Good Friday Crucifixion | ዓርብ ስቅለት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2022
✞✞✞ ዓርብ ስቅለት (የድኅነት ቀን) –የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት✞✞✞
ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. ፳፯፥፩-፶፯)፡፡ አይሁድ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነጥብ ሳይኖራቸው ነውና ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት ጲላጦሰ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?” ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡

“ክፉ የሠራ ባይኾንስ ወደ አንተ ባላመጣነውም ነበር” በሚል የሸፍጥ ቃል ሲያጕረመርሙ ጲላጦስ መልሶ “እኔ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም፤ እናንተወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት፤” አላቸው፡፡ አይሁድም ኦሪት “ኢትቅትል ብእሴ ጻድቀ ወኀጥአ ኢታኅዩ፤ ጻድቅን ሰው አትግደል፤ ኀጥኡንምከፍርድአታድን፤” ትላለችና “እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም፤” ብለዋል (ዮሐ. ፲፰፥፳፰-፴፩)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ “በሕጋችን ጻድቀ ባሕርይ ክርስቶስን መግደል አይገባንም ሙሉ በሙሉ ጥፋተኞችነን፤” ሲያሰኛቸው ነው፡፡ በኋላም እርሱ ሞቶ ዓለም ይድን ዘንድዳ ምድር መጥቷልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጥፋቱ ሞት ተፈረደበት፡፡ ስለዚህም ገርፈው ሰቀሉት፡፡
❖ ልክ አሁን የሕማማተ መስቀልን ፀሎት አንብቤ እንደጨረስኩ፤ ከጎረቤቴ ሕንጻ ጣራ ላይ ፲፫ ርግቦች ተነስተው በዙሪያዬ አንድ ጊዜና በአንድ ላይ ጅው ብለው በመብረር የተነሱበት ጣራ ላይ ተመልሰው አረፉ። ተገርሜ በመመሰጥ፤ “ምን የሚሉኝ ነገር ሊኖር ይችላል?” የሚለውን ጥያቄ ጠየቅኩ። ፲፫/13ቱ ሕማማተ መስቀል?
______________
Leave a Reply