Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2022
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ብጹዕነታቸው ባክዎ ለግራኝ በቀጥታ፤ “ሕዝቤን ልቀቅ!” ለአማራ ክልል ደግሞ፡ “መንገዱን ክፈት” ይበሏቸው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 8, 2022

✞✞✞[ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፱፥፲፫]✞✞✞

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። ማልደህ ተነሣ፥ በፈርኦንም ፊት ቆመህ በለው። የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እንዲያገለግሉኝ ሕዝቤን ልቀቅ።

🔥 እነዚኽ ፬ ኃይለ ቃላት ብቻ እኮ በቂ ነበሩ! የሙሴን አንድ መቶኛ እንኳን ማድረግ የሚችል አንድ አባት ይጥፋ?

  • ❖ እንደው የተዋሕዶ አባቶች ካላችሁ ኧረ ምነው? ኧረ ጉድ ነው! ምን ዓይነት ነገር ነው?
  • ❖ እንደው ይህ ሁሉ ግፍና ወንጀል እየተፈጸመ “በቃ!” ብላችሁ ካልተነሳችሁና ተንደላቅቆ የሚኑሩትን በጎቻችሁን፤ “ተነሱ!” ብላችሁ ካልጎተጎታችሁ ማን ሊጎተጉት ነው? ይህን እኮ ገና ትናንትና ነበር ማድረግ የነበረባችሁ።
  • ❖ ዛሬስ ምን እየጠበቃችሁ ነው? የሁለት ዓመቱ/ የአራት ዓመቱ ግድየለሽነት የተሞላበትና ተገቢ ያልሆነ ዝምታ አይበቃምን? ተዋሕዶ ክርስቲያኑ በጋችሁ እኮ ነው በአህዛብ ኦሮሞዎችና አማራዎች ሰይጣናዊ በሆነ ጭካኔ እያለቀ ያለው።
  • ❖ እንዴት ነው፤ ለግራኝ “በቃህ! ሕዝቤን ልቀቅ!” ማለት ያቃታችሁ?
  • ❖ ለምንድንስ ነው የኦሮሞን ሕዝብ የሚወክለው አረመኔ አገዛዝ በእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚጠየቅ ኦሮሞ ለተባለው ሕገ-ወጥ ክልል ማሳሰቢያ የማትሰጡት?
  • ❖ ለምንድንስ ነው የኦሮሞ ቅኝ ግዛት እንዲሆን በተደረገውና አማራ በተባለው ሕገ-ወጥ ክልል የሚኖሩት ተዋሕዷውያን በትግራይ ለሚገኙት ተዋሕዷውያን ወንድሞቻቸውና እኅቶቻቸውን መንገዱን ከፍተው ምግብና መድኃኒት ይገባለት ዘንድ ተግተው እንዲሠሩ አስቸኳይ ጥሪ የማታደርጉት?
  • ❖ በእነ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ ዳሞ፣ ደብረ አባይ፣ ማርያም ደንገላት፣ ውቅሮ ጨርቆስ የደረሰው ጥቃትና የዋልድባ ገዳም አባቶች ስቃይ ብቻ እኮ በእጅጉ ሊያነሳሳችሁ በተገባ ነበር።
  • ❖ ለኢ-አማንያኑ ሕወሓቶች እኮ ሕዝበ ክርስቲያኑ ቢወገድ፣ በተለይ አሁን ሕዝቤ ከገጠመው ከፍተኛ የመንፈሳዊ፣ የጤና እና ስነ ልቦናዊ ቀውስ የተነሳ? ወደፊት “ሽክም ይሆንብናል” ብለው ስለሚያስቡ ሕዝቤ ቢያልቅላቸው ግድም አይሰጣቸውም፤ እንዲያውም ኢ-አማንያኑን ብቻ ይዘው በቀላሉ ለመምራት ያስችላቸው ዘንድ ይህን አሰቃቂ ሁኔታ የሚፈልጉት ይመስላሉ። ኢሳያስ አፈወርቂም ያደረገው ይህን ነበር።
  • ❖ እናንተ ግን ይህን ያህል መታገሳችሁና ዝምታ ማብዛታችሁ ለጽዮናውያን ዕልቂት ከተጠያቂዎቹ አያደርጋችሁምን? በደንብ እንጅ!
  • ❖ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ኃላፊነት ለምንድን ነው የማትወጡት? እያለቁ ያሉት በጎቻችሁ ሁኔታ በእጅጉ አሳስቧችሁና በተከታታይ ወጥታችሁ አረመኔውን የኦሮሞ አገዛዝ በድፈረትና በቀጥታ መገሰጽ እኮ ግዴታችሁ መሆን ነበረበት። እንደ መስቀል ወፍ በዓመት ሁለት ጊዜ ብቅ እያሉ ማልቀስ በቂ አይደልም። እናንተ አርአያ ካልሆናችሁ ማን ሊሆን ነው? ለክርስቶስ ተቃውሚው ጭፍሮች ለምን እድሉን ትሰጧቸዋላችሁ? በጎቻችሁንስ ለምን ተስፋ ታስቆርጣላችሁ?
  • ❖ ወይንስ ቤተ ክርስቲያንን የማፍረሱ ሤራ ከእናንተም በኩል አለ?
  • ❖ ወይ በጎቻችሁን ዛሬውኑ አድኑ፤ አልያ ደግሞ ከአህዛብ ጅሃድ የሚተርፍ ገዳም ካለ ወደ ገዳም ግቡና ለሰማዕትነት ተዘጋጁ!

✞✞✞[ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፲]✞✞✞

  • ፩፤፪ እግዚአብሔርም ሙሴን። እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በግብፃውያን ያደረግሁትን ነገር ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጅህ በልጅ ልጅህም ጆሮች ትነግር ዘንድ፥ ይህችንም ተአምራቴን በመካከላቸው አደረግ ዘንድ የእርሱን የባሪያዎቹንም ልብ አደንድኜአለሁና ወደ ፈርዖን ግባ አለው።
  • ፫ ሙሴም አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፥ አሉትም። የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በፊቴ ለመዋረድ እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያገለግሉኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
  • ፬ ሕዝቤን ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ ነገ በአገርህ አንበጣዎችን አመጣለሁ፤
  • ፭ የምድሩንም ፊት ይሸፍኑታልና ምድሩን ለማየት አይቻልም፤ ከበረዶውም አምልጦ የተረፈላችሁን ትርፍ ይበሉታል፥ ያደገላችሁንም የእርሻውን ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፤
  • ፮ ቤቶችህም የባሪያዎችህም ሁሉ ቤቶች የግብፃውያንም ሁሉ ቤቶች በእነርሱ ይሞላል፤ አባቶችህ የአባቶችህም አባቶች በምድር ላይ ከተቀመጡበት ቀን ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያላዩት ነው። ተመልሶም ከፈርዖን ዘንድ ወጣ።
  • ፯ የፈርዖንም ባሪያዎች። ይህ ሰው እስከ መቼ ዕንቅፋት ይሆንብናል? አምላካቸውን እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ሰዎችን ልቀቅ ግብፅስ እንደ ጠፋች ገና አታውቅምን? አሉት።
  • ፰ ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን መልሶ አስመጣቸው። ሂዱ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን የሚሄዱት እነማን ናቸው? አላቸው።
  • ፱ ሙሴም። እኛ እንሄዳለን፥ የእግዚአብሔር በዓል ሆኖልናልና ታናናሾቻችንና ሽማግሌዎቻችን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም በጎቻችንና ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር ይሄዳሉ አለ።
  • ፲ ፈርዖንም። እናንተን ከልጆቻችሁ ጋር ስለቅቅ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ነገር ግን ክፉ ነገር በፊታችሁ እንደሚሆን ተመልከቱ።
  • ፲፩ እንዲህም አይይደለም፤ እናንተ ወንዶቹ ሂዱ፥ ይህን ፈልጋችኋልና እግዚአብሔርን አገልግሉ አላቸው። ከፈርዖንም ፊት አባረሩአቸው።
  • ፲፪ እግዚአብሔርም ሙሴን። በግብፅ አገር ላይ እንዲወጡ፥ ከበረዶውም የተረፈውን የምድርን ቡቃያ ሁሉ እንዲበሉ፥ ስለ አንበጣዎች በግብፅ አገር ላይ እጅህን ዘርጋ አለው።
  • ፲፫ ሙሴም በግብፅ አገር ላይ በትሩን ዘረጋ፥ እግዚአብሔርም የምሥራቅን ነፋስ ያን ቀን ሁሉ ሌሊቱን ሁሉ አመጣ፤ ማለዳም በሆነ ጊዜ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አመጣ።
  • ፲፬ አንበጣዎችም በግብፅ አገር ሁሉ ላይ ወጡ፥ በግብፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀመጡ፤ እጅግም ብዙ ነበሩ፤ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፥ ወደ ፊትም ደግሞ እንደ እርሱ አይሆንም።
  • ፲፭ የምድሩንም ፊት ፈጽመው ሸፈኑት አገሪቱም ጨለመች፤ የአገሪቱን ቡቃያ ሁሉ በረዶውም የተወውን በዛፉ የነበረውን ፍሬ ሁሉ በሉ፤ ለምለም ነገር ዛፍም የምድር ሣርም በግብፅ አገር ሁሉ አልቀረም።
  • ፲፮ ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ። አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ፤
  • ፲፯ አሁን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፥ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ አላቸው።
  • ፲፰ ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመነ።
  • ፲፱ እግዚአብሔርም ከምዕራብ ዐውሎ ነፋሱን አስወገደ፥ አንበጣዎችንም ወስዶ በኤርትራ ባሕር ውስጥ ጣላቸው፤ አንድ አንበጣም በግብፅ ዳርቻ ሁሉ አልቀረም።
  • ፳ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና የእስራኤልንም ልጆች አልለቀቀም።
  • ፳፩ እግዚአብሔርም ሙሴን። እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፥ በግብፅም አገር ላይ ሰው የሚዳስሰው ፅኑ ጨለማ ይሁን አለው።
  • ፳፪ ሙሴም እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፥ በግብፅም አገር ሁሉ ላይ ፅኑ ጨለማ ሦስት ቀን ሆነ፤
  • ፳፫ ማንም ወንድሙን አላየም፥ ሦስት ቀንም ሙሉ ከስፍራው ማንም አልተነሣም፤ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ግን በተቀመጡበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።
  • ፳፬ ፈርዖንም ሙሴን ጠርቶ። ሂዱ፥ እግዚአብሔርን አገልግሉ፤ ነገር ግን በጎቻችሁንና ከብቶቻችሁን ተዉ፤ ልጆቻችሁ ደግሞ ከእናንተ ጋር ይሂዱ አለው።
  • ፳፭ ሙሴም። አንተ ደግሞ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምንሠዋው መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ትሰጠናለህ።
  • ፳፮ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማገልገል ከእነርሱ እንወስዳለንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ፥ አንድ ሰኮናም አይቀርም፤ አምላካችን የምናገለግለው ምን እንደሆነ ከዚያ እስክንደርስ አናውቅም አለ።
  • ፳፯ እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ አጸና፥ ሊለቅቃቸውም አልወደደም።
  • ፳፰ ፈርዖንም። ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ አለው።
  • ፳፱ ሙሴም። እንደ ተናገርህ ይሁን፤ ፊትህን እንደ ገና አላይም አለ።

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 23, 2020

የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሞንቴ ኔግሮ ግዛት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አምፊሆሊጄ ሰሞኑን ይህን ተናገሩ፦

የሞንቴኔግሮ ፕሬዚደንት ዱካኖቪች የሰይጣንን ቤተክርስቲያን ይሰብካል እናም ኦርቶዶክስ ሞንቴኔግሮን ወደ አጋንንታዊና የሰይጣን ምድር ለመለወጥ ይሠራል”

አውሬው ከሩሲያ፣ ዩክሬይን፣ ሰርቢያና ሞንቴኔግሮ እስከ ኢትዮጵያ ባሉት ኦርቶዶክስ ዓብያተ ክርስቲያናት ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት አውጇል።

እንደ ሩሲያው ፓትርያርክ ኪሪል እና እንደ ሰርቢያው አቡ አምፊሆልጄ የመሳሰሉትን አባት ለቤተ ክርስቲያናችንም ተመኘሁ።

እንደነሱ ጀግና የሆኑ የተዋሕዶ ሌቀ ጳጳስ ቢኖሩ ኖሮ ለአውሬው አብዮት አህመድ እንዲህ ይሉት ነበር፦

አንተ ሰይጣን ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያን ወደ አጋንንታዊና የሰይጣን ምድር ለመለወጥ እየሠራህ ነው፤ እጅህን ከከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አንሳ፤ ክርስቲያኖች ደማቸዋን ላፈሰሱባት ሃገር መቅሰፍቱን እንዳታመጣ ከሃገሬ ጥፋ!”

አዎ! እንዲህ ያለ “ሰው ምን ይለኛል?” ሳይሆን “እግዚአብሔር ምን ይለኛል?” የሚል አባት ይስጠን!

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: