Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2022
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 3rd, 2022

የዲያብሎስ በቀል በኢትዮጵያ ላይ | ጂኒ ጀዋር ከቱርኩ ኤርዶጋን እና ከሳውዲው ሸህ ጋር በመካ ተገናኝተዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 3, 2022

አክስሟዊቱ ኢትዮጵያ የሉሲፈርን አምልኮ ሙሉ በሙሉ ባለመቀበሏ በእጅጉ የሚበሳጩትና በኤዶማውያኑ የዒሳው ዘሮች የሚደገፉት እማኤላውያኑ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች ዛሬ የሺህ አራት መቶ ዓመቱን የበቀል ጂሃዳቸውን በጽዮናውያን ላይ ለማጠናቀቅ በመዘጋጀት ላይ ናቸው። ይህ የመጨረሻ ሙከራቸው ነው፤ ብዙ ግፍና መከራ በሕዝባችን ላይ ያደርሳሉ፤ ሆኖም በመጨረሻ መሸነፋቸው የማይቀር ነው። እነርሱም ሆኑ ጣዖታዊው እስልምናቸው ከኢትዮጵያ ምድር ብቻ ሳይሆን ከመላው ዓለም ተጠራርገውና በኤርታ አሌ እሳት ገሞራ በኩል ተሽከርክረው በመንፈስ ወደ ጥልቁ የሲዖል ጉድጓድ ይጓዛሉ። ሙስሊም ሳይሆኑ እንደ ሙስሊም የሚራመዱትንና፤ በድንቁርና'”እንኳን ለኢድ አደረሳችሁ!” የሚሉትን ግብዞች ረዳቶቻቸውንም ሁሉ ይዘዋቸው ይጓዛሉ። ለመሆኑ ግድየለሾቹና “ብቻችንን ወደገነት እንገባለን!” ባዮቹ እነዚህ ግብዞች፤”እንኳን አደረሳችሁ!” ሲሉ፤ ማን? ለምኑ? ነው ያደረሳቸው? “እንኳን ሉሲፈር ለጣዖት በዓል አደረሳችሁ?”

የቱርኩ መሪ ኤርዶጋን በአምስት ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በመካ በመገኘትና ከጂኒ ጃዋር ጋር በ666 መሳለሚያ በመካው ካባ ጥቁር ድንጋይ ዙሪያ ሲዞር ይታያል። እ..አ በ2015 ላይ ነበር ቀደም ሲል በእነ ኦባማ ተቅብቶ የነበረው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በኤርዶጋንና በጂኒ ጃዋር አማካኝነት በመካ ጂኒ ተሞልቶ የነበረው።

በዚሁ በረመዳናቸው ዕለት ሺህ ኢትዮጵያውያን ጂኒ ተሞልተው ከሳውዲ ወደ አዲስ አበባ ተጠርፈዋል! አገር ቤት የገቡት ደግሞ በቄሮ እና ፋኖ አርበኞች አካል ውስጥ ገብተው ስራቸውን ይሠሩላቸዋል። የ፪ሺ፱ኙ የ’ኦሮማራ’ ጂሃድን እናስታውስ! በወቅቱም የይሑዳ አንበሣ አውሎ ነፋሱን ከኢትዮጵያ ተራሮች በማስነሳት ወደ መካ ልኮ አህዛብን አስጠነቀቀ! ያኔ ነፋሱ የጣለው የግንባታ መሰላል የዓለማችን መስጊዶች እናት” በምትባለው የመካ መስጊድ ላይ ወድቆ ከሦስት ሺህ እስከ ሃያ ሺህ መሀመዳውያንን መግደሉ የምናስታውሰው ነው። ያውም በእንቍጣጣሽ ዕለት፣ ያውም እኔ በጂዳ በኩል አድርጌ በአውሮፕላን በበረርኩ በማግስቱ!

የጃዋር ሆቴል፤ መካ

እንደ ሙስሊሞቹ መጽሐፍ ሃዲትከሆነ ፤ ቀጭን እግር ያለው ኢትዮጵያዊ ይህን የ666 መሳለሚያ ጥቁር ድንጋይ ያፈርሰዋል

በኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ እርዳታ ከኦርቶዶክስ ሰርቢያ በተነጠቀችው በኮሶቮ ግዛት የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ መሀመዳውያኑ የዓብያተ ክርስቲያናቱን መስቀል በጥላቻ ኃይል ሲያፈርሱ

💭 ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በጦማሬ ካቀርብኳቸው ጽሑፎች መካከል፤ ልብ እንበል፤ የኮሮና ወረርሽኝ ያኔ በሳውዲ መነሳቱን በዚሁ ጽሑፌ አውስቼው ነበር። በመካ የወደቀውን መሰላል አስመልክቶ የሚያሳየው ቪዲዮ በድጋሚ እነሆ (10:30 ደቂቃ በኋላ ይታያል)

☪ “Saudi Arabia Doubles Down on Abuse“

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 2, 2013

እነዚህ የሳዑዲ ፍጡራን ምን ያህል ደካሞች፣ ርጉሞች እና ጨካኞች እንደሆኑ አገር ቤት ያለው ወገናችን በደንብ አድርጎ የሚገነዘበው አይመስለኝም።

ሁላችንንም በጣም ሊያሳስበንና በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው ጉዳይ፡

በቅርቡ በአረብ አገሮች የተስፋፋውና “ኮሮና” የሚባለው መቅሰፍታዊ የግመል ቫይረስ ነው። ይህ ቫይረስ ወይም ተመሳሳይ የባዮሎጂ መርዝ ምናልባት በሚመለሱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ዓማካይነት በአገራችን ተስፋፍቶ ሕዝባችንን የበለጠ እንዳያዳክምብን ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተልን ማጥናት ይኖርብናል። ሳዑዲዎች ኢትዮጵያውያኑን ለማባረር የተዘጋጁት ዱሮ ነው። የኢትዮጵያውያኑ ‘ህገወጥነት‘ ጉዳይ ምክኒያቱ እንዳልሆነ ብዙዎቻችን የምናውቀው ነው።

ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣው የአውሮፕላን በረራዎችስ? የሳዑዲ አውሮፕላኖች ለዓለም ዓቀፉ የ Chemtrails ሴራ አስተዋጽዖ በማበርከት በአገራችን የዓየር ክልል መርዙን የመርጨትስ ጥሩ አጋጣሚ ፈጥሮላቸው ይሆንን? ሲ አይ ኤ በቻይና አካሂዶታል ሲባል እንደነበረው። ወደ ኢትዮጵያ የሚበሩ የአረብ አውሮፕላኖች ሁሉ በዚህ የ Chemtrails ሴራ ሊጠረጠሩ ይገባቸዋል። ቀይ ባሕርን በእጃቸው አስገብተዋል፡ የቀሯቸው ዓየራችን፣ ውሃችን እና መሬታችን ናቸው።

ባለፈው ጊዜ የመከላከያ ምኒስትራቸው ግብጽ ውስጥ ፀረ–ኢትዮጵያ የሆነውን ንግግር ማሰማቱም ከዚህ ሁሉ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው። ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ዕብድ ውሾች በየመንገዱ መታደን በጀመሩት ዕለት፡ የ Skull & Bones ምስጢራዊ ድርጅት ዓባል፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በሳዑዲ ዓረቢያ ጉብኝት እያደረጉ ነበር። ስለሁኔታው የተነፈሱት ነገር የለም።

የዓለም ዓቀፋዊ ምስጢራዊ ቡድኖች ሁሉ መናኽሪያዋ ሳዑዲ የሰይጣን መቀመጫ ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች። ይህን መናኽሪያ ሊያወድም እና ሊያጠፋ የሚችለውም “ቀጫጫ እገር ያለው ኢትዮጵያዊ” እንደሚሆን እራሳቸው ሙስሊሞች ቅዱስ ናቸው የሚሏቸው ሃዲቶች ይተነብያሉ።

ቀደም ሲል መሪዎቻችንን ገድለው ብሔራዊ አለመረጋጋትን በመፍጠር የዋሐቢዎችን እንቅስቃሴ ባገራችን ለማጠናከር ሞከሩ። አሁን ደግሞ በሚቀጥለው እርምጃቸው ይህ በታሪክ ከፍተኛ ቦታ መያዝ የሚችለው የስደተኞች እንደገና ወደ ኢትዮጵያ መጉረፍ ለዚህ ህልማቸው አስተዋጽዖ ያበረክታል ብለው ያምናሉ። ሕብረተሰባችንን በሁሉም አቅጣጫ በመተናኮልና በሕዝባችን ላይ ውጥረት እየፈጠሩ በማደናገር ዲያብሎሳዊ ህልማቸውን እውን ለማድረግ መውደቂያቸው እስኪደርስ ይታገላሉ። የመውደቂያቸው እና ኤርታዓሌ የእሳት ጉድጓድ ውስጥ የመግቢያቸው ቀን በጣም ተቃርቧል!

የሳዑዲ ዜጋ እና ከልዑሉ ቀጥሎም ሁለተኛው ኃብታም የሆኑት ሸህ ሙሀመድ አላሙዲ የኢትዮጵያውያኑን እጣ በሚመለከት ምን እያሉ ይሆን? ሳዑዲዎች በወገኖቻችን ላይ ለብዙ ዓመታት ስላደረሱት የከፋ በደል እንዲሁም ስለ ዋሃቢዝም ርዕዮተዓለም የሚሉትን ለመስማት በጣም ነው የጓጓሁት። ይህን በተመለከተ ለኢንተርቪው የሚጋብዛቸው ኢትዮጵያዊ ይኖር ይሆን?

ወገናችንን ወደ ሳዑዲ የሚልኩ፡ ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ እንዲባረሩ ካደረጉት የሚለዩ አይደሉም!

More Than a Million Ethiopians Get Together to Celebrate Life Under The Full Moon – Millions of ‘Saudis’ to Celebrate Death ‘With’ The Half Moon

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 22, 2015

ከ ፪ ዓመት በፊት በመካ ፭ሺ “ሀጂዎችን” የገደለው ፡ ከቁልቢ በቱርኮች ተሠርቆ ወደ መካ የተወሰደው የ ‘ቅ/ ገብርኤል ጽላት’ ይሆን?

ግራኝ አህመድ በቱርኮች እየተደገፈ በክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ ዲያብሎሳዊ ዘመቻውን ልክ ባካሄደበት የ16ኛ መቶ አጋማሽ ላይ ኦቶማን ቱርክ መላው አረቢያን ብሎም መካና መዲናን ትገዛ ነበር።

የግራኝ ዘመቻ ክርስትናን መዋጋትና ክርስቲያኖችንም ጨፍጨፍ ብቻ ሳይሆን፣ በተለይ የተደበቁ ቅርሶችንና መረጃዎችን ለማጥፋት፣ ጽላቶችን ለመስረቅ፡ በዚህም የእስልምናን ቅጥፈት እንዲሁም መሀመድን ጎበኘ የሚባለው የጂብሪልን ጋኔናዊነት ለመደበቅ መሆኑ እንደነበር አሁን የሚያጠራጥር ነገር አይደለም።

ነሐሴ ፪ሺ፯ ዓ.ም ላይ ከህንድ ወደ አዲስ አበባ ስበር በዱባይ ቀጥሎም በሳዑዲ አረቢያ በኩል ነበር ያለፍኩት፤ የሆነ ነገር ይሰማኝ ነበር። ከዓመት በፊት መስከረም ፪ሺ፮ ላይ መካኒሳ ቅ/ ሚካኤል ቤ/ ክርስቲያን በነበረኝ ቆይታዬ፤ ደመናው ላይ አፉን የከፈተ አንበሳ ወደ ሳዑዲ አቅጣጫ ነፋሱን የሚነፋ መስሎ ታየኝ (እታች በቪዲዮ አቅርቤዋለሁ በጊዜው)

ወደ ቤት እንደተመለስኩ፤ ቤተሰቦችና ጎረቤቶች በተሰባሰቡበት፤ “ሰሞኑን በመካ ከፍተኛ አደጋ ይኖራል”

አልኩ፡ እንዲያው በዝግታ። መቼም በእኛ ዘንድ ነገሮች እስኪከሰቱ ድረስ ይህን መሰል ነገር በደፈና መቀበል ስለሚቸግረን በጊዜው በቂ አትኩሮ አላገኝም ነበር።

ከጥቂት ቀናት በኋላ፡ በቅዱስ ዮሐንስ ዕለት በመካ ክሬኑ በኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተሰባብሮ 107 ሰዎች ሲሞቱ ከሁለት ሳምንታት በኋላም 5ሺህ የሚሆኑ ሀጂዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ዘመድ አዝማድ በሙሉ እየተገረመ ስልክ ይደውልልኝ ጀመር። እኔም ሁሉም በእጃችሁ ነው“ሂዱና ቅዱስ ሚካኤልን ወይም ቅዱስ ገብርኤልን ጠይቁ” ነበር ያልኩት።

ቁልቢ ገብርኤል ከዚህ ታሪክ ጋር ምናልባት ሊዛመድ እንደሚችል የተረዳሁት ይህ ሰውየ ያቀረበውን ቪዲዮ ከተመለከትኩ በኋላ ነበር። በጣም የሚገርም ነገር ነው፤ ብዙ ወደ ቁልቢ ገብርኤል የሚሄዱ ሰዎች እንደነገሩኝ ከሆነ በጣም ብዙ አረብ ሙስሊሞች በተለይ ለታህሣሥ ገብርኤል ወደ ቁልቢ ይሄዳሉ። ምን/ ማን ይሆን ወደዚህ ቅዱስ ቦታ እንዲጓዙ የሚገፋፋቸው? ይህ የሁላችንም የቤት ስራ ሊሆን ይገባል።

እነዚህ ትዕቢተኞች እጃቸውን ሰጥተው እስኪንበረከኩ ድረስ ገና ይንቀጠቀጣሉ!

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ድንቅ ነው! አሜሪካ የሴቶች ጽንስን ማቋረጥን ልትከለክል ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 3, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 😇 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

ይህ ጽንስ የማቋረጥ አገልግሎት የሚከለክል ሕግ ከጸደቀ ትልቅ፣ እጅግ በጣም ትልቅ የሆነ አብዮታዊ ለውጥ ነው። እንግዲህ “አደጉ” የሚባሉት ሃገራት በተለይም ከኮቪድ ክትትትባት ጋር በተያያዘ የነዋሪ ሕዝባቸው ቍጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ይችላል የሚል ከባድ ስጋት ስላለ ጽንስ የማቋረጥ መብት መታገድ እንደሚኖርበት ተረድተውታል።

በአፍሪቃስ? በሃገራችንስ? ጽንስን ምስወረዱ፣ የወሊድ መከላከያው፣ ክትትባቱ፣ ረሃቡ፣ በሽታውና ጦርነቱ በከሃዲዎቹ፣ ቅጥረኞቹና ወንጀለኞቹ አፍሪቃውያን አማካኝነት በሰፊው እንዲሰራጩ እየተደረጉ ነው። የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ቁንጮ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በቅርቡ፤ የሕዝብ ቁጥራችን በዝቷልና ብልጽግና የምንሻ ከሆነ ወሊድ መከላከያንና ጽንስን ማስወረድን በሃገሪቷ ተወዳጅ ማድረግ አለብን!” ሲል፤ ከዘር ማጥፋት ጦርነቱ ጎን ይህን ዲያብሎሳዊ የሕዝብ ቁጥር መቀነሻ ዘይቤ እንደሚከተል እየጠቆመን ነበር። እነዚህ እርኩስ የሰይጣን ጭፍሮች በጣም ከባድ የሆነ ግፍና ወንጀል እየፈጸሙ ነውና ወደ ሲዖል እንደሚወርዱ ይህ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ሊነግረን ይችላል።

ከአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሾልኮ የወጣ ሰነድ የፅንስ ማቋረጥ ሕግ ሊሻር እንደሚችል አመለከተ

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፅንስ የማቋረጥን ሕጋዊ መብት ሊሻር እንደሚችል የሚጠቁም ሾልኮ የወጣ ረቂቅ ሰነድ መነጋገሪያ ሆኗል።

ዳኛ ሳሙዔል አሊቶ ሾልኮ ወጣ በተባለው ሰነድ ላይ ፅንስን ሟቋረጥ የሚፈቅደውን የ1973ቱን ‘ሮይ ቨርሰስ ዌድ’ የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ውሳኔ “ከፍተኛ ስህተት ነው” ማለታቸውን ፖለቲኮ ዘግቧል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ ከቀለበሰ በ22 የአሜሪካ ግዛቶች ፅንስ ማቋረጥን ሕገ ወጥ ሊያደርግ ይችላል።

የዳኛ ሳሙኤል አሊቶ አስተያየት በአብላጫ ድምጽ ውሳኔውን ማስቀልበስ ከቻለ በአገሪቱ ያለው ፅንስ የማቋረጥ ሕገ መንግሥታዊ መብት ተሽሮ ግዛቶች አሰራሩን ሙሉ በሙሉ እንዲያግዱ መንገድ ይከፍታል ወይም በላዩ ላይ ተጨማሪ ገደቦችን መጣል ያስችላቸዋል።

ፍርድ ቤቱ እስከ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ድረስ በጉዳዩ ላይ ብይን ይሰጣሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ሮይ ቨርስስ ዌድ የተሰኘው የ1973 ሕግ በአሜሪካ ላሉ ነፍሰ ጡር ሴቶች በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት እርግዝና ውስጥ ፅንስ የማቋረጥ ፍጹም መብት እና በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ የተወሰኑ መብቶችን ሰጥቷቸዋል ።

የ1973 ሕግ ወደ ፍርድ ቤት እንዲመጣ ምክንያት የሆነው የሚሲሲፒ ግዛት ከ15 ሳምንታት በኋላ ፅንስ ማቋረጥ ላይ እገዳ በመጣሏ ሲሆን ይህንንም ሁኔታ ፍርድ ቤቱ ታኅሳስ ወር ላይ ተመልክቶታል።

በአሜሪካ ወደ ሪፐብሊካኖቹ ባዘነበለው ሥርዓትና የስነ ተዋልዶ መብቶች ፈተና ላይ ባሉበት ማግሥትም ነው ይህ ፅንስ ማቋረጥን የሚፈቅደው ‘ሮይ ቨርሰስ ዌድ’ አደጋ ላይ መሆኑ የተነገረው።

ፅንስን ማቋረጥ ውሳኔን ሊሽር ይችላል የተባለው ይህ ሰነድ በዲሞክራቶች ዘንድ ተቃውሞን አስነስቷል። በተጨማሪም ሰኞ ምሽት ፅንስን ማቋረጥ የሚደግፉና የሚቃወሙ ሰልፈኞች በጠቅላይ ፍርድ ቤት ድምጻቸውን በተለያየ መልኩ አሰምተዋል።

ሰኞ ምሽት አፈትልኮ ወጣ በተባለው ሰነድ ላይ ጠቅላይ ፍርድቤቱም ሆነ ዋይት ሃውስ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ሾልኮ የወጣው ረቂቅ ሰነድ “‘ሮይ ቨርሰስ ዌድ” የተሰኘው ውሳኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከፍተኛ ስህተት ነበር ሲል ያትታል።

አክሎም ሕገ መንግሥቱን አክብረን የፅንስ ማቋረጥን ጉዳይ ሕዝብ ለመረጣቸው ተወካዮች ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው ብሏል።

እንደ ዘገባው ከሆነ የነፍሰ ጡር ሴትን ነጻነት ለመጠበቅ የወጣው “‘ሮይ ቨርሰስ ዌድ” ምክንያት በተለየ መልኩ ደካማ ነበር እና መዘዞችንም አስከትሏል” ሲሉ ዳኛ ኦሊቶ ጽፈዋል።

አክለውም “ውሳኔው ብሔራዊ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ክርክርና መከፋፈልን በአገሪቱ አስፍኗል” በማለት ፖለቲኮ ዳኛ ኦሊቶን ዋቢ አድርጎ አስፍሯል።

ወግ አጥባቂው በአስተያየታቸው “ልንዘለው የማንችለው ድምዳሜ ጽንስ የማቋረጥ መብት በአገሪቷ ታሪክና ወግ ሥር የሰደደ አይደለም የሚለው ነው” ብለዋል።

የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ እና የምክርቤቱ አብላጫ መሪ ቻክ ሹመርም አፈትልኮ ወጣ በተባለው አስተያየት ላይ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሁለቱ ዲሞክራቶች በመግለጫቸው፣ ዘገባው ትክክል ከሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛውን የመብት ገደብ ለመፈፀም ተዘጋጅቷል ማለት ነው ብለዋል።

በሪፐብሊካን የተሾሙት ዳኞች ውሳኔም በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከተፈፀሙት እጅግ የከፉ እና በጣም ጎጂ ውሳኔዎች አንዱ ወደሆነው አጸያፊው ተግባር እያመራ ነው” ሲልም መግለጫው አክሏል።

ይህንን ተከትሎ ተቃዋሚዎች በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመሰባሰብ ሾልኮ በወጣው ሰነድ ላይ ያላቸውን ቁጣ ገልጸዋል።

ተቃዋሚዎቹ ” ከሰውነታችን ላይ እጃችሁን አንሱ”፣ “የሴቶች መብት ሰብዓዊ መብት ነው”፣ “አካሌ ምርጫዬ ነው” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው ወጥተዋል።

የፀረ ፅንስ ማቋረጥ ተሟጋቾች በበኩላቸው “ሮይ ቨርሰስ ዌድ” መነሳት አለበት ሲሉ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

በአገሪቷ ካሉ ፅንስን ማቋረጥን ከሚቃወሙ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነውና ናሽናል ራይት ቱ ላይፍ የተባለው ድርጅት በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠቱ በፊት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ይፋዊ አስተያየት እንደሚጠብቅ ገልጿል።

እንደ ፖለቲኮ ከሆነ ሾልኮ የወጣው ሰነድ “የመጀመሪያ ረቂቅ” ተደርጎ የተጠቀሰ ሲሆን የካቲት ወር ላይ ተሰራጭቷል። በማርቀቁ ሂደቱ ወቅትም የፍትህ ዳኞቹ ድምጽ የተለያየ እንደነበርም ታውቋል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በእንዲህ ዓይነት ጉዳዩ ላይ ብይን ሲሰጥ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። እአአ በ1992 ዳኛ አንቶኒ ኬኔዲ በመጨረሻው ሰዓት ሃሳባቸውን ለውጠው ወሳኝ የነበረውን አምስተኛውን ድምጽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው “ሮይ ቨርሰስ ዌድን” ሕግ ለመጣል ብዙኃኑን ተቀላቅለዋል።

______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Health, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: