Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2022
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የጰራቅሊጦስ ድንቅ ተዓምር፤ ሰክሬአለሁ፤ ቃላት የለኝም!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 11, 2022

😇 አዎ! ጰራቅሊጦስ ሐዋርያትን የወይን ጠጅ ሳይጠጡ እንዳሰከራቸውና በሀገሩ ሁሉ እንዳናገራቸው እኔም በእነዚህ ቀናት የሰከርኩ መስሎ ነው የተሰማኝ፤ ክርስቶስንና ቤተሰቦቹን በተመለከት ከብዙዎች ጋር በመነጋገር ላይ ነኝ፤ ሰው ሁሉ በበጎ እየቀረበኝ ነው። በእውነት ድንቅ ነው! በእውነት ጰራቅሊጦስ የሃይማኖትን አልጫነት የሚያጣፍጥ የልቡና ጨው ነው። ጰራቅሊጦስ በጭለማ ላሉ የሚያበራ የይቅርታ ብርሃን ነው።

  • ወደ ጸሎት ቤት ስገባ
  • ጸሎት ቤት ውስጥ

😇 ቅድስት እናታችንና ልጇ እግዚአብሔር ወልድ + የማርያም መቀነት + ክቡር መስቀል

ከጸሎት ቤት ስወጣ፤ ማረፊያ ወንበሩ ላይ፤ ይህን አየሁት። የሕፃን ልጅ መጫወቻ ነው፤

እንጠንቀቅ! ቀስተ ደመና የሰዶማውያን አይደለም! “ኬኛ!” ብለው ሊነጥቁን ግን ይሻሉ!

  • ከጸሎት ቤት ልክ ስወጣ ሜዳው ላይ ሰባት እርግቦችን አገኘሁ
  • ማታ ላይ ቤቴ እንደገባሁ መብራቱ ይህን ሠርቶ ነበር።
  • ጠዋት ላይ ደግሞ የእመቤታችን ሥዕል የማርያም መቀነትን ቤቴ ግርግዳ ላይ አንጸባርቆ ይታይ ነበር፤ ድንቅ ነው!

❖❖❖ እምዕርገት እስከ ጰራቅሊጦስ መዝሙር “በሰንበት ዐርገ ሐመረ” ❖❖❖

(በ፫/) በሰንበት ዐርገ ሐመረ ገሠፀ ባሕረ፤ ወገሠፆሙ ለነፋሳት፤ ወይቤሎሙ ኢትናፍቁ ወኢይምጻእ ኑፋቄ ውስተ ልብክሙ፤ በከመ ፈነወኒ አቡየ አነኒ እፌንወክሙ ውስተ ቤተ አቡየ ብዙኅ ማኅደር ቦቱ፤ ካዕበ እመጽእ ወእነሥአክሙ፤ ከመ ተሀልዉ ምስሌየ በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት።

አመላለሰ

ከመ ተሀልዉ ምስሌየ በመንግሥተ አቡየ፤

በመንግሥተ አቡየ ዘበሰማያት።

ዓራራት

ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት ወሰበረ ኆኃተ ብርት እግዚአ ለሰንበት አመ ሣልስት ዕለት ምዖ ለሞት ወዓርገ ውስተ ሰማያት።

ሰላም

ወልድ እኁየ ውእቱ ፍቁርየ ውእቱ ተንሥአ እሙታን ገብረ ሰላመ ለኵሉ ዓለም ዓርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ሎቱ ስብሐት ለዘቀደሳ ለሰንበት።

ዘቅዳሴ ምንባባት

  • ሮሜ ፲፥፩ ፡ ፍ፤
  • ፩ጴጥ ፫፥፲፭ ፡ ፍ፤
  • ግብ ፩፥፩ ፡ ፍ፤

ዘቅዳሴ ምስባክ፦

  • ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ፤
  • ወእግዚእነ በቃለ ቀርን፤
  • ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ። መዝ ፵፮፥፭

ወንጌል፦ ሉቃ ፳፬፥፵፭ ፡ፍ

ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ (እምቅድመ ዓለም)

❖❖❖ /7 እርግቦች ❖❖❖

  • ሐዋሪያት ተባበሩ
  • በአዲስ ቋንቋ እየተናገሩ
  • ቃሉን አስተማሩ

❖ ፯ / ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው

በቅዱስ መጽሐፍ አቆጣጠር ሰባት (፯) ፍጹምና ሙሉ ቁጥር በመሆኑ ከአንድ እስከ ሰባት ( ፩–፯ ) የተዘረዘሩት ምስጢራተ ቤተክርስቲያንም እንከንና ጉድለት የሌለባቸው ፍጹማን ናቸው።
ሰባት ቁጥር በመጽሐፍ ቅዱስ ሥርዓት ፍጹም ለመሆን ለማወቅ ከዚህ የሚከተሉትን ማስረጃዎች እንመልከት፦

❖ ሰባት ቁጥር ምስጢራት በቤተክርስቲያን፤

በመጽሐፍ ቅዱስና በስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ ስባት ቁጥር ብዙ ምሳሌ እንዳለው ይታወቃል፡፡ በዕብራዊያን ዘንድም ሰባት ፍጹም ቁጥር ነው፡፡ ምሳሌ ፳፬፡፲፮ እግዚአብሔር ከሰኞ
እስከ እሑድ ያሉትን ቀናት በሰባት ቁጥሮች ወስኗል ሕዝበ እስራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው በሲና በርሀ ሲጓዙ ይመሩት የነበሩት በ፯/7 ደመና እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ዘዳ ፲፫፡፳፩

ከዚህ ቀጥለንም ለቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮ የ፯ ቁጥር ምስጢራትን ምሉዕነትን የሚያስረዱ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በዝርዝር እንመለከታለን፦

❖ ሀ/ ሰባቱ አባቶች

፩. ሰማያዊ አባታችን እግዚአብሔር
፪. የነፍስ አባት
፫. ወላጅ አባት
፬. የክርስትና አባት
፭. የጡት አባት
፮. የቆብ አባት
፯. የቀለም አባት

❖ ለ/ ሰባቱ ዲያቆናት

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ
፪. ቅዱስ ፊልጶስ
፫. ቅዱስ ጵሮክሮስ
፬. ቅዱስ ጢሞና
፭. ቅዱስ ኒቃሮና
፮. ቅዱስ ጳርሜና
፯. ቅዱስ ኒቆላዎስ

❖ ሐ/ ሰባት የጌታ ቃላት /እኔ ነኝ

፩. የሕይወት እንጅራ እኔ ነኝ
፪. የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ
፫. እኔ የበጎች በር ነኝ
፬. መልካም እረኛ እኔ ነኝ
፭. ትነሣዔና ሕይወት እኔ ነኝ
፮. እኔ መንገድና ሕይወት ነኝ
፯. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ

❖ መ/ ሰባቱ ሰማያት

፩. ጽርሐ አርያም
፪. መንበረ መንግሥት
፫. ሰማይ ውዱድ
፬. ኢየሩሳሌም ሰማያዊት
፭. ኢዮር
፮. ራማ
፯. ኤረር

❖ ሠ/ ሰባቱ ሊቃነ መላእክት

፩. ቅዱስ ሚካኤል
፪. ቅዱስ ገብርኤል
፫. ቅዱስ ሩፋኤል
፬. ቅዱስ ራጉኤል
፭. ቅዱስ ዑራኤል
፮. ቅዱስ ፋኑኤል
፯. ቅዱስ ሳቁኤል

❖ ረ/ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት

፩. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
፪. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን
፫. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
፬. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን
፭. የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
፮. የፊልድልፍያ ቤተ ክርስቲያን
፯. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን

❖ ሰ/ ሰባቱ ተዐምራት

ጌታ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈጸሙ ተዐምራት

፩. ፀሐይ ጨልሟል
፪. ጨረቃ ደም ሆነ
፫. ከዋክብት ረገፉ
፬. ዐለቶች ተሠነጠቁ
፭. መቃብራት ተከፈቱ
፮. ሙታን ተነሡ
፯. የቤተ መቅደስም መጋረጃ

❖ ሸ/ ሰባቱ የመስቀሉ ቃላት

፩. አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ
፪. አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው
፫. ዛሬ ከእኔ ጋራ በገነት ትሆናለህ
፬. እነሆ ልጅሸ እናትህ እነሆት
፭. ተጠማሁ
፮. ተፈጸመ
፯. አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እስጥሃለሁ

❖ ቀ/ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን

፩. ምሥጢረ ጥምቀት
፪. ምሥጢረ ሜሮን
፫. ምሥጢረ ቁርባን
፬. ምሥጢረ ክህነት
፭. ምሥጢረ ተክሊል
፮. ምሥጢረ ንስሐ
፯. ምሥጢረ ቀንዲል

❖ በ/ ሰባቱ ዐበይት አጽዋማት

፩. ዐቢይ ጾም
፪. የሐዋርያት ጾም
፫. የፍልሰታ ጾም
፬. ጾመ ነቢያት
፭. ጾመ ገሀድ
፮. ጾመ ነነዌ
፯. ጾመ ድኅነት

ተ/ ሰባቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ነገሮች

፩. ትዕቢተኛ ዓይን ምሳ ፲፮፥፮፡፲፱
፪. ሃሰተኛ ምላስ
፫. ንፁህን ደም የምታፈስ እጅ
፬. ክፉ ሃሳብን የምታፈልቅ ልብ
፭. ለክፋት የምትፈጥን እጅ
፮. የሐሰት ምስክርነት
፯. በወንድሞች መካከል ጠብን የምታፈራ ምላስ

❖ ቸ/ ሰባቱ ፀሎት ጊዜያት

፩. ነግህ የጠዋት ጸሎት
፪. ሠለስት (የ፫ ሰዓት ጸሎት)
፫. ቀትር (የ፮ ሰዓት ጸሎት)
፬. ተሰአቱ (የ፱ ሰዓት ጸሎት)
፭. ሰርክ (የ፲፩ ሰዓት ጸሎት)
፮. ነዋም (የመኝታ ጸሎት)
፯. መንፈቀ ሌሊት (የሌሊት ጸሎት)

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: