Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2022
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 27th, 2022

China Calls for Xi Jinping to Resign as Rare COVID Rule Protests Spread Across Major Cities

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 27, 2022

😇 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

💭 ጥብቅ የሆኑትን የኮቪድ ህግጋትን በመጻረር በቻይና ዋና ዋና ከተሞች ላይ ያልተለመደ ተቃውሞ በመስፋፋቱ ፕሬዚድንት’ዢ ጂንፒንግ’ ስልጣን እንዲለቁ እየተጠየቀ ነው።

የምዕራቧ ባቢሎን አሜሪካ ከባንዲራዋ አንዷን የሉሲፈር ኮከብና ሦስቱን ቀለማት ለላይቤሪያ ቆርሳ እንደሰጣች ፤ የምስራቋ ባቢሎን ቻይናም ለሕወሓት አንዷን የሉሲፈር ኮከብና ሁለቱን ቀለማት ቆርሳ ሰጥታዋለች። አሁን ሌላዋ የግራኝ ሞግዚት ባቢሎን ቻይናም መታመስ ጀምራለች።

👉 የሚቀጥሉትን ቀናት በጥሞና እንከታተላቸው!

ሁሉም አንድ በአንድ መውደቃቸው የማይቀር ነው። አይናችን እያየ መሆኑ ድንቅ ነው። አክሱም ጽዮናዊቷን ኢትዮጵያን የደፈሩትና ለፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ መሳሪያ ያቀበሉ፣ የዲፕሎማሲና የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉት የሚከተሉት ሃገራት ከፍተኛ ቀውስ እየገጠማቸው ነው፤

  • ቱርክ
  • ኢራን
  • ሳውዲ አረቢያ
  • የተባበሩት አረብ ኤሚራቶች
  • ፓኪስታን
  • ሱዳን
  • ሶማሊያ
  • ኬኒያ
  • ቻድ
  • ዩ ኤስ አሜሪካ
  • አውሮፓ
  • ሩሲያ
  • ዩክሬይን
  • እስራኤል
  • ቻይና

💭 Protesters pushed to the brink by China’s strict COVID measures in Shanghai called for the removal of the country’s all-powerful leader and clashed with police Sunday as crowds took to the streets in several cities in an astounding challenge to the government.

Police forcibly cleared the demonstrators in China’s financial capital who called for Xi Jinping’s resignation and the end of the Chinese Communist Party’s rule — but hours later people rallied again in the same spot, and social media reports indicated protests also spread to at least seven other cities, including the capital of Beijing, and dozens of university campuses.

Largescale protests are exceedingly rare in China, where public expressions of dissent are routinely stifled — but a direct rebuke of Xi, the country’s most powerful leader in decades, is extraordinary.

Three years after the virus first emerged, China is the only major country still trying to stop transmission of COVID-19 — a “zero COVID” policy that regularly sees millions of people confined to their homes for weeks at a time and requires near-constant testing. The measures were originally widely accepted for minimizing deaths while other countries suffered devastating wavs of infections, but that consensus has begun to fray in recent weeks.

Then on Friday,10 people died in a fire in an apartment building, and many believe their rescue was delayed because of excessive lockdown measures. That sparked a weekend of protests, as the Chinese public’s ability to tolerate the harsh measures has apparently reached breaking point.

Source

______________

Posted in Ethiopia, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 27, 2022

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፮/፳፯]❖❖❖

  • ፩ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
  • ፪ ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
  • ፫ ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።
  • ፬ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
  • ፭ በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
  • ፮ እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።
  • ፯ አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ። ማረኝና አድምጠኝ።
  • ፰ አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ። አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።
  • ፱ ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።
  • ፲ አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።
  • ፲፩ አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ።
  • ፲፪ የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ።
  • ፲፫ የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።
  • ፲፬ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: