Archive for the ‘Love’ Category
ልዩነት ውበት መሆኑን ቤተክርስቲያን ብቻ ነች የምታሳየው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 20, 2019
Posted in Ethiopia, Faith, Life, Love | Tagged: ልዩነት, ሰላም, ቤተክርስቲያን, አንድነት, አዲስ አበባ, እርግቦች, ዘር, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጎሣዎች, ፍቅር, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
እግዚሐርአብ-ሰርግ-እርግብ = ሰእርግብ | ቅዱስ ጋብቻ በተዋሕዶ ብቻ እንደሚገኝ እርግቦቹ መሠከሩ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 21, 2019
ይህን ባየንበት ወቅት የሁላችንም እምባ መጥቶ ነበር። ዛሬ ማክሰኞ ነው፤ እግዚአብሔር፦ የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፦ ሕያው ነፍስ ላለውም ሁሉ ስም ያወጣላቸው ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። እግዚአብሔር ሰኞ ማክሰኞ አዕዋፋትን አመጣለት፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበርና አጭቶ፥ ወድዶ፥ ፈቅዶ እንዲገባበት ሔዋንን ከጎኑ አንዲት አጥንት ወስዶ ሴት አድርጎ ሠራለት። አዳምም፦ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” ብሎ እግዚአብሔር የሰጠውን በጸጋ ተቀበለ።
አዳምና ሔዋን በጋብቻ አንድ አካል መሆናቸው፦ ሔዋን ከአዳም የጎን አጥንት በመፈጠሯ ብቻ አይደለም። አንድ ክብር በመውረስም ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፦ “እናንተ ባሎች ሆይ ፥ ደካማ ፍጥረት ስለሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድረጋችሁ አክብሩ አቸው።” ያለው ለዚህ ነው። ፩ኛ ጴጥ ፫፥፯። ከዚህም ሌላ አንድነታቸው አንድ ልብስ በመልበስ ነው። ፈቃደ ሥጋቸው በጠ የቃቸው ጊዜም በግብር አንድ ይሆናሉ። ወንድ ቢወለድ ያንተ ነው፥ ሴት ብትወለድ ያንቺ ነው አይባባሉም። ሁለት ሆነው አንድ ልጅ ያስገኛሉ። አንድም፦ ከእናት ደም ፥ ከአባት ዘር ተከፍሎ አንድ ሰው ሁኖ ይወለዳል።
የጋብቻ ዓላማዎች ሦሰት ናቸው፦
የመጀመሪያው። “የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት” እንዲል፦ ለመረዳዳት ነው። መረዳዳት ሲባልም በሥጋ ብቻ አይደለም በነፍስም ጭምር ነው። ለሥጋቸው በሥራ ሲረዳዱ ለነፍሳችው ደግሞ በጸሎት ይረዳዳሉ። ለምሳሌ፦ ይስሐቅ፦ ሚስቱ ርብቃ ለሃያ ዓመታት መክና ልጅ አልወለደችለትም ነበር። በዚህም ምክንያት ስለ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ፥ እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም መንታ ፀነሰች ይላል። ዘፍ ፳፭ ፥፳፩። ሁለተኛው በፍትወተ ሥጋ ላለመቸገር ነው። ሦስተኛው ደግሞ፦ “ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው ፥እግዚአብሔርም ባረካቸው ፥እንዲህም አላቸው፦ ብዙ ተባዙ ፥ምድርንም ሙሉአት።” እንዲል፦ ዘር ለመተካት ነው። ዘፍ ፩፥፳፰። እነዚህም እንደ ሦስት ጉልቻዎች የሚቆጠሩ ናቸው።
አዎ! እግዚአብሔርን ስንቀርበው ፥ ይቀርበናል፤ ስንረቀው ይርቀናል። እግዚአብሔርን በቀረቡ ተዋሕዶዎች ዘንድ ፩ + ፩ = ፩ ሲሆኑ እግዚአብሔርን በራቁት በሌሎች ዘንድ ግን ፩ + ፩ = ፪ ናቸው። ስለዚህ ቅዱስ ጋብቻ በሌሎች ዘንድ የለም ለማለት ያስደፍራል…በሌሎች ዘንድ ሁሉም ነገር ሂሳብ ነው፡ ዓለማዊ ነው፤ ከጋብቻ በፊት “መልአክ” የተባለ የትዳር ጓደኛ ከጋብቻ በኋላ “ሰይጣን” ይባላል። በመላው ዓለም እንደምናየው ወንዱ ወንድነቱን ሴቷ ሴትነቷን በማጣት ፍቅር–አልቦች፣ አመጸኞች እና ጨካኞች ለልጆቻቸው ነፍስ የማይቆረቆሩ ግድ–የለሾች ይሆናሉ፤ ትዳራቸውም የሲዖል ነው። ይህ ክስተት ዛሬ “ለዘብተኞች”፣ “ፌሚኒስቶች” ፣ “ሰዶማውያን”፣ “መሀመዳውያን” በሚባሉት ዘንድ በደንብ እየተንጸባረቀ ይታያል።
ኢትዮጲያዊ ሲፋቀር አቤት ሲያምር ፥ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ጎዳና ሲራመዱ ሁሉም መዋደዱ! የምንጓዝበት መንገድ መንፈሳዊ ከሆነ በሁሉም በኩል ሰላም፣ ፍቅር፣ ብልጽግና እና ደስታ ሲነግሱ እናያለን፤ እርግቦቹ (መንፈስ ቅዱስ) እንደሚያሳዩን።
ታላቋ አገራችን ከተዋሕዶ ውጭ የሚገኙትን ትርኪምርኪ መጤ የምዕራባውያንን (ዔሳው)እና የአርቦችን(እስማኤል)አምልኮቶችን፣ ርዕዮተ-ዓለሞችንና ባሕሎችን አስገብታ መቀበል ስትጀምር ነው ፍቅር እየቀዘቀዘ፣ ሰላም እየጠፋባት፣ እንስሳቱ፣ አራዊቱ እና አዕዋፋት እየራቁባት፣ ድርቅ፣ ረሃብ እና በሽታ እየሰፈኑባት፤ ባጠቃላይ እያነሰችና እየወደቀች የመጣችው።
__________________
Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: መስከረም ፪ሺ፲፩, መንፈስ ቅዱስ, ሥርዓተ-ተክሊል, ቅኔ, ትዳር, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, እርግቦች, እግዚአብሔር አብ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጋብቻ, ፍቅር, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
ሙሽሪት ኢትዮጵያ ጠላትሽ ይንቀጥቀጥ ይሁን እያሪኮ፤ በነገድ በዘርም የእልፍነሽ አንቺኮ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2019
[ወደ ኤፌሶን ሰዎች ፭፥፲፱]
“በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ”
__________________
Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: መስከረም ፪ሺ፲፩, ሥርዓተ-ተክሊል, ቅኔ, ትዳር, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, እግዚአብሔር አብ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጋብቻ, ፍቅር, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
If You Love Something, Love it Completely, Cherish it, Say it, But Most Importantly, Show it.
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 14, 2019
_________
Posted in Love | Tagged: Heart, Life, Love | Leave a Comment »
የቅዱስ ሚካኤል ልጆች ሰርግ | ክርስቶስ ኢየሱስ በጋብቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኝልህ ጥራው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2018
እንኳን ለኅዳር ሚካኤል አደረሰን!
ሰርግ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ጳውሎስ ለቈላስይስ ሰዎች በላከው መልእክት ም.፬፥፲፪ ላይ ያለውን ኃይለ ቃል በተረጎመበት ፲፪ኛው ድርሳኑ በዘመኑ የሚፈጸመውን የሰርግ ሥርዐት መሠረት በማድረግ ሰርግን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ትምህርትን ሰጥቶአል ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሰርግ ምክንያት የሚወጡትን ወጪዎችና ግርግርና ሁካታ አጥብቆ የሚቃወም አባት ነው። በዚህም ጽሑፍ ይህን ወደማስተዋል ልንመጣም እንችላልን ። መልካም ንባብ!
ስለዚህ እንዲህ ብሎ ያስተምራል ፡– ትዳር ምንድን ነው? ትዕይንት(ትያትር) ነውን ? አይደለም። ምንም እንኳ እናንተ ለትዳርና ለምሳሌው አክብሮት ባይኖራችሁ ትዳር ግሩም ምሥጢርና የታላቅ መንፈሳዊ ምሥጢር ምሳሌ ነው ። ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ሲያስተምር “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው” ይልና ጨምሮ “እኔ ግን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ” ይላል። (ኤፌ.፭፥፴፪) ጋብቻ የቤተ ክርስቲያንና የክርስቶስ ምሳሌ ነው ፤ እንዲህ በከበረ ምሥጢር ላይ ዳንኪረኞችን በመጋበዝ ዝሙትን ታስተዋውቁበታላችሁን ? ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዱ እኔን፡– እንዲህ ስትል ደናግል ወይም ያገቡት አይጨፍሩ እያልክ ነው ፤ እንግዲያ እነርሱ በዚህ ሰርግ ላይ ካልጨፈሩ ማን ሊጨፍር ነው ? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ። ማንም አይጨፍር ነው መልሴ።
በአሕዛብ ዘንድ ይህን በመሰሉ ሥርዐቶቻቸው ዳንኪረኞች ዳንኪራቸውን ያቀርባሉ። በእኛ ግን ማንኛውም ምሥጢራት ሲከናወኑ በጸጥታ፣ በትሕትናና በጥሩ ሥነምግባር እንዲሁም በመልካም ሥርዐት ነው። ይህ የጋብቻ ሥርዐት አመንዝሮች ከተጠሩበት እግዚብሔርን የማይፈሩ ከተጋበዙበት እንዴት ብለን ነው መንፈሳዊ ጋብቻ ብለን ልንጠራው የምንችለው ? እንዲህ ከሆነ እንዴት ተብሎ ነው ሁለቱ አካላት አንድ ሆነዋል ልንል የምንችለው ?
ክርስቶስ በተገኘበት ጋብቻ ግን ዳንኪራ የለም የእምቢልታም ድምፅ አይሰማበትም። ነገር ግን ግሩም የሆነ ጸጥታ የሰፈነበት፣ በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዐት የሚከናወን ነው። በዚህ ሥርዐት አንድ አካል ወደመሆን ሲመጡ አንድነታቸው ሕይወት አልባ ፍጥረታት እንደሚኖራቸው አንድነት ወይም በዚህ ምድር የሚታየውን ዓይነት አንድነት አይደለም። ነገር ግን የእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ሆነው አንድ ይሆናሉ። ይህ ታላቅ የሆነ ምሥጢር በሚከናወንበት ሥፍራ እንደ አራዊት ታላቅ ሁካታና ረብሻ እንዲሁም ነፍስን የሚያሳድፉ ታላቅ የሆነ በደል ይፈጸማልን?
ሁለቱ አንድ አካል በመሆናቸው በዚህ ያለውን የፍቅርን ምሥጢር አስተውል። እነዚህ ሁለት አካላት ሁለትነታቸውን ይዘው የሚቀጥሉ ከሆነ ብዙ ሊሆኑ አይችሉም። ነገር ግን አንድ ወደመሆን ሲመጡ ብዙዎች ይሆናሉ። ከዚህ ምን እንማራለን ? የትዳርን ታላቅነት አይደለምን ? ሥላሴ ሁለት የሆነው አካል አንድ አድርጎ ፈጠረው ስሙንም ሰው አለው። ይህን አንድ የሆነው አካልንም ሁለት በማድረግ ገለጠው ። ምንም እንኳ እነዚህ አካላት ሁለት ቢሆኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ ግን አንድ ይሆኑ ዘንድ ነበር ።
በዚህም ምክንያት አንዱ አምሳሉን ለመውለድ ብቻውን ብቁ እንዲሆን አላደረገውም ። ስለዚህ ከተቃራኒው አካል ጋር አንድነትን ላልመሠረተ ሰው አንድ አካል የሚባለው ስያሜው አይሰጠውም ነገር ግን የሌላኛው ግማሽ አካል ይባላል። ለዚህም ምስክሩ ልጅን መውለድ አለመቻሉ ነው። ይህ እግዚአብሔር አስቀድሞ የሠራው ሥርዐት ነው። የጋብቻን ምሥጢር አስተዋላችሁን ? አስቀድሞ አንድ አድርጎ ፈጠራቸው በኋላም ነጣጠላቸው ፤ እንደገና ሁለት የነበሩትን እነዚህን ወገኖች ወደ አንድነት አመጣቸው ። እንዲህም አድርጎ ስለሠራው ሰው በትዳር አንድ ከሆኑ ወገኖች እንዲፈጠር ሆነ ።
ባልና ሚስት ሁለት አካላት አይደሉም ነገር ግን አንድ አካል ናቸው ።…. ይህን “ሰውን በአርዓያችንና በአምሳላችን እንፍጠር …ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ.1፡27) በሚለው ቃል ማረጋገጥ ይቻላል። ባል ራስ ነው ፤ ሚስት ደግሞ ቀሪው አካል ናት ። ስለዚህ አንዱ የደቀመዝሙርነት ማዕረግ ሲኖረው አንዱ የመምህርነት ቦታ ይይዛል አንዱ መሪ ሲሆን ሌላው ደግሞ ታዛዥ አደረገው። ሔዋን ከአዳም ጎን ትገኝ እንጂ ወደ ኋላ መለስ ብለን የእርሱዋን ልደት ስንመረምረው አንድ አካል እንደነበሩ ማስተዋል እንችላለን። በዚህ ምክንያት አንድ አካል እንደሆኑ ለማስረዳት ሲል እግዚአብሔር አምላክ ሴቲቱን ረዳት አላት። (ዘፍ.2፡18) በአንድነት ከመኖራቸውና አባትና እናት ከመሆን ባለፈ አንድ አካል በማድረግ አከበራቸው። (ዘፍ.2፡24)
በሌላ መልኩ ደግሞ አባት ወንድ ልጁ ወይም ሴት ልጁ የራሳቸውን አካል አግኝተው በመጣመራቸው እጅግ ደስ ይሰኛል። አባት ምንም ሀብት የተረፈው ባለጠጋ ቢሆን ወንድ ልጁ ወይም ሴት ልጁ ያላገቡ ከሆኑ ውስጡ ምንም ዓይነት መረጋጋት አይኖረውም። ይህን ታግሶ መኖርም አይቻለውም። በሌላ በኩል ደግሞ ምንም ልጅ ከእናቱ አካል ተከፍሎ የተወለደ ቢሆን በዚህ ምድር ዘሩ እንዲቀጥል ብቻውን በቂ አይደለም። ስለዚህም በራሱ ሙሉ አይደለም ማለት ነው። ስለዚህም ነቢዩ ሚልክያስ “እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድን ነው? ዘር አይደለምን? (ሚል.፪፥፲፭) ይለናል።
እንዴት ነው ታዲያ አንድ ሥጋ ወደ መሆን የሚመጡት? እጅግ ንጹሕ የሆነን ወርቅን ማግኘት ከፈለግህ ወርቅህን ከሌላ ወርቅ ጋር ትቀይጠዋለህ፤ ከእነዚህም አንድነት ልዩ የሆነ ወርቅ ይገኛል። በዚሁ መልክ እናት በደስታ ዘርን ተቀብላ ከራሱዋ ጋር በማዋሐድ፣ ፅንሱን በመመገብና እንክብካቤ በማድረግ ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም እንዲመጣ የራሱዋን ድርሻ ትወጣለች።ልጅ እንደ ድልድይ ነው ። በእርሱም ምክንያት ሦስቱ አንድ ሥጋ ይባላሉ ። ልጅ ሁለቱ አካላት ፍጹም አንድ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ። በመካከላቸው ባለው ታላቅ ወንዝ ምክንያት የተለያዩ ከተሞች በወንዙ ላይ በሚሠራው ድልድይ ምክንያት ሁለት መሆናቸው ቀርቶ አንድ እንዲሆኑ እንዲሁም ልጅም እንዲህ ነው ።
ልጅ በፊት በባልና በሚስት መካከል የተፈጠረውን አንድነት ይበልጥ ያጠናክረዋል። ለባልና ሚስት ድልድይ የሆነው ልጅ የሁለቱ ተዋሕዶ ውጤት ነውና ። ራስና ቀሪው አካል በአንገት አንድ እንዲሆን ፣ እንዲሁ ልጅም በባልና በሚስት መካከል ሆኖ በእነርሱ መካከል ያለውን አንድነት ይበልጥ ያጠብቀዋል ። ከልዩነታቸው ይልቅ አንድነታቸውን በልጅ ምክንያት ይበልጥ እየጠበቀ ይመጣል ።
እንዲሁም ዘማርያን በአንድነት ሲዘምሩ ዝማሬው አንድ ሆኖ ይወጣል። ወይም ሁለት ወገኖች እጃቸውን እርስ በእርሳቸው ቢያቆላልፉ ከእንግዲህ አንድ እንጂ ሁለት አይደለንም ማለታቸው እንደሆነ እንዲሁ ባልና ሚስትም በአንድነታቸው በሚፈጠሩት በልጅ በኩል ፍጹም የሆነ አንድነትን ይመሠርታሉ ። ስለዚህ ጌታችን ግሩም በሆነ ቃሉ “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ አለ” በተለይ በልጆቻቸው። እንዲህ ሲባል ባልና ሚስት ልጅ ካልወለዱ ሁለት እንደሆኑ አይቀጥሉም ማለት ነውን ? በፍጹም አይደለም ፤ ሁለቱ በሥጋ ሲተባበሩ አንድ አካል ወደ መሆን ይመጣሉ ። የሽቶ ዘይትን ከሌላ የሽቶ ዘይት ጋር ሲደባልቁት አንድ እንዲሆኑ ከተቀየጡም በኋላ አንድ የሽቶ ዘይት እንዲሆኑ እንዲሁ በዚህም እንዲሁ ነው ።
እኔ አሁን እንዲህ በግልጽ ስለዚህ ጉዳይ በመናገሬ አንዳንዶች ነውር ነው በማለት ትምህርቴን እንደሚጠየፉት እረዳለሁ። ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው? ይህን አሁን የምናገረውን እንደ ብልግና ንግግር ስለሚቆጥሩት ነው። እነዚህ ወገኖች በትዳር ውስጥ የሚፈጠረውን እንደዚህ ላለው አንድነት ልዩ የነቀፋ ስም ይሰጡታል (ብልግና ይሉታል)። ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን”(ዕብ.፲፫፥፬) ብሎ አስተምሮናል።
ስለምን እናንተ ክቡር የሆነውን እንደ ነውር ፣ ንጹሕ የሆነውን እንደ ርኩስ ትቆጥሩታላችሁ ? ይህ ጋብቻን እንደ ርኩሰት የሚቆጥሩትና በራሳቸው አካል ላይ ዝሙትን የሚፈጽሙ የከሃድያን አመለካከት ነው። ስለዚህም ነው ይህን ክፉ አስተሳሰብ ለማጥራትና ወደ ቀድሞው ክብሩ ለመመለስ ስል በዚህ መልክ ያስተማርኩት። በዚህም እስተምህሮ የከሃድያን አፍ ይዘጋል።
እነርሱ የእግዚአብሔርን ድንቅ ስጦታንና የልደታችን መሠረት የሆነውን ተራክቦን ሲነቅፉት ይሰማሉ።
ይህን የመገኛችን ምንጭ የሆነውን ተራክቦ እንደ ቆሻሻና እንደማይጠቅም ረብ የለሽ ከንቱ ነገር አድርገው ይቆጥሩታል። ስለዚህ እኛ ይህን አስተምህሮ ከዚህ ዓይነት አመለካከት ንጹሕ ልናደርገው ይገባናል።ተወዳጆች ሆይ ይህ ጉዳይ ሲነሣ እንደሚጠየፉት ከሃዲያን እንድንሆን አልሻም፤ ይልቁንስ ከእነርሱ አጸያፊ ሥራ ትሸሹ ዘንድ እመክራችኋለሁ። ነገር ግን በዚህ እነርሱን የምትመስሉዋቸው ከሆነ በቀጥታ እግዚአብሔርን እየተሳደባችሁ ነው።
ትዳር ለቤተ ክርስቲያን የተፈጸመላት ምሥጢር ምሳሌ እንደሆነ ላስረዳችሁን? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የራሱ ሲያደርጋትና በመንፈሳዊ ተዋሕዶ ከእርሱዋ ጋር አንድ ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ “እንደ ንጽሕት ድንግል” ይልና “እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለውና” ይለናል። (፪ቆሮ.፲፪፥፪) ታዲያ እኛ ምን ሆንን? የእርሱ የአካል ሕዋሳቶችና “ሥጋው” ሆንን። ይህን ሁሉ በማስተዋል ታላቅ ምሥጢር የሆነውን ትዳርን ከማቃለል እንቆጠብ። ሰርግ ማለት የክርስቶስ በሰዎች መካከል ሰለመገኘቱ የሚመሰልበት ታላቅ ምሥጢር ነው። ታላቅ የሆነው ይህ ምሥጢር በሚፈጸምበት ቦታ ስካር የሚገባ ነውን? ንገረኝ የንጉሥ ምስል በቆመበት ስፍራ ሆነህ እርሱን ማዋረድ ትጀምራለህን? ይህን ፈጽሞ አታደርገውም።
አሁን ግን ሰርግ ሲሲረግ ሰርጉ ለተመሰለበት ምሳሌ ተገቢውን አክብሮት ከመስጠት ይልቅ ቦታውን የኃጢአት መፍለቂያ ምንጭ አድርገነዋል። ሥርዐቱ ሙሉ ለሙሉ ተለውጦ ሕገወጥ ሥራዎች የሚፈጸሙት ሥርዐት ሆኗል። ቅዱስ ጳውሎስ “የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸው” አላለንምን? እንዲሁም “ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።” (ኤፌ.፭፥፬፤፬፥፳፱) ብሎ አላስተማረንምን? አሁን ግን በዚህ ታላቅ በሆነ ምሥጢር ላይ የስንፍና ንግግር፣ ዋዛ ፈዛዛ ነገሮች፣ ፌዝና ቀልዶች ሞልተውበታል።
እነዚህ ከንቱ ነገሮች በቀላሉ የሚቀርቡም አይደሉም እኮ እነዚህ ከንቱ ነገሮች እንደ ጥበብ ተቆጥረው በአቅራቢዎቻቸው ተቀናብረው በሰርጉ ለታደሙት ይቀርባሉ። ይህንንም ለሚያቀርቡ ሰዎችም ታላቅ ክብርና ምስጋና ይሰጣቸዋል። ይገርማል ኃጢአት እንደ ጥበብ ተቆጠረ። ከዚህም በላይ ኃጢአትን ለእኛ የሚያስተዋውቁንን ወገኖች ትዕይንት የምንከታተለው ትኩረት ሰጥተንና በጸጥታ ነው፤ ከአንደበታቸው የሚያወጡትንም ቃል በአጽንዖት በመስማት ጭምር እንጂ እንዲያው በከንቱ አናዳምጣቸውም። ስለዚህ ዲያብሎስ በዚህ የሰርግ ቤት ለእርሱ ወታደሮች ይሆኑ ዘንድ ሠራዊቶችን ይመለምላል። ስካር ባለበት ቦታ ዝሙት አለ። ከንቱ ንግግር ባለበት ቦታ ሰይጣን የራሱን አስተዋጽኦ ለማድረግ ይመቸዋል። እስቲ ንገረኝ እንዲህ በሆነ ቦታ ሰይጣን እንዲገኝ እየጋበዝህ ክርስቶስ የሚገኝበትን ምሥጢር እየፈጸምኩ ነው ትላለህን?
አንተ እኔን ለዚህ ነገር ጠንካራ ተቃዋሚ እንደሆንኩ አድርገህ ትቆጥረኛለህ። ከዚህ ጥመትህ ትድን ዘንድ አንተን በጽኑ የሚገሥጽህንም ሰው እንዲህ እንድትመለከተው አውቃለሁ። ቅዱስ ጳውሎስ አንተን “የምትበሉም የምትጠጡም ብትሆኑ ወይም ማናቸውም ተግባር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት”(፩ቆሮ.፲፥፴፩) አላለህምን ? አንተ ግን ሥራዎችህን ሁሉን ራስህን ለማዋረድና የሰውን ልጅ ለሚጎዱ ነገሮች ታውላዋለህ ። ነቢዩስ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ በረዓድም ደስ ይበላችሁ”(መዝ.፪፥፲፩) አላለህምን ? አንተ ግን ሥርዐት አልባ ሆነህ ትመላለሳለህ ።
በአንድ ጊዜ ደስታውንና ጥንቃቄውንም ማስኬድ ትፈልጋላችሁን? አጥንትን የሚያለመልም መዝሙርን መስማትስ ትሻላችሁን? በእርግጥ ከመዝሙሮች ሁሉ የሚልቅ መዝሙርን ልትሰሙ ትችላላችሁ። እናንተ ግን አትፈቅዱም፤ ብትፈቅዱ ግን ሰይጣናዊ ዘፈኖች ከመስማት ይልቅ መንፈሳዊ ዝማሬን ለመስማት ትበቃላችሁ። የመዘምራንን ግሩም የሆነ መጓደድ መመልከት ትሻላችሁ? እነሆ የመላእክት ዝማሬና መጓደድ። እንዴት ሆኖ ነው የእነርሱን ዝማሬን መስማት በልዑል ፊት መጓደዳቸው መመልከት የሚቻለው ብሎ የሚጠይቀኝ ካለ “እነዚህን ግሳንግሶችን ከነአካቴው ከተውክና በሰርግህ ክርስቶስ እንዲገኝ ከፈቀድክ ይህ ይሆናል። ክርስቶስ በሰርግህ የታደመ ከሆነ መላእክትም ከእርሱ ጋር በሰርግህ ይገኙልሃል።
ከአንተ ዘንድ ፈቃዱ ካለ እርሱ በአንተ ሰርግ መገኘት ብቻ አይደለም ውኃውን ወደ ወይን ጠጅነት በመቀየርም ሰርግህን ያደምቅልሃል። እንደ ውኃ ቀዝቃዛና ወራጅ የሆነውን የዚህን ዓለም ደስታና ፈንጠዝያ አጥፍቶ መንፈሳዊ ደስታን ከሚያጎናጽፈው ከዚህ ተአምር በላይ ምን ድንቅ ተአምር አለ!! ይህ ነው ውኃውን ወደ ወይንነት የመቀየሩ ትርጉም። እንቢልታ ነፊዎች ባሉበት ክርስቶስ ፈጽሞ አይገኝም። እርሱ በዚህ ሰርግ ቢገኝ እንኳ መጀመሪያ ይህንን አስወግዶ ነው። ከዚያም የራሱን ተአምርን ይፈጽማል። ከዚህ የሰይጣን መሳሪያ ከሆነ እቢልታ በላይ ምን የሚጠላ ነገር አለ? ሁሉ በሥርዐት ካልሆነ ምንም ነገር ያለጥቅም ይሆናል። ድካማችን ሁሉ ያለፍሬ ይቀራል እኛንም ወደ ውርደት ይጥለናል።
ከመልካም ሥነምግባር የበለጠ አስደሳች ነገር የለም፣ ሥርዐት ወዳድ ከመሆን የበለጠ ጣፋጭ የሆነ ነገር የለም፣ ጽድቅ ለመፈጸም ቆራጥ ከመሆን የበለጠ ተወዳጅ ነገር የለም። ሁሉም ሥርዐቶቻችን ልክ እኔ ስለጋብቻ ሥነ ሥርዐት ባስተማርኩት መልክ ይሁኑ። እንዲህ ከሆነ ደስተኛ ልንሆን እንችላለን።
ነገር ግን ጋብቻን ሊያደርግ የሚሻ ሰው ከማን ጋር ጋብቻውን መፈጸም እንዳለበት ይጠንቀቅ። ሴት ልጅ ያለችው ሰው አስቀድሞ እውነተኛና እርሱዋን ሊንከባከባት የሚችል ባልን ሊፈልግላት ይገባል። እንዲህ ዓይነት ወንድ ለአካል ራስ እንዲሆን ሊመረጥ ይገባዋል። ለእርሱ ስትሰጥም እንደ ባሪያ አድርጎ ሊይዛት ሳይሆን እንደ ልጁ ሊያያት ሊሆን ይገባል።
ሀብት ስላለው ወይም ከከበረ ቤተሰብ በመሆኑ ወይም ሰፊ ግዛት ስላለው እርሱን ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ አትምረጡ። ነገር ግን በነፍሱ ትሑት፣ አስተዋይ፣ ቅንነት ያለውና እግዚአብሔርን የሚፈራ የሆነን ሰው ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ ምረጡ። እንዲህ ከሆነ የምታፈቅሩዋት ልጃችሁ በደስታ ልትኖር ትችላለች። ባለጠጋ ሆኖ በምግባሩ ግን ብልሹ የሆነን ሰው ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ ያጫችሁት ከሆነ እርሱዋን አለመጥቀማችሁ ብቻ ሳይሆን እርሱዋን ነጻ ሰው ከማድረግ ይልቅ የእርሱ ባሪያ በማድረግ ትጎዱአታላችሁ። ልጃችሁ የእርሱ ሚስት በመሆኑዋ ምክንያት በምታገኛቸው ሀብት ደስ ከመሰኘት ይልቅ እርሱዋን እንደ ባሪያ ቆጥሮ በእርሱዋ ላይ የሚያደርስባት በደል የከፋ ይሆናል።
እንዲህ ዓይነት ድርጊትን ከመፈጸም ትቆጠቡ ዘንድ እለምናችኋለሁ። ነገር ግን ከእርሱዋ ጋር ተቀራራቢ ኑሮ ያለውን ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ ታጩ ዘንድ እመክራችኋለሁ። ይህ ባይሆን ምንም ሀብት ለሌለው ነገር ግን በጎ ሕሊና ላለው ሰው ትድሩዋት ዘንድ አሳስባችኋለሁ። እንዲህ በማድረጋችሁ ልጃችሁን ሌላው ቢቀር ለአንድ ጌታ ልጃችሁን እንደባሪያ ከመሸጥ ተቆጥባችሁ በትክክለኛው ትርጉም እንደ ባል ሊሆናት ለሚችል ሰው መስጠት ይቻላችኋል ።
ለልጅህ ባል የሚሆናትን ጥሩ ሥነ ምግባር የተላበሰውን ሰው በጥንቃቄ መርምረህ በማግኘት ልትድራት ስትዘጋጅ ክርስቶስ ኢየሱስ በጋብቻው ሥነ ሥርዐት ላይ እንዲገኝልህ ጥራው። በዚህ የደስታ ቀንህ እርሱን በእንግድነት እንዲገኝ ስለጋበዝከው ቅር አይሰኝም። ምክንያቱም እርሱ የሚገኝበት ምሥጢር ነውና። አዎን ከዚሀ ይልቅ ግን አስቀድመህ ለልጅህ ባል አድርገህ ያጨኸውን ሰው እርሱ እግዚአብሔር ተወዳጅ ባል ያደርገው ዘንድ ለምነው።
የአብርሃም ባሪያ እንኳ ያላደረገውን አስከፊ ድርጊት ከማድረግ ግን ራስህን ጠብቅ። እርሱ በጌታው በአብርሃም በተላከ ጊዜ እግዚአብሔርን መንገዱን ያቀናለት ዘንድ ለምኖት ነበር። እንዲህ በማድረጉም ሁሉን ነገር ሰመረለት። እንዲሁ አንተም ለልጅህ ባልን በመፈለግ አእምሮ ቢባክን ወደ እግዚአብሔር “ጌታ ሆይ አንተ የፈቀድከውን አድርግ” ብለህ ጸልይ። ለእርሱን እንዲህ በማለት ፈቃድህን አሳልፈህ ስጠው። በዚህ መልክ ለእርሱ ክብርን ስጥ፤ እርሱም በምላሹ ፈቃድህን በመፈጸም ያከብርሃል። በእርግጥ አንተን ሁለት ሥራዎች ይጠብቁሃል። እነርሱም ፈቃድህን ለእርሱ ሙሉ ለሙሉ መስጠትና፣ እርሱ የመሰከረለትን በጥሩ ሥነ ምግባር የታነጸውን ሰው መሻት ናቸው።
የልጅህን ሰርግ ለመሰረግ በምትዘጋጅበትም ጊዜ እቃዎችንና ልብሶችን ለመዋስ ስትል ቤት ለቤት አትዙር። ምክንያቱም ሰርጉ የሚፈጸመው ትዕይንትን ልታቀርብ ወይም የልጅህን ቁንጅና ልታሳይበት አይደለምና። በመሆኑም ሰርግህን ልትፈጽም በምትዘጋጅበት ጊዜ ባለህ ነገር ብቻ ቤትህ ለማስዋብ ሞክር። በመቀጠል ጎረቤቶችህን ወዳጆችህንና የቅርብ ዘመዶችህን ጥራ። እንዲሁም ጥሩ ባሕርይ አላቸው የምትላቸውን ሰዎች በሰርጉ እንዲታደሙልህ ጋብዝ። ሙዚቀኞችን ግን ፈጽመህ አትጥራ ለእነርሱ የምታወጣው ወጪ በራሱ ከፍተኛና ሊሆን የማይገባ ነው።
ከእነዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ክርስቶስን በሰርግህ እንዲገኝ ጋብዘው። እርሱን እንዴት አድርገህ እንደምትጋብዘው ታውቃለህን? “ንጉሡም መልሶ፡– እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል”(ማቴ.፳፭፥፵) እንዲል ድሆችን በሰርግ እንዲገኙ በማድረግ ክርስቶስን በሰርግህ እንዲገኝ ማደረግ ይቻልሃል። ስለክርስቶስ ብለህ ድሆች በሰርግህ እንዲገኙ ስላደረግህ ሰርግህ የተበላሸ አድርገህ አትቁጠር፤ ነገር ግን ሴሰኞችን በሰርግህ ብትጋብዝ ሰርግህ በእርግጥ የረከሰ ይሆናል። ድሆችን ወደ ሰርግህ መጥራትህ ሀብት ወደ ቤትህ እንዲገባ መጥራትህ ነው። ቅምጥሎችን ከሰርጉ እንዲታደሙ የጠራህ እንደሆነ ግን ውርደትን እየጠራህ ነው።
ሙሽሪትን በወርቅ ጌጣ ጌጦች አታስጊጣት ነገር ግን በጥሩ ሥነ ምግባርና በጭምትነት አስጊጣት እነዚያን ነገሮች ፈጽመህ አትፈልጋቸው። ግርግርና ሁካት በሰርግህ ፈጽሞ አይኑር። ሙሽራውን ጥራና ሚስቱን ይዞ ወደ ቤቱ ይግባ። በምሳና በራት ግብዣህ ላይ አስካሪ መጠጦች አይገኙ። ነገር ግን ሰርግህ በደስታ የሞላበት ይሁን።
እንዲህ አድርገህ ሰርግህን በመከወንህ ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆንክ ለማስተዋል እንድትችል በዘመኑ ሰርግ ተብለው ከሚቆጠሩት ጋር ያንተን የሰርግ ሥነ ሥርዐት አስተያይ። ሌላው ይቅርና ያንተን ሰርግ የተመለከተ ሰው ሁሉ የቁንጅና ውድድር ሳይሆን በእውነተኛ ትርጉም ሰርግን እንዳየ ምስክርነትን ይሰጥሃል። በዘመኑ ሰርግ ተብለው ከሚጠሩት ውስጥ ግን እጅግ የበዙ ክፋቶች ታጭቀው ይገኙበታል። በአዳራሽ የሚፈጸመው ሰርግ በጥንቃቄና እግዚአብሔርን በመፍራት ከሚደረገው ጋር ሲነጻጸሩ በቶሎ የሚጠናቀቁ ሰርጎች አይደሉም። ከዚህም ባለፈ በውሰት የመጡት እቃዎች ሊጠፉም ስለሚችሉ ፍጻሜው ከደስታ ይልቅ ሊቋቋሙ ከማይችሉት ከባድ ሃዘን ውስጥ ሊጥል ይችላል። ይህ የከበደ ሃዘን በአማች ላይ የሚታይ ነው ። ነገር ግን ሙሽሪትም ከዚህ ሃዘን ነጻ ልትሆን አትችልም ። በሰርጉም ፍጻሜም የቤቱ ውበቱ ጠፍቶ በሃዘን ታወሮ ይታያል ።
በጥንቃቄና እግዚአብሔርን በመፍራት በሚከናወነው ሰርግና በአሕዛብ ልማድ በሚፈጸመው ሰርግ መካከል ሰፊ የሆነ ልዩነት አለ። በዚህ ክርስቶስ ሲገኝ በዚያ ግን ሰይጣን ነግሦ ይታይበታል ። በዚህ ፍጽም የሆነ ፍስሐ ሲታይ በዚያ ደግሞ ጥቅ ያጣ አለባበስ ይተዋወቅበታል ። በዚህ ፍጹም ደስታ ሲኖር በዚያ ግን ሕማምና ሰቆቃ ይተርፈዋል ። በዚያ የወጣው ወጪ ታላቅ ሲሆን በዚህ ግን እዚህ ግባ የማይባል ወጪ ብቻ ያስተናግዳል ። በዚያ ግርግርና ሁካታ ሲታይ በዚህ ግን ግብረ ገብነት ጎልቶ ይንጸባረቅበታል። በዚያ ኃጢአት ሠልጥና ስትታይ በዚህ ግን ኃጢአት ፈጽማ አትኖርም ። በዚያ ስካሮች ሲኖሩባት በዚህ ግን ሰላም ወዳዶች ይታዩባታል ። በዚያ ሁካታና ጠብ ሲኖር በዚህ ግን እርጋትና ሰላም ሰፍነው ይታዩበታል ።
እነዚህን ሁሉ ልብ በሉ ። እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት እርሱን ለሚያፈቅሩት ካዘጋጀው ከመንግሥቱ ተካፋዮች እንድንሆን ከዚህ ቀን ጀምረን ይህን ክፉ ልማድ ከራሳችን አርቀነው እናስወግደው። የሰውን ልጅ ከመውደዱ የተነሣ ሰው በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር አብ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ዛሬም ዘወትርም እስከዘለዓለሙ ይሁን አሜን !!
ምንጭ፡
እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ። የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው። እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር። ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ። በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ። ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው። መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው። ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ።
ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ። የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው።
ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ። ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው። ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ። በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል።››
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን። ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን። ለዘለዓለሙ አሜን።
______
Posted in Ethiopia, Faith, Life, Love | Tagged: ሊቀ መልአክ, መስከረም ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም, ሰርግ, ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን, ቦሌ ሚካኤል, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ክርስቲያናዊ ሕይወት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ጋብቻ, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
A Lovely March 22
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2018
______
Posted in Love, Music | Leave a Comment »
ፕሬዚደንት፣ ጳጳስ፣ ዶክተር፣ ፈላስፋ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ ቢጫ፣ ኃብታም፥ ታዋቂ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ ብትሆን ፍቅር ግን ከሌለህ ከንቱ ነህ!!!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 24, 2018
እጅግ በጣም ኃይለኛና ልብን ኩምሽሽ የሚያደርግ ጥቅስ ነው፤ ዋውውው! እህታችን ጥቅሱን የምታነብበት ድምጽና እስትንፋስ ይህን በደንብ ይገልጹታል።
በዚህ አጋጣሚ፡ የክርስቶስ ልጆች፡ በተለይ ውጭ ያለነው፡ በያዝናቸው ቀናት አጥብቀን ልንጠነቀቅ ይገባናል! ከጃንዋሪ 10 እስከ ፌብርዋሪ 10 አካብቢ ባሉት ቀናት አጋንንት በብዛት የተለቀቁበት ግዜ ነው፤ ሥራ ቦታ፣ ትምህርት ቤት፣ በየጎረቤቱና መንገዱ እንዲሁም በሶሺያል ሜዲያ ላይ ጋኔን ተሸካሚዎቹ ፀረ–ክርስቶሳውያን በጣም ይፈታተኑናልና በተቻለ መጠን ከእነርሱ መራቅ፣ አለማናገሩና ቸል ማለቱ ይመረጣል።
መንፈስ ቅዱስ ሁሌም ከእኛ ጋር ይሁን!
______
Posted in Ethiopia, Faith, Love | Tagged: መጽሐፍ ቅዱስ, አዲስ ኪዳን, ክርስትና, ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች, ድክመት, ጥንካሬ, ፍቅር, Jesus Christ, Love, New Testament, The Bible | Leave a Comment »
“Coming To America 2” | an Ethiopian Prince Found His American Woman | Now She’s Married Into The Royal Family Of Ethiopia
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 16, 2017
American woman, 33, marries Ethiopian prince, 35, in a lavish wedding 12 years after they met in a Washington, DC nightclub
Ariana Austin, 33, married 35-year-old Joel Makonnen, a great-grandson of the last emperor of Ethiopia, on September 9 in Maryland
- The couple married 12 years after they met on the dance floor of Washington, DC nightclub Pearl
- Makonnen picked Austin up by saying she looked like a model in a Bombay Sapphire advertisement
- Makonnen, now a lawyer for Otsuka America Pharmaceutical, is related to Emperor Haile Selassie I though his second son, Prince Makonnen
- He was born in Rome, where his family lived in exile after a 1974 military coup
-
The Ethiopian royal family claims descent to the Biblical King Solomon and the Queen of Sheba
An American woman became an African princess last month when she married into the royal family of Ethiopia – after meeting her future husband at a modern day ‘ball’.
Ariana Austin, 33, married 35-year-old Joel Makonnen, a great-grandson of the last emperor of Ethiopia, on September 9 in Maryland.
The couple married 12 years after they first met on the dance floor of Washington, DC nightclub Pearl.
Makonnen told the New York Times that he hit on his future bride and her friend using a cheesy pick-up line.
‘I said, “You guys look like an ad for Bombay Sapphire,” or whatever the gin was,’ Mr. Makonnen recalled.
Makonnen says he immediately knew he wanted to date Austin.
Not even five minutes later I said, “You’re going to be my girlfriend,”‘ he said.
While Makonnen didn’t immediately tell Austin about his family, the truth about his heritage came out as they started to seriously date and it’s something that fascinates Austin.
She appears excited to be apart of a family that traces their roots back to the Biblical King Solomon and Queen of Sheba.
‘It’s unbeatable heritage and history,’ Austin said. ‘It combines sheer black power and ancient Christian tradition.’
The two married last month in an elaborate Ethiopian Orthodox Christian wedding involving 13 priests in Temple Hills, Maryland.
The bride and groom both wore crowns and capes in the ceremony, making them look like the true royals they are. While Austin may not have royal blood in her background, she does come from an African American/Guyanese family with rich histories abroad. Her maternal grandfather was lord mayor of Georgetown, the capital of Guyana.
Hours before the ceremony, they hosted a formal reception at Foxchase Manor in Manassas, Virginia where their 307 guests dined on platters of Ethiopian food and pre-boxed slices of Guyanese black cake.
Makonnen, or Prince Yoel as he is officially known, is related to the last emperor of Ethiopia, Haile Selassie I, through his second son, Prince Makonnen.
Haile Salassie ruled Ethiopia from 1930 to 1974, when he was overthrown by a Marxist Derg military coup.
Makonnen’s father, Prince David, was studying abroad at the time, and was thus able to escape imprisonment.
Makonnen was born in Rome, where his parents were living in exile, and was raised in Switzerland.
When he met Austin, he was perusing an undergraduate degree at American University.
The couple quickly stood the test of a long distance relationship when, after graduating from American in 2006, Makonnen took a six-month internship in France.
Austin went to Paris the next year, where Makonnen returned in 2008 before going back to Ethiopia to start a organization with his uncle to help Ethiopian youth.
In 2012, Austin returned to the U.S. to get a master’s degree in arts education at Harvard and the two decided to take a break that year.
But they were back together again by Valentine’s Day 2014, when Makonnen popped the question with an aptly shaped princess-cut diamond ring.
Their engagement is a funny story. Makonnen went over to his girlfriend’s house to propose, but he knocked on the door so forcefully that Austin thought someone was trying to break in and called her parents for help.
‘He was aggressively knocking so I didn’t answer. He came back, and then I opened the door,’ she said.
The two moved in together after the wedding, and are living in the Washington, DC area.
Makonnen works in the legal department at Otsuka America Pharmaceutical.
His new wife works in philanthropy at the Executives Alliance for Boys and Men of Color.
______
Posted in Ethiopia, Infos, Love | Tagged: Ariana Austin, Emperor Haile Selassie, Prince Joel Makonnen, The Royal Family, Wedding | 4 Comments »
ለምትወደው ባሏ ስትል የሾፌሩ ሱሪ እስኪወልቅ እንዲህ የምትታገል ሴት ለካስ አለች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 15, 2017
ቀኑን ሙሉ ስራ ቦታ በጭንቅላቴ ሲታየኝ፣ ሲገርመኝና ሲያስቀኝ የነበረ ቪዲዮ ነው። በስፔኗ ደሴት፡ በኢቢትሳ ሴትየዋና ባሏ ከአውቶብሱ ሾፌር ጋር የተጣሉበት ምክኒያት አይታወቅም፣ ግን ሾፌሩ ባሏን ሲነካበት ሴትየዋ ዓለም ተናወጠባት መሰለኝ ሾፌሩን በሴትነት ቁጣ ከግራና ቀኝ፣ ከላይና ከታች አጣደፈችው፦
______
Posted in Curiosity, Infotainment, Life, Love | Tagged: ስቶች, ስፔይን, ሾፌር, ኢቢትሳ, ጠብ | Leave a Comment »
It Was Another Perfect Moment Until Pride & Prejudice Reigned
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2017
„It was pride that changed angels into devils; it is humility that makes men as angels„ St. Augustine
When Being Right is Wrong: The Deadly Sin of Pride
There is a little poem by e.e.cummings which contains a line, “even on a sunday may I be wrong, for whenever men are right they are not young.” The poet is being paradoxically playful to make a point. When we are always right about everything we have not only lost the innocence of youth, but we are also guilty of the most basic sin of all, the deadly sin of pride. Pride is best understood as being right at all costs.
Some of the problems we think of as pride are really the symptoms of pride. We consider an arrogant person to be proud, but arrogance is one of the outward signs of pride. A person who displays his achievement or wealth, struts his good looks or brags about his victories is displaying the symptoms of pride, but pride is a much deeper problem and its symptoms can be seen in many other less obvious ways. A person who insists on arguing his point and will not listen to anyone else is proud. A person who simply assumes that he is right in his opinions is proud even though he may not strut or be arrogant. A person who can never be corrected, who is always defensive, who always has an excuse or always blames another person is proud because they cannot be wrong. Ever. At all.
In religious circles a person who is self righteous is proud. Now it gets tricky because a person who appears very humble and pious might, beneath the surface, be very proud of their piety and religious knowledge. At this point we have to laugh at ourselves. “What? You mean I am proud of being humble?” It’s true, some of the most incorrigibly proud people appear to be self effacing, obedient and pious souls.
This is why pride is so deadly, because it is the one sin that hides itself so effectively. The proud person, by very definition, does not realize he is proud. If he realized he was proud he would repent, but it is pride which keeps him from seeing that he is wrong or sinful in any way. Pride is a very difficult sin to do anything about because the proud person will even go so far as to admit that he is proud, and that makes him even more “right” than he was before!
What a subtle, lying, deceitful and insidious sin pride is! No wonder it is called “the first sin”. No wonder it is the first and most terrible sin of Satan who is the Father of Lies. Is pride deadly? Yes. It is deadly like a poisoned apple. It is deadly like a smiling murderer. Pride kills because the proud person cannot stand others who disagree. Not only does the proud person have to be right, but as their pride grows they must also destroy everyone else who is wrong. They cannot allow an enemy to remain. The proud person may not kill literally, but they kill reputations through gossip and detraction. They kill good will through hatred and recrimination. They kill charity through revenge and nursing a grudge. They kill friendship through arrogance, indifference to others and lack of compassion.
Humility counters pride. The word “humility” is derived from the same root as humor and “humus” which means “earth.” A humble person is down to earth. A humble person has a good sense of humor. Most of all, the humble person knows his failures, faults and foibles. He knows himself and can laugh at himself. e.e.cummings ends the poem by saying ruefully, “there’s never been quite such a fool who could fail, pulling all the sky over him with one smile.”
__
Posted in Faith, Love | Tagged: Prejudice, Pride, Sins | Leave a Comment »