Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2022
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

እናት አክሱም ጽዮን እንዴት ሰነበተች? የጽዮንን ቀለማትስ መልሰዋቸው ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2022

👉 ገብርኤል 😇 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

❖❖❖ ኅዳር ፳፩ ጽዮን ማርያም ❖❖❖

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፪፤]✞✞✞

  • ፲፫ እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።
  • ፲፬ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።
  • ፲፭ አሮጊቶችዋን እጅግ እባርካለሁ፥ ድሆችዋንም እንጀራ አጠግባለሁ።
  • ፲፮ ካህናቶችዋንም ደኅንነትን አለብሳቸዋለሁ፥ ቅዱሳኖችዋም እጅግ ደስ ይላቸዋል።
  • ፲፯ በዚያ ለዳዊት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለቀባሁትም ሰው መብራትን አዘጋጃለሁ።
  • ፲፰ ጠላቶችንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፤ በእርሱ ግን ቅድስናዬ ያብባል።

ዛሬም ስለ ጽዮን ዝም ማለቱን የመረጡትና አክሱም ጽዮንን ለአውሬው ግራኝ አህመድ ዳግማዊ አሳልፈው የሰጧት ቃኤላውያን፤ ከአምስት መቶ ዓመታት በፊትም ለግራኝ አህመድ ቀዳማዊ በተመሳሳይ መልክ አሳልፈው ሰጥተዋት ይሆን? ከነበረ ይህ ትልቅ እርግማን ነው!

ዛሬ ከአዲስ አበባ በቀጥታ የሚተላለፉትን ክብረ በዓላት እስካሁን እንዳየሁትና እንደሰማሁት ማንም ስለ ቅድስት እናታቸው ስለ አክሱም ጽዮን ሲያነሱና ከሁለት ዓመታት በፊት የተሰውትን ሰማዕታት አባቶቻችንና እናቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችንን ሲያስታውሷቸው አልሰማሁም። በጣም ያሳዝናል!

በኢራን አንዲት ምስኪን ኩርድ ወጣት ሴት በፖሊስ ተገደለችብን ብለው ኩርዶቹም፣ ፋርሶቹም፣ ባሉቺዎቹም፣ አዛሪዎቹም ሁሉም በጋራ ያው ለሦስት ወራት ያህል ቁጣቸውን በአመጽ በመግለጽ ላይ ናቸው። የኛዎቹ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዓብያተክርስቲያናት ሁሉ እናት በሆነችው በአክሱም ጽዮን ታቦተ ጽዮንን ከወራሪ አህዛብ ሰአራዊት ለመከላከል ሕይወታቸውን ለሰውት አንድ ሺህ ለሚሆኑ ወገኖቻቸው፤ በትንሹና በዝቅተኛ ደረጃ እንኳን ሲናገሩ፣ ሲሰብኩ አይሰሙም። እንኳን ከሃይማኖት ወንድሞቻቸውና እኅቶቻቸው ጎን ሆነው ለቤተ ክርስቲያናቸው ሊታገሉና ሊዋጉ። እንደው እምነት ያለ ሥራ ብቻውን ያድናልን?

❖❖❖[የያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ ፪]❖❖❖

  • ወንድሞቼ ሆይ፥ እምነት አለኝ የሚል፥ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?
  • ፲፭ ወንድም ወይም እኅት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ፥
  • ፲፮ ከእናንተ አንዱም። በደኅና ሂዱ፥ እሳት ሙቁ፥ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል?
  • ፲፯ እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
  • ፲፰ ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
  • ፲፱ እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
  • አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?
  • ፳፩ አባታችን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን በመሠዊያው ባቀረበ ጊዜ በሥራ የጸደቀ አልነበረምን?
  • ፳፪ እምነት ከሥራው ጋር አብሮ ያደርግ እንደ ነበረ፥ በሥራም እምነት እንደ ተፈጸመ ትመለከታለህን?

ለመሆኑ ብጹእነታቸው ቅዱስ ፓትርያርኩስ ምን ብለው ይሆን? ምነው ድምጻቸውን አጠፉ?

ሕወሓቶችስ አምና በኅዳር ጽዮን ዕለት በአክሱም ቤተ ክርስቲያን ላይ በድፍረት ሰቅለውት የነበረውን የሉሲፈርን/ቻይናን ጨርቅ አውርደውትና በቦታውም የጽዮንን ሰንደቅ መልሰውት ይሆን? አፈናውን ካልቀጠሉበት በቅርቡ የምናወቀው ይሆናል።

👉 ከዓመት በፊት የቀረበ ጽሑፍ

እንግዲህ አብዛኛዋ ትግራይ ከፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ “ነጻ ከወጣች” ሦስት ወራት ሞልቶታል፤ ታዲያ ለምንድን ነው እስካሁን ዝርዝር መረጃ ያልወጣው? ምን እየጠበቁ ነው? ምንስ የሚደብቁት ነገር ይኖር ይሆን?

ዛሬ በጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዕለት ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ነስተውኝ የነበሩት የሚከተሉት በጣም ከባባድ የሆኑ ጥያቄዎች ናችው፤

በትግራይ ያሉ የጽዮን ማርያም ልጆች፣ የአባታችን የአቡነ አረጋዊ ልጆች፤ አባቶቼ፣ እናቶቼ፣ ወንድሞቼ፣ እኅቶቼ እና ልጆቻቸው ምን እየተመገቡ ነው? ለምንድን ነው ምንም ዓይነት ወሬ የማንሰማው?

ይህ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከጀመረበት ዕለትና ከመጀመሩም ከዓመታት በፊት ሳወሳው የነበረው ነው። እንዲህ የሚል ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፤

እውነት እንደሚሉን በትግራይ ጦርነት እየተካሄደ ነውን? አይመስለኝም! የሚመስለኝ “ውጊያ አለ” እያሉ በሁሉም በኩል የተቀነባበር ጭፍጨፋ በትግራይ ክርስቲያን አባቶቼ፣ እናቶቼ፣ ወንድሞቼና እኅቶቼ ላይ እየተካሄደ ነው። ይህ ደግሞ የሉሲፈራውያኑ ኤዶማውያንና እስማኤላውያን ጭፍሮች የሆኑት ኦሮሞዎች፣ አማራዎች፣ መሀመዳውያንና ኢአማንያን ሁሉ ምኞትና ፍላጎት መሆኑ የታወቀ ነው። በዓብያተ ክርስቲያናት፣ በገዳማትና ታሪካዊ ቦታዎች አካባቢ፤“ውጊያ እየተካሄደ ነው!” መባሉንና ጭፍጨፋዎቹም በእነዚህ ቦታዎች እየተካሄደ እንደሆነ ልብ እንበል። “እዚህ አለን!” እያሉ በመጥራት በወገኖቻችን ሕይወት ላይ የኩኩሉሉ ድብብቆስ ጨዋታ የሚጫወቱ ይመስላል። 😠😠😠

በእውነት ህወሀቶች ከሠሩት በጣም ግዙፍ ስህተት ተምረው የወገኖቼን ስቃይ እና ሰቆቃ ማቆም ቢፈልጉና ለደቡባውያን የሰጡትን በረከትና ዕድል ወደ ሰሜን የመመለስ ፍላጎት ቢኖራቸው ኖሮ ትግራይ ሆነው ሳይሆን ጥይት መተኮስ የነበረባቸው፤ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው ግራኝን በደፉትና የጦርነቱንም አቅጣጫ ወደ ደቡብ በቀየሩት ነበር። ላለፉት ሦስት ዓመታት ስለፍፍ የነበረው ይህን ነው፤ “ባካችሁ ጡት አጥባትችሁ ያሳደጋችሁትን ሰይጣን ድፉትና ወደ አስኩም ጽዮን መጥታችሁ ንስሐ በመግባት ኢትዮጵያን የመንፈሳዊ ማንነትና ምንነት ላላቸው ትክክለኛዎቹ ኢትዮጵያውያን አስረክባችሁ ታሪክ ሥሩ!” ስል ነበር። እውነት ለመናገር ልክ ጦርነቱ እንደተጀመረ ህወሀቶች በሦስት ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ የሚል እምነት ነበረኝ። እንዴት ነው በወሬ ካልሆነ፤ አንዴም በአግባቡ ሲበቀሉ የማናያቸው?

የሚገርም ነው፤ እንደ ጋዛ ገላጣማ ከሆኑና እስራኤል 24/7 ዓይኖቿን ከምትተክለበት ትንሽ ቦታ ፍልስጤማውያኑ አሸባሪዎች ለዓመታት ሮኬቶችን ወደ እስራኤል መተኮስ ችለው ያው ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ በቅተዋል። በሌላ በኩል እነ ሳውዲና ኤሚራቶች እንዲሁ 24/7 ክትትል ከሚያደርጉባት ከገላጣማዋ የመንም የአሥር ዓመት ዕድሜ እንኳን የማይሞላቸው ሁቲነፃ አውጪዎች እስከ ጂዳና ሪያድ ድረስ የሚደርሱ ሮኬቶችንና ድሮኖችን በመላክ የበቀል እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው።

ታዲያ የኔ ጥያቄ፤ ለሃያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ የነበሩት ህወሀቶች ተመሳሳይ ተግባር ለመፈጸም እንዴት ተሳናቸው? ምንም ዓይነት የወታደራዊ ዕውቀት የሌለን እኛ ታዛቢዎች እንኳን የተባበሩት አረብ ኤሚራቶች በአሰብ ቤዛቸው ተዋጊ አውሮፕላኖችንና ድሮኖችን ለክርስቲያን ኢትዮጵያ ጭፍጭፍጨፋ እያሰፈሩ መሆናቸውን ከሁለት ዓመት በፊት ከሩቅ ሆነን ስንጠቁም ነበር። እውነት የህወሀት ጄነራሎች ይህ መረጃ ሳይኖራቸው ቀርቶ ነውን? ዛሬም ኤሚራቶች የየመንን ደሴት ለዚሁ ተግባር በማዘጋጀት ላይ ናቸው፣ ግራኝ ከቱርክ ድሮኖችን ሊሸምት ነው ወዘተ” እያልን ነው፤ ነገር ግን የትግራይም ሆኑ የኢትዮጵያ ሜዲያዎች ለዚህ ትልቅ ጉዳይ ተገቢውን ትኩረት ሲሰጡት አይታዩም።

ለመሆኑ ለምን ይሆን በትግራይ ህፃናት ላይ የኬሚካል ቦምቦችን ሲጥል የነብረውን ምርኮኛ ኦሮሞ ፓይለትን ለቅቀውት ወደ ደብረ ዘይት እንዲመለስ ያደረጉት? የትግራይ ቀሳውስትና ካህናት በሰበባሰቡ እየተገደሉ ነው፤ እያለቁ ያሉት ክርስቲያኖች ናቸው፤ ታዲያ ምናልባት ዛሬም የስጋ ማንነትና ምንነት ላላቸው ደቡባውያን እየሠሩ ስለሆኑ ይሆን፤ “ሕዝቤ” የሚሉትን ሕዝብ ሊከላከሉት ያልቻሉት/ያልፈለጉት? የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው “ብሔር በሔረሰቦች” በጋራ ተናብበው በትግራይ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ እያካሄዱ ግፍ እየሠሩ ታዲያ ህወሃቶች ዛሬም “የብሔርብሔረሰቦች እኩለነት” የሚለውን የተሰወረና የተሸፈነ ንድፈ ሀሳብ ተጠቅመው ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት በሃገረ ኢትዮጵያ የነገሰውን የስጋን ማንነትና ምንነት ማለትም የስጋን አካል እንደ መንግስት አካል (ህግ) ፣ የሞትና ባርነትን ሥርዓት ለማስቀጠል ይሻሉን?

ዛሬ በደንብ ግልጽ የሆነልን የህወሀት/ሻዕቢያ/ኢሀዴግ/ኦነግ/ብልጽግና/አብን/ኢዜማ (ሁሉም የስጋ ማንነትንና ምንነትን በኢትዮጵያ ለማንገሥ የተነሱ የምኒልክ አራተኛ ትውልድ ናቸው) የተዘጋጁበት መልክና ምሳሌ ይህ መሆኑን ነው። የኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ እና የመንፈስ ማንነትና ምንነት ካለው የትግራይ ሕዝብ ታሪክ ጋር ምንም ዓይነት ግኑኝነት በሌለው “የትግራይ ባንዲራ” ላይ ያረፈው ባለ አምስት ፈርጥ ኮከብ በሕዝባችን ላይ ያስከተለብንን ስቃይና ሰቆቃ ካየን በኋላ ዛሬም ሲውለበለብ ማየታችን እውነትም እነዚህን ቡድኖች ሉሲፈር ለስሙና ለክብሩ ፈጥሯቸዋል፣ ምኞቱንም እያሟሉለት ነው ማለት ነው። እንድምናየውም አራተኛ ትውልድ የተባለው የምኒልክ መንግስት መጨረሻ ወይም ፍጻሜ የህወሀት/ሻዕቢያ/ኢሀዴግ/ኦነግ/ብልጽግና/አብን/ኢዜማ አገዛዝ ነው። እነዚህን ቡድኖች የፀነሳቸው የምኒልክ የስጋ ምኞት ነበርና። ዛሬ ያለው አገዛዝ/መንግስት የምኒልክ መንግስት ነው።

በትግራይ ሕዝብ ላይ ከዚህ በፊት ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ግፍና በደል እየደረሰበትና በደል ፈጻሚዎቹም አረመኔዎቹ እነ ግራኝ አብዮት አህመድ መሆናቸው በግልጽ እየታወቀ፤ እንዴት ነው ህወሀቶች የበቀል እርምጃ የመውሰድ ከበቂ በላይ ብዙ ምክኒያቶች ኖሯቸው በግራኝ አገዛዝ አባላት ላይ እስካሁን አንድም የጥቃት እርምጃ መውሰድ ያልቻሉት/ያልፈለጉት? ታዲያ ህወሃት እና ኦነግ/ብልጽግና/ብአዴን/አብን በእነ ሳሙራ ዩኑስ፣ ኬሪያ ኢብራሂም እና አረከበ እቁባይ በኩል አብረው ተናብበው እየሠሩ ይሆንን?

💭 ይህ ጥርጣሬየ ከንቱ ሊሆን የሚችለው የሚከተለውን ካየን ብቻ ነው፦

  • 👉 ፩ኛ. እነ ግራኝ አብዮት በእሳት ሲጠረጉ
  • 👉 ፪ኛ. ‘ህወሀትየሚለው የመጠሪያ ስም ሲቀየር
  • 👉 ፫ኛ. ባለ ሁለት ቀለሙ እና ኮከብ ያረፈበት የሉሲፈር ባንዲራ ከትግራይ ሲወገድ

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: