Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2022
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for April 23rd, 2022

A Woman Steals over $2K in Meat From a Supermarket | እኅታችን የ፪ሺ ዶላር ስጋ ሰረቀች | ለፋሲካ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2022

በሉ፤ አንቸኩል፤ አንድ ቀን ይቀረናል፤ እንዲህ ቢያጓጓንም፤ ስጋ ባናበዛ ጥሩ ነው ፤ ለስጋም ለነፍስም እንደ ጾም ጊዜ ጤናማ የሆነ ጊዜ የለም። ይህ ለበዓላት ተብሎ ለአንድ ወይም ሁለት ቀን ብቻ ሲባል ስጋና ቅባት አግበስብሶ መፈሰኩን ማቆምና ሁሉንም በልክ ማድረግ ይኖርብናል። ሥራው ብዙ፤ ሸክሙ ብዙ፤ ውጭው ብዙ!

የሚከተለው ክቡር መስቀሉን በተመለከተ የቀረበ ጽሑፍ ዛሬ የምናየውን መከራንና ስቃይን በግልጽ ያመላክታል።

መስቀል የሚለው ቃል የተገኘው “ሰቀለ” ከሚለው የግእዝ ቋንቋ ግሥ ነው፡፡ትርጓሜውም “የተመሳቀለ” ወይም “መስቀል” ማለት ነው፡፡

መስቀል ለክርስቲያኖች የሕይወትና የድኅነት ምልክት የሆነው መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ሁለቱ ከእንጨት የተገኙት የመስቀሉ ክፍሎች (አግድም እና ቀጥታ) በጣም ትልቅ የሆን ትርጉም ነው ያላቸው።

በኦሪት መስቀል የመርገምና የመቀጫ መሣሪያ ሆኖ ይቆጠር ነበር፡፡ ”ማንም ሰው ለሞት የሚያበቃውን ኃጢአት ቢሠራ እንዲሞትም ቢፈረድበት በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር” [ዘዳ ፳፩፥፳፪፡፳፫]

የጥንት ሮማውያን ወንጀለኞችን በመስቀል ተሰቅለው እንዲሞቱ ማድረግ ልማዳቸው ነበር፡፡ክርስቶስ ኢየሱስ ለድኅነተ ዓለም ከመሰቀሉ በፊት የእርግማን ምልክት የነበረው የመስቀል ታሪክ ጌታችን ከተሰቀለበት በኃላ ግን ታሪኩ ተቀይሯል፡፡

ቀኝ (በግ ፍያታዊ_ዘየማን )እና 😈ግራ (ፍዬል – ፍያታዊ ዘፀጋ)

ቀኝ (የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙር) እና 😈 ግራ (የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር ጭፍራ)

ጥጦስ ( # ፍያታዊ ዘየማን )

እና

😈 ዳክርስ ( # ፍያታዊ ዘፀጋ )

✞✞✞✞✞✞✞

በጌታችን ቀኝና ግራ የተሰቀሉት የሁለቱ ወንበዴዎች ከስቅላት በፊትና በኃላ ያላቸው አስገራሚ ታሪክ:

✞✞✞

ሁለቱ ወንበዴዎች ጥጦስ በቀኙ የተሰቀለው ( ፍያታዊ ዘየማን ) እና ዳክርስ በግራው የተሰቀለው ( ፍያታዊ ዘፀጋ ) :- መተዳደሪያቸው ቅሚያ ነበር። ጌታችን እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ከገሊላ በወጡ ጊዜ ወንበዴዎቹ ተከትለዋቸው በበረሃ ቢፈልጓቸውም አስከ ስድስት ቀን አላገኙዋቸውም ነበር። በሰባተኛው ቀን አገኙዋቸውና ዛሬ እግዚአብሔር ከእጃችን ጣላችሁ ብለው እየሮጡ ሄዱባቸው። ሰሎሜ አስቀድማ ልብሷን ጥላላቸው ሸሸች።

✞✞✞

ወንበዴዎቹ ከእነዮሴፍ እጅ የተገኘውን ቀምተው ከሄዱ በኃላ ጥጦስ ( በቀኙ የተሰቀለው ) ዳክርስን እንዲህ አለው ይቺ ሴት ( እመቤታችንን ማለት ነው ) የነገሥታት ወገን ትመስለኛለች: ሕፃኑም ከነቢያት አንዱ ይመስለኛል: የቀማናቸውን እንመልስላቸው? ዳክርስም ( በግራ የተሰቀለው ) ጥጦስን (በቀኝ የተሰቀለው) እንዲህ ያለውን ረኀራሄ ከየት አገኘኸው? ይህን ውንብድና ያስተማርከኝ አንተ ነህ: ሌላው ደግሞ ዛሬ የቀማነው የእኔ ድርሻ ነው የራስህን ድርሻ ወስደህ የእኔን ድርሻ እንመልስላቸው ትላለህ? አለው።

✞✞✞

እነዚህ ሁለት ቀማኞች አንድ ቀን የቀሙትን አንደኛው ሲወስድ በሌላ ቀን የቀሙትን ደግሞ ሁለተኛው ይወስድ ነበር። በዚህ ዕለት የቀሙት የዳክረስ ( በግራው የተሰቀለው ) ድርሻ ነበር። ጥጦስም ከገሊላ እስከዚህ የቀማነውን አንተ ውሰድ ይህን ለእኔ ስጠኝና ልመልስላቸው አለው። ዳክርስም በዚህ ሐሳብ ተስማማ: ዳክርስ ህፃኑ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብሰሎ ፍጥረትን የሚመግብ የሁሉ ፈጣሪ መሆኑን ባለመረዳቱ ዕድሉን አልተጠቀመበትም በትንሽ ርኀራኄ ብዙ በረከት አመለጠው ወደ እርሱ ያንዣበበውን ፀጋ ለጓደኛው ሰጠው።

✞✞✞

እመቤታችን ሁለቱ ወንበዴዎች ቁመው በዚህ ሐሳብ ሲወያዩ አይታ ፈራች። ወንበዴ የቀማውን ይዞ ይሄዳል እንጂ ለምን ቁሞ ይማከራሉ? ምን አልባት ልጆቻቸው ሄሮድስ የገደለባቸው ሰወች ይሆናሉ በዚህ ሕፃን ምክንያት ልጆቻችን ሞቱብን ብለው ልጄን ሊገሉብኝ ይሆናል ብላ ጽኑዕ ለቅሶን አለቀሰች። ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስም እናቱን ድንግል ማርያምን እንዲህ አላት:- አይዞሽ እናቴ አታልቅሺ አይገሉኝም እንመልስላቸው እያሉ ነው። እኔ በቀራኒዮ ስሰቀል እነሱም በቀኜ እና በግራዬ ይሰቀላሉ አንዱ አምላክነቴን አምኖ ይድናል ሁለተኛው ግን አይድንም።

✞✞✞

ከዚህ በኃላ ጥጦስ የተባለው ወንበዴ ገንዘባቸውን መለሰላቸውና ጥጦስም ጌታን አቅፎ ይዞ ሲሄድ ሰይፉ ወድቆ ተሰበረበት። በጣም አዘነ። ጌታ የሰይፍህን ስብርባሪ ሰብስብ አለው። ጥጦስ የሰይፉን ስብርባሪ ሰበሰበ። ጌታም እንደቀድሞው ይሁንልህ አለው። ሰይፉም እንዳልተሰበረ ሆነ። ጥጦስ ሕፃኑ ከነቢያት ወገን ይመስለኛል ብሎ የገመተው ግምት እውን ሆነለት። ተአምራቱን አየና አደነቀ።

✞✞✞

ጌታ ጥጦስን እንዲህ አለው:- አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ። ጥጦስም ሄዶ ጌታ የነገረውን ሁሉ እና ያደረገለትን ተአምራት ለጓደኛው ነገረው። ጓደኛው ግን አላመነም። ጥጦስ የተባለው ወንበዴም ጌታ በተሰቀለ ጊዜ በጌታ ቀኝ ተሰቅሎ ፀሐይ ስትጨልም አይቶ የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት አምኖ ” ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ ” አለው። ኢየሱስም እውነት እልሃለሁ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው። የሉቃስ ወንጌል [፳፫፥፵፪] ጌታ አዳምን ቀድመኸው ገነት ትገባለህ ብሎ በጫካ የሰጠውን ተስፋ በመስቀል ላይ ፈጸመለት። ምነው ጌታችንን በወንበዴዎች መካከል ሰቀሉት ጌታስ ስለምን ተሰቀለ ቢሉ አይሁድ ጠልተውታልና ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ እንጂ ነህ ግራ ቀኝ ቢትወደድ ይገባሃል እያሉ ሲሣለቁበት ነው። ጌታችን ግን ኃላ በዕለተ ምፅአት ጊዜ ጻድቃንን በቀኝ ኃጥአንን በግራ አቁሜ የማጸድቅ የምኮንን እኔ ነኝ ሲል ነው።

✞✞✞

ጌታም እራሱን ወደ ጥጦስ ዘንበል አድርጎ ምድረ ግብፅ ስንወርድ የነገርኩህ ሁሉ ደረሰ ከሞት በቀር ሌላ ነገር የቀረኝ የለም ሂድ ገነት ግባ ብሎ ደመ ማኀተሙን ሰጥቶ ሰደደው የገነት ጠባቂዋ ሱራፊ መልአክ ደመ ማኀተሙን ፈርቶ እየሸሸ አንተ ማነህ የት ትገባለህ ቢለው ወንድሜ አልሰማህም አምላክ እንጂ ወርዶ ተወልዶ ዓለምን ሁሉ አዳነው አለው: አንተስ ማነህ አዳምን ነህ አብርሃምን ይስሐቅን ነህ ያዕቆብን ነህ እያለ ደጋጎቹን እየጠራ ቢጠይቀው ሁሉንም አይደለሁም እጄን በሰው ደም ነክሬ የምኖር ወንበዴ ነበርሁ አለው። ለእንደዚህ አይነት ያለ ክብር ያበቃህ ምንድነው ቢለው ፯/7 ቱ ተአምራት ሲሰሩ አይቼ አምላክነቱን ተረድቼ ብለምነው ለእንደዚህ ያለ ክብር ጸጋ አበቃኝ ብሎ ለ ፶፻፭፻/5500 ዘመን ተዘግታ የነበረችይቱን ገነት በጌታችን ደመ ማኀተም ከፍቶ አዳምን ቀድሞ ገነት ገባ።

✞✞✞

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንገተኛ ሞት ሰውሮ በመጨረሻዋ ደቂቃችንም ቢሆን እንደ ጥጦስ (ፍያታዊ ዘየማን ) በቸርነቱ አስቦ መንግሥተ እርስቱን ያውርሰን አሜን።

✞✞✞

👉 ምንጭ: የእመቤታችን ጉዞ ከገሊላ ወደ ግብፅ እና ኢትዮጵያ እንዲሁም መዝገበ ጸሎት ወመጽሐፈ ጸሎት መጽሐፍት ላይ ተቀንጭቦ የተወሰደ።

✞✞✞ የጌታ ስቅለት | በዚያን ዕለት የከርስቶስ ልጆች “ክርስቲያን”፤ የፀረክርስቶሱ “እስላም” ተባሉ ✞✞✞

ከመጽሐፈ ጸሎት የተወሰደ

✞“ሕማማተ መስቀል

ጌታም ቆላተ ዮሳፍጥ ከሚባል በረሀ አውርዶ መናውን ውሀውን ከወትሮ አብልጦ አወረደላቸው። ኃይሉን ክሂሎቱን አሳያቸው። መርዛማ እባብ አስነሥቶ ጐድናቸውን እያስቀደደ አስፈጃቸው። ሙሴም “አቤቱ ጌታዬ ሕዝበ እስራኤልን የሚመግባቸው ቢያጣ ከበረሀ አውርዶ አስፈጃቸው እንዳይሉህ መድኃኒት ፈልግላቸው” ብሎ ጸለየ። ጌታም የወዳጁን ጸሎት ፈጥኖ ይሰማልና “ብረቱን እባብ አስመስለህ በተራራ ላይ ተራዳ ተክለህ ብረቱን በዚያ ላይ ሰቅለህ አሳያቸው። ያን አይቶ ሰምቶ ያመነ ይዳን፤ ያላመነ ይፈጸም፤” አለው። ተራራው የቀራንዮ አምሳል ነው፣ ተራዳው የመስቀል፣ ብረቱ የወልደ እግዚአብሔር፣ እባብ የዲያብሎስ፣ ቍስሉ የኃጢአት፣ መርዙ የመርገመ ሥጋ የመርገመ ነፍስ፣ በረኃው የገሃነመ እሳት አምሳል ነው። ያን አይተው ሰምተው ይዳኑ ማለቱ፤ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያመኑ ሐዋርያት ሰምተው ያመኑ ምዕመናን የመዳናቸው አምሳል ነው። ያላመኑ ይፈጸሙ ማለቱ፤ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያላመኑ አይሁድ ሰምተው ያላመኑ አሕዛብ ያለመዳናቸው አምሳል ነው።

ያን አይተው ሰምተው ይዳኑ ማለት ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያመኑ ሐዋርያት፣ ሰምተው ያመኑ ምዕመናን የመዳናቸው አምሳል ነው። ያላመኑ ይፈጸሙ ማለቱ፡ ስቅለተ ክርስቶስን አይተው ያላመኑ አይሁድ ሰምተው ያላመኑ አይሁድ፣ ሰምተው ያላመኑ አሕዛብ ያለመዳናቸው አምሳል ነው።

ነፍስ ያለው እባብ የገደላቸውን ሰዎች ነፍስ የሌለው ብርት እንዳዳናቸው በባሕርዩ ሞት የሌለበት አምላክ ዲያብሎስ ያስገራቸውን ነፍሳት ተሰቅሎ ሞቶ የማዳኑ አምሳል ነው።

😇 ጽዮን የተባለች ማኅፀነ ማርያም ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሏ ነው

ጌታም እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በማኅፀነ ማርያም አድሬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው። አንድም ጽዮን የተባለ መሰቀሉ ደብረ መቅደሱ የተባለ አካሉ ነው። እነዚያ አላወቁም እንጂ እኔስ በመስቀል ተሰቅዬ ለጻድቃን ለሰማዕታት ነገሥሁላቸው በአይሁድ በመናፍቃን ነገሥሁባቸው ሲል ነው እንዲህ ፯ት ተአምራት ሲሠሩ አይተው የባሕርይ አምላክ ነው እንጂ የባሕርይ አምላክማ ካልሆነ እንዲህ ያሉ ተአምራት ባልተሠሩ ነበር ያሉ ክርስቲያን ተባሉ።

አምላክ አይደለም፣ አልተወለደም፣ አልተሰቀለም፤ የአምላክ ወዳጅ ደግ ሰው ነብይ ብቻ እንጂ ያሉት እስላም ተባሉ። እስላምና ክርስቲያን የተባለበት ያን ዕለት ነው። አይሁድ ግን አላክም ነብይም አይደለም ሐሳዌ መሲሕ ነው ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለም ብለው ካዱት።

መናፍቃን ካህናት አላውያን መኳንንት ከሀድያን ነገሥታት ሃይማኖታችሁን ጣሉ ፈጣሪያችሁን ካዱ ለጣኦት ስገዱ ብለው እንደ እኔ እራሳችሁን እየመቱ አክሊለ ሦክ ግንድ አሸክመው በብረት ቢቸነክሯችሁ መራር ሐሞት ቢያጠጧችሁ ዋጋችሁን በመንግሥት ተቀበሉት እንጂ ሃይማኖታችሁን አትጣሉ፤ ፈጣሪያችሁን አትካዱ፤ ለጣኦት አትስገዱ!” በማለት ጌታችን አስተምሮናል።

💭 This woman reportedly stole all this meat in the cart from HEB supermarket in Temple. The HEB employee is seen trying to stop it and also document the alleged theft. There is also another woman accused of the acts. Temple TX Police believes over $2,000 of meat was stolen.

  • ✞Ethiopian Christian Butchery on Easter Day/ የክርስቲያን ስጋ ቤት ፥ ለፋሲካ ዝግጅት
  • ☪️ unEthiopian Muslim Butchery/ ኢ-ኢትዮጵያዊ የሙስሊም ስጋ ቤት

The closer Ethiopians get to Easter Sunday, the bigger their celebrations and the more intense their fasting. Orthodox Christians partake in a traditional 55-day fast of all meat and animal products (abstention from animal products like meat, dairy, and eggs), and refraining from eating or drinking before 3:00 pm – with Good Friday spent in preparation for the breaking of this fast after a morning Church service.

The knife, a synecdoche of slaughtering, is an important culinary tool that is charged with the power of religious speech acts and that has a significant semiotic function in Christian-Muslim encounters in Ethiopia. The slaughtering rituals not only transform the neutral natural animal into a sacred cultural food but also invest the meat with an intense aura of disgust among followers of the other faith. The slaughtering narratives continue to manifest themselves in other public signs, namely, in the Cross and the Crescent, on butcheries, and restaurants, for example. These two universal signs are the corollaries of an anterior sign, in other words, the knife that, in the discursive realm of food and religious identity in Ethiopia, implicates the different slaughtering rituals of Orthodox Christians and Muslims.

Orthodox believers also have their own rituals for slaughtering meat, and require that all meat they eat must have been slaughtered by a Christian. In Addis Ababa, there is one Christian slaughterhouse and one Muslim one, each of which supplies all respective butchers and restaurants. At the Christian slaughterhouse, an Orthodox priest will bless all the animals with a Trinitarian blessing, a pattern that is repeated in other large towns and cities. In the countryside, this may be left to the senior male householders who pray a Trinitarian blessing over the bull, lamb or chicken before its throat is cut. Women may not fill this role.

Christian butcher shops always identify themselves with a cross painted on the stall, and Muslim shops are identified with a crescent. In many regions, Orthodox believers do not eat meat blessed by a Muslim During the 55 days of lent, Christian butcher shops are usually closed entirely, and Christian restaurants will not serve meat. True Christians don’t eat halal meat served in a Muslim restaurant.

Generally, Christians should avoid Islamic restaurants and food stores. Not only is great and devastating the spiritual harm that emanate from eating halal foods, such as meat (sacrificed to non-Christian idol gods), but the sanitation aspect of the whole Islamic culture should also be worrisome.

💭 Mysterious Vertical Red Light in Sky over Texas in US | በቴክሳስ ሰማይ ላይ ሚስጥራዊ አቀባዊ ቀይ ብርሃን

______________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

፯ቱን የናዝሬት ወጣቶችን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የገደሏቸው ሔሮድሳውያኑ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች ናቸው | 100%

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2022

✞✞✞[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬፥፳፮፡፳፯]✞✞✞

“ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።”

እነዚህን ምስኪን የክርስቶስ ደቀ መዝሙራት እንዲህ ቶሎ ረሳናቸው፤ አይደል? ይህ እኮ ዛሬ ኦሮሞዎችና አጋሮቻቸው ለሚፈጽሟቸው ዕለታዊ አረመኔ ተግባራት ትልቅ ምልክት ነበር። ልክ ታግተውና በኋላም ላይ ጡቶቻቸውን ተቆረጠው ለዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር በአኖሌ እንደተሰውት የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች።

ከሁለት ዓመታት በፊት፤ ሚያዝያ ፲/10 – ፳፻፲፪/2012ዓ.ም ላይ ልክ በዚህች በተቀደሰች ቀዳሚት ሥዑር ዕለት “ለምን ወደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ በሚል እነዚህን ምስኪን የናዝሬት ከተማ ሕፃናት በተኙበት መርዘው ገደሏቸው። 😠😠😠 😢😢😢

በምሥራቅ ሸዋ ዞን አዳማ በተባለው ወረዳ የዲቢቢሳ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን መዘምራን የነበሩ ሰባት ወጣቶች ቅዳሜ ለዕሁድ ሌሊት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰምቶ ነበር።

የብርኃነ ትንሣኤን በዓል ለማክበር በቤተክርስቲያኗ ተገኝተው የነበሩት ሰባት ወጣቶች መካከል ስድስቱ ሴቶች ሲሆኑ አንዱ ወንድ ነበር።

የሞሞታቸው ምክንያትም ጄሬኔተር ካለበት አካባቢ ተኝተው ስለነበር “ከጄሬኔተሩ በሚወጣው ጭስ ታፍነው” ሊሆን እንደሚችል የደብሩ አገልጋዮች ቢናገሩም ቅሉ፤ ወጣቶቹ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይሄዱ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸው እንደነበር በኋላ ላይ ለማወቅ ችለን ነበር። ሁሉም ወጣቶች የቤተክርስትያኒቱ መዘምራንና የዲቢቢሳ (ወለንጪቲ መውጫ) ነዋሪዎች ነበሩ።

😈 ገዳዮቻቸው አረመኔዎቹ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ + ለማ መገርሳ + ሽመልስ አብዲሳ ናቸው። እነዚህ ከሃዲዎች የናዝሬትን ከተማ ስም መጠሪያ ወደ ጣዖታዊው “አዳማ” ስያሜ በመለወጣቸው ብቻ ተፈርዶባቸዋል።

👉 በወቅቱ ይህን ጽሑፍ አቅርቤው ነበር፤

✞✞✞”የናዝሬትን ሕፃናት የገደሏቸው ሔሮድሳውያኑ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች ናቸው | 100%”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2020

የእጅ ጽሑፉ ሁሉ የእነርሱ ነው!

ግድያውን የፈጸሙትም ልክ ቃል እንደገቡት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ እንደተመኙት በብርሃነ ትንሣኤ ዕለት(በጨለማው ረመዳን መግቢያ)እንደለመዱት ጨለማን ተገን አድርገው፣ እንዳቀዱት በሴት ህፃናት የተዋሕዶ ልጆች ላይ። የለመዱትን የማጭበርበሪያ ታትክቲክ በመከተል “የጄነሬተር ጭስ፣ መጀመሪያ 6ወንዶች አንዲት ሴት ፤ ከዚያም 6ሴቶች እና አንድ ወንድ(የደምቢዶሎውን ድራማ እናስታውሳለን?)አሉን ፥ ብዙም ሳይቆዩ ፣ በበነገታው፤ ይህ የግድያ ተግባራቸው ቁጣ እንዳይቀሰቅስና ጉዳዩን ከኦሮሚያ ሲዖል ቶሎ አውጥቶ ጉዳዩን ለማስቀየስ “በደቡብ ኢትዮጵያ 9 ኢትዮጵያውያን ህጻናት በታጣቂዎች ታግተው ተወሰዱ” የሚል ዜና እንዲሠራጭ ተደረገ።

አትኩሮታቸው ሁሉ የህብረተሰቡ ምሰሶዎች በሆኑት ሴቶችና ሕፃናት ላይ ነው።

በሴት ሕፃናቶቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውና በታሪካችን አይተነውም ሰምተነውም ለማናውቀው አሰቃቂ ወንጀል ሁሉ የሚከተሉት ግለሰቦች በጥብቅ ተጠያቂዎች ናቸው፤ ኢትዮጵያውያን ስሞቻቸውን መዝግቡ፦

አብይ አህመድ ፣ ለማ መገርሳ ፣ ታከለ ኡማ ፣ ሽመልስ አብዲሳ ፣ ጃዋር መሀመድ ፣ በቀለ ገርባ ፣ ህዝቄል ገቢሳ ፣ ዳውድ ኢብሳ ፣ አምቦ አርጌ ፣ ፀጋዬ አራርሳ ፣ አደነች አቤቤ ፣ ሞፈሪያት ካሜል ፣ መአዛ አሸናፊ ፣ ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ብርቱካን ሚደግሳ ፣ ታዬ ደንደአ ፣ ሌንጮ ባቲ ፣ ሌንጮ ለታ ፣ ዳንኤል ክብረት ፣ ብርሀኑ ነጋ ፣ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ ደመቀ መኮንን ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ ፣ አንዱዓለም አንዳርጌ ፣ ታማኝ በየነ ፣ አበበ ገላው።

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምረ ቀዳሚት ሥዑር በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ | የማያቃጥለው ቅዱስ እሳት በጌታችን መካነ መቃብር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 23, 2022

  • ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ፡፡

በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በቀራንዮ ጎልጎታ የጌታ መካነ መቃብር በሚገኝበት ቅዱስ ቤተክርስትያን ውስጥ እያንዳንዱ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚት በዛሬው የሥዑር / ቅዱስ ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢየሱስ መቃብር ዙሪያ በተዓምር የሚወርደውን“ነበልባል” ለመመልከት ይሰበሰባሉ፡፡

የእግዚአብሔር እጅግ አስደናቂ ከሆኑት ተዓምራት ውስጥ አንዱ ይህ በቀዳሚት ሥዑር በኢየሩሳሌም በጌታችን መካነ መቃብር ላይ የሚወርደው የተባረከ/ቅዱስ እሳት ነው።

የምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ይህ የትንሳኤ ጉልህ ምልክት ነው ብለው ያምናሉ።

ይህ ዋና ከሆኑት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተዓምራት መካከል አንዱ ነው። ይህ ተዓምር ላለፉት ፲፻፪፻/1,200 ዓመታት በየዓመቱ እየተከሰተ እንደሆነ ይታመናል።

ሥነ ሥርዓቱ የሚጀምረው በግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ (ወይም በሌላ የኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ) በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ወደ ክርስቶስ ባዶ መካነ መቃብር ወርዶ ልዩ ጸሎቶችን በማንበብ ነው። ኦርቶዶክስ ያልሆነ ክርስቲያን ደግሞ ፓትርያርኩ ሻማዎቹን ለማብራት የሚጠቀሙባቸው የነዳጅ ዘይት መብራቶች በውስጣቸው እንዳይቃጠሉ ለማድረግ መቃብር (አነስተኛ መቃብር ዙሪያ ያለውን ትንሽ መዋቅር) እንደሚመረምሩ ተገልጻል ፡፡

ከመቃብሩ በላይ እና በዙሪያው በተከበበች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፣ ምዕመናን በአንድ ድምፅ “ኪራላይሶን”(እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!)ያሰማሉ፡፡ ቆይታው ረጅም ወይም አጭር ሊሆን ይችላል ግን ውሎ አድሮ ፓትርያርኩ ለብቻቸው በሚጸልዩበት መቃብር ላይ እንደሚታዩ ይነገራል ፡፡ ከዛም ፓትርያርኩ ከዚህ ተዓምራዊ ነበልባል ሻማዎቹን በማቀጣጠል ደወሎችን እየደወሉ በምዕመናኑ መካከል ተገኝተው እሳቱን ወደ ሌሎች ቀሳውስት ያስተላልፋሉ፡፡ በዚህ ወቅት ጨለማ የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ በተዓምራዊው የተባረክ/ ቅዱስ እሳት ያበራል፡፡

ለመጀመሪያዎቹ በርካታ ደቂቃዎች እሳቱ ይቀጣጠላል ነገር ግን አይባላም ፡፡ በዚህን ጊዜ ፣ ብዙ ምዕመናን ፊታቸውን እና እጆቻቸውን ሳይቃጠሉና ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በእሳቱ ነበልባል ውስጥ ይታጠባሉ፡፡ እሳቱ ከሻማ ወደ ሻማ ከተላለፈ በኋላ በሩቅ በሰፊው እንዲሰራጭ በመብራት ሳጥን ውስጥ ይቀመጣል፡፡

________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: