Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2022
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የሞት ኃይልን ሰብሮ ተነስቷል | ሲኦል ተሻረልን ጌታችን ተነስቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 24, 2022

✞✞✞

ተነስቷል

ወተንሥአ እንበል ………..

ትንሣኤው ልዩ ነው ………..

የመከራ ቀንበር ከእኛ አርቆልናል

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሰን!

ጽዮናውያን ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጎ ዘመን እየመጣ ነው።

😇 በዚህ የተቀደሰ ሣምንት የገጠመኝን በአጭሩ ላውሳው፤

ባለፈው የፀሎተ ኃሙስ ዕለት ብዙ ፈተና ገጥሞኝ ነበር፤ በሕልሜ አንዲት የማላውቃትና አይቻት የማልውቃት ሴት ስታሽኮረምመኝና ስትስመኝ አፌ በጥራጥሬ ሞላና ጥራጥሬውን እየተፋሁ፤ ለምንድን ነው የምትስሚኝ፤ ይኽ እኮ የጾም ጊዜ ነው፤ ተገቢ አይደለም!” ብዬ ሄድኩ። ዛሬ ደግሞ፤ ከሁለት ሰዓታት በፊት ወደቤቴ ላመራ ስል መንገድ ላይ ያልተለመደ መንገድ ተክትዬና ሳልዘጋጅበት ወደማዘወትርባት የቅዱስ ዮሴፍ ጸሎት ቤት አመራሁ። እዚያም ሌላ ሰው አልነበረም፤ ጸሎት አድርሼ ስጨረስም አንዱ ወንበር ላይ የገንዘብ ቦርሳ አየሁና፤ ስልክ ቁጥሬን ለመተው ወረቅት ሳወጣ፤ ግን እኮ ዝምብሎ የተጣለ ቦርሳ ሊሆን ይችላል እስኪ ልክፈተውበማለት ስከፍተው ሦስት የክሬዲት ካርዶች፣ የጤና ዋስታና ካርዳ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ እስከ መቶ ዩሮ የሚጠጉ ብሮች ወዘተ. አገኘሁ። የመንጃ ፈቃዱን ስከፍተው አድራሻና የብሎንዷን ሴት ፎቶ አየሁት። ወዲያውም፤ እንዴ ምናልባት በሕልሜ ያየኋት ሴት ትሆን እንዴ? ዋው!” ብዬ በመገረም፤ ሴትይዋ ወደምትኖርበት ቤት አመራሁ። ደወሏን ስደውል ውሾች አስቀድመው መጮኽ ጀመሩ፤ ከዚያም ሴትየዋ ወጣች፤ በሃያ ስምንት እና ሰላሳ ዓመት ዕድሜ አካባቢ ያለች ሴት ትሆናለች። ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ፤ ዛሬ ጠዋት ምን ጠፍቶብዎታል?” ስላት፤ አንተ ማንነህ? ምንም አልጠፋብኝም!” አለችኝ፤ እርግጠኛ መስላ። እኔም፤ ዛሬ በቅዱስ ዮሴፍ ጸልቶ ቤት ነበሩን?” ስላት፤ አዎ!” አለችኝ፤ ያኔ ቦርሳዋን ከኪሴ አውጥቼ ሳሳያት፤ በመገረምና በመደሰት፤ ትልቁን ቦርሳየን አልፈተሽኩትም! እግዚአብሔር ይስጥህ፣ ባክህ ግባ ቡና ጠጥተህ ሂድ…” አለችኝና ሃምሳ ዩሮ ገደማ አውጥታ፤ ባክህ ይህን ውሰድ፣ ከፈልግክም ለተቸገሩ ስጥልኝበማለት ልትሰጠኝ ስትሞከር፤ ኧረ በጭራሽ፤ ዛሬ የትን ሣኤ ክብረ በዓል ስለሆነ፤ ለኔ የጠፋብዎትን አምጥቼ ከመስጠት በላይ የበለጠ ስጦታ የለም፤ የቅዱስ ዮሴፍ ሥራ ነው! አይሆንምስላት እምባ እየተናነቃት ጥምጥም አድርጋ አቀፈችኝና ጉንጮቼን ሳመቻቸው። እኔም፤ ይህን ቀን ያስታውሱት፤ ከሰባት ዓመታት በፊትም መንገድ ላይ ገንዘብና ክሬዲት ካርዶች፣ መታወቂያ የነበረው ቦርሳ በጌታችን ልደት ዋዜማ አግኝቼ፤ ያኔም ለጠፋባት ሴት እንደ ገና አባት ይቁጠሩኝ፤ ለኔም ለርስዎም ትልቅ ስጦታ ነው ገንዘብ አልቀበልም ብያት ነበርስላት በድጋሚ አቀፈችኝና ተሰነባብተን ተለያየን።

በዚህ ስጦታ እጅግ በጣም ነው ደስ የተሰኘሁት፤ መጭው ጊዜ በመከራና ስቃይ ላይ ላሉት አባቶቼና እናቶቼ፣ ወንድሞቼና እኅቶቼ ብሩኽ እንደሚሆን ጥሩ ስሜት ይሰማኛል። እነዚህ ገጠመኞች ትልቅ ምልክቶች ናቸው። ጽዮናውያንን በድጋሚ የማስጠነቅቀው ግን በተደጋጋሚ ከባድ የሆኑ ስሕተቶችን የሠሩት ሕወሓቶች ዛሬም በግትርነት በሰፊው በማስተዋወቅ ላይ ያሉትን (ወዮላችሁ!) የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ እንዲያስወግዱት ነው። ይኽ ሳይውል ሳያደር መወጣት ያለባቸው ግዴታቸው ነው!

✞✞✞ No CROSS No CROWN – ያለህመም ማግኘት የለም ፥ ያለ መስቀል ፣ አክሊል የለም! ✞✞✞

______________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: