Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 12th, 2023

ዛሬ ለኢትዮጵያ ባፋጣኝ የሚያስፈልጋት እንደ ታላቁ ጀግና ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ ያለ መንፈሳዊ መሪ ብቻ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 12, 2023

💭 “ማን ይሆን ስለ ታላቁ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ የመጋቢት ፩ (ልደታ) የሰማዕትነት ቀን” ለማስታወስ የተዘጋጀ?” በሚል እነዚህን ቀናት በትዝብት ሳሳልፋቸው ነበር። እስካሁን ምንም የሰማሁት ያየሁት ነገር የለም። ዜሮ! ይህ ብዙ መዘዝና መቅሰፍት ሊያመጣ የሚችል እጅግ በጣም ትልቅ ቅሌት ነው!

ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዮሐንስን የማያከብር፣ የማያደንቅና የማይመኝ ወገን ኢትዮጵያዊም ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያንም ሊሆን አይችልም። ደቡባውያኑ ኢትዮጵያ ዘ-ስጋ አንዴም እንኳን የዐፄ ዮሐንስን ስም በበጎ ለማንሳት የማይፈልጉት የስጋ ማንነታቸውና ምንነታቸው አስሮ ስለያዛቸው ነው።

አራቱ የዳግማዊ ምንሊክ ፀረ-ኢትዮጵያ ትውልዶች የታላቁ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስን ፈለግ ባለመከተላቸውና በአድዋው ድል የተገለጸላቸውን እግዚአብሔር አምላካቸውን በመካድ የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር ተከታዮች ለመሆን በመብቃታቸው ዛሬ በግልጽ ወደምናየው መቀመቅ ኢትዮጵያ ሃገራችንን ለማስገባት በቅተዋል።

እስኪ እናስበው፤ ከሰላሳ ዓመታት በፊት ብዙ መስዋዕት የከፈሉትን የአክሱም ጽዮናውያንን ድል ከሃዲዎቹ ሕወሓቶች በዳግማዊ ምንሊክ የብሔር ብሔረሰብ ተረት ተረት መንገድ ባይሄዱ ኖሮና የዐፄ ዮሐንስን አማራጭ የሌለው ራዕይ፣ ዕቅድና ተልዕኮ በሥራ ላይ ለማዋል ጥረው ቢሆን ኖሮ ዛሬ፤ እንኳን ሕዝባችን እንዲህ ሊጨፈጨፍ፣ ሊራብና ሊዋረድ እንዲያውም ኢትዮጵያ ኤርትራንና ጂቡቲን ብቻ አይደለም እስከ ሩዋንዳና ኡጋንዳ ቪክቶሪያ ሐይቅ ብሎም ሱዳንና የመንን ሳይቀር እንደገና ጠቅልላ በመግዛት ከዓለም ኃያል ሊሆኑ ከሚችሉ ሃገራት መካከል አንዷ ለመሆን የበቃች ሃገር ነበር። ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ያመሩት የትግራይ ሰዎች ግዕዝ ቋንቋን ብሔራዊ ቋንቋ ለማድረግ ቢችሉ ኖሮ እግዚአብሔር አምላክን ቅዱስ ያሬድንና ዐፄ ዮሐንስን ምን ያህል ለማስደሰት በቻሉ ነበር።

❖ “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት፤ ሁለተኛ ክብርህ ናት፤ ሶስተኛም ሚስትህ ናት፤ አራተኛም ልጅህ ናት፤ አምስተኛም መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፤ የዘውድ ክብር፤ የሚስት ደግነት፤ የልጅ ደስታ፤ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ።” አፄ ዮሐንስ ፬ኛ

❖ ሰንደቃችንን እና አማርኛን ብሔራዊ ያደረጓቸው ታላቁ አፄ ዮሐንስ በአዲስ አበባና በመላዋ ኢትዮጵያ ለምን አንድም መታሰቢያ የላቸውም? በነገራችን ላይ ብቸኛው አባታችን እነ ቅዱስ ያሬድ፣ ዓለም አቀፋዊ ተጽ እኖ ፈጣሪዎቹ እነ ነገሥታት ሳባ/መከዳ፣ አብርሃ ወ አጽብሃ፣ ገብረ መስቀል፣ ካሌብ፣ ጀግናው ራስ አሉላ ወዘተም እንዲሁ ከትግራይ ውጭ ይህ ነው የሚባል መታሰቢያ የላቸውም። “ለምን?” ብለን እራሳችንን እንጠይቅ!

በተለይ ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላቶች ለመሆን የበቁትና የባዕዳውያኑ ኤዶማውያንና እስማኤላውያን ወኪሎች የሆኑት ጋላ-ኦሮሞዎቹ ተጸዕኖ ነውን?

አዎ! በደንብ እንጂ፤ ይህ ምንም የሚያጠራጥር አይደለም። ዛሬ በገሃድ እንደምናየው በተቻላቸው መጠን የተቀረውን የኢትዮጵያ ክፍል ከአክሱም ጽዮን ነጥሎ ለማዳካም የመቶ ሰላሳ ዓመታት ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደነበሩ ነው። ልክ እንደ መሀመዳውያኑ ወንድሞቻቸው አጋጣሚውን ነበር የሚጠብቁት። ዛሬ ሁሉንም እያታለሉ በጭካኔ፣ በድፍረትና በከህደት የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላቶችን ጋብዘው በአክሱም ጽዮን ላይ ለመዝመት ደፈሩ። ነገር ግን፤ ምንም እንኳን ብዙ መከራና ስቃይ በሕዝባችን ላይ ለማድረስ ቢበቁም በመጨረሻ ግን ከሃገረ ኢትዮጵያ ተጠራርገው ይወጡ ዘንድ ግድና ተገቢም ነው። ሌላ ምንም አማራጭ እንደሌለ ያለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት ታሪክ በሚገባ አስተምሮናል።

“ኦሮሞ ነን” የሚሉት ምስጋና-ቢስ ከሃዲዎች እጅግ በጣም ኃይለኛ የሆነ መቅሰፍት በራሳቸው ላይ በማምጣት ላይ ናቸው።

😈 ጋላ-ኦሮሙማ’ መርዝ ነው፤ የኢትዮጵያ መቅሰፍት ነው!!!

እውነቱን ትተው ውሸቱን፤ ሰፊውን ጠልተው ጠባቡን፣ የሚያኮራውን ንቀው የሚያቀለውን፣ የሚያስከብረውን አውግዘው የሚያዋርደውን፣ ግዕዝን ትተው ላቲኑን፣ የማርያም መቀነትን ትተው የዘንዶ ቀበቶን፣ ክርስቶስን ትተው ዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስን መርጠዋል። በዚህም ከኦሮማራ ጭፍሮቻቸው ጋር በቅርቡ ክፉኛ ይቀጣሉ። መዳን የሚፈልጉ ኦሮሞነታቸውን፣ ኦሮምኛ ቋንቋንና ዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈርን ትተውና ንስሃ ገብተው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ቶሎ ይሰለፉ።

ጋላ-ኦሮሞዎች ወደ ኢትዮጵያ ግዛቶች ገብተው መስፈር እንደጀመሩና ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ጋር መተዋወቅ እንደበቁ፤ ይዘውት የመጡትን የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር ድሪቶ አራግፈው የወርቅ ካባ ለመልበስ ጣዖታዊውን አምልኮቻቸውን እየተው በመጠመቅ የመንፈሳዊ ማንነቱንና ምንነቱን ለመቀበል ዝግጁዎች ነበሩ። ብዙዎች ስማቸውን በፈቃዳቸው እየቀየሩ በክርስቲያናዊ የመጠሪያ ስሞች መንፈሳዊ ኃብቱን ለመጋራት ፍላጎት አሳይተው ነበር። ነገር ግን አክሱም ጽዮናውያንን ለመከፋፈል፣ ለማስጨፍጨፍ፣ ለማስራብ፣ ለመበከልና የወንዶች ልጆቻቸውን ብልት ለመስለብ ከሉሲፈራውያኑ ሮማውያን፣ ቱርኮችና አረቦች ጋር በጋራ ሤራ ጠንስሰው ወደ አድዋ አምርተው የነበሩት ዲቃላው እነ ዳግማዊ ምንሊክ፤ “የለም የራሳችሁን ስም ያዙ፤ የስጋ ማንነትና ምንነት ይበልጣል፤ እንዲያውም የአካባቢና ከተማ መጠሪያዎቹን ሁሉ በራሳችሁ ቋንቋ ሰይሟቸው” በማለት የመሞት ነፃነቱን ሰጧቸው።

ይህም ሥራቸው ዐፄ ዮሐንስን እጅግ በጣም አስቆጥቷቸው፤ የቦታ ስሞቹን ባፋጣኝ ወደ ጥንት መጠሪያዎቻቸው እንዲመልሱ ለምንሊክ ትዕዛዝ ሰጥተዋቸው ነበር። ጋሽ ሐጎስ ቪዲዮው ላይ እንደሚተርኩልን ተንኮለኛው ምንሊክ ግን ዐፄ ዮሐንስን ለመግደልና ለባዕድ አሳልፎ ለመስጠት ወኪሎቻቸውን በካህናት ስም ልከው ለሰማዕትነት አበቋቸው።

ከዚህ በኋላ በመላዋ ምስራቅ አፍሪቃ በበላይነትና በስውር የነገሡት ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዮሐንስ አራተኛ ናቸው። ሌላ ማንም አይደለም! ዛሬ የሳቸውን ራዕይ ለመትገበርና ተልዕኳቸውንም ለማሳካት ዝግጁ የሆነ ወገን ብቻ ነው የሚድነው/ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማየት የሚበቃው።

ቪዲዮው ላይ እንደምንሰማው በእዚህ የመጨረሻው የምንሊክ ትውልድ ዘመን እንደ ፕሬፊሰሮች ጌታቸው ሃይሌ፣ ፍቅሬ ቶሎሳ እና ታየ ቦጋለ እንዲሁም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሜዲያዎቻቸው ያሉ አጭበርባሪዎች አማራውንና ኦሮማራውን አስረው ከዳግማዊ ምንሊክና በኋላ ላይ ከመረጡት ከዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር አምልኮ እንዳይላቀቅ በተንኮል ይዘውታል። ለዚህም ነው በፈጠራ ወሬና በሐሰት ውንጀል የእነ አፄ ዮሐንስን ስም ለማጠልሸት የመረጡት። ይህ ደግሞ ከባድ ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነ እያየነው ነው።

ጀግናው ንጉሣችን ዐፄ ዮሐንስ ከሚታወቁት የኢትዮጵያ ነገሥታት መካከል ብቸኛው መሪ ናቸው ለኢትዮጵያ ለሕዝባቸውና ለታቦታቸው ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡት።

ንጉሥ ዮሐንስ አራተኛ ለኢትዮጵያ፣ ለሕዝባቸውና ለቤተ ክርስቲያናቸው አንገታቸውን ሲሰጡ ፥ የቀዳማዊ ምኒሊክን ስም የሰረቁት ዳግማዊ ምንሊክ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴና መንግስቱ ኃይለማርያም ልክ እንደ ዛሬዎቹ እንደ ሕወሓቶች፣ ሻዕቢያዎችና ኦነግ/ብልጽግናዎች እነ ኢሳ አፈወርቂ (አብዱላ ሃሰን) ፣ ደብረ ጺዮን ፣ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊና ቧያለው ሳይሆኑ ለኢትዮጵያ፣ ለሕዝቧና ታቦታቱ የሚሰውት፤ ኢትዮጵያና ሕዝቧ ናቸው ለእነዚህ ከሃዲዎች በመሰዋት ላይ ያሉት። በተለይ ላለፉት አምስት መቶ እና መቶ ሰላሳ ዓመታት አክሱም ጽዮናውያን ናቸው በሜንጫም፣ በጥይትም በረሃብና በሽታም በተደጋጋሚ በመሰዋት ላይ ያሉት።

ታዲያ ሰማዕቱ ዐፄ ዮሐንስ ዛሬ ምን የሚሰማቸው ይመስለናል? ምልክቶቹ አይታዩንምን? በኤርትራ በኩል የሚኖሩትን አክሱም ጽዮናውያንን በእነ ዳግማዊ ምንሊክ በኩል ለባዕዳውያኑ ሮማውያን አሳልፎ የሰጣቸው ትውልድና ዛሬም የዐፄ ዮሐንስን ውለታ በመርሳት እንዲያውም ስማቸውን ለማጥፋት ከጋላ-ኦሮሞዎቹ ጋር ሆኖ በመስራት ላይ ያለው ትውልድ ክፉኛ እንደሚቀጣ እያየነው አይደለምን?

ብዙ ምልክቶች በተለያዩ አጋጣሚዎች ታይተውናል። በአክሱም ጽዮን፣ በደብረ ዳሞ፣ በደብረ አባይ፣ በማርያም ደንገላትና በሌሎቹ ብዙ ቅዱሳን ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ከሃዲዎቹ ሕወሓቶች ጠላትን ሊመሩት የሉሲፈርን/ ቻይናን ባንዲራ ለማውለብለብ በመድፈራቸው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አባቶቻችንና እናቶቻችን ለሰማዕትነት እንደበቁ እያየን ነው። ከሳምንት በፊት ደግሞ በአደዋው ድል ክብረ በዓል ወቅት ጋላ-ኦሮሞዎቹ የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር ባሪያዎች ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዘው ብለው በመግባት ዲያብሎሳዊ ሥራ ሲሠሩ ብልጭ ብለው የታዩኝ ዐፄ ዮሐንስ ነበሩ። ይህ እሳቸው የሚልኩልን ማስጠንቀቂያ ይሆን? በማለት እራሴን በመጠየቅ ላይ ነኝ። ሊሆን ይችላል! ትውልዱ በራሱ ላይ እባብ እየጠመጠመ ስለሆነ ባሁኑ ሰዓት መከራ ብቻ ነው አማካሪው።

በአዲስ አበባ እንኳን ለባዕዳውያኑ ለእነ ጆሞ ኬኒያታ፣ ክዋሜ ንክሩማህ፣ ኔልሰን ማንዴላ፣ ቦብ ማርሌ፣ ካርል ሃይንዝ ቡም፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ ንግሥት ኤልሳቤጥ፣ ዊንስተን ቸርችል መታሰቢያዎች ቆመውላቸዋል፣ መንገዶችና ትምህርት ቤቶች ተሰይመውላቸዋል።

እጅግ በጣም የሚገርም ነው፤ በቸርችል ጎዳና ላይ ከላይ እስከ ታች ዐፄ ዮሐንስን ዘልለው፤

  • ☆ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ለዳግማዊ ምንሊክ ኃውልት ቆሞላቸዋል
  • ☆ ወረድ ብሎ በቴዎድሮስ አደባባይ ለዐፄ ቴዎድሮስ መታሰቢያ አላቸው
  • ☆ ወረድ ብሎ ደርግ የሉሲፈርን ኮከብ መታሰቢያ በሰሜን ኮሪያ ስም አቁሟል
  • ☆ ወረድ ብሎ ብሔራዊ ቴዓትርና ለገሃር አካባቢ ለዐፄ ሃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ሠርቷል
  • ☆ ግራኝ ደግሞ ከቸርችል በስተግራ በሚገኘው በምንሊክ ቤተ መንግስት የሰዶሟን ፒኮክ ተክሏታል

👉 እያስተዋልን ነው? ከአክሱም ጽዮን የሆኑት ታላቁ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ ብቻ ናቸው ምንም ዓይነት መታሰቢያ ያልተደረገላቸው። እንዲያውም እነ፤

  • ❖ ንግሥት ሳባ/ማከዳ፣
  • ❖ ነገሥታት አብረሃ ወ አጽበሃ፣
  • ❖ ንጉሥ ካሌብ፣
  • ❖ ንጉሥ ገብረ መስቀል

እና ሌሎችም ሳይቀሩ በተሰውላቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች ምንም ዓይነት መታሰቢያ የላቸውም። ከአክሱም ጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ ስለሆኑ? አይገምምን? ለጋላ-ኦሮሞዎቹና ኦሮማራዎቹ፤ “ወያኔ” ሰበባቸው ነበር ማለት ነው። ዛሬ እንደምናየው ግን ምክኒያታቸው፤ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ትምክህት፣ እብሪትና ጥላቻ ነው። “ውደቁ/ውረዱ፤ እንደ እኛ ሁኑ፤ ከጠላትም ጋር ከሰይጣንም ጋር አብሩ፤ አታምጹ! አግዓዚነታችሁን ተውት! እንደኛ ለሆዳችሁ ለስጋችሁ ባሪያ ሆናችሁ ኑሩ፤ ከዚያም አብረን ወደ ጥልቁ እንውረድ!” ነው ነገሩ። አይይይ!

መጋቢት ፩ – አፄ ዮሐንስ ፬ኛ ንጉሠ ነገሥት ዘ-ኢትዮጵያ የፅዮን ጠባቂ ፻፴፬/134ኛው የመስዋዕት/የሰማዕትነት ቀን።

💭 “እኔ ዮሐንስ እንደሆንኩ ሐሳቤም፡ ነፍሴም፡ ሃይማኖቴም አንዲት ናት!!! የሀገሬን መደፈር የሕዝቤን መዋረድ በሕይወቴ ቁሜ አላይም፤ አልሰማም!!! የሚንቁኝንና አንበገርልህም የሚሉኝን እገጥማለሁ ብዬ ጦሬን ወደ ወንድሞቼ አላዞርም” አንገቱን የሰጠው ንጉሣችን ዩሐንስ ፬ኛ።

👉 በድጋሚ የቀረበ፦

ይህ ጉዳይ ቀላል ጉዳይ አይመስለኝም፤ ሃገርንና እያንዳንዱን ግለሰብ የሚመለከት ወቅታዊ ጉዳይ ነውና ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል በግልጽና በንጹሕ ልብ ሊነጋገርበት የሚገባው ጉዳይ ነው። ጠላት ከብዙ አቅጣጫ እየተለሳለሰ መጥቷል።

ባለፈው ጊዜ መገናኛ ላይ ሆኜ ወደ ኮተቤ የሚሄዱትን ታክሲዎች እጠብቅ ነበር። ዕለቱ ሐና ማርያም ስለነበር ወደ ኮተቤ ሐና ማርያም መሄድ ፈልጌ ነበር። መንገዱ በመሃል እየተሠራ ስለነበር ወደዚያ የሚሄድ በቂ ታክሲ ስላልነበር ብዙ አስጠበቀኝ። በአጠገቤ አንዲት የሃገር ልብስ የለበሰች ወጣት እናትአብራኝ ትጠብቅ ነበር። የሆነ ሰዓት ላይ አንድ ታክሲ የመንግሱ ኃይለማርያምን ለጥፎ ሲያልፍ አየሁትና ለሴትዮ በሀዘን “እያየሽ ነው ዘመዶቼን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው፣ የብዙ አዲስ አበባ ነዋሪዎችን ሕይወት የቀጠፈውን የመንግስቱ ኃይለማርያም ፎቶ ሙሉ አዲስ አበባ በየታክሲውና ሎንቺናዎች ላይ ተለጣጥፎ ሳይ ደሜ ይፈላል።” ስላት በሃዘን ተሞልታ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የክርስትና አባቷ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እንደሆኑና በግል ሕይወቷ ብዙ ተዓምረኛ የሆኑ ነገሮች እንዳደረጉላት እያጫወተችኝ ወደ ሐና ማርያም አብረን አመራን።

“ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!” የሚለውን አባባል ስታነሳለኝ የታየኝ፤ እንዴ ሙሉ አዲስ አበባን ብትዘዋወሩ አንድም የአፄ ዮሐንስን ወይም የራስ አሉላ አባ ነጋን ፎቶ የለጠፈ ታክሲ አታዩም። (የአፄ ቴዎድሮስ፣ የአፄ ምኒልክ፣ የአፄ ኃይለ ሥላሴ፣ የመንግስቱ ኃይለ ማርያም፣ የአብይ አህመድና ለማ መገርሳ፣ የቼጉቬራ ወዘተ ፎቶዎች በብዛት ተለጥፈው ይታያሉ)። እንዲያውም ጠለቅ ብዬ ስሄድ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ ለ አፄ ዮሐንስ እና ራስ አሉላ መታሰቢያነት ይውል ዘንድ በስማቸው የቆመ ሃውልት፣ የተሰየመ መንግድ፣ አደባባይ፣ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል አንድም የለም። ቅዱስ ያሬድ እንኳን ከሙዚቃው ትምህርት ቤትና ዘንድሮ ለይስሙላ ከተመረቀው አደባባይ በቀር መንገድም ሆነ ሰፈር አልተሰየመለትም። የቤተ ክርስቲያን አባት ለሆነው ቅዱስ ያሬድ በስሙ የተሰየመው ቤተ ክርስቲያንም አንድ ብቻ ነው። የሚገርም ነገር አይደለም? ቁልፍ የሆኑ የከተማዋ ቦታዎች ካርል አደባባይ፣ ሃይሌ ጋርሜንት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ውንጌት፣ ቸርቺል ጎዳና፣ ጆሞ፣ ፉሪ፣ ጉለሌ ወዘተ እየተባሉ በባዕዳውያኑ ስም ይጠራሉ፤ ለኢትዮጵያና ተዋሕዶ እምነቷ የሞቱላት ግን የሚያስታውሳቸው እንኳን የለም። ለእነ ቦብ ማርሊ እና ካርል ህይንስ ቡም ኃውልት ቆሞላቸዋል በመንግስቱ ኃይለ ማርያም በሲባጎ ታንቀው ለተገደሉት አቡነ ቴዎፍሎስ የተሠራው ኃውልት ግን በአደባባይ እንዳይቆም ተደርጓል። በእርኩስ ቱርክ ለተሰዉት ለእነ አፄ ዮሐንስማ የማይታሰብ ነው።

እስኪ ይህ ለምን እንደሆነ እራሳችንን በንጹህ ልብ እንጠይቅ?

  • ፩ኛ. ደገኛ የሰሜን ሰው ስለሆኑ?
  • ፪ኛ. ምርጥ የተዋሕዶ አርበኞች ስለነበሩ?
  • ፫ኛ. ጥልቅ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን ስለያዙ?
  • ፬ኛ. ሰንደቃችንን እና አማርኛን ብሔራዊ ስላደረጉ?
  • ፭ኛ. ባዕዳውያኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች ስለማይፈልጓቸው?
  • ፮ኛ. ቆላማዎቹ ኦሮሞዎች እና ሙስሊሞች ስለሚጠሏቸው?
  • ፯ኛ. ብዙ አብሮ ከመኖር የተነሳ ሰው በዋቄዮ-አላህ መተት ስለተያዘ?

በክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ቱርኮች የተጨፈጨፉት አባቶቻችን እንባቸውን እያረገፉ ነው! በቱርክ ሰይፍ የታረዱት አፄ ዮሐንስ መቃብራቸውን እይገለበጡ ነው! እግዚአብሔርም በትውልዱ እያዘነበት ነው።

በዛሬዋም ኢትዮጵያ ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት እና አፄ ዮሐንስ ችግር ያለው ከፍተኛ ችግር ያጋጥመዋል!

💭 ይህን ጽሑፍ ከአስራ ሁለት ዓመታት በፊት በጦማሬ አቅርቤው ነበር፦

የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 27, 2011

*ከማሞ ውድነህ*

“የእስበሳችን ነገር ያለ ማክረሩ ነው የሚሻለው። ጠንካራ ክንድና ብርቱ ትኩረት የሚገባው ግን እንደ አዞ ከውሀ ውስጥ ብቅ የሚለው ነው“ (አሉላ አባነጋ)

አፄ ዮሐንስ ከጉራዕ ጦርነት በኋላ ሐማሴን ውስጥ ሰነባብተው ወደ ዐደዋ ከመመለሳቸው በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ በር የተከበረና የታፈረም እንዲሆን ሲሉ ደጃዝማች ኃይሉ ተወልደ መድኅንና ራስ ባርያውን በገዥነት ሲሾሙ፡ ስመ–ጥሩውን አዋጊያቸውን ሊጋባ አሉላን በራስነት ማዕረግ አስኮፍውሰና አስጊጠው ከመረብ ማዶ ያለውን አገር በጦር አበጋዝነት እንዲጠብቁ ሾሙዋቸው። ከዚያ በኋላም የአፄ ዮሐንስ ትልቁ የሥራ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የውስጥ ጉዳይ ማደላደልና ማለሳለስ አንድነቷን ማጽናትና ሕዝቡ ፍትሕ አግኝቶ አርሶና ነግዶ እንዲተዳደር የማድረጉ ጉዳይ ነበር።

ይህን ዓላማቸውን ሊያደናቅፉባቸው እንደሚችሉ አሥግተዋቸው ከነበሩት ሁኔታዎችም ጋር መፋጠጡን ተያያዙት። በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የውስጡን ተቀናቃኝ ቀርቶ የውጭውንም ወራሪ ጠላት ከአንዴም ሁለቴ ኃያሉ ክንዳቸውን ስለአሳረፉበት ለጊዜው ረጭ ብሎላቸዋል። በምዕራብና በመካከል ኢትዮጵያም በኩል የቤገምድር የወሎና የጐጃም ሁኔታ ጋብ ብሎላቸዋል። የጥርጣሬና የሥጋት ትኩረታቸውን የሳበባቸው ግን ሸዋ ሆነ። የወጣትነት ጓደኛቸውና ምስጢረኛቸው ምኒልክ “አፄ” ተብለው ቁጥሩ እስከ ሰባ ሺህ በሚደርስ ሠራዊት ጐልብተው፡ ከሸዋም አልፈው ወሎንና ጐጃምን ለመደረብ ከሚያስፈራሩበት ደረጃ ላይ ወጥተዋል።

አፄ ዮሐንስ ግን፡ የምኒልክን ሁኔታ አንሥተው ከመኳንንቶቻቸውና ከጦር አበጋዞቻቸው ጋር በሚወያዩበት ሰዓት ሁሉ ደጋግመው የሚያነሡት ጉዳይ ነበራቸው።

“ዋናው ሥጋቱና ችግሬ የሠራዊቱ ብዛት አይደለም። ለዚህ ለዚህስ እኔም ላቅ ያለ እንጅ ከእርሱ ዝቅ ያለ ሠራዊት የለኝም። ግን እንደዚያ ማሳያ እንደሚሉት የሰይጣን መልእክተኛ የመሰለ ፈረንጅ ከአጠገቡ አስቀምጦ፡ ከነሙንዚንገር ጋርም የሚያደርገው መላላክና መስማማት ነው።

ከዚያ ሌላ ደግሞ እነዚህ ሚሲዮኖችም በዚያ በኩል ገብተዋል፡. ዋናው ዓላማቸውም ምኒልክን አሳስተውና ጦር አስመዝዘው ከኔ ጋር ለማጋጨት መሆኑን አላጣሁትም። ግዴለም የማደርገውን ዐውቃለሁ” እያሉ ዛቻ አዘልና ትካዜ–ለበስ አነጋገር ያሰሙ ነበር። እርግጥም ነው በዚያ ዘመን ፒዬር አርኖ የተባለ ፈረንሳዊ በዘይላ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ የምኒልክ ባለሟል ሆኖ የእርሳቸውንም መልእክት ይዞ ወደ ግብጽና ፈረንሣይ እየሔደ ‘ዮሐንስን ለመጣል ትልቅ መሣሪያ ይሆናችኋል‘ እያለ ያሽቃብጥ ነበር። ከእርሱም ሌላ ደግሞ በምሕጻረ ቃል “አባ ማስያስ” እየተባለ የሚጠራው ሎሬንዞ ጉልየሞ ማሳያ የሚባለው የሮማ ካቶሊክ ሚሲዮን አባል በሸዋና በከፋ ውስጥ ድርጅቱን አቋቁሞ የምኒልክን ባለሟልነትም አትርፎ ከሚሲዮናዊነቱ ይልቅ በዲፕሎማቲክና በስለላው ሙያ ተሠማርቶ ዮሐንስንና ምኒልክን ለማራራቅና ለማጋጨት በመካከላቸው ገብቶ ነበር።

እነዚሁ ሁለቱ አውሮጳውያን የምኒልክን ጉልበት ከዮሐንስ ጉልበት የጠነከረ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት ሲከታተሉት የነበሩት ዮሐንስም ክንዳቸውን በቀላሉ የማይታጠፍ ለማድረግና ምኒልክንም ለማስገበር ሲሉ የሠራዊታቸውን ቁጥር እስከ አንድ መቶ ሺህ ከአደረሱት በኋላ፥ ክዚሁ ውስጥ እስከ ዐርባ ሰባት ሺህ

የሚደርሰውን ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አስታጠቁት። ከጉንደትና ጉራዕ ጦርነቶች የተገኘው ቀላል መካከለኛና ከባድ መሣሪያም የበላይነታቸውን ያረጋገጡበት ዋናው ትጥቃቸው ነበር።

ከመሣሪያው ጥራትና ብዛትም ሌላ በአጼ ተክለ ጊዮርጊስና በግብጾች ላይ ያገኙት ድል ዝናቸውንና ጥንካሬያቸውን “አበሻ መሬት አውጥቶ በአፍሪቃ፡ በእስያና በአውሮጳ ውስጥ አስተጋብቶላቸው ነበር። በአሜሪካም ውስጥ ቢሆን፡ “የኛ የጦር መኮንኖች ያዘመቱትን የግብጽን ጦር ድል ያደረገ ብርቱ ንጉሥ” የሚል ጸጸት–ለበስ ታዋቂነት አትሮላቸው ነበር።

ታዲያ እንደዚያ ሆኖ ስሙ የገነነ ሠራዊት ሸዋ የገባ እንደሆነ ሊያደርስ የሚችለውን ብርቱ ጉዳት አስቀድመው የተረዱትና የተጠነቀቁበት ከጐልማሳው ምኒልክ ይልቅ አዛውንቱ አጐታቸው ዳርጌ ንበሩ። “ጉዳዩን በቀላሉ አትዩት፤ በየልቦናችሁ ምከሩበትና በእርቅ ይለቅ” ሲሉ አዛውንቱ “ጦር ጠማኝ” ይሉ የንበሩት የምኒልክ የጦር አበጋዝ ግን፤

“ወይ እሳቸው መጥተው፥ ያለዚያ እኛ ዘምተንባቸው ሳንሞካከር እንዴት አስቀድመን እንገብራለን” እያሉ ምኒልክን ይወተዉቱ ነበር።

በዮሐንስ ቤተ መንግሥት እንደአባት ይታዩ የንበሩት ራስ አርአያም በበኩላቸው፤

“የሁለት ወንድማማች ጠብ ማንን ጐድቶ ማንን ይጠቅም ይመስላችሁ? ኢትዮጵያን እኮ ነው የሚያዳክማት! ኢትዮጵያን እኮነው የሚያሳንሳት! ኢትዮጵያን እኮ ነው የጠላቶቿ መሳቂያ የሚያደርጋት! ታሪክ ይወቅሰናል፤ ትውልድ ያፍርብናል፤ ታቦትና መስቀል አስይዘን ካህናትን ወደ ምኒልክ እንስደድ እንጂ ጦር መምዘዙን አልስማማበትም” እያሉ የእህታቸውን ልጅ ከነጦር አበጋዞቻቸው ይቆጡ ነበር።

👉 እዚህ ይቀጥሉ

💭 የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

Click to access atseyohannesnegusmenilik.pdf

👉 በቪዲዮው የቀረበውን መልዕክት ላካፈሉን ለጋዜጠኛ ሐጎስ መኮንን የከበረ ምስጋና

💭 ቪዲዮው ላይ የሚታየው ሰንደቅ ዓላማ የዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነው። ሰንደቅ ዓላማው መቀሌ በሚገኘው የዐፄ ዮሐንስ ፬ኛ ቤተ መንግሥት ውስጥ አሁንም ይገኛል። ይህን ታሪካዊ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በካሜራዬ ያስቀረሁት መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በማስተምርበት ወቅት የዐፄ ዮሐንስ ፬ኛን ቤተ መንግሥት በጎበኘሁበት ጊዜ ነበር።

በሰንደቅ ዓላማው መሀል ላይ ያለው ምልክት የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ በብዙ አገሮች ዘንድ ሁሉ የታወቀ እንደመሆኑ በኢትዮጵያም የታወቀ ስመ ጥር ሰማዕት ነው። ለዚህ እንደ አስረጅ በእንግሊዝን፣ በግሪክ፣ በግብጽ፣ በሶርያና በሌሎች 37 የዓለም አገሮች ውስጥ የሚገኙን የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያናት ማውሳት እንችላለን። እንግሊዝ ውስጥ ብቻ በ37 ከተሞች ውስጥ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይገኛል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድም ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ጠባቂ ሰማዕት ተደርጎ ይወሰዳል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ፲፫ኛው ክፍለ ዘመን በዐፄ ዐምደ ጽዮን ዘመነ መንግሥት እንደነበር ከክብረ ነገሥቱ መረዳት ይቻላል። ክብረ ነገሥቱ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳም ውስጥ ብዙ ዓመታት የኖሩ አባ ልዑለ ቃል የተባሉ መነኩሴ ከሶርያ «ደብረ ይድራስ» ከሚባለው ገዳም የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ከገድሉ ጋር አምጥተው ለዐፄ ዐምደ ጽዮን እንዳስረከቡ፣ ዐፄ ዐምደ ጽዮንንም ቤተ ክርስቲያን አሠራለት እንዳሉና ገድሉን ከዐረብኛ ወደ ግእዝ እንደተረጎሙ ያትታል።

የዘመኑ ታሪክ ነገሥት ዐምደ ጽዮን የጊዮርጊስን ጽላት አስይዘው ከጠላቶቻቸው ጋር በመግጠም አሥር ታላላቅ ዘመቻዎችን በድል አድራጊነት እንደተወጡ፣ ንጉሠ ነገሥቱ «ቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጄና ረዳቴ ስለሆነ የኢትዮጵያ ጠላቶች ድል ሊያደርጉኝ አይችሉም» እያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነትና ረዳትነት አብዝተው ያምኑ እንደነበር ያስረዳል።

የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ጸሐፊ ትእዛዝ እንደነበሩ የሚታመነው መርቆርዮስም «አርዌ በድላይ» የተባለ ጠላት ብዙ ወታደሮች አሰልፎ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን ሊወጋቸው ሲነሳ ንጉሡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ይዘው ሠራዊታቸውን አስከትተው በመዝመት የኢትዮጵያን ጠላት ድል መትተው ተመልሰዋል ሲሉ ጽፈዋል።

ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ነገሥታት ዜና መዋዕል እንደሚነበበው ነገሥታቱ በሚዘምቱባቸው ታላላቅ ዘመቻዎች ሁሉ የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት ትተው አይንቀሳቀሱም ነበር ። ይህንን እውነት ለማረጋገጥ ቢፈለግ በዓድዋ ላይ ከኢጣልያ ጦር ጋር በተደረገው ውጊያ ማለትም በዓድዋ ጦርነት ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ አደረገው በተባለው ተሳትፎ «ኢትዮጵያን በዓለም ታሪክ በጦር ኃይል ስምንት ጊዜ እጥፍ የሚበልጣትን አገር አሸንፋ ታዋቂ የነፃነት አገር እንድትባል አድርጓታል» በሚል የሚቀርበውን ታሪክ መመልከት ይበቃል።

የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ጸሐፌ ትዕዛዝ የሆኑት ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ እንደጻፉት ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ወደ ዓድዋ ሲዘምቱ በአራዳ ገነተ ጽጌ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘውን የቅዱስ ጊዮርጊስን ጽላት አስይዘው ነው የዘመቱት። ጦርነቱንም ቅዱስ ጊዮርጊስ የእርዳታ እጁን በመዘረጋቱ ኢትዮጵያ ድል እንዳደረገችና ብዙ የጠላት ሠራዊት እንዳለቀ አትተዋል።

በወቅቱ የነበረ አንድ የኢጣልይ ጋዜጠኛ ወደ አገሩ ባስተላለፈው መልዕክት አንድ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ጀግና እንደፈጃቸውና ይህ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ሠራዊት ጎን ተሠልፎ የኢጣሊያን ሠራዊት አርበደበደው የምንዋጋው ከሰው ጋር ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔርም ጋር ሰለሆነ በጦርነት ድል ልንመታ ችለናል ሲል ዘግቧል። በዚህም የተነሣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነቱን፣ ፈጥኖ ደራሽነቱን፣ ስለት ሰሚነቱንና አማላጅነቱን የሚያምኑት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን የቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት በተተከለበት፣ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራበት፣ በዓሉ በሚከበርበትና ስሙ በሚጠራበት ሥፍራ ሁሉ እየተገኙ በጸሎትና በምስጋና ያስቡታል፤ «ፍጡነ ረድኤት» ይሉታል።

ይህንን ሁሉ ሀታተ መዘርዘሬ በዐፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት በነበረው የኢትዮጵያ ሰንደ ዓላማ መሃል ያለውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ስዕል ከሃይማኖታዊነቱ ባሻገር ትርጉሙ ጠባቂ ሰማዕት ለኢትዮጵያ መሆኑን አጽዕኖት ለመስጠት ነው።

የቅዱስ ጊዮርጊስን መስቀል በሰንደቅ ዓላማቸው መካከል ባደረጉት በእንደ እንግሊዝ፣ ዴንማርክ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ወዘተ አገሮች የየአሩን ሰንደቅ አላማ ለማክበርና ከሰንደቁ በፊት ለመውደቅ እንደ ሃይማኖታቸው ስርዓት ቃለ መሀላ በመፈጸም ዜጋ የሚሆኑት የመላው ዓለም የእስልምና እምነት ተከቻዮች የቅዱስ ጊዮርጊስ መስቀል ላለባቸው ሰንደቅ ዓላማዎች ቃለ መሃላ የሚፈጽሙትና ለማሉበት ሰንደቅ በጦር ሜዳ ሕይወታቸውን የሚሰጡት የቅዱስ ጊዮርጊስን መስቀል ትርጉም በሃማኖታዊ ምልክትነቱ ሳይሆን በአገር ጠባቂነቱ ወስደውት ነው። ኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ጭምር ነብዩ መሐመድ ስለ ኢትዮጵያ በተናገሩት መልካም ነገር የሚኮሩትና የሚጠቅሱት ሃይማኖታቸው እስላም ስለሆኑ ሳይሆን ነብዩ «ኢትዮጵያ አትንኩ» ያሉት የኢትዮጵያ ጠባቂ የአደራ ቃላቸው አገራዊ ፋይዳው ስላለው ነው።

ባጭሩ በዐፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መሀል ያለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ምልክት ትርጉምም ልክ ከተለያየ ዓለም ወደ እንግሊዝ፣ ዴንማርክ፣ ስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ፊንላንድ፣ ወዘተ አገሮች የሚሄዱ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚምሉበት ሰንደቅ ዓላማ መሃል እንዳለው መስቀል አይነት አገራዊ ትርጉምና ፋይዳ ነው ያለው።

በሰንደቅ ዓላማው መሀል የቅዱስ ጊዮርጊስ አርማ የሌለበትን የዐፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አጥብቀው ከሚጠሉት ብሔርተኞች መካከል ቀዳሚዎቹ የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው። በሌላ አነጋገር በዐፄ ዮሐንስ ሰንደቅ ዓላማ ከሁሉ በላይ የዘመቱት የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን የሚሉን የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው። ዐፄ ዮሐንስ እድል አግኝተው ቀና ቢሉ ከሁሉ በላይ የሚያፍሩት የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን በሚሉት በትግራይ ብሔርተኞች ይመስለኛል። ዐፄ ዮሐንስ በተደራቢነት የሚናገሩትን ቋንቋዬ ነው ብለው ብሔራዊ ቋንቋ ያደረጉትን አማርኛን «በትግሬ ላይ የተጫነ» ብለው ከሁሉ በላይ የዘመቱት ነውር ጌጡ የሆኑት የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው።

ዐፄ ዮሐንስ ከሰመራ ከተማ በካቲት 11 ቀን 1873 ዓ.ም. ለጀርመኑ ንጉሥ ቀዳማዊ ዊልሄለም በጻፉት ደብዳቤ፤

«[አገሬ] በምስራቅ በደቡብ ወገንም ዲካው[ድንበሩ] ባሕር [ሕንድ ውቅያኖስን ማለታቸው] ነው። በምዕራብ በሰሜን ወገንም ባሕር በሌለበቱ ከኑብያ፥ ከካርቱም፣ ከስናር ፣ ከሱዳን በስተቀር ጋላ፣ ሻንቅላ፣ እናርያ፣ አዳል የያዘው አገር ሁሉ የኔ ነው። አሁን እንኳ በቅርብ ከሸዋ በታች ያለው ሐረር የሚባል አገሬ በቱርክ ተይዟል። ይህን ሁሉ መጻፈ ያገሬ ድንበሩ ይታወቅ ብዬ ነው።»

ሲሉ ያሰመሩትን የኢትዮጵያ ድንበር አፍርሰው የዛሬዋን ኢትዮጵያ «ምኒልክ ነጻ የነበሩ የአፍሪካ አገሮችን ወርሮ የፈጠራት የብሔር፣ ብሔረስችቦች እስር ቤት የሆነች ኢምፓዬር ናት» ብለው ከሁሉ በላይ በዐፄ ዮሐንስ አገር ላይ የዘመቱት፣ የዐፄ ዮሐንስን ኢትዮጵያ ያፈረሷትና ያደሟት «የዐፄ ዮሐንስ ልጆች ነን» የሚሉን ጉደኞቹ የትግሬ ብሔርተኞች ናቸው። እነዚህ አሳፋሪዎች «አባታችን ናቸው» የሚሏቸው ዐፄ ዮሐንስ ቀና ቢሉ የትኛውን የአባታቸውን ራዕይ ወረስን ብለው ይነግሯቸው ይሆን?

ማፈሪያዎቹ የትግሬ ብሔርተኞች በዚህ አላባቁም። አዲስ አበባን እንደ ኦነጋውያን ሁሉ ፊንፊኔ እያሉ በመጥራት ከኦሮሞ ውጭ ያለው የአዲስ አበባ ነዋሪ [ትግሬን ጭምር] እንደ ኦነጋውያን ሁሉ ሰፋሪ እያሉ ሲሳደቡ የሚውሉት ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ የበረራውን የዐፄ ዳዊት ቤተ መንግሥት ላለማስደፈር በአማራው በአዛዥ ደገልሃን የሚመራው የባሌ ጦር በዛሬው አዲስ አበባ ዙሪያ ተጋድሎ ሲያደርግ አብረው ሲፋለሙ የወደቁት የትግሬ መኳንንት ሮቤል ደም የፈሰሰበትን ምድር ነው።

ታሪኩን ለማታውቁ የትግሬ ገዢ የነበሩትና በዘመነ መሳፍንት ዘመን አንጋሽ የነበሩት ራስ ሚካኤል ስሑል በረራን ከግራኝ አሕመድ ለመከላከል በተደረገው ተጋድሎ የወደቁት የትግሬ እንደርታ ተወላጁ የትግሬ መኳንንት ሮቤል ዘር ናቸው። እፍረተ ቢሶቹ የትግሬ ብሔርተኞች የስሑል ሚካኤል ልጆች ነንም ይላሉ። ይህን የሚሉን እነዚህ አሳፋሪ ፍጡራን ግን የስሑል ሚካኤል እንሽላት[ስምንተኛ ትውልድ] የሆኑት ትግሬ መኳንንት ሮቤል የወደቁበትን የዛሬውን አዲስ አበባ አካባቢ የትግሬ መኳንንት ሮቤል ትውልዶችና አብረዋቸው የወደቁት የአዛዥ ደገልሃን ልጆች ርስት አይደለም ብለው የትግሬ መኳንንት ሮቤልንና የአዛዥ ደገልሃንን ትውልዶች ሰፋሪ እያሉ ከኦነጋውያን ጋር ሲሳደቡ እየዋሉ ነው። እንደሚኮሩባቸው ሁሉ እነ ዐፄ ዮሐንስን «አባቶቻችን ናቸው» እያሉ «አባቶቼ ናቸው» በሚሏቸው ወደምት ሰዎች ታሪክና ስራ ላይ የዘመቱና የእነዚህ ቀደምት ሰዎች አሻራ ያወደሙ እንደ ትግሬ ብሔርተኞች አይነት ፍጡር በታሪክ ውስጥ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ።

ምንጭ

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: