Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2022
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 19th, 2022

ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ:- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን ፥ ልጆቹን ጨክኖ ያስራበበት ትውልዳችን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2022

❖❖❖ አክሱማውያኑ አባቶቼ የገነቡት የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ፤ አዲስ አበባ ❖❖❖

ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

✞ ይህ ግብዝ ትውልድ የቅዱስ ያሬድን ልጆች በረሃብና በጥይት እየቆላ “ፈሪሃ እግዚአብሔር አለኝ” እያለ ሲመጻደቅ፣ እንደ ፈሪሳዊው ‘ሸህ አቡ ፋና’ a.k.a አቡነ ፋኑኤል የቅዱስ ያሬድን ክብር ሲቀንስ መታየቱ ነው።

አሳዛኙ ነገር እንዲህ ያለው ድንቅ ሊቅ ፣ ጻድቅና ቅዱስ የዜማና የመጻሕፍት ደራሲ የሆነው አባት ቅዱስ ያሬድ በሀገሩ በኢትዮጵያ አንድ እንክብካቤ የጎደለውና አባቶቼ የገነቡት የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ እና አንድ የሙዚቃ ትምሕርት ቤት ብቻ በቀድሞው መንግስት እንዲሰየምለት ከመደረጉ በቀር በክብሩ መጠን አንድም ማስታወሻ የሚሆን ነገር በሀገሩ ላይ የለም። ይህ የሆነው ደግሞ የቅዱስ ያሬድም ሆነ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ትልቁ በደላቸው ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ ነው። እንግዲህ ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት ደቡባውያን ኢትዮጵያ ዘስጋ በሰሜናውያኑ ጽዮናውያን ላይ ካላቸው አጋንንታዊ ጥላቻ/ፍራቻ የተነሳ መንፈሳዊ የሆኑትን ብሎም ኢትዮጵያን ኃያል ያደረጓትን ነገሮች ሁሉ በማፈን ታሪካዊቷን ኢትዮጵያን / እስራኤል ዘነፍስን የማፍረስ ዕቅዳቸው ገና ዱሮ የጀመረ መሆኑን ነው።

አዎ! ላለፉት መቶ ሰላሳ ዓመታት አንዱም አገዛዝ ለቅዱስ ያሬድ፣ ለአፄ ዮሐንስ ለራስ አሉላ መታሰቢያ ሊሠሩላቸው አልፈለጉም፣ አንዱም አገዛዝ ከመንፈሳዊና መለኮታዊ ጥቅሙ አንፃር ኃይለኛና ቅዱስ የሆንውን የግዕዝ ቋንቋን በየትምሕርት ቤቱ እንዲሰጥና ብሔራዊ ቋንቋ ለማድረግም ሙከራ እንኳን አላደረጉም። ዛሬ በተቃራኒው አጋንንታዊ ይዘት ያላቸውን እንደ ኦሮምኛና አረብኛ ያሉ ቋንቋዎች በስፋት ሲያስተዋውቁ ይታያሉ።

የመንፈሳዊውን ጥቅም እንኳን ትተን ዓለማዊ በሆነ መለኪያ ብናየው እንኳን፤ ሰለጠኑ በሚባሉት ሃገራት አቤት አቤት! “ቅዱስ ያሬድ አውሮፓዊ ቢሆን ኖሮብዬ ሳስብ ምን ሊያደርጉት እንደሚችሉ መገመት ብቻ በቂ ነው ። መንገዱ ፣ አደባባዩ ፣ ተራራው ፣ ትምህርት ቤቱ ፣ ቁሳቁሱ ሳይቀር በስሙ በተሰየመ ነበር። አንድ ፒያኖና ቫዮሊን ይዘው ኦርኬስትራ ለመሩ ሰዎች ተአምር ለመፍጠርና ስማቸውን በመሸጥ የሀገር ገቢ ማግኛ ሲያደርጓቸው ሳይ እደነቃለሁ ። በጀርመን ሀገር በቦን ከተማ የቤትሆቨን ቤትን ለመጎብኘት ሄጄ ቅዱስ ያሬድን ሳስበው አልቅስ አልቅስ ነበር ያለኝ። ሰው ቢልዮን ዶላር የሚያስገባለትን ሀብት ከመጋረጃ ጀርባ ደብቆ እንዴት በድህነት ይማቅቃል? በቅዱስ ያሬድ አፍሮ በማያውቀው ካርል ማርክስ፣ ሌኒን፣ ቦብ ማርሌ፣ አኖሌ፣ ዊንስተን ቸርችል፣ ቻርለስ ደጎል፣ ካርል ሃይንስ ቡም፣ ክዋሜ ንክሩማህ ይመጻደቃል ።

ኢትዮጵያ ዘስጋ ለማታውቃቸው ለእነዚህ ባዕዳውያን ኃውልቶችን፣ አደባባዮችን ስትሰይም ፣ ለአቶ ቸርችል ጎዳና ፣ ለጀናራል ዊንጌት ደግሞ ትምሕርት ቤት በመሥራትና በመሰየም ያልበላትን ስታክ ትታያለች ። በአቡነ አረጋዊ ስም ቡና ቤት ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቢራ ለመሰየም ግን ቅሽሽ አይላትም ፤ የሚጠየፍና ሃይ ባይም ትውልድ የለም። ኢትዮጵያ ሀገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

አንድ የውጭ ሀገር ሰው ኢትዮጵያ ሄጄ ስለ ቅዱስ ያሬድ ላጥና ቢል መከራውን ነው የሚበላው ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በሕይወት ለመኖሯ እና በምድር ላይ እንድትቀጥል ካደረጓት ነገሮች አንዱና ዋነኛው የቅዱስ ያሬድ ሥራዎች መኖር ነው ። ያለ ቅዱስ ያሬድ ሥራዎች ቤተክርስቲያናችን ማሰብ በራሱ ከባድ ነው የሚሆነው ። ቅዱስ ያሬድ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ፣ ለሊቃነ ጳጳሳቱ ፣ ለካህናትና ለዲያቆናቱ ፣ ለመዘምራኑም ሁሉ ፤ ሞገስ ፣ ክብር ፣ እንጀራም ጭምር ነው ። ነገር ግን ይኽን ሁሉ ለሆነላቸው ጻድቅ አንዳቸውም አስታውሰው ግዙፍ ነገር በስሙ ሊሠሩ ሲነሳሱ አይታዩም።

ዛሬ ከአዲስ አበባ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሲተላለፍ የነበረውን መርሃ ግብር ለጥቂት ደቂቃዎች በቀጥታ ስከታተል ነበር። “ኡ! ኡ!” ነበር ያልኩት፤ ምክኒያቱም ወስላታው ፈሪሳዊ ሸህ አቡ ፋና a.k.a አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ ተጋብዞ በክብረ በዓሉ ላይ እንዲገኝ መደረጉ የቅዱስ ያሬድን ክብር ለመቀነስ ታስቦ መሆኑን ስለተረዳሁት።

👉 በስርጭቱ ወቅት የሚከተሉትን አጠር ያሉ መልዕክቶች ለማስተላለፍ ሞክሬ ነበር፤

ዋይ! ዋይ! ዋይ! በአክሱማውያኑ የቅዱስ ያሬድ ልጆች ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን የደገፉት እነ ሸህ አቡ ፋና a.k.aአቡነ ፋኑኤል፤ አባቶቼ የገነቧትን ብቸኛዋን የቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃን አረከሱብን! እግዚአብሔር ይይላቸው! 😠😠😠 😢😢😢

ዋይ! ዋይ! ዋይ! እነ ሸህ አቡ ፋና a.k.a አቡነ ፋኑኤል፤ አባቶቼ የገነቧትን ብቸኛዋን የቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃን አረከሱብን! እግዚአብሔር ይይላቸው! 😠😠😠 😢😢😢

የቅዱስ ያሬድ ልጆች በረሃብ እየረገፉ ነው፤ እነ ሽህ አቡ ፋና ተጋብዘው አሁንም ስለ ገንዘብና መኪና ይሰብካሉ! እግዚኦ! እግዚኦ! እግዚኦ! ማምለጥ የሚችል ከእነዚህ የዋቄዮአላህ ባሪያዎች ቶሎ ያምልጥ! እነዚህ ከሃዲዎች በጭራሽ የተዋሕዶ ልጆች አይደሉምና!

ልብ በሉ፤ ፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክብረ በዓላት በቀጥታ ሥርጭት እንዲካተቱ አድርጎ ፈቃዱን በመስጠት በመፍቀድ ለ666ቱ የ5G ቴክኖሎጂ ማስተዋወቂያ ያደረጉ ዘንድ እየተጠቀመባቸው ነው! በዚህ ረሃብና በሽታ በነገሠበት እንዲሁም ገንዘብ በጠፋበት ወቅት ዝግጅቶቻቸውን(የማንቂያ ደወል! ቅብርጥሴ) እያሉ ከኢትዮጵያ በብዛት በቀጥታ በማስተላለፍ ላይ ያሉት “ቤተ ክርስቲያንን እንወክላለን” የሚሉት ፈሪሳውያን ብቻ መሆናቸውን እንታዘብ። “ዝግጅቶቻችሁን ያለምንም መቆራረጥ በስልክ መስመር ለማስተላለፍ ከፈለጋችሁ አዲሱን/ዘመናዊውን የ666ቱን የ5G ቴክኖሎጂ ተቀበሉ!” በማለት የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ካድሬዎች ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው። የኢትዮ ቴሌኮም ሃላፊዋን እንመልከት የአቴቴ ዝናሽ አህመድ እኅት ነው የምትመስለው፤ በሁሉም ላይ የ666 የአውሬው ምልክት ተቀበሮባቸዋልና። ወስላታውን ሸህ አቡ ፋናa.k.a አቡነ ፋኑኤልን ጨምሮ።

❖❖❖ የጻድቁ ረድኤትና በረከት ከሀገራችን ከኢትዮጵያና ከህዝቧም ጋር ይሁን አሜን። ❖❖❖

💭 “ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርጓት እነ ቅዱስ ያሬድ እየመጡ ነውና ተዋሕዷውያን ወደ አንድ እንሰባሰብ”

💭 ሁሉም ከጸዳ በኋላ ቅዱስ ያሬድ በስውር እያሰለጠናቸው ያሉት ትክክለኛዎቹ ካህናት ይወጣሉ፤

እውነተኞቹን ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን የሚሰበስብ፣ ክርስቶስን የሚወድና እስልምናን የሚጠላ አንድ ቅዱስ ሰው በእግዚአብሔር ተቀብቶ ይወጣል። ያኔ የእስልምና አምልኮ ከምድረ ገጽ ይጠፋል። እውነተኞቹ ኢትዮጵያን የሚያውቋት ያውቁታልና ወደ አንድ ይሰባሰባሉ። መቶ ሚሊየን የሚሆነው ነዋሪ ኢትዮጵያን አያውቃትምና ሁሉም ይጠፋል። በአፋቸው ሳይሆን በህሊናቸው ኢትዮጵያንና ተዋሕዶን ከልባቸው የያዙት፣ ደሞዝ እየተከፈላቸው ካህናት የሆኑት ሳይሆኑ፣ በደሞዙ የሚንጠራሩት ሳይሆኑ፣ በዘረኝነት የተለከፉት ሳይሆኑ፣ ዘረኛ፣ ዘማዊና ጉቦኛ ያልሆኑት፣ ዘረኛ ያልሆኑትንና በፍቅር የሚመላለሱትን ምዕመናንን ጨምሮ ሁሉም በቅዱሱ ሰው ዙሪያ ተሰባስበሰው ኢትዮጵያን ይኖሩባታል።

†††[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፩፥፮]†††

ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይቀመጣል፥ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ታናሽም ልጅ ይመራቸዋል።”

❖❖❖ይህ ዓለም ካዘጋጀልን ወጥመድና መከራ ሰውሮ ወደ አንድነት ይሰብስበን!❖❖❖

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አባታችን ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ድንቅ ገዳም ይህ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 19, 2022

  • ✞ ቅዱስ ያሬድ የዜማ ሊቅ ብቻ አይደለም። አቡነ ያሬድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ የመጽሐፍ መምህር (ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ) ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ ልዑለ ስብከት ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ ሰማዕት ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ ባሕታዊ ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ መናኝ ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ የሱራፌል አምሳያ ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ ጥዑመ ልሳን ነው።
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ ነው።
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ነው።
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ መዓርዒረ ዜማ ነው።
  • ✞ አቡነ ያሬድ ካህን (ካህነ ስብሐት) ነው።
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ነው።
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ መዘምር ዘበድርሳን
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት)
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ ዓርከ ሊቃውንት
  • ✞ አቡነ ያሬድ መንፈሳዊ ደራሲ ነው።
  • ✞ ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያ ብርሃን ነው።
  • ✞ አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ
  • ✞ እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ
  • ✞ ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ
  • ✞ ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ
  • ✞ አእምሮው የመጠቀ
  • ✞ ድርሰቱ የተራቀቀ
  • ✞ እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ የሱራፌል አምሳያቸው ነው።

ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዱስ ያሬድን እንዲህ ሲል ያመሰገነው፦

“የመንፈስ ቅዱስ ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል”

“ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤ ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት

ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ።“

ቅዱስ ያሬድ አክሱም ጽዮንን እየተሳለማት ሣለ ክብርት እመቤታችን ለቅዱስ ያሬድ ተገልጣለት ቅዱስ ኤፍሬምንና ቅዱስ አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ አምጥታ ድርሰታቸውንና ቅዳሴያቸውን እንዲያሰሙት በማድረግ ቅዱስ ያሬድንም ዜማውን እንዲደርስ እረድታዋለች፡፡ ኹለቱንም ታላላቅ ቅዱሳን ነጥቃ ወደ ቅዱስ ያሬድ ካመጣቻቸው በኃላ “አንተ ውዳሴዬን፣ አንተ ቅዳሴዬን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ” ብላቸው እነርሱም ለቅዱስ ያሬድ ነግረውት በዜማ አድርሶታል፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመልክ በመልኩ እያደረገ ዜማውን ደረሰው፡፡ ዜማውንም ሲጨርስ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ በያዘችው የብርሃን ባርካው ተስፋውን ነግራው ዐርጋለች፡፡

ይኽም የቅዱስ ያሬድ ድርሰቱ መነሻውም ሆነ መድረሻው ፍጹም መንፈሳዊ እንደሆነ ያሳያል። አባቶቻችንም ይኽን መንፈሳዊ መገለጥ በሥዕልም ጭምር ገልጠውታል። (ሽሬ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ይኽ ዓይነት ሥዕል ከሚገኙበት ገዳማት ውስጥ የሚገኘው አንዱ ነው።)

አቡነ ያሬድ ይባርክበት የነበረው የእጅ መስቀሉ በ1985 ዓ.ም በሆድ አደር ሌቦች አማካኝነት ተሰርቆ ከሀገር ወጥቶ ነበር። በፈረንሳይ ሀገር ለጨረታ ቀርቦ በ15 ሚሊዮን ዶላር ተሸጦ ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሰርቆ ከወጣ ከ18 ዓመት በኃላ በ2003 ወደ አገራችን ተመልሶ መጥቷል። ሊመለስ የቻለውም “ሚስተር ዣክ” የተባሉ በጎ አሳቢ ሰው “…ይህን መስቀል ኢትዮጵያ ውስጥ ጎብኝቼዋለሁ፣ የኢትዮጵያ ንብረት ነው” በማለት ወደ ሀገራችን እንዲመለስ ከሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልጆች ጋር በተደረገ ርብርብ ጨረታውን በ15 ሚሊዮን ዶላር አሸንፈው የአቡነ ያሬድን የእጅ መስቀል ወደ አገራችን መልሰውታል። አምላከ ቅዱስ ያሬድ ክብር ያድልልን በእውነት!

አቡነ ያሬድ በምናኔ በኖረበት ቅዱስ ቦታ ላይ በስሙ ገዳም ተገድሞ መናንያን አሰረ ፍኖቱን ተከትለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ በረዶውንና ውርጩን ታግሠው በስሙ እየተማጸኑ ይኖራሉ፡፡ በቦታው እሁድ እሁድ ከመሬት ውስጥ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ቅዱስ ያሬድ መቋሚያውን ወርውሮ ያፈለቀው ፀበል ዛሬም አለ፡፡ ጻድቁ በተሰወረበት በደብረ ሐዊ ተራራ ላይ ብርድ በእጅጉ በጸናበትና በረዶ በሚፈላበት በዚያ አስቸጋሪ ቦታ ላይ እጅግ አስቸጋሪውን የአየር ጠባይ ተቋቁሞ በቦታው ላይ ቢያንስ 7 ቀን ሱባዔ የሚይዝ ካለ ራሱ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገለጥለት በቦታው ላይ የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ።

አክሱም አቅራቢያ ቁጭ ብሎ ከትሏ ምሳሌ ወስዶ በተማረበት ቦታ ላይ አንዲት እናት ብቻዋን ለቅዱስ ያሬድ አስደናቂ ቤ/ክ በ2010 ዓ.ም አሠርታለታለች። ይኽም ለጻድቁ ለአቡነ ያሬድ ተስላ ስለቷ ደርሶላት እንደሆነ በቦታው ላይ ተነግሮናል። ይኽም ድንቅ ምስክርነት አቡነ ያሬድ ከዜማ ደራሲም በላይ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው። በጸሎቱ ሀገርን የሚጠብቅ ባሕታዊ፣ በስሙ ለሚማጸኑት ሁሉ ከአምላኩ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን ደገኛ ጻድቅ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው።

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሙሉ አካሏና ብርሃኗ የኾነው አቡነ ያሬድ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ ሞትን ሳያይ የተሰወረው በዛሬዋ ዕለት ነው። የከበረች በረከቱ ትደርብን! በጸሎቱ ይማረን!!!

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: