Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2022
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን (ጸበል) ሕንፃ ላይ ነፈሰ = የቅዱስ ያሬድ ጸናጽል ውብ ዜማ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2022

✞✞✞ብዙ ፈውሶች የተካሄዱባት የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን (ፀበል) አዲስ አበባ ✞✞✞

የተጠመቅኩት፣ በመሰቀል የተሰቀልኩትና የተሰዋኹት ለአመኑኝና ቃሌን ለተቀበሉኝ ሁሉ ለስጋቸው በረከት ለነፍሳቸው ድኽነት ለመስጠት ነው!”

ለእያንዳንዱ ለተጠመቀው ክርስቲያን፣ ስጋው ለተቆረሠለት፣ ደሙ ለፈሰሰለትና እግዚአብሔር ሰው ለሆነለት ክርስቲያን ጠባቂ መላእክት አሉት።

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ከፍተኛ የትምህርት ተሰጥዎ ያለው በመሆኑ ትምህርቱን በጣም አስደናቂ በሆነ መንገድ ፈጽሞ ዲያቆን ሆነ ፡፡ ከመምህሩ ከአባ ጌዴዎን በተማረው መሠረት የእብራይስጥና የግሪክ ቋንቋዎችን ደህና አድርጉ ያውቅ ነበር ይባላል ፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስና እንዲሁም በውጭ አገር ቋንቋዎች የአጉቱን የመምህር ጌዴዎንን ሙያ አጠናቆ ቻለ ፡፡ ያሬድ አጉቱ ሲሞት የዐሥራ አራት አመት ልጅ ቢሆንም የአጉቱን ሙያና የትምህርት ወንበር ተረክቦ ማስተማር ጀመረ። በግንቦት ፲፩ (11) ቀን ስንክሳር በተባለው የቅዱሳን የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶና ተነሣሥቶ የዜማ ድርሰቶቹን አዘጋጀይላል።

በዚሁ ስንክሳር እንደ ተጻፈው እግዚአብሔር በዚች ምድር እንዲመስገን በፈለገ ጊዜ ያሬድን በራሱ ቋንቋ ሰማያዊ ዜማ እንዲያስተምሩት በአእዋፍ አምሳል ሦስት መላእክትን ከገነት ላከለት ይላል ፥፡ እነሱም ያሬድ ካለበት ሥፍራ አንጻር ባለው አየር ላይ ረበው(አንዣብበው) ጣዕም ያለውና ልብን የሚመስጥ አዲስ ዜማ አሰሙት ፡፡ ያን ጊዜ ያሬድ በጣዕመ ዜማቸው ተመስጦ ቁሞ ሲያዳምጥ ወዲያውኑ ወፎቹ በግዕዝ ቋንቋ ብጹዕ ወክቡር አንተ ያሬድ ብጽፅት ከርሥ አንተ ጾረተከ ውብጹዓት አጥባት አላ ሐአናከብለው በአንድነት አመስግኑት። ትርጉሙ የተመሰገንክና የተክበርክ ያሬድ ሆይ ፡ አንተን የተሸከመች ማኅፀን የተመስገነች ናት ፡፡ አንተን ያሳደጉ ጡቶችም የተመሰገኑ ናቸውብለው አመሰገኑት፡፡

ከዚያም ሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዜማ ወደ ሚዘምሩበት ወጋ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም አሳረጉት ፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመንበረ ጸባዖት ፊጓ ቁሞ ከሐያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በፍጥነት የሰማው ማኀሌት ሁቦ በመንፈስ እግዚአብሔር ተገለጸለትና በልቦናው የተሣለበትን ጰዋትዜ ዜማ በቃሉ ያዜም ጀመር ፡፡ ከዚያም ወደ ቀድሞ ቦታው ወደ አክሱም በተመለሰ ጊዜ ክጥዋቱ በ፫ ሰዓት ወደ አክሱም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ በታቦተ ጽዮን አንጻር ቆሞ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘርግቶ ፡ በከፍተኛ ድምፅ በአራራይ ዜማ ሃሌ ሉያ ለአብ ፡ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፡ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ቅዳሜሃ ለጽዮን ሰማየ ሳረረ ወዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘክመ ይገብር ግብራ ለደብተራብሉ ሥነፍጥረቱንና ሰማያዊት ጽዮንን አሰመልክቶ ዘመረ ይህችንም ማኅሌት አርያም ብሎ ጠራት ዞ አርያምም ማለት ልዕልና ሰባተኛ ሰማይ መንበረ እግዚአብሔር ማለት ነው ፡፡ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተመርቶ መላእክት እንደ ከበሮ እንቢልታ፣ ጸናጽል ፣ ማሲንቆና በገና በመሳሰሉት የማኅሌት መሣሪያዎች እየዘመሩ አምላካቸውን እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ስለስማ እነዚህን መሣሪያዎች በሥራ ላይ እንዲውሉ አደረጋቸው ፡፡

✞✞✞[ፈጥኖ የሚረዳን የቅዱስ ሚካኤል ክብር በሊቁ በቅዱስ ያሬድ ድጓ]✞✞✞

  • 😇 የ፺፱/99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ስለኾነው ስለ ቅዱስ ሚካኤል ክብር፣ ውበት፣ ምልጃ ማሕቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው እንዲኽ ይላል፦
  • ክብረ ሚካኤል ናሁ ተዐውቀ
  • በትሕትናሁ ዐብየ ወልሕቀ
  • ዲበ አእላፍ ዘተሰምየ ሊቀ
  • ዘይትዐፀፍ መብረቀ ይተነብል ጽድቀ”

(የሚካኤል ክብረ እነሆ አኹን ታወቀ፤ በትሕናውም ፈጽሞ ላቀ ከፍ ከፍ አለ፤ በአእላፍ ነገደ መላእክት ላይ አለቃን የተባለ መብረቅን የሚጐናፀፍ ርሱ ጽድቅን ይለምናል) ይላል፡

የ፺፱/99ኙ ነገደ መላእክት አለቃ ከመኾኑ ጋር ይልቁኑ ዮሐንስ በራእዩ በምዕራፍ ፰፥፪ ላይ “በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ” ካላቸው፤ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በመዠመሪያ የሚጠቀሰው ቅዱስ ሚካኤል ነውና ሊቁ ያሬድ፡

❖ “እስመ እምአፉሁ ይወጽዕ ነጐድጓድ

  • ሕብረ ክነፊሁ ያንበለብል ነድ
  • እምሊቃነ መላእክት የዐቢ በዐውድ
  • ሚካኤል ውእቱ መልአኩ ለወልድ”

(የወልድ አገልጋዩ ሚካኤል ነው፤ በዙሪያው ኹሉ ካሉት ከሊቃነ መላእክት ይበልጣል፤ የክንፉ መልክ ነባልባላዊ እሳትን ያቃጥላል፤ ከአንደበቱ ነጐድጓድ ይወጣልና) ይላል፨

❖ “አዕበዮ ንጉሠ ስብሐት

  • ለሚካኤል ሊቀ መላእክት
  • ዘይስእል በእንተ ምሕረት
  • መልአከ ሥረዊሆሙ ለመላእክት”

(የምስጋና ባለቤት ክርስቶስ ለመላእክት ጭፍሮች አለቃቸው የኾነ ስለ ምሕረት የሚማልድ የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ከፍ ከፍ አደረገው) በማለት ይጠቅሰዋል፡፡

የስሙ ትርጓሜንም ስንመለከት ሚካኤል ማለት ቃሉ የዕብራይስጥ ሲኾን ሚማለት “ማን”፤ ካ– “እንደ”፤ ኤል– “አምላክ” ማለት ነውና ሚካኤል ማለት “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት ነው፡፡

የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ይዞ

❖ “ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ

  • ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ”

(የያሬድ ልጅ ሄኖክ እንደጻፈው ከልዑል ስም ጋር ለተባበረ ስም አጠራርኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

😇 ቅዱስ ያሬድም፡

❖ “መልአከ ፍሥሐ ሚካኤል ስሙ

  • ለመላእክት ውእቱ ሊቆሙ
  • መልአኮሙ ሥዩሞሙ
  • የሐውር ቅድሜሆሙ እንዘ ይመርሆሙ”

(ስሙ ሚካኤል የተባለ የደስታ መልአክ ለነገደ መላእክት አለቃቸው ነው፤ የተሾመላቸው አለቃቸው ርሱ እየመራቸው በፊት በፊታቸው ይኼዳል) ይላል

በብሉይ ኪዳን ለአበው ነቢያት እየተገለጠ፤ ለሐዋርያትም በስብከት አገልግሎታቸው እየተራዳ፤ ለሰማዕታት፣ ለቅዱሳን አበው በተጋድሏቸው እየተገለጠላቸው አስደሳች መልኩን ያዩት ነበር።

ይኽነን የቅዱስ ሚካኤልን ውበት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡

❖ “መልአከ ፍሥሐ ዘዐጽፉ መብረቅ

  • ሐመልማለ ወርቅ ሚካኤል ሊቅ”

(መጐናጸፊያው መብረቅ የኾነ የደስታ መልአክ፤ አለቃ ሚካኤል የወርቅ ዐመልማሎ ነው)

የመልክአ ሚካኤል ደራሲም ይኽነን ውበቱን ሲገልጠው፡

❖ “ሰላም ለአክናፊከ እለ በሰማያት ያንበለብሉ

  • ከመ ሠርቀ ፀሓይ ሥነ ጸዳሉ”

(የጸዳሉ ውበት እንደ ፀሓይ አወጣጥ የኾነ በሰማያት ለሚያንበለብሉ ክንፎችኽ ሰላምታ ይገባል) ይለዋል፡፡

ቅዱስ ያሬድ ደግሞ፡

❖ “ውእቱ ሊቆሙ ወመልአኮሙ ሚካኤል ስሙ

  • ዐይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
  • ሐመልማለ ወርቅ”

(ዐይኑ የርግብ (እንደ ርግብ የዋህ፣ ጽሩይ) የኾነ ልብሱ የመብረቅ መጐናጸፊያ የኾነለት የወርቅ ዐመልማሎ ስሙ ሚካኤል የተባለ ርሱ የመላእክት አለቃቸው መሪያቸው ነው) ይላል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነትና አማላጅነት ቅዱስ ያሬድ እንዲኽ ይገልጠዋል፡

በ፲ወ፬ቱ ትንብልናከ ዐቢይ ልዕልናከ

  • በመንክር ትሕትናከ
  • አስተምህር ለነ ሰአልናከ”

(በዐሥራ አራቱ ልመናኽ ምልጃኽ፤ በታላቅ ልዕልናኽ በሚያስደንቅም ትሕትናኽ ሚካኤል ትለምንልን ዘንድ ማለድንኽ)

❖ “ዘወሀበ ትንቢተ ለኤልዳድ ወሙዳድ

  • አመ ምጽአቱ ይምሐረነ ወልድ
  • ሰአል ለነ ሚካኤል መንፈሳዊ ነገድ
  • ከመ ንክሃል አምስጦ እምሲኦል ሞገድ”

(ለኤልዳድና ለሙዳድ የትንቢትን ጸጋ የሰጠ የሚኾን ወልድ በሚመጣ ጊዜ ይምረን ዘንድ ከረቂቅ ነገድ ወገን የኾንኸው ሚካኤል ከሲኦል እሳታዊ ሞገድ ማምለጥ እንችል ዘንድ ለእኛ ለምንልን) ይላል፡፡

❖ “ከናፍሪሁ ነድ ዘእሳት አልባሲሁ ዘመብረቅ ሚካኤል ሊቀ መላእክት ውእቱ ይዕቀብክሙ ነግሀ ወሠርከ ሌሊተ ወመዐልተ” (ከናፍሮቹ የእሳት ልብሶቹ የመብረቅ የኾነ የመላእክት አለቃ ሚካኤል በተራኢነቱ በጠዋትም፤ በሠርክም፤ በቀንም በሌሊትም ይጠብቃችኊ) አለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፨

😇 ፈጣኑ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ አስቀድሞ የተጣላህን በቀል ባለመርሳት ጋሻህን አንሣ። ፈጣኑ መልአክ ሆይ ነበልባላዊ ሰይፍህን በጠላታችን በዲያብሎስ ላይ መዘህ ተነሣሣበት።

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: