Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2022
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 9th, 2022

Crazed Atheists Violently Disrupt Mass at Cathedral of Our Lady of The Angels

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2022

ሎስ አንጌሌስ | ያበዱ ኢ-አማኒያን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል ቅዳሴን በኃይል አወኩ።

እንግዲህ፤ ሴቶቻችን ጽንስ የማስወረድ መብት አይነፈጋቸው፤ የተረገዙ ጨቅላዎችን ካልፈለግናቸው የመግደል መብት አለን ፥ ሰውነቴ የእኔ ምርጫ(My Body My Choice!)” ከሚል ሉሲፈራዊ ወኔ በመነሳት ነው ትቃወመናለች!” የሚሏትን ቤተ ክርስቲያን ለማጥቃት የደፈሩት። እንግዲህ ይህ ነው ለሰይጣን መገዛት ማለት። ከእባብ መርዝ የተመረተውን የኮቪድ ክትትትባት ግን፤ ሰውነቴ የእኔ ምርጫ(My Body My Choice!)ብለው ላለመከተተብ ሲታገሉ አላየንም፤ ብዙዎቹ እንደ እንስሳ አንድ በአንድ ተከትበዋል።

በሃገራችንም፤ ላለፉት አራት ዓመታት በወኔ፤ “ጽዮናውያንን ካላጠፋን፣ ገዳማቱንና ዓብያተ ክርስቲያናቱን ካላፈረስን፣ ሴቶችን ካልደፈርን” በማለት ላይ ያሉት የዋቄዮ-አላህ ባሪያዎቹ አህዛብና ፕሬቴስታንት መናፍቃን እየፈጸሙ ያሉት ልክ ይሄንን ነው። መንፈሱ አንድ ዓይነት ነው፤ ከዲያብሎስ ነው፤ ጥልቅ የሆነ ጥላቻን ያነገበና በመላው ዓለም እንደ ሰደድ እሳት በመቀጣጠል ላይ ያለ እርኩስ መንፈስ ነው። ይህ መንፈስ ነው በተለይ እንደ አክሱማዊቷ ኢትዮጵያ፣ አርሜኒያ፣ ሩሲያና ዩክሬይን ባሉት በጥንታውያኑ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሃገራት ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንዲካሄድባቸው ትንቢት መፈጸሚያ የሆኑትን የሰይጣን አርበኞቹን በማነሳሳት ነው ጭፍጨፋ በማካሄድ ላይ ያለው።

💭 የዛሬው መረጂያዬ ሁሉ ከልደታ ጋር ተገጣጥሟል፤ ይገርማል!ሉሲፈራውያኑ የመናገርና ያቀራረብ ችሎታና ብቃት ያላትን ሄሜላ አረጋዊን ከጽዮናውያን በመንጠቅ ወይንም ለዚህ ጊዜ በአቴቴ መንፈስ ተለክፋ ጽዮናውያን ላይ ትነሳ ዘንድ መሆኑ ነው። በዚህች በዛሬዋ ዓለም ብዙ ድምጽ ለሌላቸው ለጽዮናውያን ነበር ድምጽ መሆን የሚገባት፤ ግን አልታደለችምና ነፍሷን ለመሸጥ በቅታለች። በዚህም ዓለም የመጠሪያ ስም በጣም ትልቅ ሚና ነው የሚጫወተው። ፀረ-ሰሜን፣ ፀረ-ጽዮናውያን የሆኑትን አፄ ምንሊክ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ፣ መንግሱት ኃይለማርያምና ኃይለማርያም ደሳለኝን ሥልጣን ላይ ያወጧቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዛኛው ክርስቲያን በመሆኑና ፈሪሃ እግዚአብሔር ስላለው በአንድ በኩል ሊደሉልት ሲሉ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ፤ ኢትዮጵያውያን እነዚህን የክርስቲያን ስሞች ጠልቶ ከአምላኩ፣ ሃይማኖቱና ታሪኩ እንዲፋታ ለማድረግ ነው።

  • ኢትዮጵያዊው ምንሊክ የንግሥት ሳባ ልጅ ቀዳማዊ ንጉሡን ተጸይፎ እንዲረሳው ጽዮናውያንን ከፋፍሎ ግዛታቸውን ለጣልያንና ፈረንሳይ የሸጠውን ኦሮሞ “ዳግማዊ ምንሊክን” አመጡት፣
  • ኦሮሞውን ኃይለ ሥላሴን በማምጣት ጽዮናውያን ከሥላሴ አምላካቸው እንዲላቀቂ፣
  • ኦሮሞውን መንግሱት ኃይለ ማርያምንና፣ ወላይታውን ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ሥልጣን ላይ በማውጣት ጽዮናውያን ከእናታቸው ከቅድስት ማርያም እንዲላቀቁ ለማድረግ ነበር።

ልክ መሀመዳውያኑ እናታችን ቅድስት ማርያም የምትለብሰውን ዓይነት አለባበስ ለብሰው አስቀያሚ፣ ነውረኛና ጽንፈኛ ተግባር በመፈጸም የወላዲተ አማልክን ክብር ለመቀነስ እንደሚሠሩት፣ ሸኾቻቸውም የክርስቶስ ቅዱሳንን መሰል ጢም አጎፍረው ጥላቻን፣ ሁከትንና አመፅን በመስበክ የአባቶቻችንን ስዕል በጥቁር ቀለም ለመቀባት እንደሚሹት። እንደ ጥምቀትና መስቀል ያሉት የተዋሕዶ በዓላት ከጥንት ጀምሮ ታቦት እየወጣ በአደባባይ ነው የሚከበረው፤ ይህ ያስቀናቸው የዋቄዮ-አላህ ባሪያዎች ከጥቂት ዓመታት ጀምሮ ጣዖታዊ በዓሎቻቸውን በአደባባይ ለማክበር በመወሰን የኦርቶዶክሳውያንን አደባባዮች፣ የጥመቀተ ባሕር ቦታዎቻቸውን በመንጠቅ ኦርቶዶክሳውያኑ ዲያብሎስ ጋኔኑን ባራገፈበት ቦታ ላይ ዳግም እንዳይወጡ፣ ይዞታዎቻቸውን እንዲያጡና ሥርዓታቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ ነው። የአረብ ሙስሊም ሃገራት ታሪክ ይህን ነው የሚያሳየን።

ግብረ ሰዶማውያኑ የማርያም መቀነትን/የኖህ ቀስተ ደመናን ሙሉ በሙሉ ሊነጥቁን ግማሽ መንገድ ሄደዋል። ለክልሎች የሉሲፈርን ባንዲራ የሰጧቸውም ልክ ኢለን መስክ ትዊተርን ለመጠቅለል እንደወሰነው፣ እንርሱም መቀነታችንን ሊያወልቁብን ስላሰቡ ነው።

ሌላው ደግሞ የሂትለር ናዚዎች የሠረቁትስዋስቲካ ነው። የስዋስቲካ ምስል እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ጥሩ የሆነ ትርጓሜ ከነበረው በኋላ ግን ለመጥፎ አገልግሎት በመዋሉ ስሙ ከጎደፉ ምስሎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ይህ ቅርጽ ምንጩ በሕንድ እንደሆነ የሚነገርለት ሲሆን፤ ስሙም በእጅግ ጥንታዊው ሳንስክሪት ቋንቋ ውስጥ ከሚገኝ ‹ስዋስቲ› ከሚል ሥርወቃል የተገኘ ነው – ትርጉሙም፤ ጥሩ፣ መልካም እነሆማለት ነው፡፡ ይህ ምልክትም በዓለም ላይ በብዙ ቦታዎች ላይ የሚገኝ ሲሆን በአጠቃላይ የጥሩ ነገር ምሳሌ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ይህ ቅርጽ በክርስትናም ውስጥ አገልግሎት ሰጥቷል፡፡ በክርስትና መንፈሳዊ እንቅስቃሴን – የመንፈስ ቅዱስን መውረድ እና በአጠቃላይ መንፈስ/ መንፈሳዊነትን ይጠቁማል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባለመንጠቆ መስቀልን ይጠቁማል ፥ የመንጠቆው መኖርም ክርስቶስ በሞት ላይ ድል መቀዳጀቱን የሚያመሰጥር ሲሆን በተለያዩ አብያተክርስቲያናትም ይገኛል፡፡ አንዳንዶች በአስራ ሁለተኛው ክፍለዘመን የተገኙ እና ይህንን መስቀል የያዙ አብያተክርስቲያናቶች መኖራቸውን ይናገራሉ፡፡ በላሊበላም ይህ መስቀል በመስኮቶች ላይ ይታያል፡፡

እኔ በግሌ፤ የዋቄዮ-አላህ ባሪያዎች የዳኑት ድነው ሌሎቹ እስካልተጠረጉ ድረስ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የደመራ በዓልን ማክበር አልሻም። አየን አይደል?! ዲያብሎስ አባታቸው ቀጣፊ፣ ገልባጭ፣ አታላይ፣ አስመሳይ፣ ሌባና ገዳይ አይደል።

ከአራት ዓመታት በፊት ‘አህመድ’ የተሰኘውን መጠሪያ የያዘውን ግራኝ አብዮትን ሥልጣን ላይ አውጥተው ወዲያው በብዙዎቹ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቱ ሉሲፈራውያኑን በጣም ነበር ያስደነቃቸው፤ እንዲህ በቀላሉ ይሆናል ብለው አልጠበቁምና። አሁንማ “መሀመድ” የተባለውን ጂኒ ጃዋርን የግራኝ ተተኪ ለማድረግ በመሥራት ላይ ናቸው። ሃቁ ግን፤ የዋቄዮ-አላህ ባሪያዎች የሆኑት አህዛብ ሥልጣን ላይ ወጥተው የእምቤታችን እርስት የሆነችውን ኢትዮጵያን ያስተዳድሩ ዘንድ እግዚአብሔር አይፈቀድላቸውም። ይህን “ክርስቲያን ነኝ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ!” የሚል ወገን ሁሉ በድፍረት፣ በራሱ እና በአምላኩ በመተማመን ወንድ ሆኖ ሊናገረው ይገባዋል።

💭 አሁን የጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ስም ላይ እናተኩር፤ ‘ሄርሜላ’ የእመቤታችን አያትና የቅድስት ሐና እናት ስም ነው፤

😇 ሰባተኛዪቱ እንቦሳ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየሁ (ቴክታ)

በቅድስና የሚኖሩ ነገር ግን መካን የነበሩት ቴክታና ጴጥርቃ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈች ሊቅ) አለና ሂደው ነገሩት፡፡ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም፤ እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው፡፡ እነርሱም ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም ረከብኩ ስእለትዬ፤ ረከብኩ ተምኔትዬ” /የተሳልኩትን አገኘሁ፤ የተመኘሁትን አገኘሁ/ ሲሉ ሄኤሜንአሏት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ከኢያቄምና ከሐናም በጨረቃ የተመሰለች ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡

💭 Crazed leftists stormed Sunday mass at the Cathedral of Our Lady of the Angels dressed as handmaid’s tale characters to protest in support of abortion.

The godless pro-abortion group “Ruth Sent Us” planned protests this Mother’s Day at Catholic Churches around the country.

The fact that they chose Mother’s Day for their national protest is even more ghoulish than usual. The protesters attempted to shut down the Catholic service.

Security guards and parishioners forced them out of the cathedral.

❖❖❖ Cathedral of Our Lady of the Angels ❖❖❖

What historically took centuries to construct was accomplished in three years in the building of the 11-story Cathedral of Our Lady of the Angels. This first Roman Catholic Cathedral to be erected in the western United States in 30 years began construction on May 1999 and was completed by the spring of 2002.

Spanish architect, Professor José Rafael Moneo has designed a dynamic, contemporary Cathedral with virtually no right angles. This geometry contributes to the Cathedral’s feeling of mystery and its aura of majesty.

Cathedral Design

The challenge in designing and building a new Cathedral Church was to make certain that it reflected the diversity of all people. Rather than duplicate traditional designs of the Middle Ages in Europe, the Cathedral is a new and vibrant expression of the 21st century Catholic peoples of Los Angeles.

Just as many European Cathedrals are built near rivers, Moneo considered the Hollywood Freeway as Los Angeles’ river of transportation, the connection of people to each other. The site is located between the Civic Center and the Cultural Center of the city.

“I wanted both a public space,” said Moneo, “and something else, what it is that people seek when they go to church.” To the architect, the logic of these two competing interests suggested, first of all, a series of “buffering, intermediating spaces” — plazas, staircases, colonnades, and an unorthodox entry.

Worshippers enter on the south side, rather than the center, of the Cathedral through a monumental set of bronze doors cast by sculptor Robert Graham. The doors are crowned by a completely contemporary statue of Our Lady of the Angels.

A 50 foot concrete cross “lantern” adorns the front of the Cathedral. At night its glass- protected alabaster windows are illuminated and can be seen at a far distance.

The 151 million pound Cathedral rests on 198 base isolators so that it will float up to 27 inches during a magnitude 8 point earthquake. The design is so geometrically complex that none of the concrete forms could vary by more than 1/16th of an inch.

The Cathedral is built with architectural concrete in a color reminiscent of the sun-baked adobe walls of the California Missions and is designed to last 500 years.

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግራኝ ኢትዮጵያን ለአረብ ሸጧታል | በድጋሚ መታየትና መነበበ ያለበት ከ፫ ዓመታት በፊት ልክ በልደታ ዕለት የቀረበ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2022

💭 የረመዳን ጋኔን በ አሰላ | የተዋሕዶ ልጆችን አባርራችሁ ብቻችሁን ልትኖሩባት? | አይይ! እሳት ይወርድባችኋል እንጂ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2019

“አሰላ”የሚለው ቃል “እስላም” ወይም “አላህ” ከሚባሉት ቃላት ጋር ተመሳስሎባቸዋል…

ለተጠሩበት ጂሃድ የረመዳን ጊዜን መምረጣቸው የአላሃቸው ፍላጎት ነው፣ ግራኝ አህመድ ሲያደርገውም የነበረው ቤተክርስቲያንን ማጥቃት እና ማቃጠል ነው፣ ልደታ ማርያምን ጠብቀው ቅድስት ማርያምን መዳፈራቸው ደግሞ ዲያብሎሳዊ ሤራቸውን የሚያጋልጥ ነው።

የቪዲዮው መጨረሻ ክፍል ላይ የሚታየው ነገር እንደ ትንቢት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባዋል። ከፋንም አልከፋንም ይህ ነገር መምጣቱ የማይቀር ነው፤ ፍየሎቹ እግዚአብሔር አምላክን እጅግ በጣም እያስቆጡ ነውና መልሱን በቅርቡ ይሰጣቸዋል።

የዋቄዮ አላህ ልጆች በአሰላ ክርስቲያኖች ላይ ከመስከረም ወር አንስቶ ያካሄዱት ጂሃዳዊ እንቅስቃሴ ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ነው፦

***መስከረም ፪ሺ፲፩ ዓ.***

ከወደ አሰላ የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ለረጅም ጊዜ ተዋልደውና ቤተሰብ መስርተው በሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት በማድረስ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ በሚሉ ኃይሎች፣ ከፍተኛ ጭንቀት በሰዎች ዘንድ ፈጥሯል።

የሃይማኖትማጽዳት ወንጀል በአሰላ አንዣቧል

አሰላ ከተማ በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል ተፈጥሮ ነበረው ከፍተኛ ግጭት በውይይት ተፈታ ነገር ግነ ግጭቱን ያስነሱት የቤተ ክርስቲያን አጥር ላይ የኦነግን ባንዲራ እንሰቅላለን ሲሉ አይቻል ሲባሉ በጉልበት ፤በግድ ለመስቀል ሲሞክሩ ክርስቲያኖች ተቃውመው እነዳይሰቀል ሲሞክሩ ሌላ አለማ ያለቸው አክራሪ እስለሞች ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው ክርስቲያኑን ለማጥቃት ቢሞክሩም አልተሳካለቸውም፤ በሚገርም ሁኔታ በብዛት የተጎደዱት ሙስሊሞች ናቸው በአሁን ሰዓት በአሰላ ከተማ ሰሞኑን ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በእርቅ መፈታቱ ተገለፀ።

***መጋቢት ፪ሺ፲፩ ዓ.***

በአሰላ ዜጎች ክልሉን ለቃችሁ ካልወጣችሁ እየተባሉ በዛቻ ከፍተኛ ስጋት ላይ እንደወደቁ ሕብረ ራዲዮ ዘገባ። ድርጊቱ እልቂት ከማድረሱ በፊት የክልሉ ሆነ የፌደራል መንግስት ሀላፊነቱን እንዲወጣ የከተማዋ ነዋሪዎች እያሳሰቡ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ አሰላ ሰሞኑን የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ቤት ላይ ወረቀት እየለጠፉ በተለይ የንግድ ድርጅት ያላቸውን በአስቸኳይ ለቃችሁ ሂዱ የሚል ማስፈራሪያ፣ በተደራጁ ከከተማዋ ዙሪያ በመጡ ጽንፈኛ ቄሮዎች እየተጠናከረ መምጣቱን የህብር ሬዲዮ የአካባቢው ምንጮቹን ገልጾ ዘግቧል።

የወጣቶቹ ድርጊት ለማንም የከተማዋ ነዋሪ ለአካባቢው አስተዳደር የተሰወረ አለመሆኑን የጠቀሱት የሕዝብ ራዲዮ ምንጮች፣ ይህ ዘር ላይ ያነጣጠረው ማስፈራሪያ፣ ዛቻና ወረቀት ለይቶ መለጠፍ፣ ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን ፣ የክልሉ መንግስት ሆነ የፌደራል መንግስቱ ግጭት ተከስቶ ንጹሃን ከመጎታቸው በፊት ሁኔታውን በአስቸኳይ እንዲያስቆም ሲሉ እነዚሁ የአካባቢው የህብር ራዲዮ ምንጮች ገልጸዋል ።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ወደ አካባቢው በፍጥነት መጥተው ሁኔታውን እንዲያዩ ሲሉ ለአካባቢው የዜና ምንጫችን ስጋት ላይ የወደቁት ወገኖች ጥሪ ማቅረባቸው ሕብረ ራዲዮ የዘገባ ሲሆን፣ “የመከላከያ ሰራዊቱ ዜጎች ከተገደሉ ሴቶች ከተደፈሩ ከተሳደዱና ከተፈናቀሉ በኋላ፣ ሳይሆን አስቀድሞ ሊደርስልን ይገባል። የክልሉ የአካባቢው አስተዳደር ስጋቱን በአግባቡ ተረድቶ ወጣቶቹን ለማስቆም ምንም ፍላጎት አለማሳየቱ፣ ቅስቀሳውን እያደረጉ፣ “ውጡ ፣ ለቃችሁ ሂዱ!” የሚል ወረቀት በአደባባይ በልበ ሙሉነት እየለጠፉ ዝም መባላቸው፣ በተዘዋዋሪ የሚፈልገው ስለመሆኑም አመላካች መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ከጥቂት ወራት በፊት የአሰላ ነዋሪዎች የመስቀል በ’አልን እንዳያከብሩ፣ በከነቲባዋ ወ.ሮ ዘይነባ ድጋፍ፣ ከውጭ የመጡ ቄሮዎች ህዝቡን ሲያሸብሩ ነበር።

ክልሉን በአሁኑ ጊዜ የምታስተዳድረው በኦህዴድ/ኦዴፓ ውስጥ ጽንፈኛ አመለካከት አላት የምትባለዋ ወ/ሮ ጠይባ ሁሴን ናት።

***ግንቦት ፩ (ልደታ ማርያም) ፪ሺ፲፩ ዓ.***

አሰላ ላይ ረብሻ እንዳለ የሚጠቁሙ መረጃዎች እየተሰሙ ነው። መረጃዎቹ የሚጠቁሙት አሰላ የማርያም ቤተክርስቲያን ጥምቀት ባህር ወይም የታቦት ማረፊያ ቦታ ላይ መስጊድ መሰራቱን ተከትሎ የማርያም ቤተክርስቲያን ደውል ተደውሎ በትላንትናው ዕለት መስጊዱን አፍርሰውታል። በአሰላ እየተደረገ ያለውን ተግባር በመቃወም ዛሬ ሰልፍ ወጥተው የነበሩት ክርስቲያኖች ጋር አለመግባባት ተከስቶ ከፍተኛ ረብሻ መከሰቱና እንዳልበረደም ተሰምቷል።

መረጃዎቹ የሚጠቁሙት በአሰላ ከተማ 01 ቀበሌ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ (አሁን ፖሊ-ቴክኒክ መሰለኝ) አጠገብ አንዲት የበሬ ግንባር የምታክል መሬት አለች። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተናገሩት የተወሰኑ ሰዎች በዚህ ክፍት ቦታ መስጊድ እንሰራለን ብለው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ።

መስጊዱ የሚሰራው በተለምዶ “ማሪያም ሰፈር” ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር ነው። የከተማ መስተዳደሩ ለመስጊዱ ግንባታ እውቅና እና ፍቃድ እንዳልሰጠ ታውቋል። ሆኖም ግን በዚህ ምክንያት ዛሬ በአሰላ ከተማ በክርስቲያን እና እስልምና እምነት ተከታዮች መካከል ከፍተኛ ረብሻና ብጥብጥ ተቀስቅሷል።

👉 በኢትዮጵያ የረጅም ዘመናት ታሪክ

💭 አሳፋሪ የታሪክ ወቅትና ምእራፍ | አረቡ ኢትዮጲያዊቷን ከፎቅ ወረወራት | በገዛ አገሯ ፥ በአዲስ አበባ

በአረብ አገር የሚያሰቃዮአቸው እንዳይበቃ…እንግዲህ ይህ ሁሉ መፈናቀል፣ የሽብር ጥቃትና ግድያ ሆን ተብሎ በሉሲፈራውያኑ ቀደም ብሎ በደንብ የተቀነባበረ ነው፤ ከሃዲዎቹ እነ ዶ/ር አብዮት መሣሪያዎቻቸው ናቸው።

ሉሲፈራውያኑ የሕዝባችንን አእምሮ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ብሎም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በዓለም ፊት ለማዋረድ ያስችላቸው ዘንድ የህዝባችንን ሞራል ዛሬም እንደገና በመስበር ላይ ይገኛሉ…ዛሬ ቀዝቃዛ ውሃ ነገ ደግሞ ሙቅ ውሃ እያፈሰሱ የወጣቱን አእምሮ በማጠብ ላይ ናቸው። ዛሬ ማር፣ ነገ እሬት፤ ዛሬ ያፈናቅላሉ፣ ከፎቅ ይወረውራሉ፣ ይገድላሉ፥ ነገ ደግሞ እያለቃቀሱ እርቅና ሰላም ፈጥረናል ይላሉ ፥ ዛሬ“አስደሳች ዜና…” ነገ ደግሞ “አሳዛኝ ዜና…” ቅብጥርሴ እያሉ ተለዋዋጭ የሆነ ፕሮፓጋንዳን በመንዛት ያልጠረጠሩትን ኢትዮጵያውያንን የመርዛማ ጥቃታቸው ሰለባ ያደርጓቸዋል።

➕ በተጨማሪ፤

💭 ለአምስት ሺህ ዓመታት በነፃነት የኖረችዋ ኩሩዋ ኢትዮጵያ ዛሬ ለምዕራባውያኑ እና ለአረቦች የባርነት ቀንበር ተጋልጣለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 12, 2018

ግማሾቻችንን ይህ ሊከነክነን ይችላል፤ ሃቁ ግን፡ ከአፄ ምኒሊክ ዘመን አንስቶ መሪዎቻችንን የሚመርጡልን ሉሲፈራውያኑ ናቸው። ቀደም ሲል፡ አገር ወዳዶቹ አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ገና በእንጭጩ ሲገደሉ፤ እነ አፄ ምኒልክ፣ ኃይለ ሥላሴ እና ጠ/ ምኒስትር መለስ ደግሞ ከእንቅልፋቸው መንቃት ሲጀምሩና ወደ ተዋሕዶ ክርስትናም ለመመለስ ሲወስኑ ተገድለዋል። ያልተገደሉት መንግስቱ ኃ/ማርያም እና ኃ/ማርያም ደሳለኝ ብቻ ናቸው። ለምን? ለሉሲፈር አስፈላጊውን መስዋዕት ለማቅረብ ስለበቁና ባለውለታቸው ስለሆኑ ነው። አገር ወዳድ የሆነ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መንግስታዊ ሥልጣኑን መያዝ የለበትም” የሚል መመሪያ ሉሲፈራውያኑ አላቸውና ነው።

የአንዋር መስጊድ በአዲስ አበባ ከተተከለበት ዘመን አንስቶ በኢትዮጵያ የነገሠው መንፈስ እስላማዊው የሉሲፈር መንፈስ ነው። በደርግ ጊዜ ቤተክርስቲያንን ከመስጊድ ጋር እኩል በማድረግ የመጀመሪያውን በር ከፈቱ፣ ላለፉት 27 ዓመታት ደግሞ፡ በአላሙዲን መሪነት ህዝበ ክርስቲያኑን በማድከምና አቅመቢስ በማድረግ ለአገሩና ለቤተሰቡ ያለውን ፍቅር እንዲያጣ፣ እንዲታመም፣ ልጅ–አልባ እንዲሆን፣ የማንነት ቀውስ እንዲገጥመው እና በመሰደድ አገሩን እንዲለቅ ተደረገ። በተቃራኒው ግን፡ የኢትዮጵያ ጠላት ለሆኑት የአረብ ወኪል ሙስሊሞች በፖለቲካ፣ በማህበረሰባዊ፣ በምጣኔ ኃብት እና በሃይማኖት መስኮች ኢትዮጵያን እንዲቆጣጠሩ አጎልብተዋቸዋል።

/ ሚንስትር መለስ በተገደሉበት ማግስት የአላሙዲን ወኪል የሆነው አቶ ደመቀ መኮንን፤ “እኔ ቁርአንን በአረብኛ ሸምድጀዋለሁ፤ አሁንም እቀራዋለሁ” በማለት “የሥራ ማመልከቻውን” አቀረበ፤ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝንም ለመተካት እጩ ሆነ (በጊዜው “አህመድ” የሚለውን ስም የያዘ ፖለቲከኛ በክርስቲያን ኢትዮጵያ መሪ ይሆን ዘንድ እድል የለውም የሚል እምነት ነበርና። ያቀዱት ጊዜ ሲደርስ ግን በደንብ ያዘጋጁትንና የኢትዮጵያ ሕዝብ መስማት የሚፈልገውን ሊናገር የሚችለውን ግራኝ አብይ አህመድን በመሪነት ለመምረጥ ወሰኑ።

አሁን፡ አቶ አብይ አህመድ እና አቶ ደመቀ መኮንን፡ ከፍተኛ ሥልጣኑ በየቦታው ከተሰጣቸው የሉሲፈራውያን አረብ ወኪሎች ጋር በመሆን፡ በሰይጣናዊው የሻሪያ ህግ የሚተዳደር የእስላም መንግስት ለመመስረት የሽግግሩን ሂደት በማፋጠን ላይ ናቸው። ግን፡ አንድ በአንድ ተፈርፍረው ያልቃሉ እንጂ አይሳካላቸውም!

ነጠብጣቦቹን ስናገናኝ፦

  • + የኢትዮጵያ መንግስት ለ ሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን እና አረቦች ለምን እጁን ለመስጠት እንደሚሻ
  • + በኢትዮጵያ ውስጥ ህወከትና ግድያዎችን ማን፡ ለምን እንደሚፈጥር
  • + የሕዳሴው ግድብ ግንባታ ለምን ለማዘግየት እንደተፈለገ
  • + ኢንጂነር ስመኘው በቀለ፡ ለምን፡ በማን እንደተገደለ
  • + ግራኝ አብይ አህመድ ለምን እህቶቻችንን ለአረብ አገሮች እንደ ዕቃ በርካሽ ለመሸጥ እንደወሰነ
  • + ኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣኑን ለእስላማዊ መንግስት ለማስረከብ እየተዘጋጁ እንደሆነ

💭 ሞኙ ኢትዮጵያዊ በአዲስ አበባ ጉዳይ እርስበርስ ሲባላ የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ በሱዳን እና ሶማሊያ ዳግማዊ ግራኝ አህመድን በመናሳሳት ላይ ነች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 5, 2019

ምንም የሌላቸው ውዳቂዎች ውቂያኖስ አቋርጠው ሌሎች ሃገራትን ለመያዝ ይሞክራሉ፤ ዓለምን የመግዛት ፀጋና ስጦታ ያለን እኛ ኢትዮጵያውያን በዘረኝነት፣ ጐጠኝነት፣ ጠባብነት፣ ብሔርተኝነትና መንደርተኝነት በሽታ እራሳችንን ለማጥፋት ተነሳስተናል።

በሱዳን የተፈጠረውን ውጥንቅጥ ሁኔታ በመጠቀም (እስከ መቶ ሰዎች በዚህ ሰሞን ተገድለዋል) .አይ.ኤና ቱርክ የመለመሉትን ሱዳናዊውን ወታደር መሀመድ ሃምዳን ዳጎሎን፡ “ሄሜቲ” ስልጣን ላይ ለማውጣት እያዘጋጁት ነው፤ ልክ እንድ ኮሎኔል (እንዴት ያገኘው ማዕረግ ነው?) /(ማን የሰጠው ማዕረግ ነው?) አብዮት አህመድ። ሙርሲ= አህመድ = ሄሜቲ።

በአሜሪካ እና ጀርመን እርዳታ ለኢትዮጵያ እንኳን የተረፈ ጨቃጨርቅ ፋብሪካ የገነባቸው እርኩሷ ቱርክ የቀድሞዋን የኦቶማንን/ኦስማን ግዛት መልሳ ለማምጣት ደፋ ቀና በማለት ላይ ነች። ይህ የኦስማን ግዛት ግራኝ አህመድን ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በማነሳሳት ተዋሕዶ ኢትዮጵያን ለማዳከም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች። ሦስት ሚሊየን አርሜኒያውያን እና አሽሩ ክርስቲያን ወገኖቻችንን የጨፈጨፈችው የአሁኗ ቱርክም የኢትዮጵያውያን ደም አሁንም ጠምጧታል፤ የግራኝ አህመድን መዋረድ ለመበቀል ወደ ኢትዮጵያ እና አካባቢዋ በየዘመኑ ዘልቃ በመግባት አሉ የተባሉትን የኢትዮጵያ መሪዎች ለመግደል በቅታለች። ከመቶ ሠላሳ ዓመታት በፊት የሃገራቸውን ዳር ድንበር ከወራሪ ጠላት ለመከላከል፤ እንደ ተራ ወታደር በጀግንነት ተፋልመው መተማ ላይ አንገታቸውን ለቱርክ ወኪሎች ለነበሩት ለድርቡሽ ሱዳናውያን የሰጡበት ድንቁን አፄ ዮሐንስ ንጉሠ ነገስት ዘኢትዮጵያን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

ዛሬም ተመሳሳይ ነገር እየታየ ነው፤ በሱዳን እና በሶማሊያ የመሀምዳውያኑ ቱርኮች ቅጥረኞች ተነስተው በኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ እንደገና ለመዝመት እየተዘጋጁ ነው። ለጊዜውም ቢሆን አሁን ሁኔታው በጣም አመቺ ሆኖላቸዋል፤ ዳግማዊ ግራኝ አህመድን በዶ/ር አብዮት በኩል ለማምጣት ችለዋል፣ ልክ በግራኝ እና ጣልያን ወረራዎች ጊዜ እንደታየው በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ሊነሳ የሚችል እስላማዊ ሠራዊት በተለይ “ኦሮሚያ” እና “ሶማሊያ” (እግዚአብሔር ይይላችሁ በተለይ እነዚህ ሁለት ክልሎች እንዲመሠረቱ ፈቃዱን የሰጣችሁ) በተባሉት ክልሎች ወቅቱን እና ትዕዛዙን በመጠባበቅ ላይ ነው።

ከታሪክ ለመማር ፈቃደኞች ብንሆን ነው አሁን ለምንገኝበት አሳፋሪ ሁኔታ አንጋለጥም ነበር። ፍዬሎቹ ጠላቶቻችን እነማን እንደሆኑ አንዴም፣ ሁለቴም፣ ሦስቴም… በተደጋጋሚ ለማየት በቅተናል፤ ግን ከታሪክ ስለማንማር እንደ ቱርኮችና አረቦች ከመሳሰሉት ውዳቂዮች መጫወቻ ሆነናል።

በደርግ ጊዜ መንግስቱ ኃይለማርያም አሉ የሚባሉትንና ልምዱ ያላቸውን ጄነራሎችና የጦር መሪዎች በመረሸን አገሪቱን አድክሞ ስለነበር እንደ ሶማሊያ ያሉ ውዳቂዎች እስከ ጂጂጋ ድረስ ሰተት ብለው ገቡ፤ በዚህ በሚሊየን የሚቆጠሩ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን አጡ። ዛሬም የዶ/ር አብዮት አህመድ መንግስት ልምዱ ያላቸውን የጦር መሪዎች በጴንጤዎችና ሙስሊሞች እየተካ የኢትዮጵያን ሠራዊት በማድከም ላይ ይገኛል። ቱርኮችና አረቦች በሶማሊያና ሱዳን በኩል በቅርቡ ለሚጀምሩት ወረራ ሕዝባችን ከመቼውም ጊዜ በከፋ ተጋልጦ ይገኛል። ሠራዊቱ ውስጥ የገቡት ጴንጤዎች መሳሪያዎቻቸውን እየወረወሩ ወደ ኬኒያ ያመልጣሉ እንጅ ለኢትዮጵያ ብለው አይሞቱም፥ ሙስሊሞቹም ለቱርክ፣ አረብና ግብጽ “ወንድሞቻቸው” ሲሉ ጡት ያጠባቻቸውን ኢትዮጵያን በመክዳት ከታሪካዊ ጠላቶቿ ጋር ተሰልፈው እንደሚወጓት 100% እርግጠኛ ሆኜ መናገር እደፍራለሁ። ባለፉት አንድ ሺህ ዓመታት ይህን በተደጋጋሚ አይተናል፤ ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም!

ባለፈው ዓመት ቱርክ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሠላሳ አራት ሺህ በጎችን ለበዓል ሰጥታ ነበር፥ ባለፈው ሳምንት ደግሞ አስራ አምስት ሺህ ወደ አማርኛ የተተረጎሙ እኩስ ቁርአኖችን በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ አከፋፍላ ነበር። (መጀመሪያ በጉን፣ ቀጥሎ ቁርአንን፣ ከዚያም ሜንጫውን) ይታየን፤ እኔ በአንካራ ከተማ መንገዶች ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ላከፋፍል ሲፈቀድልኝ! ክርስቲያኖች በሚረገጡባት ቱርክ ፈጽሞ የማይቻልና የሚያስገድል ተግባር ነው። የአገራችን በር ግን ለማንም ውዳቂ ክፍት ነው። በጣም ያስቆጣል! ወገን፤ ሰዓቱ ተቃርቧልና ለመጨረሻው ፍልሚያ እራስህን በሚገባ አዘጋጅ!

“… ናፖሊዮ ራሱን ትልቅ አድርጎ ያይ ይሆናል። እኔ ግን ዛሬም ታላቅ ነኝ። እሱ በቅርብ አመታት የተጎናጸፋቸው ድሎች ይሆናል ታላቅ ያደረጉት። የእኔ ግን ታላቅነት ከጥንት… የሚነሳ ታሪክ፤ ገናና ሀገር ያለኝ መሆኔን ሊያውቅ ይገባል።“ [አፄ ቴዎድሮስ]

“… የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት፤ ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት። ሁለተኛ ክብርህ ናት። ሶስተኛም ሚስትህ ናት። አራተኛም ልጅህ ናት። አምስተኛም መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከታቲነት እንዲህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ።” [አፄ ዮሐንስ ፬ኛ]

💭 ቤኒ ሻንጉልን እስላም አድርገው ጨርሰዋል፤ አሁን ከሃዲ ዐቢይ አህመድ ግድቡን ለአረብ ሊያስረክብ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 2, 2020

💭 የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ኢትዮጵያውያንን በማሳረድ ዛሬም መሪነቱን ይዛለች | የሰው ቄራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 29, 2020

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ልደታ ለማርያም ወረብ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2022

❖❖❖በሰንበት ተማሪዎች የቀረበ ወረብ❖❖❖

የቅድስት ልደታ ለማርያም ክብረ በዓል ፩ ግንቦት ፪ሺ፱ ዓ.ም

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት | ምስጋና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2022

❖❖❖ ልደታ ለማርያም፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች ❖❖❖

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግንቦት አንድ ቀን (የግንቦት ልደታ) የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሚከበርበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት” ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ “ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች” [ኢሳ ፯፡፲፬] ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡ ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ” የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።” [መዝ ፵፬፡፱] ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ “ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት።”[ራዕ ፲፪፡፩] ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡ የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡

የድንግል ማርያም ልደት በነቢያት አንደበት

መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡ መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡ [መዝ ፹፮፥፩፡፯]

እግዚአብሔር የዝማሬና የትንቢት ጸጋን ያበዛለት ክቡር ዳዊት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥርወ ልደት አስቀድሞ በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት ተገልጾለት “መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን /መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው/” በማለት ትንቢት ተናግሯል፡፡ “የተቀደሱ ተራሮች” ያለውም የእመቤታችን ሥርወ ልደት ከቤተ መንግሥትና ከቤተ ክህነት ከሆኑት ከተቀደሱት ከኢያቄምና ከሐና የመሆኑን ነገር ሲያመለክት ነው፡፡ ይህንን ትንቢትና እውነተኛውን የእመቤታችንን የትውልድ ሀረግ አስማምታ ቤተክርስቲያን “የእመቤታችን ማርያም ትውልዷ ባባቷ በኩል ከንጉሡ ከዳዊት ወገን ነው፤ በናቷም በኩል ከካህኑ ከአሮን ወገን ነው፤ የአባቷ ስም ኢያቄም ነው፤ የእናቷም ስም ሐና ነው፡፡” ብላ ታስተምራለች፡፡

ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ፡ ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል፡፡ [ኢሳ. ፲፩፡፩]

ቁጥሩ ከዐበይት ነቢያት ወገን የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስም ጥበብንና እውቀትን በሚገልጽ ስለሚመጣውም ነገር ትንቢትን በሚያናግር በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ከነገደ ዕሴይ እንደሚሆንና እርሷም ጽጌ (አበባ) የተባለ አካላዊ ቃል ክርስቶስን በሕቱም ድንግልና እንደምትወልድ ተገልጾለት “ትወፅእ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ /ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ አበባም ከእርሷ ይወጣል/” በማለት ታላቅ ትንቢትን ተናግሮ ነበር፡፡ ይህች በትርም ከእሴይ ዘር የተገኘችው በዚህች ዕለት ነውና ልደቷን በታላቅ ድምቀት እናከብራለን፡፡ ይህንን መሰረት በማድረግ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም “መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ከእሴይ ሥር የተገኘሽ መዓዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ” በማለት በውዳሴ አመስግኗታል፡፡ “በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ” [መዝ.፻፴፩፡፲፫]” የተባለልን የአባቶቻችን ልጆች እኛም እንዲሁ እያልን እናመሰግናታለን፡፡

ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ፡ ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፡፡ [መኃ ፬፡፰]

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት መሰረት የእመቤታችን የትውልድ ስፍራ ሊባኖስ የተባለው ተራራማ ሀገር ነው፡፡ በሊባኖስ ስለመሆኑ አስቀድሞ ጠቢቡ ሰሎሞን “ንዒ እምሊባኖስ መርዓት ንዒ እምሊባኖስ ንዒ ወተወፅኢ እምቅድመ ሃይማኖት እምርእሰ ሳኔር ወኤርሞን አምግበበ አናብስት ወእምአድባረ አናምርት /ሙሽራዬ ሆይ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነዪ ከአማና ራስ ከሳኔር ከኤርሞን ራስ ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮችም ተራራ ተመልከች/” በማለት ተናግሮ ነበር፡፡ የዚህ ትንቢት ምስጢርም የእመቤታችን መካነ ልደት የሊባኖስ ተራራ ስለመሆኑ የሚያጠይቅ እንደሆነ ምስክርነታቸው የታመነ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡ ትንቢቱም ሲፈጸም ቅድስት ድንግል ማርያም ግንቦት ፩ ቀን በ፲፭ ዓ.ዓ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በሊባኖስ ተራራ ተወልዳለች፡፡

ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ የተባለው የነገረ ማርያም ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እመቤታችን በሊባኖስ እንደምትወለድ አስቀድሞ ሰሎሞን የተናገረው ቃልም መፈጸሙን ሲገልጽ “….የአናብስት ልጅ አልኩሽ፡፡ ሰሎሞን እንዲህ ሲል እንደተናገረ፡- ሙሽራዪት ሆይ ከሊባኖስ ተራራ ነዪ፤ ከአንበሶች ጒድጓድ ወጥተሽ ነዪ፤ ከምርጥ ነገድነት የተነሣ ከሚመካ ወገን የመወለድሽ ዜና እጅግ ግሩም ነው፡፡” በማለት አመስጥሮታል፡፡ እመቤታችንም በሊባኖስ ተራራ እንድትወለድ ምክንያት የሆነው በማሕፀን ሳለች የአርሳባንን ልጅ ዓይን በማብራቷና ሳሚናስ የሚባለውን የጦሊቅን ልጅ ከሞት በማስነሳቷ አይሁድ በቅናት ተነሳስተውባቸው ስለነበር ሐናና ኢያቄም ወደ ሊባኖስ ተራራ እንዲሄዱ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለኢያቄም ተገልጾ ስለነገራቸው እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡

የድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌ

ከትንቢቱ በተጨማሪም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በራዕይና በምሳሌም አስቀድሞ የተገለጸ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ከእርሷ ሰባት ትውልድ አስቀድሞ ለነበሩት ደጋግ ሰዎች እንዲሁም ለእናትና ለአባቷ የተገለጹት ምሳሌዎች በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ሰፍረው ይገኛሉ፡፡

ሰባተኛዪቱ እንቦሳ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋ ደግሞ ፀሓይን ስትወልድ አየሁ (ቴክታ)

በቅድስና የሚኖሩ ነገር ግን መካን የነበሩት ቴክታና ጴጥርቃ ነጭ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ ፤ እንቦሳይቱ እንቦሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ፤ ስድስተኛዪቱ ጨረቃን ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አይተው በሀገራቸው መፈክረ ሕልም (ሕልም ፈች ሊቅ) አለና ሂደው ነገሩት፡፡ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ፤ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ፡፡ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም፤ እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው፡፡ እነርሱም ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ ወለዱ፡፡ ስሟንም “ረከብኩ ስእለትዬ፤ ረከብኩ ተምኔትዬ” /የተሳልኩትን አገኘሁ፤ የተመኘሁትን አገኘሁ/ ሲሉ “ሄኤሜን”አሏት፡፡ ሄኤሜን ዴርዴን፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ ሐናን ወለደች፡፡ ሐና ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ ይሁዳ ለተወለደ ኢያቄም ለሚባል ደግ ሰው አጋቧት፡፡ ከኢያቄምና ከሐናም በጨረቃ የተመሰለች ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡

ፀዓዳ ርግብ ሰባቱ ሰማያትን ሰንጥቃ መጥታ በማሕፀኔ ስታድር አየሁ (ቅድስት ሐና)

ኢያቄምና ሐና መካን ስለነበሩ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ጸልየው፤ ሲሰጣቸውም መልሰው ለእርሱ እንደሚሰጡ ስዕለትን ተስለው ነበር፡፡ ጸሎታቸው ሲደርስ ለሐና በሕልም ተገልጾላት ለባለቤቷ ለኢያቄም “ብእሴሃ አነኑ ርኢኩ በሕልምየ ርግብ ጸዐዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርእስየ ወቦአት ውስተ እዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርሥየ /ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብቶ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ፡፡” ብላዋለች፡፡ የዚህ ራእይ ምስጢርም ርግብ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስትሆን፤ ፀዓዳ (ነጭ) መሆኗ ንጽሕናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕፀኔ ስትተኛ አየሁ” ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክን የምትፀንሰውን ንጽሕት ርግብ የተባለችውን እመቤታችንን የምትወልድ መሆኗን ሲያጠይቅ ነው::

ከሰባተኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ (ቅዱስ ኢያቄም)

በተመሳሳይ ኢያቄምም በሕልሙ ያየውን ለባለቤቱ ለሐና “እንዘ ይትረኀዉ ሰብዐቱ ሰማያት ዖፍ ጸዐዳ መጽአ ኀቤየ ወነበረ ዲበ ርእስየ /ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ዖፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” ብሎ በሕልሙ የተገለጸለትን ነግሯታል፡፡ የዚህም ራዕይ ምስጢር ዖፍ የተባለው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባሕርዩ ነው፡፡ ኢያቄም “ከላይ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” ማለቱ የኢያቄምን ባሕርይ ባሕርይ እንደሚያደርግ የሚያጠይቅ ሲሆን ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ባህርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩና መንግስቱ ናቸው።

የድንግል ማርያም ልደት በሐዲስ ኪዳን ሊቃውንት

የሐዲስ ኪዳን ሊቃውንትም ትንቢተ ነቢያትንና ወንጌልን በማጣጣም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት አመስጥረው አስተምረዋል፤ አመስግነዋል፤ ተቃኝተዋልም፡፡ የእርሷን ልደት እጅግ ብዙ ሊቃውንት በስፋትና በጥልቀት ያመሰጠሩት ሲሆን ለምሳሌ ያህል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡

ማርያምስ ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች (ቅዱስ ያሬድ)

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ልደት “ማርያምሰ ተኀቱ እምትካት ውስተ ከርሱ ለአዳም ከመ ባሕርይ ጸዓዳ/ ማርያምስ (ማርያም ግን) ከጥንት ጀምሮ በአዳም ባሕርይ ውስጥ እንደ ነጭ ዕንቁ ታበራለች፡፡” በማለት እርሷ በደፈረሰው ዓለም በንጽሕና፣ በቅድስናና በድንግልና ስታበራ እንደነበርና ኋላም የዓለም ብርሃን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን መውለዷን አመስጥሮ ተናግሯል፡፡ በተጨማሪም ስለ ሥርወ ልደቷ “እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ…ሐረገ ወይን/ ሥሮቿ በምድር ጫፎቿም በሰማይ ያሉ…የወይን ሐረግ” በማለት የተወለደችው በምድር ከነበሩት ኢያቄምና ሐና መሆኑን የወለደችው ግን ሰማያዊውን ንጉሥ እንደሆነ በማመስጠር ዘምሯል፡፡ በዚህም ሰውና እግዚአብሔርን ያገናኘች መሰላል መሆኗል ገልጾ አስተምሯል፡፡

ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ (አባ ሕርያቆስ)

የብህንሳው ሊቀ ጳጳስ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴ ማርያም “ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ/ ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም፤ በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ” በማለት የድንግል ማርያም ጽንሰትና ልደት እንዴት እንደነበር በድርሰቱ አስፍሮታል፡፡ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት የሁላችን እናት ድንግል ማርያም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐናና ከኢያቄም ነሐሴ ፯ ቀን ተፀንሳ ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ ግንቦት ፩ ቀን ተወልዳለች፡፡ እርስዋም ስትፀነስ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ከጥንተ አብሶ (original Sin) ጠብቋታል፤ አበሳው አልነካትም፡፡ ይህንንም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ በኃጢአት በተከበበ፣ መርገም በሞላበት ዓለም ውስጥ ከኃጢአት ከበደል ርቃ (ተለይታ) እንደ ጌዲዮን ጸምር በንጽህና የጠገኘች ንጽህት ዘር መሆኗን ሲያስረዳ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር፡፡”[ኢሳ.፩፡፲፱]በማለት ተናግሯል፡፡ እንዲሁም ጠቢቡ ሰሎሞን ንጽህናዋን በትንቢት መነጽር አይቶ “ወዳጄ ሆይ፣ ሁለንተናሽ ውብ ነው፣ ምንም ነውር የለብሽም፡፡ ሙሽሪት ሆይ ከሊባኖስ ነዪ፡፡”[መሓልይ ፬፡፯፡፲፮] በማለት በንጽህና በቅድስና ያጌጠች፣ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ያልነካት፣ የድህነታችን ምክንያት፣ የንጽህናችን መሰረት የሰው ባህርይ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲዋሀድ ምክንያት የሆነች ንጽሕት የሰርግ ቤት ድንግል ማርያም በሊባኖስ የመወለዷን ነገር አስቀድሞ ነግሮናል፡፡

ይህች ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀባት ዕለት ናት (ቅዱስ እንድርያስ)

የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ የከበረ ስለሆነው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ታላቅነት “ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምሳሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል፤ የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ ዕለት (ጌታ) መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” በማለት ገልጾታል፡፡ በእውነት የእርሷ ልደት የልዑል ማደሪያው መቅደስ የተሰራበት ዕለት ነውና ሁላችን እናከብረዋለን፡፡ በዚህም ዕለት “ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም/ እነሆ ዛሬ በእመቤታችን ልደት ደስታ ሆነ” እያልን እንዘምራለን። ይህችን የልዑል ማደሪያ እናቷ ሐናና አባቷ ኢያቄምም በእጅጉ ተደስተው በተወለደች በስምንተኛ ቀኗ ስሟን “ማርያም” ብለው ሰይመዋታል፡፡

የእመቤታችን የልደት በዓል አከባበር

አባታችን አዳም በኃጢአት ከወደቀ በኋላ፣ ንስሃ በገባ ጊዜ አምላካችን ጌታ እግዚአብሔር የድህነት ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃል ኪዳኑም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚል ነበር፡፡ ስለሆነም አዳም ፶፻፭፻/5500 ዘመን የሕይወት ምክንያት የሆነች የልጅ ልጁ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከአብራኩ ከተከፈሉ ቅዱሳን ልጆቹ የምትወለድበትን ቀን ተስፋ እያደረገ ኖረ፡፡ የእመቤታችንን የድንግል ማርያምን የመወለዷን ዜና ተስፋ በማድረግ “ሴት” ይላት የነበረውን ሚስቱን ሔዋንን በእመቤታችን ምሳሌነት “ሔዋን”፣ የሕያዋን ሁሉ እናት ብሎ ሰየማት፡፡ [ዘፍ.፫፡፳] ዳግማዊ አዳም የተባለ ክርስቶስም የአዳምን ተስፋ በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ እውነተኛዋን ሔዋን (ዳግሚት፣ አማናዊት ሔዋንን) ድንግል ማርያምን በዮሐንስ ወንጌላዊ በኩል ለሕያዋን ምዕመናን ሁሉ እናት አድርጎ ሰጠ፡፡ [ዮሐ. ፲፱፡፳፮] ይህን የከበረ ምስጢር የማይረዳ “ክርስቲያን” እንዴት ያሳዝናል!? እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን የቀዳማዊ አባታችንን የአዳምን፣ እንዲሁም በዳግም ተፈጥሮ ያከበረንን ዳግማዊ አዳም የተባለ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ተቀብለን “የሕያዋን ሁሉ እናት” ድንግል ማርያምን ልደቷን በፍፁም ደስታ እናከብራለን፣ ከተወደደ ልጇ ምሕረትን ትለምንልን ዘንድም ወደ እርሷ እናንጋጥጣለን፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለን ምዕመናን ከጌታችን ልደት ቀጥሎ በታላቅ ድምቀት የምናከብረው የልደት በዓል የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደት ቀን ነው፡፡ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ “በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”[ሉቃ ፩፡፲፬] ከተባለ የድንግል ማርያም ልደት ምንኛ የሚያስደስት ይሆን?! የነቢያቱ ትንቢት የተፈፀመበት፣ የታየው ራዕይም በገሀድ የተከናወነበት፣ የብሉይ ኪዳን ማብቂያ የሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ናትና ልደቷ ለሰው ልጆች ሁሉ (ለሕያዋን ሁሉ) ታላቅ የደስታ ቀን ነው፡፡ ሰማያውያን ቅዱሳን መላእክትም በንጽህናዋ በቅድስናዋ ተደንቀው “እህትነ ነያ/እህታችን እነኋት” ብለው ያመሰግኗታል፡፡ በዘመናችን ያሉ የሰዎች ልደት በድምቀት የሚከበር ከሆነ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት የሆነች የአምላክ እናት የተወለደችበት ቀን ምንኛ ሊከበር ይገባው ይሆን?! ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደት በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ከዚህ ታላቅ በዓል በረከት ረድኤትን እንድናገኝበት ነው፡፡ የሕይወት ክርስቶስ እናት ዛሬ ተወልዳለችና፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትዉፊት መሰረት ሐና እና ኢያቄም ከአይሁድ ለማምለጥ ተሰደዉ በአድባረ ሊባኖስ ስር እመቤታችንን ወለዱ፡፡ በወቅቱ ከቤት የወጡት ለሽሽት ነበርና ስንቅ ስላልያዙ ምግባቸዉ “ንፍሮና ጥራጥሬ” ነበር፡፡ይህንን ትዉፊት በመያዝ በዓሉ ከቤት ዉጭ ንፍሮ እየተበላ ይከበራል፡፡ነገር ግን በበጎ ነገሮች ሰበብ ክፉ ዓላማዉን ማስፈጸም የሚፈልገዉ ዲያቢሎስ በማር መካከል መርዝን ከሚጨምርባቸዉ መንፈሳዊ በዓላት አንዱ የግንቦት ልደታ (የእመቤታችን የልደት በዓል) ነዉ፡፡ በዚህ ዕለት አንዳንዶች ባለማወቅ ሌሎች ደግሞ በድፍረት “ለአድባር አዉጋር ነዉ፤ ቆሌዉን ለመለመን ነዉ” እያሉ ለማያውቁት አምልኮ ንፍሮ የሚበትኑ፣ ቡና የሚረጩ፣ ቅቤ የሚቀቡ፣ የከብት ደም የሚያፈሱ አሉ፡፡ እውነታው እነዚህ በእርግጥም ጣዖት አምላኪዎች ናቸው፡፡ እኛ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ግን እነዚህን የሃይማኖት ለዋጮች ሥራቸውን እንጸየፋለን፡፡ ስለሆነም ከእንደዚህ ዓይነቱ ባዕድ አምልኮ በመለየት ይህንን ታላቅ በዓል በተገባና በተረዳ ነገር ልናከብረው ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን ሥርዓት መሰረት በቀናች በተዋሕዶ እምነት ሆነን፤ በምሕረቱ የጎበኘንን አምላካችንን ብቻ እያመለክን፤ የድኅነታችን ምክንያት የሆነችውን ድንግል ማርያምንም እያመሰገንን ልናከብረው ይገባል፡፡

አምላካችን እግዚአብሔር ከእመቤታችን ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: