን የነዳጅ ዘይት በነካው ጣሳ። በጥንባሆ ይልቅ የማጨሻ ቱቦውን በእንስሳት ፋንድያዎች በመሙላት ማጨስ ይወዳል። ፀጉሩን ለመቆርጥ መቀስን አይጠቀምም፤ በእሳት ነበልባል ላይ ያቃጥለዋል። በክረምት ወቅት በአሮጌ የጦርነት ቆብ ጭንቅላቱን ያሞቃል።
ሃጂ በእውነቱ ቤት የለውም ፤ ምድር የእርሱ መኖሪያ ናት። በመቃብር እንዳለ ሆን በዋሻ ውስጥ ይኖራል። አንዳንድ ጊዜ የመንደሩ ነዋሪዎች በሚሠሩት ክፍት የጡብ ጉድጓድ ውስጥ ይተኛል። በአካባቢው ነዋሪዎች “አሙ ሃጂ” ይባላል። «አሙ» በፋርስኛ ቋንቋ፡ አረጋዊ ደግ ሰው ማለት ነው።
የሃጂ የአኗኗር ዘይቤ በጣም ልዩ ነው። የመንደሩ ነዋሪዎች በወጣትነት ዕድሜው ከባድ የስሜት መጎሳቆል ደርሶበት እንደነበር ይናገራሉ። ይህም እነዚህን የከፉ ምርጫዎች እንዲፈጽም አድርጎታል። እንደዚያም ሆኖ በትላልቅ ቤቶች ውስጥ በምቾትና በመንደላቀቅ ከሚኖሩ ሰዎች ይልቅ ደስተኛ ይመስላል። ሃጂ ለዚህም አለም ግድ የለውም። ምንም የሚጎድልበት ነገር የለም፣ ምንም ፍርሃት የለውም።