Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

Posts Tagged ‘ሀወሃት’

ታቦተ ጽዮን ያለባትን ከተማ ነክተን ጠላት ሱዳን መጣብን ፥ ታዲያ ዛሬ የወልቃይት መሬት-አስመላሽ የት ገባ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 4, 2021

ወንድሞቻችን ላይ ሲሆንና ወገንህን ለማጥቃት ምላስህ ንግግርህ ረጅም፣ እጅህ ረጅም፣ እግርህ ረጅም! እስኪ አሁን በትግራይ ላይ ያሳየኸውን ወኔህን በሱዳን ላይ አሳየን! አዎ! ለወገኖቻችን፣ ለወንድሞቻችን አልሆንም፤ ለዛም ነው ጠላት የደፈረን!

ደርግ የአፄ ኃይለ ሥላሴን ጄነራሎች፣ መኳንንትና ወታደሮችን ጨፈጨፈ ፥ ለአይጧ ሶማሊያ ወረራ ተጋለጥን፤ ዛሬ ደግሞ ግራኝ አህመድ ዳግማዊና ደርግ 2.0 በአንድ ላይ ሆነው የወያኔን ጄነራሎችና ሠራተኞች ሁሉ ከስልጣን አባርረውና በውጭ ሠራዊታት እየተደገፉ የትግራይን ሰራዊትን ሲያዳክም፤ የተረፉትን ሃሞት ያላቸውን ትግሬ ኢትዮጵያውያንን ሲያርቅና ሲያግልል፤ እባቦቹ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሱዳን፣ ግብጽ፣ ቀጥሎም ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ እና ኬኒያ ከእነ አልሸባብ፣ አይሲስ እና አልቀይዳ ያለምንም ተቃውሞ ሰተት ብለው ለመግባት በመዘጋጀት ላይ ናቸው።

በሱዳን መተት የተያዘው ወገናችን ግን ይህን እያየ እንኳን በግራኝ አብዮት አህመድ ላይ ለመዝመት ከመነሳሳት ተቆጥቧል። ምክኒያቱ? ለኑሮው ሁሉ ትርጉም የሚሰጠው በትግሬ ወንድሞቹ ላይ ያለው ጥላቻ ብቻ ስለሆነ ነው። ሰነፍ ሁላ!

አሁን ተገላልጦ የወጣው ጥላቻ በህወሃት ላይ ብቻ እንዳልሆነ ነግሮናል፤ ጥላቻው በመላው የትግራይ ሕዝብ ላይ ነው ፤ ይህ ደግሞ አሁን የተከሰተ ነገር አይደለም፤ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት በተለይ ከአድዋው ድል በኋላ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚታይ የጥላቻ እንቅስቃሴ በሁሉም የፖለቲካ፣ የማሕበረሰባዊ፣ የምጣኔ ሃብታዊ ብሎም የመንፈሳዊ ህይወት ይታያል። ዋናው ጥያቄ ከምን የመጣ ነው?

መልሱ አንድ እና አንድ ነው፤ በሃገራችን ትክክለኛውን ኢትዮጵያዊነትን፣ ጥልቅ መንፈሳዊነትንና ሃሞት ያለው ወኔን ይዘው የቆዩት ትግሬ ኢትዮጵያውያን፤ ምናልባትም በላስታና ላሊበላ አካባቢ የሚገኙት የቤተአምሐራ ኢትዮጵያውያን ብቻ ስለሆኑ ነው። ለዘመናት፡ በረሃቡም፣ በበሽታውም በጦርነቱም ክፉኛ እየተጠቁ ያሉት እነዚህ አካባቢዎች ናቸው፤ የሁሉም ሉሲፈራውያን አትኩሮት በአኩስም እና ላሊበላ ላይ ነው፣ ከዚህ አካባቢ በተገኙት በእነ አፄ አምደ ፅዮን፣ አፄ ዮሐንስ ፥ ዛሬም በእነ ጄነራሎች አሳምነውና ሰዓረ እንዲሁም አቶ ልደቱ አያሌው ላይ የተደረገውና እየተደረገ ያለው ጥቃት የሚሰነዘረው የክስተቱን ጥልቅ መንፍሳዊ ልኬት ይጠቁመናል።

ስለዚህ አሁን በሰነፉትና በተዳከሙት ኢትዮጵያውያን ላይ እየታዩ ያሉት እንደ ቅናት፣ ምቀኝነትና አድመኛነት የመሳሰሉ በጣም አደገኛና ገዳይ የሆኑ የሰው ልጅ ባሕርያት ወደ ጥላቻ ስለሚወስዱን ፣ የተመሰቃቀለ፣ አከፊና መከራ የበዛበት መራራ ኑሮን ለመኖር እንገደዳለን ማለት ነው።

[የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ ፫፥፲፮]

ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።”

[የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፪፡፫]

ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤ ትለምናላችሁ፥ በምቾቶቻችሁም ትከፍሉ ዘንድ በክፉ ትለምናላችሁና አትቀበሉም።”

[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]

ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፳፡፩፥፳፫]

ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።”

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የአህዛብ ግራኝ አህመድ እና አፈቆርኪ ሠራዊት የመቀሌ ነዋሪዎችን በሽብር ሲያሳድዳቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 23, 2020

👉 ፕሮጀክት ኦሮሙማ የሰሜን ግንባር

ስልጣን ላይ ለሃያ ሰባት ዓመታት ያህል የነበሩትና በሃገረ ኢትዮጵያ ሁሉንም ነገር ከመቆጣጠርም ተርፈው በመላዋ አፍሪቃ በጸጥታ አስከባሪነት ተሰማርተው የነበሩት ህወሀቶች “ህዝቤ” የሚሉትን ምስኪን ኢትዮጵያዊ እንዴት ዛሬ ሊከላከሉት አልቻሉም? በእጃቸው የነበረውን መሳሪያ ሁሉ፣ ታንኩንም ተዋጊውንም ለአህዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች እንዲሁ በቀላሉ አስረክበው እንዴት ወደ መቀሌ ሊያመሩ ቻሉ? ለአስተማሯቸው ላሰለጠኗቸው ለእነ ግራኝ አብዮት አህመድ እንዲሁ በቀላሉ ባስረከቧቸው መሳሪያዎች እኮ ነው የትግራይ ህዝብ ዛሬ እየተጨፈጨፈ ያለው! በየትኛዋ የዓለማችን ሃገር ነው እንዲህ ያለ ሃላፊነት የጎደለው የስልጣን ሽግግር ተካሂዶ የሚያውቀው? እኔ አላውቅም!

___________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: