ቅዱስ ኡራኤል ኢትዮጵያን የቃል ኪዳን ሃገርሽ ብሎ ለጽዮን ማርያም ሰጥቷታል፤ መሬቱ የእግዚአብሔር እንጅ ‘ኬኛ!’ አይደለም
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2022
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 😇 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
❖❖❖ የሰው አሸናፊ የለም ፥ ሁሌ አሸናፊው እግዚአብሔር ብቻ ነው❖❖❖
አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ተግተው እየሠሩ ያሉትና የኤዶማውያኑ ምዕራባውያንና የእስማኤላውያኑ ምስራቃውያን ወኪሎች የሆኑት “የወልቃይት አስመላሽ ኮሚቴ” አባላትና ሲ.አይ.ኤ ያደራጃቸው እንደ ኢትዮ360 ያሉ ከሃዲ ጎሠኛ የኦሮማራ ሜዲያዎች ይህን ሰምተውት ይሆን?
መሬቱም፣ አፈሩም፣ ውሃውም፣ አየሩም፣ ሃገርም የእግዚአብሔር ነው። ታዲያ በእግዚአብሔር ምድር ላይ፣ በእግዚአብሔር ሃገር ላይ፣ የኛ መሬትና ሃገር ባልሆነ ለምንድን ነው፤ “ይህ የአማራ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞ፣ የሶማሌ ወዘተ መሬት ነው ሻንጣህን ጠቅልለህ ከዚህ ውጣ፣ ኬኛ፣ እርስቴ” እየተባባልን የራሳችን ባልሆነው ለምን እንበላላለን? ሰይጣን አዕምሯችንን እየሰለበና የእኛ ባልሆነው እያባለን ስለሆነ እንጂ ዓለም ሁሉ እኮ የእግዚአብሔር ናት፣ ሃገር የተባለነው ከዘረኝነት የጸዳነው እኛ ክርስቲያኖች ነን። አገራችን ምድር ላይ አይደለም፤ ሰማይ ላይ ነው!
______________
Leave a Reply