Orthodox Christians NOVAX & ARYNA Triumph in Australia | What Could be the Message?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 31, 2023

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 😇 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 መርቆርዮስ 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
🎾 በዘንድሮው የአውስትራሊያ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖቹ ኖቫክ ጆኮቪች (ኖ-ቫክስ) እና አሪና ዛባሌንካ ድል በድል ሆኑ | መልእክቱ ምን ይሆን?
የሰርቢያ ቴኒስ ኮከብ ኖቫክ ጆኮቪች እሑድ ቀን በሜልቦርን ከተማት ግሪካዊውን እስጢፋኖስ ትሲሲፓስን በሦስት ስብስቦች ነበር በቀጥታ በመቅጣትና ታላላቅ ውድድሮችንም በብዛት በማሸነፍ (፳፪/22 ግራንድ ስላም)የዓለምን የቴኒስ ክብረወሰን እኩል ያደረገው። አራቱ ታላላቅ የሜዳ ቴኒስ ውድድሮች፤ የአውስራሊያው ክፍት፣ የፈረንሳይ ክፍት፣ የእንግሊዙ ዊምብልደን እና የአሜሪካ ክፍት ናቸው።
ኖቫክ ጆኮቪች የኮቪድ ክትባትን ለመከተብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ባለፈው ዓመት መወዳደር አልቻለም ነበር።
ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት የሜዳ ቴኒሱን ዓለም በበላይነት በመቆጣጠር ላይ ያለውና የአሁኑ የዓለማችን ቍ. ፩ የቴኒስ ስፖርተኛ የሰርቢያ ኦርቶዶክሱ ኖቫክ ጆኮቪች እሑድ ዕለት የዘንድሮውን የአውስትራሊያ ክፍት ውድድር በአስገራሚ መልክ በማሸነፍ ታሪክ ሠርቷል።
ባለፈው ዓመት ላይ፤ በዚህ ቪዲዮ እንዳወሳሁት፤ ፀረ-ኮቪድ ክትባት አቋም ያለው ኖቫክ ጆኮቪች በአውስራሊያው ውድደ እንዳይወዳደር ታግዶ ነበር። እንዲያውም ወደ እስር ቤት ከገባ በኋላ ከሜልበርን አውስራሊያ ተጠርፎና የሦስት ዓመት ቪዛ እገዳ ተደርጎበት ነበር።
እ.ኤ.አ. በ 2022 ኖቫክ ጆኮቪች በመጀመሪያ ታሰረ እና ከዚያ የተባረረ ከዚያ ከተባረረ በኋላ ከቀድሞ የኢሚግሬሽን ሚኒስትር አሌክስ ሀይክ ኖቫክ ጆኮቪችን የኮቪድ ክትባትን ባለመከተቡና ፤ለሕዝብ ጤና እና ሥርዓቱ አደጋ ነው’ በማለት ከአውስራሊያ እንዲጠረፍ ተደርጎ የነበረው።
ዘንድሮ ግን ያውም የክትባቶች ቀንደኛ አቀንቃኝ ከሆነው የማይክሮሶፍት ባለቤት ከባለኃብቱ ቢል ጌትስ ፊት መቀዳጀቱ ድሉን የበለጠ ያጣፍጠዋል። ፍትሕ ሁሌም በመጨረሻ ታሸንፋለችና!
💭 የ2023 አውስትራሊያ ክፍት ውድድር ለመጨረሻው ዙር የደረሱት አራቱ ስፖርተኞች፤
- ❖ ኖቫክ ጆኮቪች፤ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ
- ❖ እስጢፋኖስ ትሲሲፓስ፤ የግሪክ ኦርቶዶክስ
- ❖ አሪና ዛባሌንካ፤ የቤሉሩሲያ ኦርቶዶክስ
- ❖ ኤሌና ሪባኪና፤ የሩሲያ-ካዛክ ኦርቶዶክስ
የሚገርመው፤ ኦርቶዶክስ ቤላሩሲያዊቷ “አሪና ዛባሌንካ” እና ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያዊቷ የረጅም እርቅት ሩጫ ንግሥት እና የዓለም ክብረ ወሰን ሰባሪዋ ለተሰንበት ግድይ ገጽታቸው መመሳሰሉ ነው።
🎾 Orthodox Christian Novak Djokovic Wins Australian Open a Year After Deportation
💭 The Serbian tennis star beat Stefanos Tsitsipas in three sets in the final in Melbourne on Sunday. Djokovic was unable to compete in the tournament last year over his refusal to have the COVID vaccine.
In 2022, Novak Djokovic was first jailed and then deported from Australia after former immigration minister Alex Hawke found the tennis star posed a risk to public health and order because Novaxx was not vaxxed.
💭 Australian Open 2023 — The four Finalists:
- ❖ Novak Djokovic: Serbian Orthodox
- ❖ Stefanos Tsitsipas: Greek Orthodox
- ❖ Aryana Sabalenka: Belarusian Orthodox
- ❖ Elena Rybakina: Russian-Kazakh Orthodox
Surprisingly, Orthodox Belorusian “Aryina Sabalenka” and Orthodox Ethiopian track and field queen and multiple world record holder, Letesenbet Gidey are similar in appearance.

______________
Leave a Reply