Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2022
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ለምንድን ነው ሕወሓቶች ምርኮኞችን ብቻ እያሳዩን ስለ ደብረ ዳሞ ገዳም አባቶች ዝም ያሉት? ምን የሚደብቁት ነገር አለ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 22, 2022

❖❖❖ Debre Damo Monastery / አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ ገዳም ❖❖❖

💭 ለመሆኑ የጽዮን እና ቀለማቷ ጠላቶች እነማን ናቸው? ቀለማቷን በሉሲፈር ኮከብ ☆ መተካት ይፈልጋሉን? ልክ እንደ፤

  • ደብረ ዳሞ
  • ✞ አክሱም ጽዮን
  • ደብረ አባይ

❖ ስለ ምርኮኞች፣ ዕለታዊ የፕለቲከኞች መግለጫ ብዙ እናያለን፣ እንሰማለን። ቤተ ክርስቲያንን ከፋፍለው ለማዳከም በመሻት ቤተ ክህነትንና ተቋማትን ለመመስረት ጥድፊያ ላይ ናቸው፤ ያው እንግዲህ ዓመት ሊሞላው ነው ስለ መነኮሳቱ፣ ካህናቱ፣ ቀሳውስቱ፣ ምዕመናኑ፣ ገዳማቱና ዓብያተ ክርስቲያናቱ ሁኔታ ግን ዝም፣ ጭጭ ብለዋል። የትግራይ ሙስሊሞች ረመዳን ሲያከብሩ እንኳን አሳይተውናል፤ ጽዮናውያን ግን ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ከትግራይም ከሱዳን ስደተኞች ካምፖችም ምንም ዓይነት መረጃ አይተንም ሰምተን አናውቅም። በዘር ማጥፋት ጦርነቱ የመጀመሪያ ወራት የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ትግራይን በሚቆጣጠርበት ወቅት ግን ብዙ መረጃዎች፣ ቪዲዮዎችና ምስሎች ሲለቀቁ እንደነበር እናስታውሳለን። ይህ ለምን ሆነ?

በደንብ እናስተውል፤ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ አባይ፣ ደብረ ዳሞ ሁሉም በጽዮን ማርያም መቀነት፤ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሸበረቁ ገዳማት ናቸው፤ ይህን ከትግራይ ሕዝብ ለመንጠቅና ተዋሕዷዊውንም ከአምላኩና ከጽዮን እናቱ ጋር ለማጣላት አህዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች፣ መናፍቃንና ሰለጠንን ባዮቹ “ኢ-አማንያኑ” የክርስቶስ ተቃዋሚዎች በህብረት ተግተው እየሠሩ ነው።

ይህን ያወሳሁት እነዚህ ገዳማት በተጨፈጨፉ ማግስት ነበር። እንግዲህ በዘንድሮው የኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያንን በሉሲፈር/ቻይና ባንዲራ ሸፍነዋት ነበር፤ አዎ! የጽዮንን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ሙሉ በሙሉ ከቤተ ክርስቲያኑ ሕንጻ አስወግደው። እንግዲህ የከሃዲዎቹ ኢ-አማንያን (አክሱማዊ ሆኖ ኢ-አማኒ? እጠየፈዋለሁ፤ ዋይ! ዋይ! ዋይ!) ተልዕኮና ዓላማ ምን እንደሆነ ለመረዳት ከዚህ የተሻለ ማስረጃ ሊኖር አይችልም። ሕወሓቶች ከሻዕቢያ፣ ኦነግ/ብልጽግና እንዲሁም ከዓለም አቀፉ የኤዶማውያንና እስማኤላውያን ኃይሎች ጋር አብረው እየሠሩ ያሉት የአክሱም ጽዮናውያንን የአምስት ሺህ ዓመት እምነት፣ ታሪክና ባሕል አስወግደው የራሳቸውን ሉሲፈራዊ አምልኮ ታሪክ እና ባሕል በሕዝቡ ላይ ለመጫን ነው፤ ‘የራሳቸውን’ ርካሽ ታሪክ ለመሥራት ነው። ወዮላቸው!

✞✞✞[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፪፥፲፪]✞✞✞

“እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።”

  • በቅዱሷ አክሱም ጽዮን ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል!
  • ❖ ከዋልድባ ገዳም ፩ሺህ መነኮሳትን ዓምና ልከ በዚህ ጾመ ሑዳዴ ያባረረውንና ድርጊቱንም የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
  • ❖ በደብረ አባይ ገዳም ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
  • ❖ በደንገላት ቅድስት ማርያም ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
  • ❖ በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
  • ❖ በውቅሮ አማኑኤል ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል
  • ❖ በዛላምበሳ ጨርቆስ ጭፍጨፋውን የፈጸመውን + የደገፈውን ሁሉ እግዚአብሔር በቅርቡ ይበቀለዋል

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: