Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2022
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ወደ ኤፌሶን ሰዎች ፬ | እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 14, 2022

  • ❖ ትሕትና
  • ❖ የዋሕነት
  • ❖ ቸርነት
  • ❖ እውነተኛነት
  • ❖ ርኅሩሕነት
  • ❖ ትዕግሥት
  • ❖ ፍቅር
  • ❖ ሰላም
  • ❖ አንድነት

❖ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ❖

በእውነት ይህ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት በጣም ድንቅ ነው። ለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ትውልድ የተላለፈ ሆኖ ነው ያገኘሁት።

በትግራይ በኩል አንዳንድ ግብዞች ባይጠፉም፤ ግን ዛሬ ይህ ሁሉ ግፍና በደል ደርሶባቸው እንኳን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለአንድነት እየሰሩ ያሉት የትግራይ ጽዮናውያን ብቻ ናቸው። እስኪ በዙሪያችን እንመልከት! ሜዲያዎቹን እንዳስስ፤ በተለይ “በአማራ” ስም “ለኢትዮጵያና ተዋሕዶ ክርስትናዋ እንታገላለን፣ ስለ ጽዮን ዝም አንልም!” የሚሉትን ግብዞች እንታዘባቸው። እውነቱን ተጋፍጠው እራሳቸውን ለይቅርታና ንስሐ ዝግጁ በማድረግ ፈንታ፤ በፈርዖናዊ ልበ-ደንዳናት “እግዚአብሔር አያውቀውም!” በሚል እርጉም እራስን የማታለያ አካሄዳቸው ዛሬም ከቸርነት፣ ከሰላም፣ ከፍቅርና ከአንድነት ይልቅ የጸበኝነትን፣ የጥላቻንና የውንጀላን እኩይ ተግባር አሰልቺ በሆነ ግትረኝነት፣ እልኸኝነትና በስንፍና ሲፈጽሙት የሚታዩት/የሚደመጡት። እስኪ ለመናዘዝ፣ ለመጸጸትና ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ የሆነ አንድ የአማራ ልሂቅ እንፈልግ። አሉ የተባሉትን “መምህራኑን” እና የሜዲያ ሰዎችን ጨምሮ አንድም አስተዋይ ሰው አይታይም/አይሰማም! ከዚህ ሁሉ ጉድ በኋላ እንኳን አማራው ከትግራይ ክርስቲያን ወንድሞቹ ጎን ከሚቆም ይልቅ ዛሬም ከአረብ፣ ከቱርክ፣ ከሱዳን፣ ከግብጽ፣ ከአፋር፣ ከሶማሌ ወይም ከኦሮሞ አህዛብ ጎን ለመቆም የመረጠ ይመስላል። ቅዱስ ጳውሎስ “እርስ በርሳችሁ ቸሮች ርኅሩሖች ሁኑ” አለን እንጅ “ለአሳዳጆቻችሁና ገዳዮቻችሁ አብልጣችሁ ቸሮች ርኅሩሖች ሁኑ!” አላለንም። እያየን ያለው ግን ሁሉም ሰሜናውያን እርስ በርስ አብልጠው ቸርና ርኅሩሕ በመሆን ፈንታ ገዳይ ጠላቶቻቸውን ሲያስቀድሙ ነው። የራሳቸውን ሕዝብ ከማዳን ይልቅ በጠላት ዘንድ መሞገሱን ይሻሉ። በጣም ያሳዝናል! እንደው ምን ያህል በአህዛብ ተጽዕኖ ሥር እንደወደቁና በተግባርም እንደ አህዛብ እየኖሩ ነው። አንዳቸውም እነዚህን ወርቃማ ክርስቲያናዊ ባሕርያት እንደማይከተሉ ዛሬ በግልጽ እያየነው ነው። እኔ በግሌ ምናልባት ከዲያቆን ቢንያም ፍሬው በቀር ሌሎቹ ሁሉ የእነዚህ ክርስቲያናዊ ባሕርያት ተጻራሪዎች ናቸው።

እነዚህን ክርስቲያናዊ የሆኑትንና መንፈሳዊ ማንነትን የሚያንጸባርቁትን ባሕርያት ሁሉ ያላሟላ እንዴት “ቄስ፣ ዲያቆን፣ ካህን ወይም ጳጳስ ነኝ” ለማለት ይደፍራል?! በእውነት ክርስቶስን እንደዚህ ስላልተማሩ ነውን? ወይንስ የቅዱሳኑ አባቶቻችን እርግማን?

❖❖❖ ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ ፬ ❖❖❖

  • ፩ እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤
  • ፪ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤
  • ፫ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።
  • ፬ በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤
  • ፭ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤
  • ፮ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።
  • ፯ ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን።
  • ፰ ስለዚህ። ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮን ማረከ ለሰዎችም ስጦታን ሰጠ ይላል።
  • ፱ ወደ ምድር ታችኛ ክፍል ደግሞ ወረደ ማለት ካልሆነ፥ ይህ ወጣ ማለትስ ምን ማለት ነው?
  • ፲ ይህ የወረደው ሁሉን ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ደግሞ ያው ነው።
  • ፲፩ እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤
  • ፲፪-፲፫ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።
  • ፲፬ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል በሰዎችም ማታለል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን ሕፃናት መሆን ወደ ፊት አይገባንም፥
  • ፲፭ ነገር ግን እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤
  • ፲፮ ከእርሱም የተነሣ አካል ሁሉ እያንዳንዱ ክፍል በልክ እንደሚሠራ፥ በተሰጠለት በጅማት ሁሉ እየተጋጠመና እየተያያዘ፥ ራሱን በፍቅር ለማነጽ አካሉን ያሳድጋል።
  • ፲፯ እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።
  • ፲፰ እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤
  • ፲፱ ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።
  • ፳ እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤
  • ፳፩ በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤
  • ፳፪ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥
  • ፳፫ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥
  • ፳፬ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
  • ፳፭ ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።
  • ፳፮ ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤
  • ፳፯ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
  • ፳፰ የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።
  • ፳፱ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
  • ፴ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
  • ፴፩ መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
  • ፴፪ እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: