“በዚያ ወራት ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል” [ዳን ፲፪.፩]
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2022
✞✞✞
እያንዳንዱ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ ቅዱሳን መላእክት አሉት
የእግዚአብሔር መልአክ ስሙ ድንቅ ነው … ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ
😇 ፈጣኑ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ አስቀድሞ የተጣላህን በቀል ባለመርሳት ጋሻህን አንሣ፤ ፈጣኑ መልአክ ሆይ ነበልባላዊ ሰይፍህን በጠላታችን በዲያብሎስ ላይ መዘህ ተነሣሣበት።
ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ኃይልህን የስው ኃይል ሊተካከለው አይችልምና የክርስቶስን ልጆች ጽዮናውያንን፤ “እንግደላቸው፣ ከምድረ ገጽ እናጥፋቸው ብለው በአባቶቼና እናቶቼ ላይ፣ በወንድሞቼና እኅቶቼ እና ልጆቻቸው ሁሉ ላይ የዘመቱትን የዋቄዮ-አላህ-ዲያብሎስ ጭፍሮች ጠላቶቻችንን ጭጋን በቀላቀለ ዓውሎ ነፋስ በታትነህ ከገጸ ምድር አጥፋቸው። ሕፃናትን በርሃብ ለመፍጀት የጨከኑትን እነዚህን አውሬዎች በእሳት ጠራርጋቸው። ድል አድራጊው መልአክ ሆይ፤ ያ የቀድሞ አመፀኛው አውሬ ዲያብሎስ የጥንት ተንኰሉ ሊተው አልቻለምና የጦር መሣሪያህን ታጥቀህ፣ መጥተህ እነ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊንና ጭፍሮቹን ሁሉ ድምጥማጣቸውን አጥፋቸው።
😇 እንኳን ለሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ የንግስ በዓል አደረሳችሁ። በዓሉን የበረከት በዓል ያድርግልን።
😇 ሊቀ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቅን
______________
Leave a Reply